“ጀግናው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ” የአዳም ልጆችን ከቤት ማዋል ከጀመረ ሳምንታት ተቆጥረዋል:: አንዳንዶች 2020 ይዞብን የመጣው የዘመናችን ጣር ስለሆነ ዓመተ ምህረት ከሚባል ይልቅ ዓመተ መከራ ቢባል ይሻላል እያሉ ብስጭታቸውን ይገልጻሉ::
እንዲያውም የባሰባቸው ተናዳጆች በሁለቱ ዜሮዎች መካከል የቫይረሱን ክብ ቅርጽ በመሳል የዓመቱን አስፈሪነት አጉልተው ለማሳየት ሲሞክሩ ይስተዋላል:: እርግጥ ነው ቤቱን ለማደሪያነት ብቻ ይገለገልበት የነበረው ብዙው የዓለማችን ሕዝበ አዳም ሳይወድ በግድ በግቢው ውስጥ ተከርችሞ እንዲውል አስገዳጅ ተፈጥሯዊ ትዕዛዝ ተላልፎበታል:: ተቆልፈው የሚውሉ ደጃፎች ወለል ተደርገው ተከፍተው በባለቤቶቹ ጠረን መድመቅ ጀምረዋል::
በሀገራችን ደረጃ እንኳ ካሁን በፊት ለቅንጡ ወገኖች ብቻ ቤተኛ የነበረው ሳኒታይዘርና ፈሳሽ ሳሙና የሁሉም ቤት እጅ ማበሻ ሆኗል:: ተመስገን ነው:: እኛም ብቻ ሳንሆን መላው የዓለም ሕዝብ እጁን በሳኒታይዘር ሳያሽ፣ በአልኮል ሳያለዝብ፣ በውሃ ሳይታጠብ እንደማይውል እየተመለከትን ነው::
ከጣጣውና ከብዙ ተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች ጋር የአቅርቦቱ አሳሳቢነት እንዳለ ቢሆንም ሕዝባችንም የአቅሙን ጥንቃቄ ማድረጉ አልቀረም:: የሬዲዮና የቴሌቪዥን ዜናዎችም ከመቼውም ዘመን ይልቅ በመርዶና በሀዘን ሪፖርቶች ተጥለቅልቀዋል:: “ምን ያህል ሰው ሞተ?” የተለመደ የወትሮ ጥያቄ ከሆነም ውሎ አድሯል:: በዚሁ ሰሞን በደጃፌ ላይ ቆሜ ለዓመታት የኖርኩበትን፤ ነገር ግን ባተሌነቴ እረፍት አሳጥቶኝ ባዕድ የሆንኩበትን አካባቢዬን በአርምሞ ተውጬ በመቃኘት ላይ እያለሁ በአጋጣሚ በአጠገቤ በዝግታ የሚያልፉ የአንድ አባትና ልጅ ጭውውት ቀልቤን ስለሳበው ሳልወድ በግድ ጆሮዬን ቀስሬ ንግግራቸውን ማድመጥ ጀመርኩኝ::
ልጅ አባቱን እንዲህ ሲል ጠየቀ፤ “አባባ የብሔራዊ ፈተናችን ጉዳይስ?” እንደመሰለኝ ልጁን ያስጨነቀውና ያሳሰበው እየተዘጋጀበት ያለው የአሥራ ሁለተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ጉዳይ ሳይሆን እንዳልቀረ ገምቻለሁ:: አባትየው በልጁ ትከሻ ላይ እጁን ጣል አድርጎ ስሜቱን ላለመጉዳት እንደተጠነቀቀ በሚያስታውቅ ድምጸት፤ “አይዞህ ልጄ ትደርስበታለህ:: ይህ ችግር በቅርቡ ማለፉ አይቀርም::
አሁን ሀገራችንንና ሕዝባችንን እያስጨነቀ ያለው የከፋው ብሔራዊ ፈተና ይሄ ከቤት ኮርኩዶ ያዋለን ወረርሽኝ ነው:: ያጋጠመን ይህ ወቅታዊ ፈተና በቀላሉ ዘለን የምናልፈው አይደለም:: ተግዳሮቱ እጅግ የከፋ ውጤት ሊያስከትል እንደሚችል ይገመታል:: ቢሆንም ግን መታለፉ አይቀርም::” የአባትና የልጅ ጭውውት በምን እንደተቋጨ አላወቅሁም:: እርምጃቸው እየራቀኝ በሄደ ቁጥር ድምጻቸው ጠፋብኝ::
በዚያ ቅጽበት የተለዋወጧቸው ኃይለ ቃላት ግን ከተራ ጭውውት ከፍ ያሉና ሞጋች ሃሳቦች ስለነበሩ ከህሊና ሙግት አላስጣሉኝም:: “ብሔራዊ ፈተና!?” የሚለው ሀረግና የዚያ ተስፈኛ ወጣት ድምጽ ደግሞ ደጋግሞ በአእምሮዬ ውስጥ እያቃጨለ እረፍት ነስቶኝ ሰነበተ::
መልክ ጥፉን በስም ይደግፉ፤
“ኮሮና” እየተባለ በዓለም ሕዝቦች ዘንድ ነጋ ጠባ ስሙ የሚጠቀሰው (ስሙን ቄስ ይጥራውና) የኮቬድ 19 ወረርሽኝ የሞት ልጓሙን ፈትቶ በምድራችን ላይ መጋለብ ከጀመረ ገና በሦስት ወራት የሚቆጠር ዕድሜ ቢኖረው ነው:: “መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ” እንዲሉ “corona” የሚለው የላቲን ሥርዎ ቃል በተለምደው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ሲተረጎም “crown” የሚል አቻ ፍቺ ተሰጥቶታል:: “crown” ዘውድ ወይንም አክሊል እንደ ማለት ነው::ይህንን ስም ያሰጠው የቫይረሱ ክብ ቅርጽ እንደሆነ የባለሙያዎቹ ትንታኔ ያስረዳል:: “crown” ከሚለው ቃል የተገኘው “coronation” ወይንም በእኛው ቋንቋ “ሥርዓተ ንግሥና” የሚባለው ጽንሰ ሃሳብ መፈጠሩንም ልብ ይሏል::
እርግጥ ነው በሽታው በዓለማችን ላይ ሰልጥኖ ንግሥናውን በማወጅ በበትረ ሥልጣኑ በዐሥር ሺህዎች የሚቆጠሩ የዓለማችንን ሕዝቦች እስትንፋስ ነጥቋል:: ቋንቋ፣ ዘር፣ ብሔር፣ ሥልጣን፣ ሀብትና ዝና፣ ድህነትና ብልፅግናን ሳይመርጥም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወገኖችን በክፉ ደዌው አልጋ ላይ ጥሏቸዋል::
የወረርሽኙን ምስል በቴሌቪዥን መስኮት ባስተዋልኩ ቁጥር የሚታወሰኝ የንግሥና ዘውዱ ወይንም የክብር አክሊል አምሳያነቱ ሳይሆን በሟች ወዳጅ መቃብር ላይ የሚቀመጠውን ክብ የአበባ ጉንጉን ያስታውሰኛል:: ስለዚህም ነው “መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ” የሚል ንዑስ ርዕስ የሰጠሁት:: የሥርዓተ ንግሥናን ጉዳይ “coronation” በተመለከተ ፈታ የሚያደርግ አንድ ታሪክ አስታውሼ ልለፍ::
“ዓለምን አንቀጥቅጦ ገዝቷል” እየተባለ የጀብድ ታሪኩ የሚተረክለት የፈረንሳዩ ገዢ ቀዳማዊ ናፖሊዮን ቦናባርቴ ((1769- 1821) በአንድ ወቅት የነገሥታት ደም ሳይኖረው እንደምን ሊነግሥ እንደቻለ ተጠይቆ ነበር ይባላል:: እጅግ በሚገርም ምጸታዊና ተምሳሌታዊ ገለጻ ለጠያቂዎቹ እንዲህ ሲል መለሰ ይባላል:: “እንዴት ንጉሥ ልትሆን ቻልክ? እያሉ ብዙዎች ለሚጠይቁኝ ጥያቄ መልሴ ይህ ነው::
እርግጥ ነው በደሜ ውስጥ የነገሥታቶቻችን ደም አልተቀላቀለም:: እንኳንስ በውኔ በህልሜም እነግሣለሁ የሚል ቅዠት አልነበረኝም:: አስቤውም አላውቅም:: ነገር ግን የወደፊት ዕጣ ፈንታዬ ምን ሊሆን እንደሚችል እያውጠነጠንኩ በፓሪስ አውራ ጎዳናዎች ላይ እየተጓዝኩ ስራመድ በመንገዴ ላይ አንድ ያረጀ ዘውድ (obsolete corona) ወድቆ አየሁ:: እኔም የተዋረደው ይህ ያፈጀና ያረጀ ዘውድ ምን ሊሠራ በመንገዴ ላይ እንቅፋት ለመሆን ተቀመጠ በማለት ተናድጄ ወደ ጥሻ ልወረውረው በእግሬ ወደ ላይ ሳጎነው ድንገት ዘውዱ (corona) ሳላሰብ አናቴ ላይ ወጥቶ ተከመረ:: ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ራሴን ንጉሥ ሆኜ አገኘሁት::”
ይህ የናፖሊዮን ቦናፓርቴ ገለጻ የሚሠጠን የሞራል ትምህርት ንግሥንና ፈልጎት ሳይሆን በአጋጣሚ እንዳገኘው ነው:: ዓለምስ መች የኮሮናን ንግሥና ፈለገች? ድንገት አይደል አናቷ ላይ ፊጥ ብሎ የነገሠው? የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ዓለምን ከዳር ዳር የወረረው ሀገራት ተዘናግተውና ተረጋግተው ባሉበት ሁኔታ ውስጥ ነው:: እንዲህ ዓይነት ክፉና ፈታኝ አጋጣሚ ይደርስብናል ብሎ የተጠናቀቀ ሀገር አልነበረም ማለቱ ይቀላል::
ይልቁንስ ኃያላን ሀገራት በጉልበታቸው ተመክተው ደካማውን ሀገር ለማስገበር ሲጥሩ፣ ጥለኞች ለመበቃቀል ሲጨካከኑ፣ ጦረኞች ቀስታቸውን ገትረው “ጠላት” ብለው በፈረጁት ላይ ሊያስወነጭፉ ሲያነጣጥሩ፣ ፖለቲከኞች ሥልጣን ለመናጠቅ ሲፋለሙ፣ ድሆች ለዕለት እንጀራቸው ሲባትሉ ወዘተ… ሁሉም በየፊናው የፊናውን ሊከውን ሲጣደፍ ነበር ዓለም አቀፉ ወረርሽኝ በዓለማችን ጭንቅላት ላይ ፊጥ ብሎ “ንግሥናውን በማወጅ” ሁሉንም ከንቱ የከንቱ ከንቱ ያደረገው:: ዳሩ ወራሪ ምን ርህራሄ አለውና!
መከራና ዕዳ፣ እንግዳና ሞት በድንገት፤
በዓለማችን ላይ የነገሠው የኮሮና ወረርሽኝ እንዳሻው በፕላኔታችን ላይ ለመቦረቅ እንዲያስችለው የአዳምን ልጆች በሙሉ ከአደባባዮቻቸው አርቆ፣ ከጎዳናዎቻቸው ላይ አባሮ፣ ከሥራ ገበታቸው ላይ አፈናቅሎ፣ ከስፖርትና ከመዝናኛ ሥፍራዎች ከልክሎ ማዕቀብ በመጣል “አንበርካኪነቱን” ለማረጋገጥ የፈለገ ይመስላል::
አሜሪካኖች “የአሜሪካ መንፈስ – American spirit” ብለው የሚጠሩት የባህል ማዕከላትን፣ የጥበባት ስቱዲዮችን፣ የሙዚቃ አዳራሾንና ታላላቅ ተቋማትን አቅፎ የያዘው ዝነኛው የኒዮርክ ታይምስ ስኩዌር ድምቀቱ ፈዞ ሞገሱ ተገፏል:: በአጭሩ ኮሮና ቫይረስ የጥፋት ሪከርዱን የሰበረበት የአጭር ርቀት የቤት ውስጥ መሮጫ ትራኩ አድርጎታል ማለቱ ይቀላል::
የሜሪካ ብሔራዊ መታወቂያና የነጻነት ሐውልት (1924) በቀኝ እጇ ከፍ አድርጋ የያዘችው ችቦ ብርሃኑ ደብዝዟል:: በብብቷ የታቀፈችው ምሥጢራዊ መጽሐፍም የእንቆቅልሹን ፍቺ ሊያመላክታት አልቻለም:: “I am a New Yorker” ትምክህት ከኒውዮርክ ነዋሪዎች አንደበት ከጠፋ ሰነበተ:: አልፎም ተርፎ ከበሽታው ስጋት የተነሳ ከኒዮርክ የመጣ እንግዳ “ነዎሩ!” የመባል ወጉን እየተነፈገ ፊት ይነሳል::
በአጭሩ ኮሮና ቫይረስ በተቀዳሚነት ዙፋኑን ዘርግቶከሚያስጨንቃቸው የዓለም ከተሞች ግንባር ቀደሟ ኒዮርክ ነች ማለቱ ይቀላል:: ይሄው ወረርሽኝ በሁለተኛነት መናገሻ ያደረገው ጣሊያንን ነው:: የጣሊያን ከተሞችም ሆኑ ዋናዋ ከተማ ሮም አንገታቸውን ዘልሰው በማንባት ለወረርሽኙ ገብረው አሜን ማለት የጀመሩት በአስገራሚ ፍጥነት ነው:: ቅድመ ልደተ ክርስቶስ 753 ዓመተ ዓለም የተመሠረተችውና “ዘላለማዊቷ ከተማ – Eternal City of the World” እየተባለች የምትሞካሸው “ታላቂቷ ሮም” ዛሬ አልጋ ላይ ወድቃ ሕዝቦቿም ደጃፋቸው ተቆልፎባቸዋል:: የሊዮናርዶ ዳቬንቺ ሞናሊዛ እንደ ቀድሞ መሳቋን አቁማለች::
የሚካኤል አንጂሎ ዳዊትም ጎሊያድን የሚጥልበት ጠጠር ከኮሮጆው ውስጥ ተሟጦበት ሐውልቱ የድንጋይ ጥርብ ብቻ ሆኗል:: 280 ቁጥር ያላቸው የከተማዋ የመዝናኛ ፏፏቴዎችና 900 አብያተ ክርስቲያኖቿ የድምጻቸውና የደውላቸው ልሳን ተዘግቶ የጎብኝ ድሃ ሆነዋል:: ራስ ገዟ የፓፓው መቀመጫ ቫቲካንም ክፉኛ ተክዛለች:: በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የሚርመሰመው ምዕመን ደጃፉ ከውስጥ ተቆልፎበት በሞት ፍርሃት ውስጥ ወድቋል::
ቅድስናን የተጎናጸፉት ፓፓው ለብቻቸው አደባባዩን ሲያቋርጡ የሚያሳየው ምስል ከተለቀቀ በኋላ ዓለም በአንድነት እንባውን በቁሙ አዝርቷል:: ሦስተኛዋ የቫይረሱ “ዓፄያዊ መንበር” ስፔን ነች:: ዋና መዲናዋ ማድሪድ የሀዘን ማቅ ለብሳ ማንባት ከጀመረች ሰንብታለች::
ዛሬ ዜጎቿ በነፍሳቸው እየተወራረዱ በጎዳናዎቿ ላይ የሚያደርጉት የኮርማዎች ግብግብና ፍልሚያ (Bullfi ghting) በእነርሱ አጠራር (Corrida de toros) መልኩን ቀይሮ ፍልሚያው ከኮሮና ቫይረስ ጋር ሆኗል፤ (Corona fi ghting) ልንለው እንችላለን:: ክብ እየተሠራ (plaza de toros) ከኮርማዎች ጋር ራስን እንደ ኮርማ ቆጥሮ መዋጋት ሳይሆን ክቡን “ኮቪድ 19” መፋለም ሆኗል ብንልም ያስኬደናል::
ዕድሜ ጠገቦቹ የዓለማችን ታላላቅ የእግር ኳስ ቡድኖቿና ክዋክብት ሪያል ማድሪድ (1866)፣ አትሌቲኮ ማድሪድ (1828) እና ሰቪላ ስፔን (1772) ስታዲዬሞቻቸው በቫይረሱ ቀይ ካርድ አስገዳጅነት ደጃፋቸው ተከርችሟል፤ የቅሪላዋ ጠቢባንም ጫማዎቻቸውን ሰቅለው እቤት ውለዋል::
እብዱና ወፈፌው፣ ምሁሩና ተራው ዜጋ፣ ፖለቲከኛውና አክቲቪስቱ፣ ሸቃዩና ገብይው በ“ሃይ ባይ ሙሉ ነጻነት” የሚተራመስበት የለንደኑ ሃይድ ፓርክ (Hyde Park) ከተጎራባቹ ገናናው የኤልሳቤጣዊያን ባኪንግሃም ቤተ መንግሥት ጋር አብረው መርዶ ተቀምጠዋል:: ጠቅላይ ሚኒስትሯና ልዑሏ በወራሪው ጠላት ተማርከው ደዌው የፊጥኝ አስሮ ለሆስፒታል ዳርጓቸዋል:: የሩሲያዋ ገናና መዲና ቅዱስ ፒተስበርግም ከተዘጋች ሰነበተች::
ሼክስፒር በሕይወት ቢኖር ኖሮ ለውቧ ከተማ ቅኔ ሳይሆን የመርዶ ግጥም ይጽፍላት ነበር:: የኤፍል ማማ (Eiff el Tower 1889) መታወቂያዋ የሆነው የፈረንሳዩዋ ፓሪስም ጥቁር ከል ለብሳለች:: የጥበብና የፋሽን፣ የሽቶና የቅባት ማራኪ ጠረኖቿም ከደማቋና ውቧ ከተማ አየር ላይ ተንነው ጠፍተዋል:: በምትኩ ደረት ጥለው የሚያለቅሱ ሙሾ አምሺ ሕዝቦቿ በየቤታቸውየሀዘን ፍራሽ አንጥፈው ለቅሶ ተመቀምጠዋል::
ከአፍሪካ አህጉር ውስጥም በሀብት የበለፀገችው ደቡብ አፍሪካ በማህጸኗ ሸሽጋ የያዘቸው የዓለማችን 90 ከመቶ የፕላቲኒዬም ማዕድኗና 41 ከመቶ የወርቅ ክምችቷ ኮሮናን ለመታደግ አቅም አልሆናትም:: የፈርኦን ግዛቷ ግብፅም እንባዋን እያዘራች “የአባይን አማልክት” እየተለማመነች ትገኛለች::
ፒራሚዶቿን ለመጎብኘት የሚጎረፉት ቱሪስቶቿ ነጥፈውባትም ኢኮኖሚዋ ላሽቋል:: ኮሮናን እንደ ሸቀጦቿ ለዓለም ያከፋፈለችው ቻይናም ሆነች በቅርቡ ከእሳት ወላፈን የተረፈችው አውስትራሊያ፣ ጀርመንም ሆነች ካናዳ፣ ብራዚልም ሆነች አርጀንቲና፣ ግሪክም ሆነች ስዊስ ከዓለማችን አጥናፍ እስከ አጥናፍ የተዘረጉት ሀገራት በሙሉ ለወረርሽኙ በግዛትነት ፀድቀው ዜጎቻቸው እየረገፉ፣ ህሙማኖቻቸው እያጣጣሩ በኤሎሄ ጣር እየቃተቱ ነው:: በእናት ሀገሬ ምድርም እስከ አሁን ድረስ ከአርባ በላይ ውድ ዜጎቻችን አልጋ ላይ ወድቀው ሁለቱን ቀብረናል:: ልዑል አምላክ ይህንን ቀሳፊ መቅሰፍት በጥበቡ እንደሚገታልን ፅኑ እምነት አለን::
የጨለማው መበርታት ከዋክብቶችን ያደምቃል፤
እርግጥ ነው የዓለማችን ኢኮኖሚ ቅስሙ እየተሰበረ ነው:: የፖለቲካው መነቃቃትም ፈዞ ተክዟል:: የማሕበራዊ ቁርኝቱ ሰንሰለት እየሰለለ ሰው ሁሉ የራሱን ነፍስ ሊያድን እየጣረ ነው:: ቤተ እምነቶች ተዘግተው የምዕመኑ አምልኮ በየዓለም ክፍሎች ሁሉ ተቋርጧል:: እማይካደው እውነት ኮሮና እንደ ስሙ ዙፋን ላይ ተኮፍሶ ነፍሶችን እየቀጠፈ፣ ሚሊዮኖችን ለአልጋ ቁራኛ ዳርጓል:: ይሁን እንጂ ተስፋ ግን አለ::
ጠቢባን እንዳረጋገጡልን፤ “ያለ ምግብ አርባ ቀናት፣ ያለ ውሃ ሦስት ቀናት፣ ያለ አየር ስምንት ደቂቃ መኖር ይቻላል፣ ያለ ተስፋ ግን አንድ ሰከንድ በሕይወት መኖር አይቻልም::” ስለዚህም ተስፋ አይቆረጥም:: የፈጣሪ ቸርነት ተጨምሮበት የሀገራችንና የዓለም ጠቢባን በቅርቡ መድኃኒት ተገኘ ብለው የምሥራቹን እንደሚያበስሩን እናምናለን::
“የብሔራዊ ፈተናችን ጉዳይስ?”
አውነቱን ሳንሸሽግ እንነጋገር ካልን ሀገራችን በዚህ ክፉ በሽታ ክፉኛ ልትፈተን እንደምትችል እናውቃለን:: ሕዝባችንም ግራ ቢጋባ አይፈረድበትም:: ይሁን እንጂ የመከራ ቀናት አጭር ስለሆኑ ይህንን ክፉ ጊዜ እንደምንሻገረው ልንጠራጠር አይገባም:: ለሀገራችን የምንመኘው ብልፅግናም ሆነ ሕዝባችን የጓጓለት የህዳሴ ግድብ ብሥራት እውን ሆኖ በሀገራችን ሰማይ ላይ በሀሴት የምንዘምርበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም::
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ ፈጣሪ ለምልጃ መዘርጋቷ እንዳለ ሆኖ ለልማትም ወደ ምድር መዘርጋቷ በቅርቡ እውን ይሆናል:: ሕዝቦቿ ለምህረት የሚቃትቱትን ምልጃ ፈጣሪ ከልቡ ሰምቶ የልባችንን መሻት እንደሚሞላልን ከልብ እናምናለን:: በእስካሁኑ ጉዞ ቫይረሱን ለመቆጣጠር መንግሥት ላከናወናቸው መልካም ጥረቶች “አበጀህ!” ብለን ባናመሰግነው አደራ በል እንሆናለን::
መንግሥት የጀማመራቸው ሥራዎች በእጅጉ የሚያበረታቱ ናቸው:: የሀገራችን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም ከባህላዊ የመድኃኒት ጠቢባን ጋር አብሮ ለመሥራት መወሰናቸው በእጅጉ ያስመሰግናቸዋል:: በቅርቡም ለእኛ ብቻም ሳይሆን ለዓለም በሞላ መልካም ዜና እንደሚያሰሙን ተስፋ እናደርጋለን::
በረጂሙ የሀገራችን ጉዞ ውስጥ ያልተጋፈጥናቸውና በአሸናፊነት ያልተወጣናቸው የፈተና ዓይነቶች እንደሌሉ አበውና ታሪክ ምስክር ናቸው:: ይህ ተግዳሮት በዘመናችንና በትውልዳችን ፊት ቢገሸርም በአሸናፊነት መወጣታችን ግን እውነት ነው:: እስከዚያው እንተጋገዝ፣ እንተባበር፣ እጆቻችንን አዘውተረን እንታጠብ፣ በተቻለ መጠን ባይመችም እንኳ ከማሕበራዊ ትፍግፍግና ቅርብርብ ራሳችንን ለመጠበቅ እንሞክር::
የመንግሥትና የጤና ባለሙያዎችን ምክር እናክብር:: ፖለቲከኞች የጨዋታ ሜዳችሁን ግብግብ ለሥልጣን ሳይሆን የጊዜውን ፈታኝ ወረርሽኝ ለማንበርከክ ይሁን:: ነጋዴዎች በዚህ ክፉ ጊዜ ክፉ ተግባር ላለመፈጸምና ክፉ ጠባሳ በግላችሁና በቤተሰባችሁ ታሪክ ላይ ላለማሳረፍ ጥንቃቄ አድርጉ::
ይህንን ክፉ አጋጣሚ ለግል ብልፅግና ትርፋማ ለማድረግ ህሊናችሁን ቀብራችሁ ለክፋት የምትሰሩ ወገኖች ወደ አእምሯችሁ ተመልሳችሁ አደብ ግዙ:: ያኔ ብሔራዊ ፈተናችንን በድል ተወጥተን አንድ የታሪክ አምድ በታሪካችን ሰገነት ላይ እናቆማለን:: ሰላም ይሁን!!!
አዲስ ዘመን መጋቢት 30/2012
በጌታቸው በለጠ/ዳግላስ ጴጥሮስ)