በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ አዳሚ ቱሉ ወረዳ ቡልቡላ ከተማ እየተገነባ ላለው የቡልቡላ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ የግብርና ምርቶችን መጠነኛ እሴት በመጨመር ለማቅረብ እየተገነቡ ካሉ የገጠር ትራንስፎርሜሽን ማዕከላት ውስጥ አንዱ ነው። ግንባታውም በ10 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ኤም.ሲ.ጂ በተሰኘ ደረጃ አንድ የግንባታ ተቋራጭ ከመስከረም ወር 2012 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ ይገኛል – የመቂ ገጠር ትራንስፎርሜሽን ማዕከል።
የማዕከሉ ግንባታ በልዩ ልዩ ምክንያቶች መጠነኛ መዘግየቶች የታዩበት ሲሆን፣ የፊዚካል ሥራው 56 ከመቶ የፋይናንስ አፈፃፀሙ ደግሞ 50 ከመቶ መድረሱን ከግንባታ ተቋራጩ የተገኙ መረጃዎች ያሳያሉ። ይሁንና አፈፃፀሙ ከተቀመጠው እቅድ ጋር ሲነፃፀር በተለይ የፊሲካል ሥራው በ19 ከመቶ መዘግየቱን ያመለክታል። የግንባታ ተቋራጩን እየገጠሙት ያሉ ወቅታዊ ሁኔታዎች ደግሞ የማዕከሉን ግንባታ ሊያዘገዩት እንደሚችሉ ተገምቷል።
በኤም.ሲ.ጂ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የመቂ ገጠር ትራንስፎርሜሽን ማዕከል ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ አቶ ከድር ቡሽራ እንደሚገልፁት፤ የፕሮጀክቱ ኮንትራት ስምምነት ነሐሴ 2011 ዓ.ም የጀመረ ሲሆን፣ በዚሁ ወር መጨረሻ የግንባታ ቦታውን በመረከብ ወደ ሥራ ተገብቷል። ይሁን እንጂ ወቅቱ ክረምት ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ሥራው ለጊዜው ቆሞ በመስከረም ወር 2012 ዓ.ም ዳግም እንዲጀመር ተደርጓል።
በማዕከሉ ለተለያዩ ጥቅም የሚውሉ 11 ሕንፃዎች እየተገነቡ ሲሆን፣ ግንባታቸውም በተለያየ ደረጃ ላይ ይገኛል። ሆኖም የሕንፃዎቹ ግንባታ በተያዘለት እቅድ እየሄደ ባለመሆኑ አፈፃፀሙ አጥጋቢ ነው ማለት አይቻልም። ይህም ሊሆን የቻለው በወቅቱ የነበረው አማካሪ ድርጅት የግንባታ ቦታው ላይ ገብቶ ከዲዛይን ጋር የተያያዙ ሥራዎችን መፈፀም ባለመቻሉ ነው። በዚህም ምክንያት ፕሮጀክቱ ዘግይቷል።
በሌላ በኩል ደግሞ በግንባታው ቦታ ላይ የሚገኘው አፈር ሕንፃዎቹን ለመገንባት ምቹ ባለመሆኑ ለግንባታው ሦስትና አራት ሜትር ወደታች ቁፋሮ ማድረግ አስፈልጓል። ለዚሁ ሙሌት የሚያስፈልግ ሴሌክት ማቴሪያልለማምጣትም እስከ 23 ኪሎ ሜትር ርቀት ለመሄድ አስገድዷል። ከወረዳ አስተዳደሩና ከወጣት አደራጅ አካላት ጋርም ውይይት ተካሂዷል። ይህም ለፕሮጀክቱ መዘግየት የራሱን አስተዋፅኦ አድርጓል።
እንደ ሥራ አስኪያጁ ገለፃ፤ የማዕከሉ ግንባታ ከተጀመረ ሰባተኛ ወሩን የያዘ ሲሆን፣ በነዚህ ወራት ልዩ ልዩ ሥራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል። ፕሮጀክቱን ለማስፈፀምም በአጠቃላይ 590 ሚሊዮን ብር ተመድቦ በሰባት ወር ለፕሮጀክቱ ክንውን 240 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል። የፕሮጀክቱ የፋይናንስ አፈፃፀምም 50 ከመቶ ደርሷል። በማዕከሉ ከሚገነቡት ሕንፃዎች መካከል የአትክልትና ፍራፍሬ ማከማቻ ግንባታ አንዱ ሲሆን፣ 54 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ተይዞለት እስካሁን ባለው ሂደት 16 ሚሊዮን ብር ፈጅቷል። የሥራው አፈፃፀምም 29 ከመቶ ደርሷል።
የቀንድ ከብቶች መቀበያ ሕንፃው 20 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ተይዞለት እስካሁን ድረስ 11 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ፈጅቶ አፈፃፀሙ 52 ከመቶ ላይ ደርሷል። የቀንድ ከብቶች ማዘጋጃ ሕንፃው ደግሞ 20 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር የተያዘለት ሲሆን፣ እስካሁን ድረስ 14 ሚሊዮን ብር ፈጅቶ አፈፃፀሙ 66 ከመቶ ደርሷል። የጠቅላላ አገልግሎት ሕንፃ ግንባታም 57 ሚሊዮን ብር ተመድቦለት እስካሁን ድረስ 24 ሚሊዮን ብር ወስዶ አፈፃፀሙ 45 ከመቶ ሆኗል። የአጥር ሥራዎችን ጨምሮ ሌሎች ግንባታዎችም በማዕከሉ እየተከናወኑ ይገኛሉ። አቶ ከድር እንደሚሉት፤ የፕሮጀክቱ ፊዚካል አፈፃፀም 56 ከመቶ የደረሰ ሲሆን፣ የንዑስ መዋቅር ሕንፃ ሥራዎች ተጠናቀው ከውጭ ሀገር የሚገቡ ተገጣጣሚ ብረቶችን ብቻ ይጠብቃል። ይህም የመንግሥትን ጣልቃ ገብነት ይጠይቃል። ብረቶቹ በአፋጣኝ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ከሆነም ሥራው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ ይሆናል።
የቀንድ ከብት፣ አትክልትና ፍራፍሬ መቀበያ ሕንፃዎች ግንባታም ውስጣቸው ተጠናቆ በቀጣዮቹ ሳምንታት ጣራ የማልበስ ሥራ ይሰራል። የጠቅላላ አገልግሎት ሕንፃና የመገባበያ ሕንፃውም የመጀመሪያ ወለል ስላቭ ሥራ ተጠናቋል። ብረት የመስቀል ሥራዎች በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል። የዌር ሃውስ ሥራዎችም ከውጪ የሚገቡ ብረቶችን ይጠብቃሉ።
የወተት መቀበያ፣ መመርመሪያና ማከማቻ ሕንፃዎችም ጣራ የማልበስ ሥራ በቀጣዩ ሳምንት ይከናወናል። የአትክልትና ፍራፍሬ የቅዝቃዜ ማከማቻና ማርና የማር ውጤቶች ማከማቻ ሕንፃ ቢም የመሙላት ሥራ እየተከናወነ ይገኛል። ከውስጥም የመጨረሻ የአርማታ ሙሌት ሥራ ተከነውኗል። የጣራ ብረቶችም ተሰርተዋል። ሁለቱ የእንቁላል ማከማቻ ሕንፃዎችም ከውጭ አገራት የሚገቡ ብረቶችን ይጠብቃሉ። አቶ ከድር እንደሚያብራሩት፤ በኮንትራት ስምምነቱ መሠረት ግንባታው አስር ወራትን ይፈጃል።
ከሦስት ወራት በኋላም 85 ከመቶ ያህሉ የማዕከሉ ሥራዎች ይጠናቀቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይሁን እንጂ ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች በተፈጠረው መዘግየትና በአሁኑ ወቅት በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሚጠበቀውን ያህል ሠራተኞች በሥራ ገበታቸው ላይ እየተገኙ ባለመሆናቸው የግንባታው ጊዜ በኮንትራት ስምምነቱ ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ በላይ ሊራዘም ይችላል።
በዚሁ ቫይረስ ምክንያት ለሕንፃዎቹ ግንባታ የሚያስፈልጉ ፒ.ኢ.ቢ ብረቶችና ሌሎችም ዕቃዎች እስካሁን ድረስ ወደ አገር ውስጥ የገቡ ካለመሆናቸው አኳያም ፕሮጀክቱ በተባለው ጊዜ ላይጠናቀቅ ይችላል። ሆኖም እነዚህ ችግሮች የሚፈቱ ከሆነ ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ ይጠናቀቃል። የኦሮሚያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ከፍያለው ቱሉ በበኩላቸው እንደሚገልጹት፤ የኦሮሚያ የመቂ ገጠር ትራንስፎርሜሽን ማዕከል ግንባታው በመጪው ሰኔ ወር ይጠናቀቃል ተብሎ ውል ተገብቷል።
አፈፃፀሙም ሲታይ በተቀመጠው የኮንትራት ስምምነት እየሄደ ይገኛል። ይሁን እንጂ በወቅታዊ የኮሮና ቫይረስ ምክንያት ባጋጠመ የውጪ ምንዛሬ እጥረት ተገጣጣሚ ብረቶችን ከውጭ አገር ለማስገባት አልተቻለም። በዚሁ መነሻነት ኮርፖሬሽኑ ድጋፍ እንዲደረግለት ለተለያዩ አካላት አሳውቋል።
የድጋፍ ደብዳቤዎችንም ለንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና ለንግድ ባንክ አቅርቧል። ይሁንና እስካሁን ድረስ በቂ ምላሽ አላገኘም። ይህም በማዕከሉ ግንባታ ላይ የመጓተት ስጋት አሳድሯል። በሌላ በኩል ደግሞ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሠራተኞች እንደልብ ወጥተው ሥራቸውን እያከናወኑ ባለመሆኑ በፊት እንደስጋት ያልታየ ይሁንና በቀጣይ ፕሮጀክቱን ሊያጓትቱ ከሚችሉ ስጋቶች ውስጥ አንዱ ሆኗል።
አዲስ ዘመን መጋቢት 29/2012
አስናቀ ፀጋዬ
ስጋት ያንዣበበበት የመቂ ገጠር ትራንስፎርሜሽን ማዕከል