መንግሥት በተለያዩ ወቅቶች ከሕብረተሰቡ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለማቃለል በርካታ መፍትሔ አቅጣጫዎችን እየቀየሰ ሲሠራ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ በተለይም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የችግሮች ምንጭ በሆነው የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ በልዩ ትኩረት እየሠራ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ ሕብረተሰቡን ለእንግልት የሚዳርጉ የተንዛዙ አሠራሮች እንዲሁም የሥራ ኃላፊዎችና ፈፃሚ ባለሞያዎች በቅንነት የአገልጋይነት ስሜት ተላብሰው ኃላፊነታቸውን አለመወጣታቸው አጥጋቢ ውጤት ላለመገኘቱ ምክንያት እንደሆኑ ይነሳል፡፡ መንግሥትም ባደረገው ጥልቅ ግምገማ በጉልህ ነጥሮ የወጣው የሕዝባዊ ወገንተኝነት መላላት መሆኑ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡
ለዚህም የሕዝብና የመንግሥት የሥራ ኃላፊነት የተጣለባቸው አመራሮች ፈፃሚ ባለሞያዎች ላይ ጣታቸውን ሲቀስሩ፤ ሠራተኞች ደግሞ የኃላፊዎች አሳምኖ የማሠራትና በዕውቀት የመምራት ችግርን እንደ ክፍተት ሲያነሱ ይደመጣል፡፡ የዛሬ ፍረዱኝ አምድ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ውስጥ የሚሠሩ ሠራተኞችን አቤቱታ ይዞ ቀርቧል። እነሆ!
ቅሬታ አቅራቢዎቹ
ከቅሬታ አቅራቢዎቹ መካከል አንዷ የሆነችው ወይዘሮ ኢክራም አብዱልወኪል በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽሕፈት ቤት የግዢና ንብረት ባለሞያነት ስትሠራ መቆየቷንና ከጽሕፈት ቤቷ ውጪ በውሰት በወረዳው ወሳኝ ኩነቶችና ምዝገባ ማስረጃ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት እንድትሠራ መጠየቋንና በወቅቱም እርሷን ጨምሮ ዘጠኝ ሠራተኞች በፈቃደኝነት ወደ ሥራ እንደገቡ ትናገራለች። በዚሁ ክፍልም ለሰባት ወራት አገልግለዋል።
በዚህ መሀልም በወረዳው በተደረገው አዲስ የሠራተኞች ምደባ መሰረት የትምህርትና የሥራ ዝግጅቷ በሚፈቅደው ልክ ከሐምሌ 1 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮም በውሰት ከተወሰደችበት ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽሕፈት ቤት ወደ ንግድና ኢንዱስትሪ ጽሕፈት ቤት የንግድ ቁጥጥር ባለሞያ ሆና ምደባ ይደርሳታል፡፡ ምደባውን በመቀበልም ወደሥራው የገባችውም የወረዳው ንግድና ኢንዱስትሪ ጽሕፈት ቤት የሥራ ኃላፊ ለቦታው ብቸኛ ባለሞያ በመሆኗ በቦታው ላይ ሥራውን ልታከናውን እንደሚገባት ስለተገለጸላት ነው።
በአዲሱ ምደባዋ በሥራ ላይ እያለች ግን የወረዳው ፐብሊክ ሠርቪስና ሠው ሀብት ልማት ጽሕፈት ቤት በድጋሜ ወደ ወሳኝ ኩነቶችና ነዋሪዎች አገልግሎት ጽሕፈት ቤት እንድትመለስ ደብዳቤ እንደፃፈላት የምትገልፀው ኢክራም፤ በምን አግባብ ይህ ጥያቄ እንደቀረበላት ስትጠይቅ ከከተማ አስተዳደሩ ሰርኩላር ደብዳቤ እንደወረደና መሥራት እንዳለባት ምላሽ እንደተሰጣት ትናገራለች፡፡ ነገር ግን ሰርኩላር ደብዳቤው የሚመለከተው ቀድሞ በጽሕፈት ቤቱ በቋሚነት ተመድበው ይሠሩ የነበሩና የተለያዩ ሥልጠናዎችን ሠልጥነው ወደተለያዩ ጽሕፈት ቤት የተደለደሉ ሠራተኞችን እንጂ በውሰት ሲሠሩ የነበሩትን እንዳልሆነ ታስረዳለች፡፡ በዚህ መሠረት ሌሎቹ ሠራተኞች ሲመለሱ እነርሱ ግን ውሰት ስለነበሩ በሰርኩላር እንደማይገደዱ ለሚመለከተው ክፍል እንዳሳወቁም ነው የምታስረዳው፡፡
የወረደው ሰርኩላር ደብዳቤ የማይመለከታት በመሆኑ በአዲሱ ምደባዋ ላይ ሥራዋን እንደቀጠለች የምትገልፀው ኢክራም፤ የወረዳው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወደ ጽሕፈት ቤቱ እንድትመለስ ትዕዛዛ ቢሰጥም ፈቃደኛ ሆና አለመሄዷን ትናገራለች፡፡ የጽሕፈት ቤቱ ሥራ በአግባቡ እየተሠራና ባለጉዳይ እየተስተናገደ ቢሆንም በውሰት የሄዱትን ሠራተኞች ኃላፊው በግዳጅ ለማስገባት እያደረጉ ያሉት ጥረት መነሻው ምንድን ነው? ብለው ቢጠይቁም ምላሽ ሊሰጣቸው የቻለ አካል አለመኖሩን ትገልፃለች፡፡
ዋና ሥራ አስፈፃሚው አስገድዶ ማስገባት የሚችልበት መመሪያ እንደሌለ ቢገልጹላቸውም፤ ‹‹በሥልጣኔ አዝዣለሁና ግቡ›› የሚል ቀጭን ትዕዛዝ ተሰጥቶናል ትላለች። በመቀጠልም ዋና ሥራ አስፈፃሚው ሌሎች የሥራ ኃላፊዎችን በመሰብሰብ ከሥራ እንዲታገዱ ትዕዛዝ አስተላለፉ። ትዕዛዙም ተፈጻሚ ሆኖ እሷና ሌሎች ሦስት ባልደረቦቿ ከሥራ እና ከደመወዝ ታግደዋል።
የወረዳው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ከመመሪያ ውጪ ለፈፀሙባቸው ድርጊትም ቅሬታ ለማቅረብ ወደ ወረዳው ፐብሊክ ሰርቪስና ሠው ሀብት ልማት ጽሕፈት ቤት እንዳቀኑና መመሪያ ሲጠይቁ ሊሰጣቸው ፈቃደኛ እንዳልነበር ትናገራለች፡፡ የሥራና የደመወዝ እግዱ ከመመሪያ አንጻር ትክክል አለመሆኑን ካጣሩ በኋላ ወደ ወረዳው ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ፣ ምክር ቤት፣ ኢህአዴግ ጽሕፈት ቤት ቅሬታቸውን ያሳውቃሉ፡፡ ነገር ግን ያገኙት ምላሽ ዋና ሥራ አስፈፃሚው በማለቱ ብቻ ፈጽሙ ከማለት የዘለለ መመሪያን ማዕከል ያደረገ ምላሽ ሊያገኙ አልቻሉም።
እግዱ በተላለፈ በ10ኛው ቀንም ዳግም ሌላ “በውሰት በጽሕፈት ቤቱ ይሠሩ የነበሩ ሠራተኞች ሌላ ተለዋጭ ሰርኩላር እስኪመጣ ድረስ እንዲቆዩ” የሚል ደብዳቤ መጣ፡፡ ይህንን እንዳወቁም ዋና ሥራ አስፈፃሚውን በፐብሊክ ሰርቪስ ሕግ መሠረት በደብዳቤ የታዘዘውን እንደሚቀበሉና ለመሥራትም ዝግጁ መሆናቸውን በመግለጽ እግዱ እንዲነሳላቸው ጠየቁ፤ ያቀረቡት ጥያቄ ግን ተቀባይነት አላገኘም፡፡ ለምን ብለው ሲጠይቁም፤ በእግድ ላይ የሚገኙ ሠራተኞች ይቅርታ ቢጠይቁም ሳይከሰሱ ወደ ሥራ ገበታቸው እንደማይመለሱ በዋና ሥራ አስፈፃሚው ትዕዛዝ እንደተሰጠ እንደተገለፀላቸው ትናገራለች፡፡
በሌላ በኩል እግዱ ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ ከሥራና ከደመወዝ ከታገደ በ15 ቀናት ውስጥ ለዲሲፕሊን ኮሚቴ ክስ ሊቀርብበት ይገባልና የሚቀርብባቸውን ክስ መጠባበቅ መጀመራቸውን፡፡ ወይዘሮ ኢክራም ትናገራለች። ነገር ግን ‹‹ተቸግራችሁ የምትበሉት ስታጡና ስትራቡ እግሬ ስር ትወድቃላችሁ›› ከሚለው መርህ ዘለል የዋና ሥራ አስፈፃሚው ምላሽ ውጪ ምላሽ አለማግኘታቸውን ገልጸላች። በዚህ መንገድም ከቆዩ ከ50 ቀናት በላይ ካሳለፉ በኋላ የክስ መጥሪያ ደርሷቸዋል።
ከአራቱ ሠራተኞች መካከልም፤ በእነዚህ ከሥራና ከደመወዝ በታገዱባቸው ቀናት ውስጥም ግልጽ ባልሆነ ምክንያት አንደኛው ተበዳይ አዲስ ወደተመደበበት የሥራ መደብ መመለሱንና ደመወዙም እንደተለቀቀለት ትናገራለች። ለምን የሚል ጥያቄ ቢያቀርቡም፤ ዋና ሥራ አስፈፃሚው ግን ‹‹በግልሽ ቢሮዬ መጥተሽ እንድታናግሪኝ›› የሚል ምክንያቱ ያልታወቀ ግብዣ እንዳቀረቡላት ቅሬታ አቅራቢዋ ታስታውሳለች፡፡ ለሁለቱ እግድ የተጣለባቸው ሠራተኞችም ‹‹ኢክራም ለብቻዋ ቢሮዬ መጥታ እንድታናግረኝ ጥሩልኝ›› የሚል መልዕክት እንደተላከባት፤ እርሷ ግን ስለ ሥራ ለመነጋገር ከሆነ በጋራ ከታገዱት ከቀሪዎቹ ሁለት የሥራ ባልደረቦቿ ጋር እንጂ ለብቻዋ ልታነጋግራቸው እንደማትችል ምላሽ መስጠቷን ትገልጻለች።
ለቀረበባቸው ክስም ለዲስፒሊን ኮሚቴ ምላሽ ሰጡ፤ ኮሚቴውም የደረሰበትን ድምዳሜ በመያዝ በአሠራሩ መሰረት የውሳኔ ሃሳቡን ለዋና ሥራ አስፈፃሚው አቅርቧል። በተባራሪ ባገኙት መረጃም ኮሚቴው ወደ ሥራ ገበታቸው እንዲመለሱ ውሳኔውን አሳልፎ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ዋና ሥራ አስፈፃሚው ውሳኔውን የማሻሻል ሥልጣን ስላላቸው ከኮሚቴው ውሳኔ የተለየ ቅጣት ጥለውባቸዋል፡፡ በዚህም ቅሬታ አቅራቢዎቹ የተከሰሱበትና ከሥራ የታገዱበት መነሻ ምክንያት አንድ ቢሆንም በስተመጨረሻ የደረሳቸው ውሳኔ ግን የተለያየ መሆኑን ታመለክታለች፡፡ በዚህም ሁለቱ ቅሬታ አቅራቢዎች ላይ ሙሉ ደመወዛቸው አንድ ሦስተኛ እየተደረገ እንዲቆረጥ ብሎም አንድ ደረጃ ዝቅ እንዲደረጉ ቅጣት የተጣለባቸው ሲሆን፤ በእርሷ ላይ ደግሞ በተመሳሳይ መልኩ ደመወዟ ተቆርጦ ሁለት ደረጃ ዝቅ እንድትል ይወሰንባታል፡፡
በአሁኑ ወቅትም ደመወዝ ሳይሰጣቸው ሁለት ወራት ከ 11 ቀናት እንዳለፋቸው የምትገልጸው ኢክራም፤ ከዋና ሥራ አስፈፃሚው ጋር መጋጨታቸው መመሪያውን መሠረት አድርጎ ሊያስተናግዳቸው የሚችል አካል እንዲያጡ እንዳደረጋቸው ትናገራለች፡፡ በዚህም ምክንያት ለብቻዋ የምታሳድጋትን አንድያ ልጇን ወርሐዊ የትምህርት ቤት ክፍያ እንኳ መክፈል እንዳልቻለችና በቀጣይም ከአራት ሺህ ወደ አንድ ሺህ ብር ዝቅ ባለው ደመወዟ ኑሮን እንድትገፋ መፈረዱ ግፍ እንደሆነባት ገልጻለች።
በተመሳሳይም የዚሁ ወረዳ ሠራተኛ የሆኑትና ተመሳሳይ በደል ተፈጽሞብናል የሚሉት አቤኔዘር አየለ እና ሀያት ሙደሲር ከሌሎች ሠራተኞች ተነጥለው መታገዳቸው ግርታን እንደፈጠረባቸውና በዚህም ምክንያት ወርሐዊ ወጪያቸውንና የትምህርት ክፍያዎቻቸውን ለመፈጸም እንደተሳናቸው አስታውቀዋል። ቅሬታቸውን በየደረጃው ያቀረቡባቸው ቢሮዎች ያሉ የሥራ ኃለፊዎችም የተበላሸ አሠራርን ከማረም ይልቅ ለአመራር በመወገን ጉዳያቸውን እንዳድበሰበሱትና ፍትህ እንደነፈጓቸው ነው የሚናገሩት።
ሰነዶች
ዝግጅት ክፍላችን ባለጉዳዮቹ ባቀረቡት ቅሬታ መሰረት የሰነድ ማስረጃዎችን ለመመልከት ሞክሯል። በዚህም መሰረት ጉዳዩን በተመለከተ ከቅሬታ አቅራቢዎቹና ከወረዳው የሰነድ ማስረጃዎችን አግኝተናል፡፡ በዚህም የወረዳው የወሳኝ ኩነቶችና ምዝገባ ማስረጃ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ለክብር መዝገብ ሹሞች አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ሥልጠና ለመስጠት የነደፈው የሥራ ማሳለጫ ዕቅድ ማሳያ (የሥልጠና ፕሮፖዛል) አንዱ ነው፡፡ በሥልጠናው ላይም ቅሬታ አቅራቢዎቹ እንደተገኙ በቀን 29/06/2011 ዓ.ም የተወሰደው የተሳታፊዎች ሥም ዝርዝር ያመለክታል፡፡ የዲሲፕሊን ኮሚቴ የሠራተኞቹ እግድ ተነስቶ ወደ ውሰት ወደተመደቡበት ጽሕፈት ቤት እንዲገቡ ውሳኔ ሐሳብ ያቀረቡበት ቃለ ጉባዔ እንዲሁም ዋና ሥራ አስፈፃሚውን ጨምሮ አስተዳደሩ ሠራተኞቹን አወያይቶ ወደ ሥራ ለማስገባት ያደረገውን ጥረት የሚያሳይ ቃለጉባዔም ተመልክተናል፡፡
በዚህም አስተዳደሩ ጽሕፈት ቤቱ ላይ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለማቃለል አገልግሎት አሰጣጥን ማቀላጠፍ እንደሚገባ መግለጹንና ፤ በጽሕፈት ቤቱ የፀጥታ ችግር ያለ በመሆኑ የፀጥታ አካል መመደብ ካለበት እንዲታሰብበት ሐሳቦች መነሳታቸውንም ከቃለ ጉባዔው ያሳያል፡፡ በተያያዘ በውሰት ሲወሰዱ ቃል ተገብቶ እንደነበርና ጥቅማ ጥቅማቸውንም እንደተከለከሉ ከሠራተኞች ሃሳብ የተነሳ ሲሆን፤ ዋና ሥራ አስፈፃሚውም በወረዳው የተሠሩ መልካም ተግባራትን የሚያጠለሹ ችግሮች እንዳይከሰቱ ሠራተኞች ሁኔታውን ተረድተው ወደ ሥራ እንዲገቡና የተነሱ ክፍተቶችን አመራሩ እንደ ግብዓት ወስዶ እንደሚፈታም ማወያየታቸውን ለመረዳት ችለናል፡፡
ቅሬታ አቅራቢዎቹ በውሰት ወደተመደቡበት ጽሕፈት ቤት አገልግሎት እንዲሰጡ ያሳወቀባቸው ደብዳቤዎች፣ በድጋሚ በውሰት ወደነበሩበት ጽሕፈት ቤት እንዲመለሱ የተገለጸበትና ይህን ተላልፈው ከተገኙ ግን በመንግሥት ሠራተኛ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ መሠረት አስተዳደራዊ ዕርምጃ እንደሚወሰድ በቋሚነት የተመደቡባቸው ጽሕፈት ቤቶች የፃፉባቸው ደብዳቤዎችም የተመለከትናቸው ሰነዶች ናቸው፡፡ ይህን ተከትሎም በትውስት አገልግሎት እንዲሰጡ በተደጋጋሚ በቃልና በጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም ትዕዛዝ ባለማክበር ሕብረተሰቡን በማጉላላት ጥፋት ስለፈጸሙ ከሥራና ከደመወዝ ታግደው ለዲሲፕሊን ኮሚቴ እንዲቀርቡ የተወሰነባቸው ደብዳቤዎችም ይገኛሉ፡፡
ሠራተኞቹ ላይ የዲሲፕሊን ክስ መመስረቱን የሚያሳዩ ደብዳቤዎችንም አግኝተናል፡፡ ደብዳቤዎቹ በቀን 13/01/2012 ዓ.ም በመዝገብ ቁጥር ኮ/ቀ/ክ/ከ/ወ/12/የሰ/ኃ/010/12 ወጪ ሆነው የወጡ ሲሆኑ፤ በውሰት በተመደቡበት ጽሕፈት ቤት በመመሪያው መሠረት ለማገልገል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የዲሲፕሊን ኮሚቴ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጣቸው ከሥራና ከደመወዝ እንዲታገዱ ጽሕፈት ቤቶቻቸው በመጠየቃቸው ኮሚቴው ጉዳዩን መርምሮ ውሳኔ እንደሚሰጥም ማሳወቁ በደብዳቤው ይነበባል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና ሠው ሀብት ልማት ቢሮ በቀን 3/11/2011 ዓ.ም በቁጥር 11-ጠ11-01/02/012 ወጪ አድርጎ ለክፍለ ከተሞች የላከው ደብዳቤ ሌላኛው ሰነድ ሲሆን፤ በዚህም በተለያዩ ጊዜያቶች በዘርፉ ሥልጠና ወስደው ወደሌሎች ዘርፎች የተደለደሉ ካሉ በውሰት ሲያገለግሉ በቆዩበት ጽሕፈት ቤት ሆነው ተለዋጭ መመሪያ እስኪተላለፍ ድረስ እንዲሠሩ ያዛል፡፡ በተያያዘ በቀን 14/12/2011 ዓ.ም በመዝገብ ቁጥር 03-ጠ11-24-21-251 ቢሮው ለአስሩም ክፍለ ከተሞች በጽሕፈት ቤቱ በትውስት የሚሠሩ ሠራተኞችን በተመለከተ ያወረደው ሰርኩላር ደብዳቤ ይገኛል፡፡
በደብዳቤው በአዲሱ መዋቅር የተደረገው የሠራተኛ ድልድል መሠረት ወደተመደቡበት ቋሚ ሥራ መደብ እንዲመለሱ ጫና እየተደረገና ደመወዛቸውም እየተቆረጠ መሆኑ፣ የዲጂታል መታወቂያ ህትመት ለማከናወን የለውጥ እንቅፋ መሆኑን ኤጀንሲው ማሳወቁን ያትታል፡፡ በመሆኑም በትውስት የሚያገለግሉ ሠራተኞች ተለዋጭ መመሪያ እስኪተላለፍ በጽሕፈት ቤቱ እንዲቆዩ በጥብቅ ደብዳቤው ያሳስባል፡፡ በዚህ መሀል በሠራተኞች ላይ በሚፈጠረው እንግልትና በሥራው ለሚደርሰው ችግር ተጠያቂነት የሚያስከትል መሆኑንም ያሳያል፡፡
አቤቱታ የቀረበላቸው ተቋማት ምላሾች
የፍረዱኝ ባለጉዳዮቻችን ቅሬታ የቀረበለት የወረዳው ኢህአዴግ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ብዙአየሁ ማርቆስ፤ ጉዳዩ ለጽሕፈት ቤቱ አግባብነት ባለው መልኩ የተደራጀ ቅሬታ እንዳልቀረበለት ይናገራሉ፡፡ በዚህም የጽሕፈት ቤቱ ድርጅት ኮሚቴ ጉዳዩን የአጀንዳው አካል አድርጎ ለመገምገም እንዳልቻለ የሚናገሩት አቶ ብዙአየሁ፤ አቤቱታውን በተመለከተ ወረዳው ያየበትና ችግሩን ለማቃለል የወሰደው ዕርምጃ ትክክልና ተገቢ እንደሆነ ነው የገለጹልን።
ሌላኛው በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የወረዳው ፐብሊክ ሰርቪስና ሠው ሀብት ልማት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ግዛቸው ይበልጣል በበኩላቸው፤ በአዲሱ በጀት ዓመት መጀመሪያ በተደረገው አዲስ ምደባ ከመካሄዱ አስቀድሞ ቅሬታ አቅራቢዎቹ፤ በውሰት ይሠሩ እንደነበር ነው የሚያስረዱት፡፡ በዚህም ቅሬታ አቅራቢዎቹ ወደተለያዩ ጽሕፈት ቤቶች ምደባ ተሰጥቷቸዋል፡፡
ነገር ግን ከከተማ አስተዳደሩ ፐብሊክ ሰርቪስና ሠው ሀብት ልማት ቢሮ የወረደው ሰርኩላር ደብዳቤ ደግሞ በውሰት በጽሕፈት ቤቱ ሲሠሩ የነበሩና ሥልጠና የወሰዱ ፈፃሚ ባለሞያዎች በሥራው ላይ እንዲቆዩ ለሁለተኛ ጊዜ አቅጣጫ ሰጠ፡፡ ይህንን መነሻ በማድረግም በተለያዩ ጊዜያት የወረዳው ፐብሊክ ሰርቪስና ሠው ሀብት ልማት ጽሕፈት ቤት መድረክ ፈጥሮ ቅሬታ አቅራቢዎቹ ሥራውን እንዲሠሩ ለማወያየት ቢሞክርም፤ መደበኛ በሆነ ስብሰባም ጭምር ለማግባባት ቢሞከረም ሦስቱ ሠራተኞች ግን አቅጣጫውን ተቀብለው ለመሥራት ፈቃደኛ ሊሆኑ አልቻሉም፡፡
ይህ ተደጋጋሚ ሙከራ ውጤት ባለማምጣቱ የጽሕፈት ቤቶቻቸው የቅርብ ኃላፊዎች ወደ ሥራ እንዲመለሱ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷቸዋል፡፡ ባለጉዳዮቹ ግን ምንም ዓይነት ማስተካከያ አላደረጉም። በዚህም ቅሬታ አቅራቢዎቹ ከጽሕፈት ቤቱ በመነሳታቸው ምክንያት ጽሕፈት ቤቱ ባዶ ሆኖ አገልግሎት መስጠት አቁሞ ነዋሪዎች ለከፍተኛ እንግልት ተዳርገው እንደነበር አቶ ግዛቸው ያስታውሳሉ፡፡ ቅሬታ አቅራቢዎቹ የተሰጣቸውን ሥራ ከማከናወን ይልቅ አመራሩን መስደብና መመሪያ መጣስን እንደ አማራጭ በመውሰዳቸው ከሥራ ታግደው በዲሲፕሊን ኮሚቴ እንዲታይ ተደርጓል ይላሉ፡፡
የወረዳው ዲሲፕሊን ኮሚቴ የውሳኔ ሃሳቡን ለወረዳው የበላይ ኃላፊ ለሆኑት ዋና ሥራ አስፈፃሚው የሰጠ ሲሆን፤ ኃላፊውም እንደ ተከሳሾቹ ድርጊት ውሳኔውን የማሻሻል፣ ከፍም ሆነ ዝቅ የማድረግ ሥልጣን ያላቸው በመሆኑ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ያሳረፈውን ውሳኔ ከፍ በማድረግ አሻሽለው ወስነዋል፡፡ በዚህም በተለያየ ጊዜ የወረደ ሰርኩላር ደብዳቤ ባልተቀበለችውና አመራርን በሰደበችው በአንደኛዋ ቅሬታ አቅራቢ፡፡ ኢክራም ላይ ከፍ ያለ ቅጣት ለመጣሉ ምክንያት ሲሆን፤ በቀሪ ሁለቱም ላይ በተመሳሳይ ቀጣይ ለእነርሱም ሆነ ለሌሎች ማስተማሪያ ይሆናል ተብሎ የታመነበት የእርምት ዕርምጃ እንደተወሰደ አቶ ግዛቸው ያስረዳሉ፡፡ በሒደቱ በተለይም ፡፡ ኢክራም ከባድ የዲሲፕሊን ጥሰት የፈፀመች መሆኑንም አክለው ተናግረዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ቅሬታ አቅራቢዎቹ ከደመወዝ ውጪ እንደሆኑ በማንሳት፤ ምን ያህል ተገቢ ነው? ስንል ለአቶ ግዛቸው ላነሳነው ጥያቄ ማብራሪያ ሲሰጡም፤ በሁለት ወር ውስጥ ወይንም በ60 ቀናት ውስጥ ውሳኔ የማያገኙ ከሆነ ተከሳሾች ባለመብት ይሆናሉ ብለውናል። የቅሬታ አቅራቢዎቹ ጉዳይ የታየው 60 ቀናት ሊሞላ ጥቂት ቀናቶች ሲቀሩ ነውና ስለምን ይህን ያክል ጊዜን መጠበቅ አስፈለገ? ቀጥለን ያቀረብነው ጥያቄም ነበር፡፡ “በአንድ በኩል ዋና ሥራ አስፈፃሚው በሥልጠና ምክንያት ባለመኖራቸው ሲሆን፤ በዋናነት ግን ቅሬታ አቅራቢዎቹ የፈፀሙት ከባድ የሥነምግባር ግድፈት እንዲማሩ ለማድረግ አስበን ነው እስከ 50 ቀናት የቆየው” ሲሉ የዘገየበትን ምክንያት አብራርተዋል።
የዲሲፒሊን ኮሚቴው
የወረዳው ዲሲፕሊን ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ጌቱ ወልደጊዮርጊስ፤ መጀመሪያ ከሳሾችን በደብዳቤ መረጃ እንደጠየቁ ነው የሚናገሩት፡፡ ይሁን እንጂ ከሳሽ የሆኑት ጽሕፈት ቤት መረጃ እንዲያቀርቡ በተጠየቁበት ቀን ሊያቀርቡ አልቻሉም፡፡ በዚህም ኮሚቴው ሠራተኞቹ እግዱ ተነስቶላቸው በውሰት ወደተመደቡበት ጽሕፈት ቤት ወደ ሥራ እንዲገቡ ውሳኔውን ያሳርፋል፡፡ ዋና ሥራ አስፈፃሚው ድጋሜ እንዲታይ እንደጠየቁ በማንሳት፤ ኮሚቴው በድጋሜ የማየት ሥልጣን ስላሌለው ጥያቄውን ሊቀበል እንዳልቻለም ያስረዳሉ፡፡
በጉዳዩ ላይ የወረዳው ዋና ሥራ አስፈፃሚ፣ የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚና ፐብሊክ ሰርቪስና ሠው ሀብት ልማት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና ሠው ሀብት ልማት ቢሮ የሠው ሀብት ሥራ አመራር ኢንስፔክሽን ዳይሬክተር የሰጡትን ምላሽ በጥቅምት 17 ቀን 2012 ዓ.ም ዕትማችን ይዘን እንደምንቀርብ እንገልፃለን፡፡
የሚል ጥያቄ ቢያቀርቡም፤ ዋና ሥራ አስፈፃሚው ግን ‹‹በግልሽ ቢሮዬ መጥተሽ እንድታናግሪኝ›› የሚል ምክንያቱ ያልታወቀ ግብዣ እንዳቀረቡላት ቅሬታ አቅራቢዋ ታስታውሳለች፡፡ ለሁለቱ እግድ የተጣለባቸው ሠራተኞችም ‹‹ኢክራም ለብቻዋ ቢሮዬ መጥታ እንድታናግረኝ ጥሩልኝ›› የሚል መልዕክት እንደተላከባት፤ እርሷ ግን ስለ ሥራ ለመነጋገር ከሆነ በጋራ ከታገዱት ከቀሪዎቹ ሁለት የሥራ ባልደረቦቿ ጋር እንጂ ለብቻዋ ልታነጋግራቸው እንደማትችል ምላሽ መስጠቷን ትገልጻለች።
ለቀረበባቸው ክስም ለዲስፒሊን ኮሚቴ ምላሽ ሰጡ፤ ኮሚቴውም የደረሰበትን ድምዳሜ በመያዝ በአሠራሩ መሰረት የውሳኔ ሃሳቡን ለዋና ሥራ አስፈፃሚው አቅርቧል። በተባራሪ ባገኙት መረጃም ኮሚቴው ወደ ሥራ ገበታቸው እንዲመለሱ ውሳኔውን አሳልፎ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ዋና ሥራ አስፈፃሚው ውሳኔውን የማሻሻል ሥልጣን ስላላቸው ከኮሚቴው ውሳኔ የተለየ ቅጣት ጥለውባቸዋል፡፡ በዚህም ቅሬታ አቅራቢዎቹ የተከሰሱበትና ከሥራ የታገዱበት መነሻ ምክንያት አንድ ቢሆንም በስተመጨረሻ የደረሳቸው ውሳኔ ግን የተለያየ መሆኑን ታመለክታለች፡፡ በዚህም ሁለቱ ቅሬታ አቅራቢዎች ላይ ሙሉ ደመወዛቸው አንድ ሦስተኛ እየተደረገ እንዲቆረጥ ብሎም አንድ ደረጃ ዝቅ እንዲደረጉ ቅጣት የተጣለባቸው ሲሆን፤ በእርሷ ላይ ደግሞ በተመሳሳይ መልኩ ደመወዟ ተቆርጦ ሁለት ደረጃ ዝቅ እንድትል ይወሰንባታል፡፡
በአሁኑ ወቅትም ደመወዝ ሳይሰጣቸው ሁለት ወራት ከ 11 ቀናት እንዳለፋቸው የምትገልጸው ኢክራም፤ ከዋና ሥራ አስፈፃሚው ጋር መጋጨታቸው መመሪያውን መሠረት አድርጎ ሊያስተናግዳቸው የሚችል አካል እንዲያጡ እንዳደረጋቸው ትናገራለች፡፡ በዚህም ምክንያት ለብቻዋ የምታሳድጋትን አንድያ ልጇን ወርሐዊ የትምህርት ቤት ክፍያ እንኳ መክፈል እንዳልቻለችና በቀጣይም ከአራት ሺህ ወደ አንድ ሺህ ብር ዝቅ ባለው ደመወዟ ኑሮን እንድትገፋ መፈረዱ ግፍ እንደሆነባት ገልጻለች።
በተመሳሳይም የዚሁ ወረዳ ሠራተኛ የሆኑትና ተመሳሳይ በደል ተፈጽሞብናል የሚሉት አቤኔዘር አየለ እና ሀያት ሙደሲር ከሌሎች ሠራተኞች ተነጥለው መታገዳቸው ግርታን እንደፈጠረባቸውና በዚህም ምክንያት ወርሐዊ ወጪያቸውንና የትምህርት ክፍያዎቻቸውን ለመፈጸም እንደተሳናቸው አስታውቀዋል። ቅሬታቸውን በየደረጃው ያቀረቡባቸው ቢሮዎች ያሉ የሥራ ኃለፊዎችም የተበላሸ አሠራርን ከማረም ይልቅ ለአመራር በመወገን ጉዳያቸውን እንዳድበሰበሱትና ፍትህ እንደነፈጓቸው ነው የሚናገሩት።
ሰነዶች
ዝግጅት ክፍላችን ባለጉዳዮቹ ባቀረቡት ቅሬታ መሰረት የሰነድ ማስረጃዎችን ለመመልከት ሞክሯል። በዚህም መሰረት ጉዳዩን በተመለከተ ከቅሬታ አቅራቢዎቹና ከወረዳው የሰነድ ማስረጃዎችን አግኝተናል፡፡ በዚህም የወረዳው የወሳኝ ኩነቶችና ምዝገባ ማስረጃ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ለክብር መዝገብ ሹሞች አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ሥልጠና ለመስጠት የነደፈው የሥራ ማሳለጫ ዕቅድ ማሳያ (የሥልጠና ፕሮፖዛል) አንዱ ነው፡፡ በሥልጠናው ላይም ቅሬታ አቅራቢዎቹ እንደተገኙ በቀን 29/06/2011 ዓ.ም የተወሰደው የተሳታፊዎች ሥም ዝርዝር ያመለክታል፡፡ የዲሲፕሊን ኮሚቴ የሠራተኞቹ እግድ ተነስቶ ወደ ውሰት ወደተመደቡበት ጽሕፈት ቤት እንዲገቡ ውሳኔ ሐሳብ ያቀረቡበት ቃለ ጉባዔ እንዲሁም ዋና ሥራ አስፈፃሚውን ጨምሮ አስተዳደሩ ሠራተኞቹን አወያይቶ ወደ ሥራ ለማስገባት ያደረገውን ጥረት የሚያሳይ ቃለጉባዔም ተመልክተናል፡፡
በዚህም አስተዳደሩ ጽሕፈት ቤቱ ላይ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለማቃለል አገልግሎት አሰጣጥን ማቀላጠፍ እንደሚገባ መግለጹንና ፤ በጽሕፈት ቤቱ የፀጥታ ችግር ያለ በመሆኑ የፀጥታ አካል መመደብ ካለበት እንዲታሰብበት ሐሳቦች መነሳታቸውንም ከቃለ ጉባዔው ያሳያል፡፡ በተያያዘ በውሰት ሲወሰዱ ቃል ተገብቶ እንደነበርና ጥቅማ ጥቅማቸውንም እንደተከለከሉ ከሠራተኞች ሃሳብ የተነሳ ሲሆን፤ ዋና ሥራ አስፈፃሚውም በወረዳው የተሠሩ መልካም ተግባራትን የሚያጠለሹ ችግሮች እንዳይከሰቱ ሠራተኞች ሁኔታውን ተረድተው ወደ ሥራ እንዲገቡና የተነሱ ክፍተቶችን አመራሩ እንደ ግብዓት ወስዶ እንደሚፈታም ማወያየታቸውን ለመረዳት ችለናል፡፡
ቅሬታ አቅራቢዎቹ በውሰት ወደተመደቡበት ጽሕፈት ቤት አገልግሎት እንዲሰጡ ያሳወቀባቸው ደብዳቤዎች፣ በድጋሚ በውሰት ወደነበሩበት ጽሕፈት ቤት እንዲመለሱ የተገለጸበትና ይህን ተላልፈው ከተገኙ ግን በመንግሥት ሠራተኛ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ መሠረት አስተዳደራዊ ዕርምጃ እንደሚወሰድ በቋሚነት የተመደቡባቸው ጽሕፈት ቤቶች የፃፉባቸው ደብዳቤዎችም የተመለከትናቸው ሰነዶች ናቸው፡፡ ይህን ተከትሎም በትውስት አገልግሎት እንዲሰጡ በተደጋጋሚ በቃልና በጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም ትዕዛዝ ባለማክበር ሕብረተሰቡን በማጉላላት ጥፋት ስለፈጸሙ ከሥራና ከደመወዝ ታግደው ለዲሲፕሊን ኮሚቴ እንዲቀርቡ የተወሰነባቸው ደብዳቤዎችም ይገኛሉ፡፡
ሠራተኞቹ ላይ የዲሲፕሊን ክስ መመስረቱን የሚያሳዩ ደብዳቤዎችንም አግኝተናል፡፡ ደብዳቤዎቹ በቀን 13/01/2012 ዓ.ም በመዝገብ ቁጥር ኮ/ቀ/ክ/ከ/ወ/12/የሰ/ኃ/010/12 ወጪ ሆነው የወጡ ሲሆኑ፤ በውሰት በተመደቡበት ጽሕፈት ቤት በመመሪያው መሠረት ለማገልገል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የዲሲፕሊን ኮሚቴ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጣቸው ከሥራና ከደመወዝ እንዲታገዱ ጽሕፈት ቤቶቻቸው በመጠየቃቸው ኮሚቴው ጉዳዩን መርምሮ ውሳኔ እንደሚሰጥም ማሳወቁ በደብዳቤው ይነበባል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና ሠው ሀብት ልማት ቢሮ በቀን 3/11/2011 ዓ.ም በቁጥር 11-ጠ11-01/02/012 ወጪ አድርጎ ለክፍለ ከተሞች የላከው ደብዳቤ ሌላኛው ሰነድ ሲሆን፤ በዚህም በተለያዩ ጊዜያቶች በዘርፉ ሥልጠና ወስደው ወደሌሎች ዘርፎች የተደለደሉ ካሉ በውሰት ሲያገለግሉ በቆዩበት ጽሕፈት ቤት ሆነው ተለዋጭ መመሪያ እስኪተላለፍ ድረስ እንዲሠሩ ያዛል፡፡ በተያያዘ በቀን 14/12/2011 ዓ.ም በመዝገብ ቁጥር 03-ጠ11-24-21-251 ቢሮው ለአስሩም ክፍለ ከተሞች በጽሕፈት ቤቱ በትውስት የሚሠሩ ሠራተኞችን በተመለከተ ያወረደው ሰርኩላር ደብዳቤ ይገኛል፡፡
በደብዳቤው በአዲሱ መዋቅር የተደረገው የሠራተኛ ድልድል መሠረት ወደተመደቡበት ቋሚ ሥራ መደብ እንዲመለሱ ጫና እየተደረገና ደመወዛቸውም እየተቆረጠ መሆኑ፣ የዲጂታል መታወቂያ ህትመት ለማከናወን የለውጥ እንቅፋ መሆኑን ኤጀንሲው ማሳወቁን ያትታል፡፡ በመሆኑም በትውስት የሚያገለግሉ ሠራተኞች ተለዋጭ መመሪያ እስኪተላለፍ በጽሕፈት ቤቱ እንዲቆዩ በጥብቅ ደብዳቤው ያሳስባል፡፡ በዚህ መሀል በሠራተኞች ላይ በሚፈጠረው እንግልትና በሥራው ለሚደርሰው ችግር ተጠያቂነት የሚያስከትል መሆኑንም ያሳያል፡፡
አቤቱታ የቀረበላቸው ተቋማት ምላሾች
የፍረዱኝ ባለጉዳዮቻችን ቅሬታ የቀረበለት የወረዳው ኢህአዴግ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ብዙአየሁ ማርቆስ፤ ጉዳዩ ለጽሕፈት ቤቱ አግባብነት ባለው መልኩ የተደራጀ ቅሬታ እንዳልቀረበለት ይናገራሉ፡፡ በዚህም የጽሕፈት ቤቱ ድርጅት ኮሚቴ ጉዳዩን የአጀንዳው አካል አድርጎ ለመገምገም እንዳልቻለ የሚናገሩት አቶ ብዙአየሁ፤ አቤቱታውን በተመለከተ ወረዳው ያየበትና ችግሩን ለማቃለል የወሰደው ዕርምጃ ትክክልና ተገቢ እንደሆነ ነው የገለጹልን።
ሌላኛው በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የወረዳው ፐብሊክ ሰርቪስና ሠው ሀብት ልማት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ግዛቸው ይበልጣል በበኩላቸው፤ በአዲሱ በጀት ዓመት መጀመሪያ በተደረገው አዲስ ምደባ ከመካሄዱ አስቀድሞ ቅሬታ አቅራቢዎቹ፤ በውሰት ይሠሩ እንደነበር ነው የሚያስረዱት፡፡ በዚህም ቅሬታ አቅራቢዎቹ ወደተለያዩ ጽሕፈት ቤቶች ምደባ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ነገር ግን ከከተማ አስተዳደሩ ፐብሊክ ሰርቪስና ሠው ሀብት ልማት ቢሮ የወረደው ሰርኩላር ደብዳቤ ደግሞ በውሰት በጽሕፈት ቤቱ ሲሠሩ የነበሩና ሥልጠና የወሰዱ ፈፃሚ ባለሞያዎች በሥራው ላይ እንዲቆዩ ለሁለተኛ ጊዜ አቅጣጫ ሰጠ፡፡
ይህንን መነሻ በማድረግም በተለያዩ ጊዜያት የወረዳው ፐብሊክ ሰርቪስና ሠው ሀብት ልማት ጽሕፈት ቤት መድረክ ፈጥሮ ቅሬታ አቅራቢዎቹ ሥራውን እንዲሠሩ ለማወያየት ቢሞክርም፤ መደበኛ በሆነ ስብሰባም ጭምር ለማግባባት ቢሞከረም ሦስቱ ሠራተኞች ግን አቅጣጫውን ተቀብለው ለመሥራት ፈቃደኛ ሊሆኑ አልቻሉም፡፡ ይህ ተደጋጋሚ ሙከራ ውጤት ባለማምጣቱ የጽሕፈት ቤቶቻቸው የቅርብ ኃላፊዎች ወደ ሥራ እንዲመለሱ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷቸዋል፡፡
ባለጉዳዮቹ ግን ምንም ዓይነት ማስተካከያ አላደረጉም። በዚህም ቅሬታ አቅራቢዎቹ ከጽሕፈት ቤቱ በመነሳታቸው ምክንያት ጽሕፈት ቤቱ ባዶ ሆኖ አገልግሎት መስጠት አቁሞ ነዋሪዎች ለከፍተኛ እንግልት ተዳርገው እንደነበር አቶ ግዛቸው ያስታውሳሉ፡፡ ቅሬታ አቅራቢዎቹ የተሰጣቸውን ሥራ ከማከናወን ይልቅ አመራሩን መስደብና መመሪያ መጣስን እንደ አማራጭ በመውሰዳቸው ከሥራ ታግደው በዲሲፕሊን ኮሚቴ እንዲታይ ተደርጓል ይላሉ፡፡
የወረዳው ዲሲፕሊን ኮሚቴ የውሳኔ ሃሳቡን ለወረዳው የበላይ ኃላፊ ለሆኑት ዋና ሥራ አስፈፃሚው የሰጠ ሲሆን፤ ኃላፊውም እንደ ተከሳሾቹ ድርጊት ውሳኔውን የማሻሻል፣ ከፍም ሆነ ዝቅ የማድረግ ሥልጣን ያላቸው በመሆኑ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ያሳረፈውን ውሳኔ ከፍ በማድረግ አሻሽለው ወስነዋል፡፡ በዚህም በተለያየ ጊዜ የወረደ ሰርኩላር ደብዳቤ ባልተቀበለችውና አመራርን በሰደበችው በአንደኛዋ ቅሬታ አቅራቢ፡፡ ኢክራም ላይ ከፍ ያለ ቅጣት ለመጣሉ ምክንያት ሲሆን፤ በቀሪ ሁለቱም ላይ በተመሳሳይ ቀጣይ ለእነርሱም ሆነ ለሌሎች ማስተማሪያ ይሆናል ተብሎ የታመነበት የእርምት ዕርምጃ እንደተወሰደ አቶ ግዛቸው ያስረዳሉ፡፡ በሒደቱ በተለይም ፡፡ ኢክራም ከባድ የዲሲፕሊን ጥሰት የፈፀመች መሆኑንም አክለው ተናግረዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ቅሬታ አቅራቢዎቹ ከደመወዝ ውጪ እንደሆኑ በማንሳት፤ ምን ያህል ተገቢ ነው? ስንል ለአቶ ግዛቸው ላነሳነው ጥያቄ ማብራሪያ ሲሰጡም፤ በሁለት ወር ውስጥ ወይንም በ60 ቀናት ውስጥ ውሳኔ የማያገኙ ከሆነ ተከሳሾች ባለመብት ይሆናሉ ብለውናል። የቅሬታ አቅራቢዎቹ ጉዳይ የታየው 60 ቀናት ሊሞላ ጥቂት ቀናቶች ሲቀሩ ነውና ስለምን ይህን ያክል ጊዜን መጠበቅ አስፈለገ? ቀጥለን ያቀረብነው ጥያቄም ነበር፡፡ “በአንድ በኩል ዋና ሥራ አስፈፃሚው በሥልጠና ምክንያት ባለመኖራቸው ሲሆን፤ በዋናነት ግን ቅሬታ አቅራቢዎቹ የፈፀሙት ከባድ የሥነምግባር ግድፈት እንዲማሩ ለማድረግ አስበን ነው እስከ 50 ቀናት የቆየው” ሲሉ የዘገየበትን ምክንያት አብራርተዋል።
የዲሲፒሊን ኮሚቴው
የወረዳው ዲሲፕሊን ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ጌቱ ወልደጊዮርጊስ፤ መጀመሪያ ከሳሾችን በደብዳቤ መረጃ እንደጠየቁ ነው የሚናገሩት፡፡ ይሁን እንጂ ከሳሽ የሆኑት ጽሕፈት ቤት መረጃ እንዲያቀርቡ በተጠየቁበት ቀን ሊያቀርቡ አልቻሉም፡፡ በዚህም ኮሚቴው ሠራተኞቹ እግዱ ተነስቶላቸው በውሰት ወደተመደቡበት ጽሕፈት ቤት ወደ ሥራ እንዲገቡ ውሳኔውን ያሳርፋል፡፡ ዋና ሥራ አስፈፃሚው ድጋሜ እንዲታይ እንደጠየቁ በማንሳት፤ ኮሚቴው በድጋሜ የማየት ሥልጣን ስላሌለው ጥያቄውን ሊቀበል እንዳልቻለም ያስረዳሉ፡፡
በጉዳዩ ላይ የወረዳው ዋና ሥራ አስፈፃሚ፣ የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚና ፐብሊክ ሰርቪስና ሠው ሀብት ልማት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና ሠው ሀብት ልማት ቢሮ የሠው ሀብት ሥራ አመራር ኢንስፔክሽን ዳይሬክተር የሰጡትን ምላሽ በጥቅምት 17 ቀን 2012 ዓ.ም ዕትማችን ይዘን እንደምንቀርብ እንገልፃለን፡፡
አዲስ ዘመን ጥቅምት 12/2012
ፍዮሪ ተወልደ