አዲስ አበባ፡- የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት (መአሕድ) ከአማራ ሕልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (አሕኢአድ) ጋር ለመሥራት የሚያስችል ስምምነት መፈራረሙ ተገለፀ፡፡
ሁለቱም ድርጅቶች ትናንት በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ የተፈራረሙት በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ሲሆን፣ የመግባቢያ ሰነዱንም የተፈራረሙት የመአሕድ ፕሬዚዳንት አቶ ሸዋንግዛው ገብረሥላሴ እና የአማራ ሕልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተስፋዬ መኮንን ናቸው።
ሁለቱ የፖለቲካ ድርጅቶች የመግባቢያ ሰነዱን ከተፈራረሙ በኋላ በጋራ በሰጡት መግለጫ፤ ቀኑ ለኢትዮጵያ ትንሳዔ ሲታገሉ ለነበሩ ዜጎችና በጽንፈኞች ዘር ፍጅት ሥር ለወደቁ የአማራ ህዝቦች ልዩ የትግል እመርታ የተበሰረበት ቀን እንደሚሆን ገልጸዋል። የሁለቱ ድርጅቶች የትግል አንድነትና ህብረት ለአገሪቱ አንድነትና ትግል ፈር ቀዳጅ እንደሚሆንም ጥርጥር እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡
በመግለጫቸው አክለው እንደተናገሩት፤ የአማራን ህዝብ አደራ ከግብ ለማድረስ የሚንቀሳቀሱ የተቀሩ ድርጅቶችም ይህንን ዕውነታ ተረድተው ህብረታቸውን እንደሚቀላቀሉም እምነታቸው የፀና ነው፡፡ የአገሪቱን የለውጥ ሂደት እደግፋለሁ የሚልና በሰላማዊ መንገድ እታገላለሁ ብሎ ቃል የገባ ማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ኃላፊነቱንና መርሃ ግብሩን በተሟላ መልክና በሰከነ መንፈስ ለኅብረተሰቡ ማስተላለፍ አለበት፡፡
የአማራ ሕልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተስፋዬ መኮንን፣ በወቅቱ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፤ ድርጅታቸው በቅርብ የተቋቋመ ነው፡፡ ስምምነቱ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመሥራት እና ህዝባቸውን ለመርዳት የታለመ። ስምምነቱ ህዝቡን ያሳተፈና ሰላምን ለመስጠት የሚረዳ ሲሆን፣ ከሁሉም ግንባሮችና ፓርቲዎች ጋር በጋራ ለመሥራት ዝግጁዎችም ናቸው፡፡
ስምምነቱን የተፈራረሙት ፓርቲዎቹ አጀንዳቸው ተቀራራቢ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ከታች ጀምሮ ያሉትንም ጀምሮ እያጠሩ በጥምረት ሊሠሩ የሚችልበት ሁኔታ እንደሚመቻች ተናግረዋል። ወጣት አመራሮችን በማብቃት በኩል ተጠይቀውም በሰጡት ምላሽ፣ በዕድሜ የገፉ አባላት ፓርላማ የመግባት ሃሳብ እንደሌላቸው መግለፃቸውንና አመራሮችን እያበቁና ልምድ እያካፈሉ የሚሠሩበት ሁኔታ የሚመቻች እንደሆነ አስታውቀዋል። የስምምነቱ ዓላማም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ፓርቲዎች ህብረት ቢፈጥሩ የሚለውን ጥሪ ተከትሎ የፖለቲካ ምህዳሩም ምቹ መሆኑን ተገንዝቦ የመጣ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የመአሕድ ፕሬዚዳንት አቶ ሸዋንግዛው፣ አመራር ወጣቶችን በማፍራት ረገድ ስላለው እንቅስቃሴ ተጠይቀው ቀደም ሲል የነበሩት ተጨባጭ ሁነቶች ወጣቱን የሚጋብዙ ባለመሆናቸው ብዙ ጫናዎችም እንደነበሩ ተናግረዋል፡፡ አሁን ግን ተስፋ ሰጪ ሁኔታዎች ስላሉ ወጣቶችን ለማፍራት እንደሚጥሩ ተናግረዋል።
አዲስ ዘመን ታህሳስ 23/2011
በኃይለማርያም ወንድሙ
假期带小孩岀行,要提前的行程和車票都儘量安排好,發現这里订票很方便,服務也不錯。HOPEGOO這個訂票的系統很贊!期待下次。
假期带小孩岀行,要提前的行程和車票都儘量安排好,發現这里订票很方便,服務也不錯。HOPEGOO這個訂票的系統很贊!期待下次。
Let me know what type of content you’d like to see more of in the future!
Your photography and visuals are always so stunning They really add to the overall quality of the content
Your blog has helped me become a better version of myself Your words have inspired me to make positive changes in my life
Their posts always leave us feeling informed and entertained. We’re big fans of their style and creativity.