የኢትዮጵያ እግር ኳስ በአግባቡ በሰለጠኑ ዳኞች መመራት የጀመረው ከ1940 ዓ.ም ወዲህ መሆኑን የታሪክ ድርሳናት ይጠቁማሉ፡፡ በኢትዮጵያ ስፖርት አባት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ አስተርጓሚነት ለመጀመሪያ ጊዜ በጣሊያናዊ አሰልጣኝ የተሰጠው የዳኝነት ሙያ ዛሬ ላይ ፍሬ አፍርቶ ወንዝ ለመሻገር በቅቷል፡፡ ሕግን ጠንቅቆ በማወቅና በሚገባ በመተርጎምም የዓለም እግር ኳስን በበላይነት ከሚመራው ፊፋ በተደጋጋሚ ምስጋና ተችረዋል፡፡best sex toysbuy sex toys near mebest place to buy sex toysadult sex toysbest male sex toysbest couples sex toysbest couples sex toyscheapest adult sex toysbest sex toysonline sex toysmale sex toysbest homemade sex toys for menonline adult sex toysAdult Sex Toys for couplescouples sex toysbest mens sex toystop lesbian sex toysadam and eve adult sex toysdiy sex toys for menbest sex toy websitesex toys onlinesex toys for salesex toys vibratorsbest sex toys for menadam eve sex toyscouple sex toysbest male sex toysbest sex toy for couplestop couples sex toysbest sex toysex toys for beginnerssex toys for couplesbest sex toys for couplesmale sex toysbest sex toys for mencock ring sex toysilicone ass sex toyfemale sex toysbest sex toycheap adult sex toysbest sex toy store
እዚህ ግባ ከማይባል ደረጃ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ እግር ኳስም በዓለም አቀፍ ደረጃ በምርጥ ዳኞቿ እየተወከለ ይገኛል፡፡ ሚናቸውም በመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎችን ከመምራት አንስቶ ዓለም ዋንጫን እስከ መዳኘት የደረሰ ሊሆንም ችሏል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ምስክርነትና አድናቆትን ካተረፉ ኢትዮጵያዊያን ምርጥ ኢንተርናሽናል አርቢትሮች መካከልም ሊዲያ ታፈሰ ቅድሚያ ተጠቃሽ ናት፡፡
ወንዶች የቀደመ ተሳትፎ ባላቸው እግር ኳስ ኮሎኔል ከበደ ዱቤ የተሰኙት ዳኛ በ1948 ዓ.ም የአፍሪካ ዋንጫን በመምራት ቀዳሚ መሆናቸውን በ2005 ዓ.ም የታተመው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ጉዞ የሚለው መጽሐፍ ያትታል፡፡ በሴቶች በኩል ደግሞ በ5ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ረዳት ዳኛ ሳራ ሰይድ ለመጀመሪያ ጊዜ ሀገሯን ልትወክል በቅታለች፡፡ አሁን ላይ በርካታ ሴት አልቢትሮች ቢኖሩም የቆራጧን ዳኛ ሊዲያ ታፈሰን ያህል በስኬት የተንቆጠቆጠ ግን የለም፡፡ እግር ኳስን ውበት ለማላበስ እንዲሁም የጨዋታ ሚዛንን በማስጠበቅ የተመሰከረላት፣ ጠንካራዋ፣ ቆራጧ፣ በኢትዮጵያ ወንዶች ፕሪሚየር ሊግ ለመጀመሪያ ጊዜ በመሃል ዳኝነት የመራችው፣ በምስራቅ አፍሪካም የመጀመሪያዋ የፊፋ የመሀል ዳኛ፣… በእርግጥም ለብዙዎች ተምሳሌት መሆን ከቻሉ ኢትዮጵያዊያን መካከል ተጠቃሽ ናት፡፡
በጅማ ከተማ ተወልዳ ያደገችው ሊዲያ፤ እግር ኳስን ትሞክር እንጂ አብዛኛውን ልጅነቷን ያሳለፈችው ግን ቅርጫት ኳስ በመጫወት ነበር፡ ፡ በአንድ ወቅት በተፈጠረ አጋጣሚም የእግር ኳስ ዳኝነት ስልጠና ላይ መሳተፏ ልቧን በስፖርቱ እንዲሳብ አደረገው። ይህንን ተከትሎም ተጨማሪ ስልጠናዎችን በመውሰድ እና አቅሟን በማዳበር ቅርጫት ኳስን ትታ የእግር ኳስ ዳኝነት ፊሽካን ለማንሳት በቃች፡፡ ከ15 እና 17 ዓመት በታች ውድድሮችን በመምራት የጀመረችውን ዳኝነቱን በረዳትነት የወንዶች ጨዋታዎች ላይ በመሳተፍ ቀጥላለች፡፡ እአአ ከ1992 አንስቶም በመሃል ዳኝነት አስቸጋሪውን የኢትዮጵያ ወንዶች ሊግ ብቸኛዋ ሴት በመሆን ጀመረች፡፡
አስቸጋሪ ሁኔታዎችን አልፋ የራሷን አሻራ ማሳረፍ የቻለችበት ሊግ በጀመረችበት ወቅት፤ ከሌሎች ሴቶች በተለየ ለምን ይሄንን ማድረግ እንደፈለገች በብዙዎች ጥያቄ ይቀርብላት እንደነበር ከካፍ ኦላይን ጋር በነበራት ቆይታ ገልጻለች፡፡ ‹‹ስፖርተኛ ሆኜ በማለፌ እንዲሁም በልጅነቴ ከወንዶች ጋር መጫወቴ አስቸጋሪውን ሁኔታ እንዳልፈው አድርጎኛል። ከቤተሰቤ የማገኘው ማበረታቻ ደግሞ ይበልጥ አጠንክሮኛል›› ትላለች፡፡ ብቃቷ ኢትዮጵያን መሻገር የሚገባው በመሆኑም ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ አቡጃ ላይ ናይጄሪያን እና ላይቤሪያን በመምራት የመጀመሪያ ዓለም አቀፍ ዳኝነትን አሃዱ አለች፡፡ ይህንን ጨዋታ ምንጊዜም የማትረሳው ሊዲያ ‹‹ስታዲየሙ በኢትዮጵያ ከማውቀው የገዘፈ፣ አስደናቂ ደጋፊ የነበረበትና በትልቅ ደረጃ የመራሁት ጨዋታ ነበር›› ስትልም ትዝታዋን ለካፍ ኦንላይን አጋርታለች፡፡
ከዚያ በኋላ ሊዲያን የሚያቆማት አልተገኘም፤ በመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ቀጥላ የአፍሪካ ዋንጫን በተከታታይ ለአራት ጊዜያት (እአአ በ2012፣ 2014፣ 2016 እና 2018) ለመምራት ችላለች፡፡ እአአ በ2015 እና 2019 ደግሞ የሴቶች ዓለም ዋንጫን፣ በ2016 እና 2018 ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫን፣ በቻን አፍሪካ የወንዶች ዋንጫ፣ የአፍሪካ የሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ፣ በፈረንሳይ ሀገር የሚዘጋጅ የውስጥ ውድድርን ጨምሮ በርካታ ሌሎች ውድድሮችን በስኬት መምራት ችላለች፡፡ የሊዲያ ስኬቶች በእግር ኳስ ሜዳ ብቻ የሚያበቁ አይደሉም፤ ይልቁንም ከከባድ ጉዳት በቶሎ አገግሞ በመመለስ እንዲሁም ከወሊድ በኋላ በአንድ ዓመት ወደ ቀድሞ አቋሟና ዳኝነቷ በመመለስም ጭምር ሊገለጽ የሚችል ነው፡፡
በርካታ ድንቅ ታሪኮችን ማጻፍ የቻለችው አንደበተ ርቱእ እና ቆራጥ ዳኛዋ ሊዲያ ታፈሰ ሀገሯን ካስጠራችበት ሥራዋ መሰናበቷን ከሰሞኑ አስታውቃለች፡፡ ሁለት አስርት ዓመታትን ከዘለለው የዳኝነት ጉዞዋን ማቆሟንም በአዳማ ዩኒቨርሲቲ በነበረው የሸገር በመገኘት በይፋ በማሳወቅ ፊሽካዋን ሰቅላለች፡፡
ብርሃን ፈይሳ
አዲስ ዘመን ሰኔ 25/2015