
ታሪኩን፣ ባህሉንና አገራዊ እሴቶቹን የማያውቅ፣ አውቆም ለህብረተሰብ ዕድገት የማይጠቀምበት ቢኖር እርሱ ዕውቀትና ታሪክ ጠል ዜጋ ለመሆኑ ከድርጊቱ በላይ ማረጋገጫ ሊኖር አይችልም፡፡ ኢትዮጵያ በየማህበረሰቡ የሚከወኑ ቀደምት የሥነ-ፅሑፍ ፣የኪነ-ሕንፃ፣የሙዚቃ፣የሽምግልናና እርቅ፣ እንዲሁም ሌሎች ባህላዊ እሴቶችና ትውፊቶች መገኛ ነች። ለዚህም ይመስላል ሀገሪቱ በታሪክና በባህል ተመራማሪዎች ዘንድ « የባህል ሙዚየም» የምትባለው።
ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የተመዘገቡ በርካታ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ተፈጥሯዊና ባህላዊ ቅርሶች ባለቤትም ነች። በኢትዮጵያ በብዙ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች የሚከናወኑ የማህበራዊ ፣የኢኮኖሚያዊና የፖለቲካዊ አስተዳደር፣ የሥነ-ምግባር፣የስነ-ልቡና፣የቋንቋ፣የታሪክ፣የስነ-ቃል፣የምግብ አዘገጃጀት፣የአመጋገብ ስርዓት ፣ቤት አሠራር፣ አልባሳት ፣ጌጣጌጦች፣ባህላዊ እምነቶች፣ ሃይማኖቶችና ሌሎችም እሴቶች የህዝቦች የባህል አካል ተደርገው ይወሰዳሉ።
ይህ የባህል ዓውድ ከወሊድ፣ ከጋብቻና ከሞት ጋር የተያያዙ ስነ ስርዓቶችና ጉርብትናን የመሳሰሉ ማህበራዊ የትብብር መርሆዎች ፣ባህላዊ የጤና አጠባበቅ ዘዴዎች፣የማህበረሰብ አስተዳደሮችና ሌሎች የማህበረሰብ ገፅታዎችንም ያጠቃልላል።
የባህል ዓውዱ ቃላዊ ሀብትን፣እደጥበብን፣ኪነ-ሕንፃን፣ አልባሳትን፣ምግብና መጠጥን በማካተት ቁሳዊ የባህል ዘርፍ፤ ሙዚቃን፣ ውዝዋዜንና ድራማዎችን ሲያካትት ሀገራዊ ክዋኔ ዘርፍ፤ ክብረ በዓላትንና የህይወት ዑደትን የሚያካትተው ሀገረሰባዊ ልማድ ዘርፍ፤ የቁጥሮችን፣ የቀለሞችንና የምልክቶችን ትርጓሜና አንድምታ ሲይዝ ማህበረሰባዊ ውክልና ዘርፍ፤ እንዲሁም የእርቅ ፣የአውጫጭኝና የገዳ ስርዓቶችን በስሩ ሲያጠቃልል ደግሞ ማህበረ ፖለቲካዊ ባህሎች ዘርፍ፤ በሚል በስድስት ዋና ዋና ክፍሎች ተመድቦ የሚገኝ ነው።
ይህንን ዘርፍ ለማበረታታትና ለመደገፍ ሀገራት የባህል ፖሊሲ ቀርፀው በሥራ ላይ አውለው ውጤታማ ሆነዋል። ይህ ፖሊሲያቸው የአንድን ሀገር የኪነ ጥበብ ሥራዎችና በባህል ውስጥ ያሉና ከፈጠራ ውጤቶች ጋር የተያያዙ እንቅስቃሴዎችን ለመቆጣጠር፣ ለመጠበቅ፣ ለማበረታት፣ በገንዘብም ሆነ በሃሳብ ለመደገፍ ረድቷቸዋል።
በአገራችንም ስለ ቅርስ ጥናትና አጠባበቅ የሚደነግግ አዋጅ ቁጥር 209/1992 ማውጣቷ ይታወሳል፡፡ ይህንን አዋጅ ተከትሎም የኢትዮጵያ የባህል ፖሊሲ ከታኅ 2008 ዓ.ም ጀምሮ ማሻሻያ እንደተደረገበት ይታወቃል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያውያን የራሳቸው ታሪክና ባህል ያላቸው ብዙ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች የሚገኙባት፣ ሕዝቦቿም ባሳለፉት የረጅም ዘመን ታሪክ በዓለም የባህል ቅርስነት የተመዘገቡትን ጨምሮ የበርካታ ቅርሶች ባለቤት መሆን ቢችሉም፤ ተተኪው ትውልድ ስለ ማንነቱ መገለጫ ለሆነው ታሪኩና ባህሉ በሚፈለገው መጠን ጥልቅና ሰፊ ግንዛቤ ለማስጨበጥ በጥንካሬ ባለመሠራቱ በተለይ ከወጣት እስከ ጎልማሳ ያለው የህብረተሰብ ክፍል ባህላዊ ማንነቱን እንዳይጎናፀፍ አድርጎታል፡፡
ኢትዮጵያ ያላት የሚዳሰሱትም ይሁኑ የማይዳሰሱት የቅርስ ሀብቶች አገሪቱ ካላት የኢኮኖሚ አቅም በላይ የገዘፉ መሆኑ ይታወቃል፡፡ እነዚህ ሀብቶች ለቱሪዝም አገልግሎት ብቻ ሳይሆን ለመልካም ማህበረሰብ ግንባታ ሥራ የጀርባ አጥንት መሆናቸው የሚያጠያይቅ አይሆንም፡፡
ከማይዳሰሱት ታላላቅ ማህበረሰባዊ እሴቶቻችን መካከል አንዱ የገዳ ስርዓት ዴሞክራሲ እንደአሁኑ ታዋቂ ባልሆነበት ዘመን ማኅበረሰቡ አምኖበት ሲጠቀምበት ዓመታት ማስቆጠሩ ለራሳችን «በእጅ የያዙት ወርቅ…» አደረግነው እንጂ ዓለምን ያስደመመ ነው፡፡
የክልል መንግሥታት የብሄር ብሄረሰቦችን ባህላዊና ታሪካዊ እሴቶች ለማሰባሰብ፣ ጠብቆ ለማቆየትና ሳይበረዙ ለትውልድ ለማስተላለፍ ዓይነተኛ መሳሪያ መሆናቸው ቢታወቅም የባህል ማዕከላት የሰጡት ትኩረት አነስተኛ በመሆኑ ከውጤታማነት ይልቅ የባህል ዝንጋታን አስከትሎ በመጤ ባህል እየተተካ ይገኛል፡፡
በአንድ ወቅት የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች መጤ ባህሎችና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፉ መሆኑን በጥናት ግኝቱ አመላክቶ ነበር። ጥናቱ በዘጠኙ ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ናሙናዎችን በመውሰድ የተካሄደ ሲሆን፤ ግሎባላይዜሽንን ተከትሎ የሚገቡ መጤ ባህሎችና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች በከፍተኛ ፍጥነት መስፋፋት ለትውልድ ስጋት እንደሆኑ ተጠቅሷል፡፡ ሱስ አስያዥና አደንዛዥ እጾችን መጠቀም፣ የራቁት ዳንስ፣ ከተመሳሳይ ጾታ ጋር ወሲብ መፈጸም፣ በማሳጅ ቤቶች ወሲብ መፈጸም እየተስፋፉ ከመጡ መጤ ባህሎችና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች መካከል ተጠቃሽ ሆነዋል።
የወጣቱ ትውልድ ከድረ ገጾች የወሲብ ፊልሞችን መመልከትና ያልተገቡ አለባበሶችን መኮረጅ እየተስፋፉ መሆኑ በተለይም «ፍሪ ዞን፣ ፍሪ ሳተርዴይ እና ኖ ሼም ግሩፕ» በሚል ወጣቶች በቡድን የሚፈፅሟቸው መጤ እና ጎጂ ልማዶች በአዲስ አበባና በአንዳንድ ክልሎች በስፋት እንደሚስተዋሉ በጥናቱ ተመላክቷል።
እነዚህ የባህል መዘንጋቶች፣ መጤ ባህሎችና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች መስፋፋት ማህበረሰባዊ ክስረትን ከማድረስ አልፈው ለአገሪቱ ዕድገት እንቅፋት እንደሚሆኑ ይታመናል፡፡ የኢኮኖሚ ዕድገትና ባህል ጥበቃ ተደጋግፈው ካልሄዱ የህዝቡን መልካም እሴቶችና ባህል የሚያጠፋ፣ የታላላቆቹን ምክር የማይቀበል ፣ የታሪክን ምንነት የማይረዳ፣ ታሪክን ለማወቅ የማይፈልግ፣ መላው አካሉን ለመጤ ባህል ያስገዛ ትውልድ በማፍራት ለአገር የማይጠቅም ትውልድ ታቅፎ ለመቀመጥ የምንገደድ ስለሚሆን፤ ይህ የትውልድ ጠንቅ ስር ሳይሰድድ ተረባርበን ልናስወግደው ይገባል፡፡ ለዚህ ደግሞ ያሉንን መልካም ባህላዊ እሴቶችን ትውልዱ እንዲያውቃቸው መሥራት የግድ ይላል፡፡
አዲስ ዘመን ጥር 3/2011
This blog serves as a reminder to take care of our mental health and well-being Thank you for promoting a healthier and happier mindset
Your writing style is so engaging and makes even the most mundane topics interesting to read Keep up the fantastic work
This post is jam-packed with valuable information and I appreciate how well-organized and easy to follow it is Great job!
From the insightful commentary to the captivating writing, every word of this post is top-notch. Kudos to the author for producing such fantastic content.
This blog is like a safe haven for me, where I can escape the chaos of the world and indulge in positivity and inspiration
Your blog is so much more than just a collection of posts It’s a community of like-minded individuals spreading optimism and kindness
This post hits close to home for me and I am grateful for your insight and understanding on this topic Keep doing what you do
I love how this blog gives a voice to important social and political issues It’s important to use your platform for good, and you do that flawlessly
Fast and reliable service! They arrived on time and took great care of my car. Highly recommended!
Excellent service! They arrived quickly and safely towed my car to the nearest garage. Highly recommend!
Pre-trip Preparation: While roadside assistance is crucial in emergencies, preventing these situations by maintaining the vehicle and preparing an emergency kit can reduce the need for recovery services. Ensuring your vehicle is in good condition before a trip is a proactive approach.
Superb service! They arrived on time and made the whole process stress-free. Highly recommended!
Excellent towing service! They arrived quickly and handled my car with great care. Highly recommended!
Superb service! They arrived on time and made the whole process stress-free. Highly recommended!
AquaSculpt is a one-of-a-kind weight management formula that naturally boosts metabolism, curbs cravings, and enhances energy levels.