አዲስ አበባ ፡- ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍ ሎች ተውጣጥተው ለስድስት ወራት ውይይት ሲያ ደርጉ የነበሩ ተሳታፊዎች የመጪዋን ኢትዮጵያ የሚያመላክቱ አራት እጣ ፋንታዎች(ሴናሪዎችን) ይፋ አደረጉ።
የውይይቱ ውጤት ከትናንት በስቲያ በስካይ ላይት ሆቴል ይፋ በተደረገበት ወቅት የዴስቲኒ ኢትዮጵያ አስተባባሪ አቶ ንጉሴ አክሊሉ እንደገለጹት፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከአክቲቪስቶች፣ ከሲቪል ማኅበራትና ከሚዲያ ባለሙያዎች፣ ከምሑራን ወዘተ የተውጣጡ 50 አባላትን ያቀ ፈው ቡድን ለስድስት ወራት ባደረገው ውይይት የመጪዋን ኢትዮጵያ እጣ ፈንታ የሚያመላክቱ ዝርዝር ጉዳዮችን አስቀምጧል።
ለስድስት ወራት በውይይት መድረኩ ላይ ሲሳተፉ የነበሩት ሰዎች የተለያየ አመለካከትና አስተሳሰብ ያላቸው እንደሆኑ የጠቀሱት አስተባባሪው፣ በወንድማማችነትና በእህትማማችነት፣ በሀገር ልጅነት መንፈስ ሆነው አሁን ባለው የሀገራችን ሁኔታ ላይ እንዲነጋገሩ ዕድል የፈጠረ መድረክ መሆኑን ተናግረዋል።
አሁን ላይ በፖለቲካ አስተሳሰብ ምክንያት የሚፈጠሩ ግጭቶች ለሁሉም ዜጎች ስጋት እየሆኑ በመምጣታቸው ከዚህ አጣብቂኝ ለመውጣት ቁጭ ብሎ መነጋገርና መጪውን ጊዜ የተሻለ ለማድረግ ከወዲሁ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት አማራጭ መንገዶችን መመልከት እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በመጪዎቹ 20 ዓመታት(የምንፈልጋት ኢትዮጵያ 2032) ውስጥ የሚገጥሟት እጣ ፈንታዎችም ተለይተዋል። እነዚህም ንጋት፣ የፉክክር ቤት፣ አጼ በጉልበቱ እና ሰባራ ወንበር በሚል የተሰየሙ እጣፈንታዎች እንደሆኑ ተገልጿል።
‹‹ንጋት›› እጣ ፈንታ የኢትዮጵያ እድገት ደረጃ በደረጃ እውን የሚሆንበትን ተስፋ የሚያመላክት እንደሆነም ተገልጿል። ‹‹የፉክክር ቤት›› የሚለውም ልክ የፉክክር ቤት ሳይዘጋ እንደሚያድር ሁሉ የተለያዩ ቡድኖችና ክልሎች ያገኙትን አዲስ ነጻነት እነርሱ እንዲፈልጉትና እንደመሰላቸው መጠቀማቸውን የሚያሳይ፣ ክፍተቶችና ክፍፍሎች መኖራቸውንም የሚያመላክት ነው። ሶስተኛው እጣ ፈንታ ‹‹አጼ በጉልበቱ›› ሲሆን ፈላጭ ቆራጭ የሆነና ጥብቅ ቁጥጥርን ያማከለ ሥርዓት መሆኑ ተመላክቷል።
አራተኛው ደግሞ ‹‹ ሰባራ ወንበር›› በሚል የተመሰለ ሲሆን ገና ሲነኩት የሚሽመደመድና ቀላል ክብደትን እንኳን የማይሸከም ነው። የአቅም ማጣቱ በህብረተሰቡ ውስጥ በየደረጃው ለሚነሱ የልማት ፍላጎቶች ተግባራዊ ድጋፍ ለመስጠት እንደማያስችለው ተመላክቷል።
የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል በመድረኩ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር መድረኩ ሁላችንም ለኢትዮጵያ እንደምናስፈልጋት ያስተማረ መሆኑን ገልጸዋል። ሂደቱ በአብሮነት እና በመቀራረብ ውስጥ ያለውን የልብና የጆሮ መሰጣጣት ያመላከተ መሆኑንም ጠቅሰዋል። አዲስ የፖለቲካ ባህልን ለመገንባት አስቻይ መንገድን ያሳየንም እንደሆነም ገልጸዋል።
ራስን እንዴት ማሸነፍና መስራት እንደሚቻል እንዲሁም እንዴት ህግን ማክበር እንደሚቻል ያስተማረ መሆኑንም ጠቅሰዋል። በመጨረሻም ይህ ረዥም ጊዜ የወሰደው ውይይት ውጤቱ ለመንግስት ግብዓት ሆኖ የሚያገለግል መሆኑንም ነው ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት የገለፁት።
በመጨረሻም የመድረኩ ተሳታፊዎች በውይይታ ቸው የአቋም መግለጫ ያወጡ ሲሆን ሁሉም ለኢትዮ ጵያዊ በይቅርታ እና በወንድማማችነት መንፈስ በመነ ሳሳት ለሀገር ሰላም እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል።
አዲስ ዘመን ህዳር 25/2012
ኢያሱ መሰለ