ከውጭ ተመላሾች በለይቶ ማቆያ ማዕከላት ለ14 ቀናት እንዲሰነብቱ እየተደረገ ነው፡፡ በማዕከላቱ በሚኖራቸው ቆይታ የጤና ምርመራ ተደርጎላቸው ከኮሮና ቫይረስ ነፃ ከሆኑ ሕዝባቸውን እንዲቀላቀሉ ይደረጋል:: ቫይረሱ ከተገኘባቸውም የሕክምና ክትትል ማድረግ ይጀምራሉ፡፡
ይህ ዛሬ በየትኛውም ዓለም እየተተገበረ ያለ አሠራር ነው፡፡ የእኛን አገር ልዩ የሚያደርገው ወደ ለይቶ ማቆያ ማዕከላቱ የሚገቡት አንዳንድ ዜጎቻችን ግራ የሚያጋባ ድርጊት ነው፡፡ ወደ ማዕከላቱ ከገቡ በኋላ ለጥበቃ ሠራተኞች ጉቦ ሰጥተው የወጡ ሰዎች ተገኝተዋል፡፡ ቀደም ብሎ አንድ ከሳዑዲ አረቢያ የተመለሰ ግለሰብ የኮሮና ቫይረስ ምልክት ታይቶበት ተጠርጥሮ ወደ ለይቶ ማቆያ በአምቡላንስ በሚወሰድበት ጊዜ አምልጦ ወደ ትውልድ መንደሩ በመመለስ ላይ ሳለ በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወሳል።
የእነዚህ ሰዎች ተግባር የኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያምን ንግግር ያስታው ሰኛል፡፡ ኮሎኔሉ ወደዘመቻ የሚላኩ ወጣቶች ከመኪና ላይ እየዘለሉ ለማምለጥ ሲጥሩ አደጋ እንደሚደርስባቸው ሲገልጹ «ገና ለገና ጦር ሜዳ ሄጄ እሞታለሁ በሚል ከመኪና ላይ እየዘለለ የሚሞት ወጣት ነው ያለው» ብለው ነበር፡፡ የኮሮና ዘመን ፈርጣጮችም ገና በሽታው እንዳለባቸው ሳይረጋገጥ በደመነፍስ በሚያደርጉት ሽሽት ወዲ ወዲያ ሲሉ ለቫይረሱ ተጋልጠው ሊያርፉ ይችላሉ፡፡
ፖዘቲቭ ከነበሩም ወገኖቻቸው ላይ ሊያስተላልፉና በገዛ እጃቸው የመሞት ዕድላቸውን ሊያሰፉ ይችላሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ከመቆያ ማዕከላቱ ከወጡ በኋላ ወዴት ነው የሚሄዱት? ወላጆቻቸው ጋ ወይስ ልጆቻቸው ጋ ? በበኩሌ ሁለቱም ጋር የሚሄዱ አይመስለኝም፡፡ እንደእኔ ከመቆያ ማዕከላቱ አምልጠው ከወጡ በኋላ እዚህም እዚያም እየተደበቁ የሎሬት ጸጋዬን «ተወኝ» የተሰኘ ግጥም በመጠኑ አስተካክለው ለኮሮና የልምምጥ ደብዳቤ የሚጽፉለት ይመስለኛል፡፡ እንዲህ የሚል፡-
ላታስታምም አትመመኝ
ላትጥል አታንጠልጥለኝ
ይቅር ካንጀትህ ቁረጠኝ ኮሮና አልነካህም በለኝ፡፡
እጅ እጅ አልበል አታባክነኝ
ባክህ ወንድ ነው ቆራጡ እንትፍ
እርግፍ አድርገህ ተወኝ፡፡
አየህ እኔ አባት አለኝ ርቀትሽን ሳትጠብቂ ጉድ አደረግሽኝ
አስበላሽኝ የሚለኝ
አየህ ደግሞ እህት አለኝ
እጅሽን ዘርግተሸ ጨብጠሽ ሰው
ነክተሽ ነው የምትለኝ
እና ተወኝ ባክህ ተወኝ
እንድታውቀው አለኝ እናት
እምትመስለኝ እምመስላት
ጎረቤት ፊት የምታፍር ልጅሽ ታመመች ሲሏት !
እና አልይዝሽም በለኝ
ባክህ ካንጀትህ ቁረጠኝ
ምስጢሩ እንደሁ ከእኔ ይቀራል
እኮ ለማን ለማ ይወራል
ማን ይተርፋል ማን ይኖራል
ብቻ ከወጥመድህ ለየኝ
አልችልህም ንቀህ ማረኝ
ኮሮና ደብዳቤው ሲደርሰው የሚገረም ይመስለኛል፡፡ ያው ከለይቶ ማቆያ ማዕከል ያመለጡት ተቅበዝባዦች ተረጋግተው አንድ ቦታ መቀመጥ ስለማይችሉ በአድራሻቸው መልስ ሊጽፍላቸው አይችልም፡፡ ነገር ግን ያው አደን ላይ ነውና ሁኔታውን በማጤን የደበበ ሰይፉን «አደን» የተሰኘች ግጥም አስታውሶ አንዲት ቃል ሳይጨምር ሳይቀንስ እንዲህ የሚል ይመስለኛል፡-
አሳዳጄን አመለጥኳት
አመለጠችኝ ያሳደድኳት፡፡
ኗሪ ሆንኩኝ እንደ ፍየል
በነብርና ቅጠል መሃል፡፡
አቤት አለች ያልጠራኋት
የጠራኋት ድምጽም የላት፡፡
ራቂኝ የምላት ጎኔ ወድቃ
ቅረቢኝ የምላት ከእኔ ርቃ
አንዴ ስታደን አንዴም ሳድን
ዕረፍት አጥቼ ስባክን
የእድሜዬን ጀምበር ብታዘባት
ልትጠልቅ ምንም አልቀራት፡፡
ለአሁኑ የአዲስ አበባ ከተማ ኗሪዎች በሰጡት ጥቆማ ታግዞ ፖሊስ ከለይቶ ማቆያ የወጡ ሦስት ሰዎችን ወደ ኅብረተሰቡ ሳይቀላቀሉ ወደ ማቆያ እንዲመለሱ ማድረግ ችሏል። ድርጊቱ ስጋት የገባው መንግሥት ከውጭ አገር የሚመጡ ሰዎች በሚያርፉባቸው ሆቴሎች፣ የሕክምና ተቋማትና በሌሎች ለይቶ ማቆያነት በተዘጋጁ ስፍራዎች የተጠናከረ ጥበቃ ማድረግ ጀምሯል፡፡
ወደ መቆያ ማዕከላቱ ላለመግባት ትንቅንቁ የሚጀምረው በአየር ማረፊያ ነው:: ሸገር ራዲዮ መጋቢት 15 ቀን 2012 ዓ.ም ከዱባይ ወደ አዲስ አበባ የመጡ አንድ መንገደኛ ወደ ሀገር ከገቡ በኋላ አየር መንገድ ውስጥ ባሉ ሰዎቻቸው ታግዘው ወደ ለይቶ ማቆያ ማዕከላት ሳይገቡ በቀጥታ ወደ ኅብረተሰቡ መቀላቀላቸውን የሚገልጽ ዘገባ አቅርቦ ነበር፡፡ በቅርቡም አንድየሃይማኖት አባት ወደ አገር ውስጥ ከገቡ በኋላ በቀጥታ ማህበረሰቡን እንደተቀላቀሉ ሲገለጽ ተሰምቷል፡፡
እነዚህ ሁኔታዎች ጥቂት የማይባል የኅብረተሰቡ ክፍል ስለቫይረሱ ያለው ግንዛቤ ክፍተት እንዳለበት ይጠቁማሉ:: መሰራት ያለባቸው ተጨማሪ ሥራዎች ከወዲሁ ካልተሰሩ በቀጣይም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በሚደረገው እንቅስቃሴ ላይ ጥላ ያጠላሉ፡፡ በቅርቡ የጤና ሚኒስትሯ እንደተናገሩት፤ አዲስ አበባ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ከጀመሩ ሦስት ተቋማት በተጨማሪ በክልሎችም ለማስጀመር እየተሰራ ነው።
አሁን ላይም በአራት ቦታዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ለማድረግ ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጸው፤ ከእነዚህም መካከል በመቀሌ የምርመራ ሥራ ጀምሯል። ባህርዳር፣ አዳማና ሃሮማያ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ምርመራውን ለመጀመር አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋል።
በተጨማሪም በጂግጂጋ፣ በአርሲ፣ በጅማ፣ በጎንደርና በሐዋሳ ምርመራውን ለመጀመር ሥልጠናዎች ተጠናቀው አስፈላጊው ቁሳቁስ እየተሟላላቸው ነው። ጎን ለጎንም አዲስ ለሚቋቋሙት የምርመራ ማዕከሎች የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስፈላጊውን የቴክኒክ ድጋፍ እየሰጠ ነው።
በቀጣይ ደግሞ በደሴና በአርባምንጭ ምርመራውን ለማስጀመር ለጤና ባለሙያዎች ሥልጠና መስጠት ይጀመራል። እነዚህ ተግባራት በክልሎች አካባቢ የሚደረገውን የምርመራ ሥራ በከፍተኛ ደረጃ ያጠናክራሉ። ነገር ግን እያየን ካለነው ሽሽት በመነሳት ምርመራ ለማድረግ ፍቃደኛ የማይሆኑ ብዙ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ሊኖሩ ስለሚችሉ የበሽታው ስሜት የተሰማው ሰው ለጤና ተቋማት በማሳወቅ ምርመራውን በአፋጣኝ ማድረግ እንደሚገባው ለማስገንዘብ ሰፊ ስራ መሰራት አለበት። የኮሮና ጀምበር ትጥለቅ!
አሳዳጄን አመለጥኳት
አመለጠችኝ ያሳደድኳት፡፡
ኗሪ ሆንኩኝ እንደ ፍየል
በነብርና ቅጠል መሃል፡፡
አቤት አለች ያልጠራኋት
የጠራኋት ድምጽም የላት፡፡
ራቂኝ የምላት ጎኔ ወድቃ
ቅረቢኝ የምላት ከእኔ ርቃ
አንዴ ስታደን አንዴም ሳድን
ዕረፍት አጥቼ ስባክን
የእድሜዬን ጀምበር ብታዘባት
ልትጠልቅ ምንም አልቀራት፡፡
አዲስ ዘመን መጋቢት 30/2012
የትናየት ፈሩ
ሽሽት ከኮሮና ለማምለጥ