“የክልሉ ህዝብ አሸባሪውን ህወሓት ለማጥፋት የሚጠበቅበትን ተጋድሎ ያደርጋል” -አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

 አዲስ አበባ፦ የክልሉ ህዝብ አሸባሪውን የህወሓት ቡድን ለማጥፋት ከመላው የሀገሪቱ ህዝብ ጎን ተሰልፎ የሚጠበቅበትን ተጋድሎ እንደሚያደርግ የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ አስታወቁ ። አቶ ሙስጠፌ ትናንት የመከላከያ ሠራዊትንና የሶማሌ ክልል... Read more »

“ጀፍሪ ፊልትማን ልዩ መልዕክተኛ ሆነው የተሾሙት በኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለውን ጫና ለማጠናከር ታስቦ ነው”- አቶ ደጀን የማነ በወሎ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር

አዲስ አበባ፡- ለሁለተኛ ጊዜ አዲስ አበባ የሚመጡት በአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጀፍሪ ፊልትማን በኢትዮጵያ ላይ የሚደረጉ ዓለም አቀፍ ጫናዎችን ለማጠናከር ታስቦ በልዩ ሁኔታ በባይደን የተሾሙ መሆ ናቸውን በወሎ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና... Read more »

“አሸባሪው ህወሓት እየሰራ ያለውን የኢኮኖሚ አሻጥር ህዝቡ ሊታገለው ይገባል”- ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር ተሾመ አዱኛ የኦሮሚያ ክልል ፕላኒንግ ኮሚሽን ኮሚሽነር

 አዲስ አበባ፡- አሸባሪው ህወሓት በሰላማዊ ትግል ያጣውን የፖለቲካ የበላይነት በኢኮኖሚ አሻጥር ለማግኘት የጀመረውን እንቅስቃሴ ህዝቡ ሊታገለው እንደሚገባ የኦሮሚያ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር ተሾመ አዱኛ አሳሰቡ ። የኢኮኖሚ ባለሙያው ዶክተር ተሾመ... Read more »

‹‹በክብር በመሞት ህዝብና ሀገርን በማስከበር ታሪክ እንሰራለን እንጂ ተዋርዶ የመሞት ስነልቦና የለንም›› – አቶ ግዛቸው ሙሉነህ የአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር

አዲስ አበባ፡- በክብር ሞተን ህዝብና ሀገርን በማስከበር ከፍ ያለ ታሪክ እንሰራለን እንጂ ተዋርዶ የመሞት ስነልቦና የለንም ሲሉ የአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ገለፁ፡፡የሽብር ቡድኑ በአማራ ህዝብና... Read more »

ዛምቢያ የሀገሪቷ ፕሬዚዳንት ለሦስተኛ ጊዜ የተወዳደሩበት ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አካሄደች

የዛምቢያ ዜጎች ፕሬዚዳንታቸው እና ተፎካካሪ ያቸው በደቡብ አፍሪካዊቷ ሀገር የተረጋጋ ዴሞክራሲን ለማስፈን ውጥረት በተሞላበት ሁኔታ 3ኛውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሀሙስ ዕለት አካሂዳለች። የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኤድጋር ሉንጉ ለ3ተኛ ጊዜ በፕሬዚዳንትነት ለመመረጥ በዕጩነት የቀረቡ ሲሆን፤... Read more »

‹‹ስግብግብ ነገዴዎች እየፈጸሙት ያለው ኢኮኖሚያዊ አሻጥር አሸባሪው ህወሓት አገር ለማፍረስ ከከፈተው ጦርነት ያልተናነሰ ነው›› – የአዲስ አበባ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፡- ስግብግብ ነገዴዎች እየፈጸሙት የሚገኘው ኢኮኖሚያዊ አሻጥር አሸባሪው ትህነግ አገር ለማፍረስ ከከፈተው ጦርነት ያልተናነሰ ድርጊት መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች አስታወቁ ፡፡የኢኮኖሚ አሻጥሩ የተጠና የኢኮኖሚ ጦርነት መሆኑን በመገንዘብ ህዝቡ እና መንግሥት... Read more »

ግብርናውን በማዘመን የውጭ ጣልቃ ገብነትን ማስቆም እንደሚገባ ተገለጸ

አዲስ አበባ፡- ግብርናን በማዘመን የውጭ ጣልቃ ገብነትን ማስቆም እንደሚገባ የአማራ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡አሜሪካ አሁን ለደረሰችበት ዓለም አቀፍ የበላይነት ለግብርናው ዘርፍ ትኩረት መስጠቷ ትርጉም ያለው አስተዋጽኦ እንዳለው አመለከቱ። የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና... Read more »

በዳኝነት ስርዓቱ ተጠያቂነትን ማስፈንና ሙስናን መከላከል የቀጣዩ ዓመት ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፡- በዳኝነት ስርዓቱ ተጠያቂነትን ማስፈንና ሙስናን መከላከል የተቋማቸው የቀጣዩ ዓመት ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ አስታወቁ። ፕሬዚዳንቷ ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ትናንት በጽህፈት ቤታቸው በሰጡት... Read more »

በኢትዮጵያ ላይ እየተደረጉ ያሉ የውጭና የውስጥ ጫናዎችን ለመቋቋም ከመንግሥት ጎን እንደሚቆሙ የዲያስፖራ ማህበራት አስታወቁ

አዲስ አበባ፡- በውጭና በውስጥ ኃይሎች በኢትዮጵያ ላይ እየተደረጉ ያሉ ጫናዎችን ለመቋቋም በሚደረገው ጥረት ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎች ከመንግሥት ጎን እንደሚቆሙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበራት ጥምረት እና የኦሮሚያ ዲያስፖራ ማህበር አስታወቁ፡፡ ማህበራቱ ትናንት በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ... Read more »

“የአሸባሪውን ህወሓት አገር የማፍረስ ሴራ ለማስቆም የትግራይ ህዝብ ትልቅ ኃላፊነት አለበት” – ኮማንደር ገ/ መስቀል ወ/ሚካኤል በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የደቡብ ምስራቅ ዞን የሀገረ ሰላም ከተማ ሚሊሻ ፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ

አዲስ አበባ፡- የአሸባሪውን ህወሓት አገር የማፍረስ ሴራ ለማስቆም እና የቡድኑን አባላት ለፍርድ ለማቅረብ የትግራይ ህዝብ ትልቅ ኃላፊነት እንዳለበት በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የደቡብ ምስራቅ ዞን የሀገረ ሰላም ከተማ ሚሊሻ ፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ ኮማንደር... Read more »