
ኢትዮጵያ ከፍተኛ መጠን ያለው ሀብት ወደ ውጭ እንዲሸሽ ከሚደረግባቸው ሀገሮች አንዷ ሆናለች ፡፡በቅርቡ ይፋ የተደረገ አንድ መረጃ እንዳመለከተውም ሀገሪቱ ባለፉት 27 ዓመታት 36 ቢሊዮን ዶላር ወይም አንድ ትሪሊዮን 80 ቢሊዮን ብር ገደማ የሚገመት ገንዘብ ከሀገሪቱ ወደ ውጭ እንዲሸሽ ተደርጓል፡፡
ይህ የገንዘብ አቅም ሀገሪቱን እና ህዝቦቿን ሊለውጡ የሚችሉ በርካታ ፕሮጀክቶች ሊገነቡበት የሚችል ነበር፡፡ ለአብነትም ይህ ሀብት በ80 ቢሊዮን ብር ሂሳብ እያንዳንዳቸው 6500 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጩ 13 የህዳሴ ግድቦችን ለመገንባት የሚያስችል ነው፡፡
አሁን በሀገራችን እየተገነቡ ከሚገኙት የኢንዱስትሪ ፓርኮች አንጻር ሲታይ ደግሞ በግዙፍነቱ እና ዘመናዊነቱ በሀገሪቱ አንደኛ እንደሆነ የሚነገርለትን፣ ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ሲገባ ለ60 ሺ ዜጎች የሥራ እድል መፍጠር የሚችለውና በዓመት አንድ ቢሊዮን ዶላር ሊያስገኝ የሚችለው የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን የሚያክሉ 144 ኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመገንባት ለ8ሚሊዮን640ሺ ዜጎች የሥራ እድል የሚፈጥር፣ በየዓመቱ ከእያንዳንዱ ፓርክ አንድ ቢሊዮን ዶላር ገቢ በማስገኘት በዓመት 144 ቢሊዮን ዶላር ማስገኘት የሚያስችልም አቅም የሚፈጥር ነው፡፡
በተመሳሳይም በ1ነጥብ8 ቢሊዮን ዶላር የተገነባውን እና1ሺ870 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመርተውን የግልገል ጊቤ3ን አይነት 20 የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድቦችን መገንባት 37ሺ400 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም መፍጠር ያስችላል፡፡ የሀገራችንን የኤሌክትሪክ ሽፋን መቶ በመቶ ማድረስ የሚችል አቅም የሚፈጥር ነው፡፡ በሌሎች ፕሮጀክቶች ቢሰላም በርካታ ፕሮጀክቶች በመገንባት ለወጣቶች የሥራ እድል በመፍጠር፣ መላው የሀገራችን ህዝቦች ከድህነት በማላቀቅ መካከለኛ ገቢ ለመድረስ የጀመርነውን ጉዞ ማሳጠር የሚያስችል ይሆን ነበር፡፡
ከሀገራችን መዳፍ ውስጥ እየተፈለቀቀ ወደ ባእድ ሀገር እንዲሸሽ የተደረገው ይህ ሀብት ምን ያህል ሀገሪቱንና ዜጎቿን ሊለውጥ እንደሚችል ከመረጃዎቹ መረዳት ይቻላል፡፡ በዚህ ገንዘብ ከሀገር መውጣት የተነሳም ሀገሪቱና ዜጎች ምን ያህል ኢኮኖሚያቸው፣ ፖለቲካቸው እና ማህበራዊ ህይወታቸው እንደተጎሳቆለም መረዳት አያዳግትም፡፡
ይህ የሀገር ሀብት ከሀገር እንዲሸሽ ሲደረግ የኖረው በተለያዩ መንገዶች ነው፡፡ በወጪ እና የገቢ ንግዱ ላኪም ተቀባይም አንድ ኩባንያ በመሆን በዋጋ ላይ በመጫወት የሀገሪቱ ገቢ እንዲቀነስ ተደርጓል፡፡በተለይ ችግሩ በውጭ ምንዛሪ ግኝቱ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ አሳርፏል፡፡ ለሀገሪቱ የወጪ ንግድ ገቢ መቀነስም መንስኤ ነው፡፡
ላለፈ ክረምት ቤት አይሠራም ቢባልም በቀጣይም ክረምት ይመጣልና ጥንቃቄ ማድረግ ግን ይገባል፡፡ ለእዚህም በወጪ ንግዱ ተዋንያን ላይ ፍተሻ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ግብይት ትስስር የሀገር ሀብት እንዲሸሽ ሲደረግ እንደመቆየቱ የሀገሪቱን ምርቶች የሚቀበሉ ሀገሮች ብቻ ሳይሆኑ መታየት ያለባቸው ምርቱን የሚቀበሉ አካላት ማንነትም መፈተሸ ይኖርበታል፡፡
ላኪዎቻችን የሀገርን ብሄራዊ ጥቅም ምን ማለት መሆኑ እንዲገባቸው በማድረግ ታማኝ እንዲሆኑ አጥብቆ መሥራትም ያስፈልጋል፡፡ የሀገርን ጥቅም ለራሳቸው የሚያውሉና አሳልፈው የሚሰጡ ላኪዎች በጭራሽ አያስፈልጉም፡፡ በዚህ አይነት መልኩ ምርት ባይላክም ይሻላል፡፡
ላኪዎቻችንና ተቀባዮቻችን ምን ያህል ጤነኛ የንግድ ግንኙነት እየተከተሉ እንደሚገኙ ከታወቀ በኋላም በወጪ ንግዱ ላይ ቁጥጥርን እና ክትትልን ማጠናከር የሀገርን ሀብት ለመታደግ ያስችላል፡፡ስለሆነም መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ ሊሠራበት ይገባል፡፡
ሌላው የሀገር ሀብት እንዲሸሽ የተደረገበት መንገድ ደግሞ በመንግሥት ባለሥልጣናት እጅ እንደሆነ ይገለጻል፡፡ ይህን ያህል ግዙፍ ገንዘብ ከሀገር እንዲሸሽ ሊደረግ የሚችለው በተራ ዜጋ እንዳልሆነም ነው የምጣኔ ባለሀብት ባለሙያዎች የሚገልጹት፡፡ የዚህ አይነት ወንጀል በተራ ዜጋ የሚፈጸም አይደለም፡፡ የከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ትስስርና ሽፋን በእጅጉ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ ቀደም ለተደረገው ተጠያቂ አካል መጠየቅ አለበት፡፡ ከአሁን በኋላ ደግሞ እንዳይፈጸም ባለሥልጣኖቻችን ከዚህ አይነቱ የሀገር ሀብትን ከሚያጠፋ ተግባር ንጹህ መሆን አለባቸው፡፡ በዚህ ተግባር ተሳትፈው ከተገኙም ፈጣንና አስተማሪ እርምጃ በመንግሥት ሊወሰድ ይገባል፡፡ የሀገር ሀብት መታደግ የሚቻለው የህግ የበላይነትን በማስከበር ነውና፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃም ሲታይ ግዙፍ ገንዘብ ከሀገር ሲያሸሹ የሚገኙት መሪዎችና ቁልፍ ኃላፊነት ላይ የሚገኙ ባለሥልጣናት እና ተባባሪዎቻቸው የውጭ ኩባንያዎች ናቸው፡፡ ከሀገራችን እንዲሸሽ የተደረገው ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ሲታሰብም እነዚህን አይነት ባለሥልጣናት በወንጀሉ ውስጥ የሉበትም ማለት አይቻልም፡፡ ምክንያም በሀገሪቱ የመጣውን ለውጥ ተከትሎ መንግሥት በሀገሪቱ የተደራጀ ሌብነት እና ዝርፊያ ሲፈጸም መቆየቱን መግለጹ ማረጋገጫ ነው፡፡
የሀገር ሀብትን ለመታደግ መፍትሄውም ሊሆን የሚችለው የወጪና ገቢ ንግዱ ላይ ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል ማድረግ እንዲሁም የመንግሥት ባለሥልጣናቱን ንጽህና ማረጋገጥ ነው፡፡ ለሀገራቸውና ለህዝባቸው ታማኝ የሆኑ ባለሥልጣናትን ማፍራት፣ ሥራቸውን እና ግንኙነታቸውን በቅርብ መከታተልም ያስፈልጋል፡፡ በዚህም የሀገሪቱን ሀብት ወደ ውጭ ከሚያሸሹ ወገኖች መታደግ ይገባል፡፡
አዲስ ዘመን ታህሳስ 23/2011
2
3
0
1
1
0
2
1
0
0
1
1
0
0
SIGMASLOT : Situs Slot Online dengan RTP Tinggi dan Menang Terjamin
SIGMASLOT : Situs Slot Online dengan RTP Tinggi dan Menang Terjamin
SIGMASLOT : Situs Slot Online dengan RTP Tinggi dan Menang Terjamin
SIGMASLOT : Situs Slot Online dengan RTP Tinggi dan Menang Terjamin
SIGMASLOT : Situs Slot Online dengan RTP Tinggi dan Menang Terjamin
SIGMASLOT : Situs Slot Online dengan RTP Tinggi dan Menang Terjamin
SIGMASLOT : Situs Slot Online dengan RTP Tinggi dan Menang Terjamin
0
2