ሊሴ ገብረማሪያም ትምህርት ቤት በ1939 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪዎችን ተቀብሎ ሲያስተምር ቆይቶ የሕንጻው ስራ ተገባዶ የተመረቀው ከ68 አመታት በፊት በዚህ ሳምንት ሚያዝያ ሁለት ቀን 1944 ዓ.ም ነበር፡፡ የሊሴ ፍራንኮ ትምህርት ቤት ምርቃት ላይ የትምህርት ሚንስትሩ አቶ አካለ ወርቅ ሀብተ ወልድ፣ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ኤደዋርድ ቤርላ፣ ከፈረንሳይ መንግስት ተልከው የመጡ ሰዎችና ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ስላሴ ተገኝተው ነበር፡፡ ፍሬ ከናፍር ዘ ቀዳማዊ አጼ ኃይለስላሴ ንጉሠ ነገስት ዘኢትዮጵያ ሁለተኛ መጽሐፍ ላይ እንደሰፈረው ሊሴ ሳይከፈት በፊት ንጉሱ ተማሪዎቻቸውን ወደ እስክንድሪያ እየላኩ ያስተምሩ ነበር፡፡
በዚያ ሊሴ ፍራንሴ የሚባል ትምህርት ቤት ነበረ፡፡ እዚያ የተማሩ አገራቸው እየተመለሱ ይሾሙና ለሌላ ከፍተኛ ትምህርት ወደ ሦስተኛ አገር ይላኩ ነበር፡፡ የሊሴ ገብረማርያም መከፈት ይህን ሂደት በከፊል አስቀርቷል፡፡ ከሊሴ ገብረማሪያም ሃያ አመታት ቀድሞ በአሌክስአንድሪያ በተቋቋመው ሊሴ ፍራንሴ ትምህርት ቤት ቀዳማዊ አጼ ኃይለስላሴ የላኳቸውን 30 ወጣቶች እንደ አባት መክረው እንደ መምህር ቀጥተውና አስተምረው ተመልሰው አገራቸውን እንዲያገለግሉ ያደረጉት የሚሲዮን ላይክ ዋና ጸሐፊ የነበሩት ሙሴ ማርሴል ፎርም በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተው ነበር፡፡ የወቅቱ የትምህርት ሚኒስትር የምርቃት ስነ-ስርዓቱን ለማስጀመር ባደረጉት ንግግር የገለጹት የትምህርት ቤቱ ታሪክ እንደሚያስረዳው ሊሴ ገብረማሪያም ትምህርት ቤት የተከፈተው ከተመረቀበት ዕለት አስራ አንድ ዓመት ቀድሞ ነው፡፡
ትምህርት ቤቱ ከተከፈተበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ሰባት ዓመት ድረስ ትምህርት ይሰጥ የነበረው በአማርኛና እንግሊዝኛ ነበር፡፡ ከንግግሩ መረዳት እንደሚቻለው ለሰባት አመታት ትምህርት ሲሰጥበት የቆየው ትምህርት ቤት ሊሴ ገብረ ማሪያም ተብሎ የሚጠራ አልነበረም፡፡ በጣሊያን ወረራ ምክንያት በኢትዮጵያና በፈረንሳይ መካከል የነበረው የእውቀት ግንኙነት ተቋርጦ ነበርና እንደገና እንዲያብብ ተፈልጎ በትምህር ቤቱ የነበሩ ተማሪዎችና መምህራን ወደሌላ ቦታ እንዲዛወሩ ተደርጎ ሊሴ ገብረ ማሪያም ትምህርት ቤት ተመሰረተ፡፡
ከዚያን ጊዜ አንስቶ ትምህርት ቤቱ በሚሲዮን መምህራን ትምህርት በአማርኛና በፈረንሳይኛ የሚሰጥበት ሆኖ አራት ዓመታትን ከዘለቀ በኋላ ለመመረቅ በቃ፡፡ የትምርት ቤቱ ርዕሰ መምህር የነበሩት ሙሴ ቤርላ በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር የሊሴፍራንኮ ገብረ ማሪያም ትምህርት ቤት ከአራት ዓመታት በፊት በሮቹን ለተማሪዎች ክፍት ማድረጉን ገልጸው ስራ ሲጀምር ስምንት መምህራንና 176 ተማሪዎች ብቻ እንደነበሩት ጠቅሰዋል፡፡ የመምህራንና ተማሪዎቹ ቁጥር እየጨመረ ሄዶ በተመረቀበት ዓመት 30 የውጭ አገርና ዘጠኝ ኢትዮጵያውያን መምህራን እንዲሁም 1 ሺ 31 ተማሪዎች ነበሩት፡፡ የተማሪዎቹ ብዛት ተጨማሪ ቦታና ቤት ማስፋት እንዲኖር አስገድዶ ከምርቃቱ በኋላ በነበሩ ዓመታት ተጨማሪ ግንባታዎች ተካሂደዋል፡፡
ትምህርት ቤቱ ሲመሰረት የኢትዮጵያ መንግስት 658 ሺ 925 ብር የሚያወጣ ቦታ፣ የመማሪያና መምህራን መኖሪያ ቤቶች እንዲሁም የትምህርት ቁሳቁሶች ሲሰጥ ተማሪዎቹ በየወሩ ከሚከፍሉት ገንዘብ በቀር በየዓመቱ 50 ሺህ ብር ወጪ ያደርጋል፡፡ ሚሲዮን ላይክ በበኩሉ ወጪውን ችሎ መምህራንንና ሌሎች ሰራተኞችን በመስጠትና ትምህርት ቤቱን በማስተዳደር ዕርዳታ ያደርግ ነበር፡፡ ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ስላሴ በዕለቱ ባደረጉት ንግግር “በኢትዮጵያና በፈረንሳይ መካከል ከረጅም ጊዜ ጀምሮ የቆየውን የእውቀት ግንኙነት ጠብቆ ለመጪው ትውልድ አስተላላፊ የሆነውን ይህን የገብረማሪያምን ትምህርት ቤት ስንመርቅ እጅግ ደስ እያለን ነው፡፡” ብለው ነበር፡፡ ቀደም ባለው ጊዜ በሊሴ ገብረማሪያም ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን የሚከታተሉት የአርበኞች ልጆች እንደነበሩ ይነገራል፡፡ ‹‹ዲ ደብሊው›› ከሁለት ዓመታት በፊት ባስነበበው ስለሊሴ ገብረማሪያም የቀድሞ ተማሪዎች ማህበር የሚያትት ጽሑፍ እንደገለጸው ዛሬ በሊሴ ገብረማሪያም ትምህርት ቤት ፈረንሳይኛ መናገር የሚችል ወይም የሚፈልግ ማንኛውም ሰው መማር ይችላል። ክፍያው እንደ ዜግነቱ ይለያያል።
ኢትዮጵያውያን 78 ሺ ብር ሲከፍሉ ፈረንሳውያን 88 ሺ ሌሎች የውጭ ሀገር ዜጎች ደግሞ 120 ሺ ብር በዓመት ይከፍላሉ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኘው በተጨማሪ በዓለም ዙሪያም 460 የሊሴ ትምህርት ቤቶች ይገኛሉ። ከነዚህም አንዱ ለሆነው የሊሴ ገብረ ማሪያም ትምህርት ቤት የፈረንሳይ መንግሥት በየዓመቱ 4 ሚሊዮን ዮሮ ያወጣል። ሊሴ ገብረማሪያም ትምህርት ቤት እንደ አምባሳደር ዘውዴ ረታ ያሉ በርካታ የአገር ባለውለታዎችን ማፍራት የቻለ አንጋፋ ትምህር ቤት እንደሆነ ይነገርለታል፡፡
ትምህርት ቤቱ በስማቸው የተሰየመላቸው ገብረማሪያምን ብዙዎች እንደማያውቁም ይነገራል፡ ፡ ጋዜጠኛ ደረጀ ኃይሌና አዜብ ወርቁ በአንድ ወቅት በሬዲዮ ፋና በሚያቀርቡት “የደራው ጨዋታ” የተሰኘው ዝግጅታቸው አድማጮችን “ገብረማርያም ማን ነው?” ብለው ጠይቀው በርካታ አድማጮች ትክክለኛውን መልስ መስጠት ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡ እንድ አድማጭ እንዲያውም “የሊሴ አባት ነው” ብሎ መልሷል፡፡ በኋላ ሁለገብ ባለሙያዋ አዜብ ወርቁ ሊሴ ማለት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማለት መሆኑን ተናግራለች፡፡
በአንድ ወቅት የኢትዮጵያ ታሪክ ተመራማሪው ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፖንክረስት በቸርችል ጎዳና ሲያዘግሙ አንዱን የሊሴ ተማሪ አስቁመው “ገብረማርያም ማን ነው?” አሉት፡፡ ልጁም አሰብ አርጎ “…ምን አልባት ትምህርት ቤቱ ያረፈበት መሬት ባለቤት ይሆናል” አላቸው፡፡ ሪቻርድ በተማሪው መልስ ተገርመው በ1995 ዓ.ም “The French Lycee; Who Was Geberemariam?” በሚል ርዕስ አዲስ ትሪቡን መጽሔት ላይ አንድ መጣጥፍ ጽፈዋል፡፡ ትምህርት ቤቱ በስማቸው የተሰየመላቸው ኢትዮጵያዊ ሙሉ ስማቸው ደጃዝማች ገብረማርያም ጋሪ ጎዳና ይባላል፡፡ አባታቸው አቶ ጋሪ ጎዳና እና እናታቸው ወይዘሮ ሌሎ ጉቴ ያወጡላቸው ስም ገሜሳ የሚል ነበር፡፡
ገብረማሪያም የክርስትና ስማቸው ነው፡፡ ጠላትን በፈረስ ሲያርበደብዱ የኖሩ አርበኛ አባ ንጠቅ ገብሬ በሚለው ስም ነው ይበልጥ የሚታወቁት፡፡ ገብረማርያም በ1866 ዓ.ም አገምጃ በሚባል አካባቢ የተወለዱ ሲሆን ለወላጆቻቸው 13ኛው ልጅ ናቸው (በሚገርም መገጣጠም በስማቸው የሚጠራው ሊሴ ገብረማሪያም ትምህርት ቤት እስከ 13ኛ ክፍል ነው የሚያስተምረው)፡፡ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ እና ደጃዝማች ገብረማሪያም ጋሪ የአንድ አካባቢ ልጆችና በአጼ ምንሊክ ጦር ተማርከው ለከፍተኛ ማዕርግ የበቁ የአገር ጀግኖች ናቸው፡፡
ገብረማሪያም በ22 ዓመታቸው ከባልቻ ጋር አድዋ ዘምተው 25ሺ ሰው በአንድ ጀምበር ባለቀበት ውጊያ ብቃታቸውን በማስመስከራቸው በአድዋ ድል ማግስት ለፊታውራሪነት በቁ፡፡ በ1922 ዓ.ም ፊታውራሪ ገብረ ማርያም ጋሪ ጎዳና በደጃዝማችነት ማዕረግ የሐረርጌ ጠቅላይ ግዛት እንደራሴ ሆነው ተሾሙ፡፡
ከ40 ዓመት በኋላ ጣሊያን የመርዝ ጋዝ ይዞ ሲመጣ ደግሞ በ62 ዓመታቸው ሲዳሞ ላይ ጠብቀውት ከራስ ደስታ ዳምጠው ጋር ሆነው ተፋለሙት፡፡ አባ ንጠቅ ገብረማርያም በመጀመሪያውም በሁለተኛውም የጣሊያን ጦርነቶች ታላቅ ጀብድ የፈጸሙ ጀግና ናቸው፡፡ ከጣሊያን ጋር ባደረጉት የመጨረሻው ፍልሚያ በደቡብ ሲዋጉ ቆሰሉ፡፡ ቆስለውም እየተንፏቀቁ ከደቡብ ተነስተው እስከ ትውልድ አገራቸው አገምጃ ድረስ ዘለቁ፡፡ የጣልያን ጦር ተከትሎ ሲከባቸውና ጦርነቱ የመጨረሻቸው እንደሆነ ሲያውቁ ዛሬ ሰርጌ ነው አሉ፡፡ ለውድ አገሬ ለሰንደቅ ዓላማው ግዳጄን ፈጽሜ ሕይወቴን አሳልፋለሁ፡፡ከዚህ እልፍ አልልም፡፡ ካሉ በኋላ የወንድማቸውን ልጅ ሻቃ በቀለ ዋያን መርቀው ካሰናበቱ በኋላ ባካሄዱት ከፍተኛ ፍልሚያ ከጠላት በተተኮሰ ጥይት ተመተው የካቲት 18 ቀን 1929 ዓ.ም አርፈዋል፡፡
አዲስ ዘመን መጋቢት 30/2012
የትናየት ፈሩ
የሊሴ ገብረማሪያም ትምህርት ቤት መመረቅ