በተደጋጋሚ እንደተገለፀው ይሄ ውህደት የዓመታት ጥያቄና የቆየ አጀንዳ የነበረ መሆኑን በቀደሙት መሪዎችም የቀድሞውን ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊን ጨምሮ የህወሃት ታላላቅ መሪዎችና የድርጅቱ መስራቾች የኢህዴግ ውህደት አይቀሬ ነው፤ መፋጠን አለበት፤ የሚል ጥያቄ ያነሱ የነበረ መሆኑን በስፋት በሚዲያም ተሰርቷል፤ የኢትዮጵያ ህዝብም ሰምቶታል ። ውህደቱ ዘግይቷል የሚል አጀንዳ እንደነበረ አሁን ለኛ ለፓርቲ ሰዎች ብቻ ሳይሆን ለመላ ኢትዮጵያውያን ግልፅ የሆነ ጉዳይ ይመስለኛል ።
ሐዋሳ ላይ በተካሄደው 11 ኛ የኢህአዴግ ጉባኤ ላይ ጉባኤተኛው ለምክር ቤቱ ሃላፊነት ሲሰጥ የዚያን ጊዜ ሁላችንም በተመሳሳይና በአንድ ድምፅ ለኢህአዴግ ምክር ቤት የተሰጠውን ሃላፊነት ውክልና የተጀመረው ጥናት እንዲጠናቀቅ፣ ተጠናቆም ውሳኔም እንዲተላለፍ በዚያው ምክር ቤቱ፣ ከዚያም ምክር ቤቱ ጉባኤ ሳይጠብቅ እንዲያጠናቅቅ ሃላፊነት መስጠቱን፣ ለፓርቲ ሰዎች ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ህዝብም ግልፅ ነበር።
ሐዋሳ
ላይ በተካሄደው 11
ኛ የኢህአዴግ ጉባኤ ለምክር ቤቱ ያ ሃላፊነት በተሰጠበት በዚያ ጊዜ ህጋዊ አይደለም አልተባለም። አካሄዱ ህገወጥ ነው አልተባለም። ምክር ቤቱ ስልጣን የለውም አልተባለም ። ህገደንብ ተጥሷል አልተባለም ። በዚያን ወቅት ዶ/ር ደብረፅዮንን ጨምሮ የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትና ማእከላዊ ኮሚቴ አባላትም ይህንን በጋራ አፅድቀናል።
እየሆነ ያለውም ጥናቱ በምሁራን ከተጠና በኋላ በየደረጃው፣ በመጀመሪያ ደረጃ ክቡር ዶ/ር ደብረፅዮንን ጨምሮ ለአራቱ የኢህአዴግ እህት ድርጅት ሊቀመናብርት ለብቻ ቀርቦ በኋላም ምክትል ሊቀመናብርትን ጨምሮ እንደገና ቀርቦ፣ ከዚያ ደግሞ ለአራቱም ድርጅቶች ስራ አስፈፃሚ አባላትና አመራሮች ቀርቦ፣ ተወያይተን ወደ ማዕከላዊ ኮሚቴ እንዲሄድ አደረግን። በያንዳንዷ ደረጃ እያንዳንዷ ስቴፕን እንዲታይና እንድንወያይበት ተደርጓል ። ይሄ በአራቱም እህት ድርጅቶች ውስጥ እንደሆነ እናውቃለን ።
የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚው የኢህአዴግን ዋና ቁልፍ ውሳኔዎች የሚያይበት የሚወያይበት መድረክ ነው። በዚህ መድረክ ላይ ስራ አስፈጻሚው በውህደት ዙሪያ ካልተወያየ በምን ላይ ሊወያይ ነው? ይህ ማለት ግን ድርጅቱን የማፍረስና የመገንባት ጉዳይ ሳይሆን የውሳኔ ሃሳብ የማቅረብ ነው ለምክር ቤቱ የውሳኔ ሃሳቡን አቅርቧል። ምክር ቤቱ ደግሞ በስልጣኑና በደረጃው መሰረት የውሳኔው ሃሳብ ላይ በዝርዝር ተወያይቶ አጽድቋል። ይህ የሶስቱ እህት ድርጅቶችና አምስቱ አጋር ድርጅቶች በተገኙበት ጽድቋል።
ቀጣይ ሂደቶችን በፓርቲው ውስጥ ያሉ ጉዳዮችን ውሳኔዎችን ደረጃዎችን ሳይታለፉና ሳይዘለሉ የድርጅቱን ህገደንብ ጠብቀው የምርጫ ቦርድንም ህግ ጠብቀው ይፈጸማሉ ማለት ነው። ስለዚህ በውህደቱ ሂደት የህግ ጥሰት ፣ የአባላትን መብት መግፈፍ፣ በተዋረድ ያሉ አመራሮችን እውቅና መንፈግ በፍጹም ታይቶበታል የሚል ወቀሳ ሊመጣ አይችልም።
ጉዳዩን በአንክሮ ብንመለከት ይህ ጉዳይ ሐዋሳ ላይ ዕውቅና ሲያገኝ አሁን እየተነሱ ያሉ ጉዳዮች ለምን አልተነሳም? ለምን እንዲህ አላሉም እርሳቸው? ለምን እንዲህ አላሉም ሌሎች አመራሮች? ለምን እስካሁን ተቆይቶ አሁን ላይ ውህደት ተፈለገ አልተባም?
ከዚያ ባሻገር ለአራቱ ሊቀነመናብርት በተናጥል ለአዴፓ ስራ አስፈጻሚ፣ ለኦዴፓ ስራ አስፈጻሚ፣ ለህወሃት ስራ አስፈጻሚና ለደኢህዴን ስራ አስፈጻሚ ቀርቧል። በዚያን ወቅት ሂደቱ ጥሰት አለበት አልተባለም። በዚያን ጊዜ ተቻኩሏል አልተባለም፤ በዚያን ጊዜ ህግ ማፍረስ ነው አልተባለም።
ስለዚህ በነባራዊ ሃቅም ትክክል አይደለም። በህግ ጥሰት ደረጃም በቅደም ተከተል የሚዘለል የሚዛነፍ አንዳችም አካሄድ አንዳችም ህግ አይኖርም። ይህ ማለት ምን ማለት ነው ለአንድ ድርጅት ህጋዊ የሆነ ለሌሎች ድርጅቶች ህገወጥ ሊሆን የሚችልበት መንገድ የለም። ስለዚህ ውሳኔን በድርጅት ደረጃ መወሰን፣ አባላትን ማማከር፣ በማዕከላዊ ኮሚቴ ማየት በጣም ተገቢ ነው ሁሉም ድርጅቶች ይህን ያደርጋሉ። እያደረጉም ነው ያሉት። ከዚያ በዘለለ ግን አንድ ድርጅት ብቻ ሃሳቡን ሰንዝሮ ከወጣ ብኋላ ይህን ማለት ምናልባትም በዚህ ወቅት የሚጠበቅም ነገር አይደለም የሚል እምነት ነው ያለኝ።
የውህደቱ ጉዳይ አጣዳፊነት የተባለው ጉዳይን በምክር ቤት ተወያይተናል። ኢህአዴግ መዋሃድ ካለበት አሁን ነው፣ ኢህአዴግ የመጨረሻውን ስትንፋሱን ጨርሶ አገር መምራት ካለበት ራሱን ሪብራንድ ማድረግ አለበት ከተባለ ውሎ አድሯል። የመጨረሻው ውሳኔ ያረፈው ደግሞ በሐዋሳው 11ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ ነው። ጉዳዩ መፋጠን አለበት ተብሏል።
የኢህአዴግ ወደ ቀጣዩ ምርጫ በቀድሞው ቁመናው፣ በቀድሞው ችግሩ ከነበሽታው ሳይፈወስ ሳይድን ለኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ ነኝ ብሎ ሊቀርብ የሚችልበት ቁመና የለውም የሚል ግምገማ አድርገናል። ስለዚህ ከበሽታው የሚፈውሰው ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚቀርብ አገራዊ እንድነትን ህብረብሄራዊነትን የሚያጠናክር የፌዴራል ስርዓቱን ደግሞ በወረቀት ላይ ብቻ ሳይሆን እውነተኛ ፌዴራሊዝም እንዲሆን፣ ኢትዮጵያዊያን ከጫፍ እስከጫፍ የሚያምኑበት በአራት ክልሎች ያሉ አመራሮች ብቻ የሚወስኑበት ሳይሆን አፋሩም፣ ሶማሌውም፣ ጋምቤላውም፣ ቤንሻንሁሉም፣ ሐረሪውም ሁሉም አጋር የተባሉት ድርጅቶች የሚወክሏቸው ህዝቦችም ቤተኛ የሆኑበት ድርጅት መመስረት አለብን።
ካልሆነ ግን ከፋፋይ ሆኗል ህብረተሰቡን ከፋፍሏል፣ በህብረተሰቡ መካከል ግጭት ቁርሾና ቂም አምጥቷል፤ ይህን የሚሽር አስተሳሰብም አደረጃጀትም መገንባት አለብን የሚል ስለሆነ ኢህአዴግ መዋሃድ ካለበት አሁን ነው። ይህን ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብም በተለያየ ሁኔታ አስተያየት እየሰጠበት አባላትም በየደረጃው ያለው የድርጅቱ መዋቅርም እያየ በመጣበት ጊዜ ሁሉ እያደነቀውና በተስፋ እየጠበቀው ያለ ስለሆነ ይህን ተስፋ የሚያጨልም ወሳኔ ሊወሰን አይገባም በማለት ነው።
ጥድፊያ የሚለው ጉዳይ ሌሎች ጉዳዮች ላይ ቅድሚያ ሊሰጥ ይገባ ነበር፤ ሌሎች ጉዳዮች ቅድሚያ ሊያገኙ ይገባ ነበር፤ የውህደት አጀንዳ ይዘግይ ብለን ነበር የሚል ሃሳብ ተሰንዝሯል። በምክር ቤትም ቀርቦልን የተወያየነው ምክር ቤቱ በስራ አስፈጻሚ አጀንዳ አድርጎት ስራ አስፈጻሚው ቀደም ብሎ የያዘው ቀጠሮ በቀጠሮው የተገናኘው ምክር ቤትም ይህን ጉዳይ ብቻ ሊያይ መሆኑን ተወያይተን አጽድቀናል።
በምክር ቤት ደረጃም በሌሎች አጀንዳዎች ላይ መወያየት አይገባም ትኩረት አይሰጣቸውም ከሚል ሳይሆን ከቅድሚያ ቅድሚያ አሁን ፓርቲው የህግ የበላይነትን የሚያረጋግጥ ፓርቲ ከሆነ፣ የኑሮ ውድነትን የሚቀርፍ ፓርቲ ከሆነ፣ የኢትዮጵያ ህዝቦችን ችግር የሚፈታ ፓርቲ ከሆነ፣ ሰላም የሚያረጋግጥ ፓርቲ ከሆነ፣ ራሱን መጀመሪያ ጤናማና አንድ ፓርቲ መሆን መቻል አለበት።
አገር የሚመራ ፓርቲ ቁመና መላበስ አለበት። ይህን ቁመና እየተላበሰ፣ የህግ የበላይነትን እያሰከበረ፣ የህግ የበላይነትን ለመስከበር እኮ የፓርቲው ቁመና እኮ ነው አንዱ ችግር። ይህን እያደረገ የኢትዮጵያን ህዝቦች ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥያቄዎች እየፈታ መሄድ አለበት የሚል ነው።
አሁን ላይ እየተነሳ ያለው አዲስ ፓርቲ የሚፈጥርበት ነው የሚለው ሃሳብ መነሳት የነበረበት የዛሬ አስር ዓመት ነው። ምክንያቱም የዛሬ አስር ዓመት ፓርቲው መዋሃድ አለበት ተብሎ ፓርቲው ሲቀጥር፣ ሲገመግም፣ ሲንደረደር የነበረና ጥናት እንዲጠና እና አቅጣጫ አስቀምጦ ጥናቱን ሲከታተል የነበረ ድርጅት ነው።
እንደውም እኮ ጥናቱን ሲያስፈጽሙ የነበሩት የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ በነበሩበት ወቅት የህወሃት ስራ አስፈጻሚ አባል የሆኑት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ናቸው። እርሳቸውም የድርጅቱን ጸ/ቤት በመሩበት ጊዜ የህን ጥናት ሲከታተሉት ነበር። ስለዚህ ውህደት ፓርቲዎቹ ያስቀመጡት፣ ያቀዱት፣ ጉባዔ አቅጣጫ ያስቀመጠው እንጂ አዲስ ፓርቲ መፍጠሪያ ሊሆን አይችልም።
ይህን ፓርቲ እናዋህድ የሚል እቅድ ተይዞ ጥናት ተጠንቶ፣ እየጸደቀ መጥቶ ምክር ቤት ጉባዔ አቅጣጫ ሲያስቀምጥ አይ ይሄ አዲስ ፓርቲ መመስረት እንጂ ውህደት አይደለም ተብሎ መቃወም ነበረበት።
ስለዚህ ይህንን እኔ የማየው አሃዳዊነትን ለመመለስ ነው፣ የፌዴራል ስርዓቱን ለማፍረስ ነው፣ ህገመንግስት ለመጣስ ነው፣ ጸረዴሞክራሲያዊነትን ለማንገስ ነው እንደሚሉት ማስፈራሪያና ማደናገሪያ ካልሆነ በስተቀር አንዳችም ህጋዊም፣ ፖለቲካዊም ምክንያትና አስረጂነት የለውም ይህ ሃሳብ።
ፖለቲከኛ ሳይሆን ማንም ዜጋ እንደሚገነዘበው እውነቱ ሲመረመር እነዚህ አጋር ድርጅቶች የሚገኙባቸው አካባቢዎችና የአጋር ድርጅት አመራሮች ኢህአዴግ በሚወስናቸው ውሳኔዎች ኢትዮጵያዊያንን በሚጠቅሙ ኢትዮጵያ አጀንዳ በሆኑ አቅጣጫዎች ፖሊሲዎች፣ ደንቦች፣ በሚቀረጹበት ወቅት ይካተቱ ነበር ወይ? ሁለተኛ አፈጻጸሞች ሲገመገሙ ነበር ? አቅጣጫ ያስቀምጡ ነበር ወይ ብለን ብናይ ዋና ዋና የሚባሉት አገር የሚመራባቸው መስመሮች የሚተለሙት በኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ነው።
እነዚህ አመራሮች የስራ አስፈጻሚው አባላት አይደሉም። ቀጥሎ የስራ አስፈጻሚ ሃሳቦች የሚሰጡት ለምክር ቤት ነው፤ እነዚህ ወገኖች የምክር ቤት አባላት አይደሉም። ኢህአዴግ እነዚህን አቅጣጫዎች ካስቀመጠ ብኋላ እንደድርጅት እቅዶች ካስቀመጠ ብኋላ፣ ፖሊሲዎች ከነደፈ ብኋላ ወደመንግስት ነው የሚወስደው። ስለዚህ ወደ መንግስት በሚሄድበት ጊዜ ብቻ ኢህአዴገ የ የፈጨውንና የቦካውንና ጋገረወን እንካችሁ ተቀበሉን ቢጥማችሁም ባይጥማችሁም ብሉ ነው የሚባሉት።
ይህ ብቻ አይደለም ራሳቸውም ከዛሬ አስር ዓመት በፊት የአጋር ድርጅት አመራሮች ጥያቄ አድርገው ሲጠይቁት የነበረው እኛ ኢህአዴግያዊያንም ይህን ጥያቄ አጀንዳ አድርገን ስናነሳ የነበረነው ኢህአዴግ የቀደሙት አመራሮች ለምንድነው አጋሮች የሚገለሉት መቼ ነው ቤተኛ የሚሆኑት ሲባል የነበረ አሁንም ደግሞ ጥያቄው ጎልቶና ጎልብቶ የመጣው በተለይ ከአጋር ድርጅቶች መሆኑ ይህን ለማየት የሐዋሳው ጉባዔ በተደረገበት ጊዜ በመክፈቸቻ ንግግሩ፣ አንድም አጋር ፓርቲ የውህደትን አጀንዳ ሳያነሳ አላለፈም። ይህን ማየት ይቻላል። ውህደት ይፋጠን እንደምታዋህዱን እናምናለን፤ ጉባዔው በዚህ ውሳኔ ላይ እንደሚወስን እናምናለን፤ የሚል ጥሪ ሁሉ ሲያስተላልፉ በመጨረሻውም የጉባዔው የአቋም መገለጫ ጭምር የውህደት አጀንዳ ተቀባይነት ያለውና አጋር ፓረቲዎቻችንም በሚቀጥለው ጊዜ አብረን የአገር አቅጣጫን እንደምንተልምና አብረን ተዋህደን እንደምንቀጥል ቃል የተገባንበት ነው አንዱ ይህ ነው።
ሌላው ደግሞ አጋር ድርጅቶችን በማስገደድ ነው የተባለው በደንብ ማስተዋል የሚገባው ነገር የማስገደድ ዘመን አልፏል ነው። ማንም ማንን አስገድዶ ይህን ፈጽኝ አይባልም። አጋር ድርጅቶች እኮ ውህደትን የናፈቁበት አንደኛው ራሳቸውም እንደሚገልጹት የቀድሞው አሰራር አስገዳጅነት ስለነበረ ነው። በመንግስት አስገዳጅነት በፓርቲ አስጋዳጅነት ሃይል ይጫንባቸው ነበር። የሞግዚተ አስተዳደር ነበር፣ አሁን ከለውጡ ወዲህ ግን የሞግዚት አስተዳደር ቀርቷል።
ሌላው የአጋር ድርጅቶች አመራሮች የታገሉትና የመታገያ አጀንዳቸው የሞግዚት አስተዳደር ይቅር ነው። ሌላኛው አሁን እኮ አጋር ድርጅቶች ከምክር ቤት ውሳኔ ብኋላ ፈጥነው ወደ ውሳኔ የገቡት እኮ አጋር ድርጅቶች ናቸው። አብዴፓ ወስኗል፣ ቤጉህዴፓ ወስኗል፣ ሶዴፓ በስራ አስፈጻሚ ደረጃ ወስኗል፣ ሌሎቹም ይቀጥላሉ፤ የቀረ የለም ማለት ነው።
ከእኛ እህት ድርጅቶች ከሆነው ፈጥነው በጉባዔቸው ያጸደቁ ናቸው፤ፈጥነው እንዲሰበሰቡ፣ ፈጠነው በጉባዔ እንዲያጸድቁ አንድም ሰው ድምጹ ልዩነት እንዳያመጣ አቅጣጫ ተቀምጦ ተገደው ከሆነ ምናልባትም ተገደዋል የሚባል ከሆነ እነዚህ ወገኖች ከዚህ ቀደም ስታሰብ እንደነበረው እዛው የቀሩ የመሰለ አስተሳሰብ ስለሆነ ይህንን ተገዳችኋል አልተገደዳችሁም የሚለውን እናንተም እንደሚዲያ አጋር ድርጅቶችን አመራሮችንም፣ አባላትንም ህዝቡንም ፍላጎትን ብትሰሩበትና ለኢትዮጵያ ህዝብ ግልጽ ቢሆን መልካም ነው።
ምክንያቱም ቀድሞ እኛ ስለእነርሱ የምንናገርበት ዘመን የነበረው ነው ፣ እኛ ስለእነርሱ የምንናገርበት የምንወስንበት ዘመን ስላከተመ ማስገደድ የሚባል በኢትዮጵያ ውስጥ የማይሰራበት ዘመን ላይ ስለደረስን ይህን የሰጡበት አስተያየት መነሻው ምንም ይሁን ምን እኔ ትክክል አስተያየትም በዚያ ደረጃም አገር ከሚመራ አመራርም ይጠበቃል የሚል እምነት የለኝም።
የኢህአዴግ ውህደት ህጋዊ መስመር መከተልን በተመለከተ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ለኢቢሲ የሰጡት ማብራሪያ