የኖብል ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ወረርሽኝ በተለይ ሐብታሞቹን አገራት እያተራመሳቸው ይገኛል።የበትሩ መበርታት ሕዝቦቻቸውንም ግራ መጋባት ውስጥ ጥሏል።የንፅህና ጉድለት (የሳኒቴሽን) ችግር ጎጆ የሰራባት አፍሪካ ከአሜሪካ እና አውሮፓ አገራት አንፃር ስትመዘን የቫይረሱ ሥርጭትና ጉዳት እስካሁን እጅግ አነስተኛ መሆኑ በተአምርነቱ አነጋጋሪ ሆኗል።
ቁጥሮች ስለአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ በቻይና መከሰቱ ከተሰማ አራት ወራት ገደማ ቆጥሯል። ቫይረሱ የቻይናን ዉሀን ግዛት መነሻውን አድርጎ በአሁኑ ወቅት 205 አገራትና ግዛቶችን አዳርሷል። በእነዚህ አጭር ጊዜያት ከ 1 ነጥብ 2 ሚልየን በላይ የዓለም ሕዝብ በቫይረሱ የተጠቃ ሲሆን ከ67 ሺ በላይ ሕዝብ ለሞት ተዳርጓል።
(ወርልድ ሜትርስ) በአሁኑ ወቅት እንደ ጣልያን ባሉ አገራት በ24 ሰዓት ጊዜ ውስጥ ከ800 በላይ የሰዎች ሞት የሚመዘገብ ሲሆን፤ በአፍሪካ ግን ባለፉት አራት ወራት በድምሩ በሞት የተነጠቀችው ልጆችዋ ቁጥር 330 ብቻ ነው። ዩናይትድስቴትስ አሜሪካ እስከ እሁድ መጋቢት 27 ቀን 2012 ዓ.ም ዕለት ድረስ ከ322 ሺ በላይ የኮሮና ተጠቂዎችን በመያዝ የመሪነቱን ደረጃ ከቻይና ከተረከበች ዋል አደር ያለች ሲሆን፣ ስፔን ከ130ሺ በላይ ተጠቂዎችን በመያዝ ትከተላለች።
ቻይና 81 ሺ በላይ ህሙማንን በማስመዝገብ ደረጃዋ ወደ ስድስተኛ ዝቅ ብሏል። በሞት ሪፖርትም ቢሆን ጣልያን 15 ሺ 887፣ ስፔን 12ሺ418፣ አሜሪካ 9ሺ 149 በመያዝ በቅደም ተከተል ተቀምጠዋል። ዓለም በአጠቃላይ በኮሮና ህመም የተያዙ ህዝቦችዋ ቁጥር ከ1 ነጥብ 2 ሚልየን የዘለለ ሲሆን የሟቾች ቁጥርም ከ67 ሺ በላይ ተሻግሯል። የአፍሪካ አህጉር ግን በንፅፅር እስካሁን በቫይረሱ የተጠቁ ልጆቿ ቁጥር ሲገመገም ተመስገን የሚያስብል ነው።
በአፍሪካ እስከ እሁድ መጋቢት 27 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ በድምሩ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥሩ 8ሺ ተሻግሯል። 330 ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል። በአልጀሪያ 105፣ በግብፅ 66፣ በሞሮኮ 50 ያህል ከፍ ያለ የሞት መጠን ተመዝግቧል። ይህ ብቻ እንዴት ሊሆን ቻለ? ምስጢሩስ ምንድነው? የሚለው አሜሪካ እና አውሮፓውያኑን ማስጨነቁ ቀጥሏል። እውነት ግን ሚስጥሩ ምን ይሆን? ብዙዎች አፍሪካ በቂ የሆነ ምርመራ አለማድረጓን ያነሳሉ። በእርግጥም ይህ ምክንያት ውሃ የሚያነሳ ይመስላል።
ባለፈው እሁድ ዕለት ብቻ አንድ ሚለየን ህዝብ ያላት ጅቡቲ 252 ሰዎች በ24 ሰዓት እድሜ መመርመር ስትችል፤ ከ100 ሚልየን የላቀ ህዝብ ያላት ኢትዮጵያ 59 ብቻ መርምራለች። እሁድ መጋቢት 27 ይፋ እንደተደረገው በ 24 ሰዓት ጊዜ ውስጥ በኬንያ 530 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 16 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በጅቡቲ 252 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 8 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።
በኢትዮጵያ 59 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 5 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ቁጥሩ ብቻውን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ለመለየት ገና ብዙ ርቀት መጓዝ የሚጠበቅብን መሆኑን ይናገራል፡፡ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አንዳንዶች ባለሙያዎች ግን በዚህ ሀሳብ አይስማሙም። በአፍሪካ የቫይረሱ ስርጭት ስር ሰዶ ቢሆን እየታመመ ወደ ጤና ተቋማት የሚመጣው ህዝብ ቁጥር ይጨምር ነበር የሚል መከራከሪያ ያቀርባሉ። ያም ሆነ ይህ በፈጣሪ ረቂቅ ሥራ ከኮሮና ስጋት ጋር እነሆ አራት ወራት ተራምደናል።
ከዚህ በኋላ ሰፋ ያለ ችግር አፍሪካን ቢገጥማት ምን እንሆናለን የሚለው ስጋት ግን አልተቀረፈም። አንዳንድ ያነበብኳቸው መረጃዎች እንደሚጠቅሱት በአለም የጤና ድርጅት የጤና ተቋም ምዘና ደረጃ ጣሊያን ከፈረንሳይ ቀጥላ ከአለም 2ተኛ ስትሆን ከ191 ሀገራት ኢትዮጵያ በ180ኛ ላይ ትገኛለች። ይህ አሃዝ አቅማችንን የሚያሳይ ነው። በአሁኑ ሰዓት ከ110 ሚሊዮን ህዝብ ከ 2ሺ ሰው በታች እየተመረመረ ነው። በቀን 3 እና 2 ሰው ተገኘ እየተባለ እስከአለፈው እሁድ ድረስ ብቻ 43 ደርሰናል።
አሜሪካ በቀን ውስጥ እስከ 300 ሺ ሰዎችን ምርመራ ስታደርግ ውጤቱ በ15 ደቂቃ ውስጥ ይፋ የሚደረግ ነው። የአለም ጤና ድርጅት ይህ ወረርሽኝ በአንድ ሀገር ከገባ ከ50 እስከ 60 በመቶ አጠቃላይ ህዝብ ያጠቃል ብሎ የወረርሽኙን አቅም ያስቀመጠ ሲሆን ይህም በኢትዮጵያ ስናሰላው ከ110 ሚሊዮን ህዝብ ውስጥ ወደ 60 ሚሊዮኑ በቫይረሱ ሊጠቃ ይችላል። ከነዚህ ውስጥ ደግሞ 20 በመቶ ማለትም 12 ሚሊዮኑ የሀኪም እገዛ ሊለያቸው አይገባም። በተቀመጠው ስሌት መሰረት ከ60 ሚሊዮኑ 5 በመቶ ማለትም 3 ሚልየን ህዝብ አጋዥ የመተንፈሻ የሜዲካል መሳሪያ (Ventilator) የሚያስፈልጋቸው ናቸው።
አንዳንድ የህክምና ባለሙያዎች የመተንፈሻ መሳሪያ ሊያስፈልጋቸው ይችላል ተብሎ የሚገመቱ ወገኖች ቁጥር ወደ 200 ሺ ዝቅ ያደርጉታል። በእኔ አተያይ ግን ይህ ቁጥር በጣም ዝቅ አድርገን ወደ 50 ሺ ብናወርደው እንኳን አገሪቱ ልትመልሰው የማትችለው መሆኑን ሳስብ መደንገጤን መደበቅ አልሻም።
ያስደነገጠኝም ምክንያት በአሁን ሰዓት በአገሪቱ ውስጥ ያለው የአርቴፊሻል የመተንፈሻ መሳሪያ ቁጥር 430 ብቻ መሆኑን ማወቄ ነው። በተለይ በአሁን ሰዓት ከኮሮና ቫይረስ ስርጭት ጋር ተያይዞ ታላቋ አሜሪካንን ጨምሮ እነ እንግሊዝ የመተንፈሻ መሳሪያ እጥረት ገጥሟቸዋል። ቢቢሲ እንደዘገበው እንግሊዝ በአንድ ሳምንት እድሜ ውስጥ በአስቸኳይ 18 ሺ የመተንፈሻ መሳሪያ ያስፈልገኛል ብላለች።
በአለም ገበያ እርዳታው ቀርቶ በግዥ እንኳን መሳሪያዎቹን በዚህ ወቅት በቀላሉ ማግኘት ፈታኝ መሆኑ አይቀሬ ነው። ይኸን ጠለቅ ብለን ስናስብ የተጋረጠብን ፈተና የቱን ያህል ከባድና የማንችለው መሆኑን እንረዳለን። እኛ ግን በተቃራኒው ልበ ደንዳና ሆነናል። የሰዎች እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እንኳን ሲታይ እምብዛም አመርቂ ለውጥ አለማሳየቱ ሲበዛ አሳሳቢ ሆኗል። ምናልባት ተከታዩ ወዳጄ ታምሩ ገዳ ያሰፈረው መጣጥፍ ጠቃሚ በመሆኑ እጋራዋለሁ። በኮሮና መሰቃየት በእኛ ይብቃ! እኛ በጣሊያን አገር ሚላን ነው የምንኖረው።
አሁን ላይ በሚላን ህይወት ምን እንደሚመስል ልገልጽላችሁና በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ውስጥ ሆኜ እናንተ እኛ ከሰራነው ስህተትና በውጤቱም ከገባንበት አጣብቂኝ ህይወት የምትማሩት ቁም ነገር አለ ብዬ ነው ይህንን የምጽፍላችሁ።አሁን ላይ ሁላችንም በማቆያ (Quarantine) ውስጥ ነው ያለነው።ፖሊሶች ጥብቅ ቁጥጥር እያደረጉ ሲሆን ማንኛውንም ከቤት ውጪ ሲዘዋወር ያገኙትን ሁሉ በቁጥጥር ስር ያውላሉ፡፡ ሁሉም ነገር ዝግ ነው፡- የንግድ ሱቆች፣ ሞሎች፣ የሽያጭ እቃ ማዕከሎች ሁሉም ነገር ዝግ ነው።
የአለም ፍጻሜ ነው የሚመስለው! ለኑሮ ተስማሚና ጤናማ ህይወት ታስተናግድ የነበረችው ጣልያን ዛሬ ላይ በእያንዳንዱ ሰዓታትና ቅጽበት ከጨለማ ውጪ ምንም የሌለባት የተወረረች ከተማ መስላነው የምትታየው።እኔ ራሴ ተመልሼ በዚህች መሬት ላይ እንደቀድሞው በህይወት እኖራለሁ የሚለው ተስፋዬ ጨልሟል።እዚህ አገር ህዝቡ ግራ ገብቶታል፣ በመከፋት አንገቱን አቀርቅሯል፤ተስፋ በመቁረጥም ይህ ሁሉ መዓት እንዴት እንደታዘዘበትና ይህም በቅዠት እንጂ በውን የማይመስል የጭንቅ ወቅት መቼ እንደሚያበቃ ግራ ገብቶት በየቤቱ ተዘግቷል፡፡ ይህ ክፉ ቀን ግን የጀመረው ዝም ብሎ አልነበረም። አንድ ትልቅ ስህተት ነበር።ገና የኮሮና ቫይረስ (COVID19) አገራችን ጣሊያን እንደገባ በይፋ በተነገረባቸው የመጀመሪያዎቹ ጊዜያት ህዝቡ ምንም ነገር እንዳ ልተፈጠረ አኗኗሩን እንደተለመደው ቀጠለ።ህዝቡ ወደ ስራ መሄዱን አልተወም፣ወደ መዝናኛ ቦታዎች እንደተለመደው በጋራ ይሄዳል እንደ እረፍት ጊዜ ከጓደኞቹ ከሌሎቹም ጋር እንደተለመደው በብዙ ቁጥር መንጎዱን አላቆመም።ሁሉም መጨረሻውን ሳያስብ ትክክል ያልሆነ የኑሮ ዘይቤውን ቀጠለ፤ እናንተም እንደዚህ እየሆናችሁ ነው።ልለምናችሁ፤ እየቀለድኩ አይደለም፤እባካችሁ ተጠንቀቁ! የምትወዷቸውን ሁሉ፣ቤተሰቦቻችሁን፣ወላጆቻችሁን፤አያቶቻችሁን ከዚህ መቅሰፍት ጠብቁ! ይህ በሽታ በተለይ ለነሱ እጅግ አደገኛ ነው፡፡ እዚህ በቫይረሱ ምክንያት በየእለቱ የ200 ሰዎች ህይወት እየተቀጠፈ ነው።
ይህ የሚሆነው ሚላን ውስጥ ያለው መድሐኒት ስለማይረባ አይደለም፤ከመድሀኒት ጋር ባለ ብቃት ሚላን ከዓለም ከፊት ተርታ ከሚሰለፉት አንዷ ነች። ለበርካቶች በየእለቱ ሞት ምክንያት እየሆነ ያለው ደግሞ ለእያንዳንዱ ለቅርብ ክትትል የሚበቃ በቂ ቦታ ባለመኖሩ ነው።
በዚህም ምክንያት ብታምኑም ባታምኑም ሀኪሞች ማንን እናትርፍ ሳይሆን ማን ቢሞት ብዙዎችን መታደግ ይቻላል የሚል አጣብቂኝ ሁኔታ ውስጥ ገብተዋል። ይህ ሁሉ የሆነው ቫይረሱ ወደዚህ ቦታ መግባቱ በተነገረበት የመጀመሪያዎቹ ጊዜያት በህዝቡ ዘንድ የነበረው ሞኝነትና ችግሩን ተገንዝቦ ፈጥኖ ጥንቃቄ ከማድረግ ይልቅ ህይወት በነበረው ሁኔታ እንዲቀጥል በማድረጉ ነው፡፡
ጣሊያን ውስጥ መላ አገሪቱ ማቆያ (Quarantine) ውስጥ እንዳለች ቁጠሩት፤ 60 ሚሊዮን ህዝቧ ማቆያ (Quarantine) ውስጥ ነው እንደ ማለት! ታዲያ ህዝቡ በመጀመሪያ ላይ የተሰጡ ማስጠንቀቂያዎችን አዳምጦ ተግባር ላይ ቢያውል ኖሮ ይህ ሁሉ መጥፎ ቀን እንዳይመጣ ማድረግ ይቻል ነበር።እናም እባካችሁ ሳይመሽ ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችሁንና የምትወዷቸውን ሁሉ ጠብቁ! እንደመቋጫ እንደ አገር አደጋ ላይ ነን።
ምንም እንኳን መንግስት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የተለያዩ ጥረቶች እንዲሁም መመሪያዎችን በማውጣት ሥራ ላይ ያዋለ ቢሆንም በአቅም ማነስ እና በቸልተኝነት ምክንያት የታሰበው ለውጥ እየመጣነው ማለት አይቻልም። በቤት ውስጥ መቀመጥ፣ ርቀትን መጠበቅ፣ መጨባበጥን ማስቀረት፣ እጅን አዘውትሮ መታጠብና የመሳሰሉ የጥንቃቄ መንገዶች ለመተግበር ጥሩ ጅማሮ ቢኖርም የተጠናከረ ነው ማለት አይቻልም። ሌላው የመንግስት ለአደጋ ምላሽ ለመስጠት ያለው አቅምና ዝግጁነት ከክልል ክልል የሚለያይ የመሆኑ ጉዳይ ነው።
ሪፖርተር እንደዘገበው በኢትዮጵያ በፊትም በአንፃራዊነት የተሻለ የጤና አገልግሎት ደረጃ ያላቸው አራቱ ክልሎች ብቻ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ዝግጁ እንደሆኑ፣ የዓለም ጤና ድርጅት የኢትዮጵያ ቢሮ ያደረገው ግሞገማ አመልክቷል።
የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በተቀመጠው ዓለም አቀፍ መመዘኛ መሥፈርቶች መሠረት ከተመዘኑት ዘጠኙ የክልል መንግሥታት መካከል አራቱ ዝቅተኛውን የዝግጅት ደረጃ እንዳሟሉ፣ የዓለም ጤና ድርጅት የኢትዮጵያ ቢሮ መገምገሙን ሪፖርተር ያገኘው የሰነድ መረጃ አመልክቷል።
ቢሮው የግምገማውን ውጤት የያዘ ሪፖርት ለመንግሥት ተቋማት፣ በተጠናቀቀው እ.ኤ.አ. ማርች ወር ላይ ማቅረቡን መረጃው ያመለክታል። አገሮች የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያስችላቸውን አቅም እንዲገነቡ የዓለም ጤና ድርጅት ዘጠኝ መሠረታዊ መሥፈርቶችን ያስቀመጠ ሲሆን፣ በእነዚህ መመዘኛ መሥፈርቶች ድምር ውጤት መሠረት ከ80 በመቶ በላይ ያመጡ ዝግጁ ተብለው እንደሚቆጠሩ ከመረጃው ለመረዳት ተችሏል። በእነዚህ መመዘኛ መሥፈርቶች ተገምግመው ከ80 በመቶ በላይ ያመጡት ክልሎች ኦሮሚያ፣ አማራ፤ ደቡብና የትግራይ ክልሎች መሆናቸውን መረጃው ያመለክታል።
በዚህም መሠረት ኦሮሚያ 82 ነጥብ 7 በመቶ፣ አማራ 80 ነጥብ 9 በመቶ፣ ደቡብ 94 ነጥብ 5 በመቶ እና ትግራይ 85 ነጥብ 5 በመቶ በማግኘት ወረርሽኙን ለመከላከል ዝግጁ እንደሆኑ ሪፖርት ማድረጋቸውን መረጃው ያመለክታል። ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጤና ባለሙያዎች የተገኘ መረጃ እንደሚያሳየው የአፍሪካ መዲና ተብላ የምትጠራው አዲስ አበባም ቢሆን የኮሮናን ሥርጭት ለመከላከል ያለው ዝግጁነት አናሳ መሆኑ ብቻ ሳይሆን የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ እንዲህ አይነት ወረርሽኝ ለመመከት የሚያስችል የአደረጃጀትና የሰው ኃይል ችግር አለበት።
ሌላው ቀርቶ ቤት ለቤት የሚደረግ የሙቀት ልኬት መጀመር ባይቻል እንኳን እንደናይጄሪያ መንግሥት፤ በጎዳናዎች ላይ ተሸከርካሪዎችን እና መንገደኞችን ላይ የሚደረጉ ድንገተኛ የሙቀት ልኬት ሥራዎች አለመጀመሩ በአሳሳቢነቱን ባለሙያዎቹ ያነሳሉ።
እናም የመንግሥት እና የሕዝብ የተቀናጀ ጥረት የሚቀጥል ከሆነ ይኸን የመከራ ጊዜ በአሸናፊነት እናልፈው ይሆናል። አዎ! ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አሕመድ ሰሞኑን “ምንም እንኳ እየገጠመን ያለው ችግር ከዚህ በፊት እንዳየናቸው አደጋዎች የማያልፍ ቢመስልም ማለፉ ግን አይቀርም።ስለተመኘን ሳይሆን በትብብር ስለምንሰራ ይህ ጊዜ ያልፋል” ብለዋል።አዎ! ፈጣሪ እንደምኞታችን ይፈጽምልን! በተጨማሪም በግልና በጋራ ከምናደርገው ጥንቃቄ በተጨማሪ በየእምነታችን መጸለይ ተስፋችንን ለማለምለም መልካም መንገድ መሆኑን አንዘንጋ፡፡
አዲስ ዘመን መጋቢት 30/2012
ፍሬው አበበ
የፈተና ጊዜውን እናልፈው ይሆን?