የጤና ባለሙያዎች አገልግሎት የመስጠት ፍላጎት፣ የጊዜ እጥረት፣ የራስን ፍላጎት እውቅና አለመስጠት ወይም አለመገንዘብ፣ ፍርሃት፣ ጭንቀት ወይም ውጥረት ስሜት እያጋጠማቸው እንኳን ድጋፍ ከመጠየቅ ሊያግዷቸው ይችላሉ። የጤና ባለሙያዎች በተለያዩ አሉታዊ ተፅዕኖ ስር ወድቀው እንዳይጎዱ መበረታታት እና የተለያዩ እገዛዎች ሊደረግላቸው ይገባል።
በእነዚህ የሥራ መስኮች ውስጥ ያሉ ሰዎች ከራሳቸው ፍላጎት ይልቅ የሌሎችን ፍላጎት ቅድሚያ ስለሚሰጡ፣ ራሳቸውን ለመንከባከብ ጊዜ ላይኖራቸው ይችላል። ስለሆነም የጤና እንክብካቤ ሰጭዎችን መደገፍ እና ማበረታታት፣ በነገሮች ላይ ሀላፊነት እንዲሰማቸው በማድረግ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ የራስ-እንክብካቤ ስልት በተለያየ መልኩ እና በትክክል ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ነው።
በሥራ ፈረቃ ጊዜ የጤና አገልግሎት ሰጪዎች ሊያዳብሯቸው የሚገቡ ባህሪዎች ምንድናቸው?
• ራስን መቆጣጠር እና ማረጋጋት
• ከሥራ ባልደረቦችዎ፣ ከቤተሰብዎ እና ከጓደኞችዎ ጋር አዘውትረው መነጋገር
• በአጋርነት ወይም የቡድን ስራን ማዘውተር
በቂ የሆነ የመዝናኛ ጊዜ እና እረፍት መውሰድ
• በመደበኛነት ከስራ አጋርዎት ጋር ምክክር ማድረግ
• ራስን መንከባከብ እና ዕረፍት ለማድረግ ጊዜ መውሰድ
• በመደበኛነት ውሳኔ ሲወስኑ የሙያ አጋርዎን በማነጋገር ትክክለኛ ውሳኔ መወሰን
• በአስፈላጊ ጉዳዮች ላይ ከራስ ጋር ምክክር ማድረግ እና ከመጠን በላይ የሆኑ ፍራቻዎችን ለማስወገድ የተቻላቸውን ሁሉ ማድረግ
ጥረታቸውን መለወጥ በሚችሉት ጉዳዮች ላይ ማተኮር
• መለወጥ የማይችሏቸውን ሁኔታዎች ለመቀበል ዝግጁ መሆን
• አንድን ነገር የመቻል፤ የትዕግስት እንዲሁም የተስፋ መንፈስን ማዳበር
መወገድ የሚገባቸው ተግባራት
• ከሥራ ባልደረባዎ ጋር ሳይገናኙ ለረጅም ጊዜ መሥራት
• ካለ እረፍት ለረጅም ጊዜ መስራት
• በተደጋጋሚ በበቂ ሁኔታ እንዳልሰሩ በመሰማት ውጥረት ውስጥ መግባት
• ጣፋጭ ምግቦች ወይም መጠጦችን እና ካፌይን ከመጠን በላይ መጠቀም
አላስፈላጊ ያልሆኑ እራስን ከመንከባከብ የሚገቱ ሀሳቦች ላይ ማተኮር፡ ለምሳሌ/“ለማረፍ ጊዜ መመደብ ራስ ወዳድነት ነው….”
“ሌሎች በየሰዓቱ እየሠሩ ናቸው፣ እኔ ደግሞ…….”
“የታካሚዎች ፍላጎት ከጤና ረዳቶች ፍላጎት የበለጠ አስፈላጊ ናቸው….”
“ሁል ጊዜ በመስራት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከት እችላለሁ……”
“የእኔ ብቻ ሀላፊነት ነው ……”
ከስራ ሀላፊነትዎ በኋላ የተከሰተውን ውጥረት ለመቋቋም መወሰድ የሚገባቸው እርምጃዎች
ከCOVID-19 ታካሚዎች በተለይም ለይቶ ማቆያ
ውስጥ ላሉት እንክብካቤ ካደረጉ በኋላ፣ የማገገሚያ ጊዜ መውሰድ ይጠበቅቦታል። ለምሳሌ:-
• ማህበራዊ ድጋፍ መፈለግ እና መጋራት
• ከስራ ባልደረባዎ ጋር በመገናኘት የሥራ ልምድዎን መለዋወጥ
• ምክክርን እና የስራ አጋሮትን ድጋፍ ማሳደግ
• ከስራ ውጭ ጊዜ መውሰድ
ሊወገዱ የሚገባቸው ተግባራት
አሉታዊ ውጥረትን (ስትረስ) ለመቋቋም ተብለው የሚወሰዱ ተግባራት ሊወገዱ ይገባል፤
የእንቅልፍ ዑደቶች የሚያዛቡ መድኃኒቶችን እና ረጅም ጊዜ ለማገገም የሚፈጁ
(ለምሳሌ አልኮሆል፣ ሕገወጥ መድኃኒቶች ወይም ከመጠን በላይ የሆነ መድኃኒት) ማዘውተር
• በድንገት ትልቅ የሕይወት ለውጥን ማድረግ
• በበቂ ሁኔታ ስራቸውን ቢያከናውኑም አስተዋፅዎን አሉታዊ በሆነ መልኩ መገምገም
• እራስን ከመጠን በላይ በሥራ መጥመድ
• ስለ ሥራ ልምዶች ከሌሎች ጋር ለመነጋገር አለመፈለግ
• ጭንቀቱ ከሁለት እስከ ሶስት ሳምንታት በላይ የሚቆይ ከሆነ እና ስራዎን የሚያደናቅፍ ከሆነ፣ የስነ ልቦናና የአእምሮ ጤና ህክምና አገልግሎት ማግኘት ይኖርባቸዋል።
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 9/2012
ሳባ ፈይሳ
(ሳይክ-ኢን-አክሽን ክበብ፤ ሳይኮሎጂ ት/ቤት አ.አ.ዩ)