በዚህ ዘመን ከሥራም ሆነ ከተለያየ ጉዳይ ፋታ ሲገኝ ምን ተባለ? ለማለት ብዙዎች ከሰው ምላሽ አይጠብቁም። የእጅ ስልክ አንስቶ ማህበራዊ ድረ ገጾችን(ሶሻል ሚዲያ) ፈተሸ ፈተሸ ማድረግ በቂ ነው። ማህበራዊ የትስስር ገፆች ከእውነቱ ውሸቱ የበዛባቸው ነው ቢባል እንኳን ሳይፈልጉም ቢሆን መጎብኘት የተለመደ ነው። እርግጥ ነው ሰልችቷቸው እራሳቸውን ለመገደብ የሞከሩም አይጠፉም። ማን ምን አለ ብለው ለመታዘብ ብቻ ጎራ የሚሉም አሉ።
የዛሬው ትዝብቴ ግን ከነዚህም የተለየ ነው። ለመሳደብ ወደ ማህበራዊ ሚዲያው ስራዬ ብለው ጎራ የሚሉ ሰዎችን ይመለከታል። ስራዬ ብለው ለመሰዳደብና ለመበሻሸቅ ወደ ማህበራዊ ሚዲያው ብቅ የሚሉ ግለሰቦች እዚሁ አገር ውስጥ ቢኖሩም በርካቶቹ በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወይም ትውልደ ኢትዮጵያውያን ናቸው። እርግጥ ነው ማህበራዊ ሚዲያዎችና ተከታዮቻቸውን ተጠቅመው አገርና ወገንን የሚጠቅም ለስጋም ለነብስም እረፍት የሚሰጥ አስደማሚ የረድኤት ተግባራትን የሚሰሩ ብዙዎች አሉ። ከእነሱ በተቃራኒ ስራዬ ብለው ለስድብ የተሰማሩ ግለሰቦች ቁጥር ግን ቀላል አይደለም።
በነዚህ ግለሰቦች ዘንድ የፖለቲካ፣ ብሔር ምናምን ጉዳዮች የመሰዳደቢያ አጀንዳዎች መሆናቸው የተለመደ ነው። አስገራሚው ነገር ከዚህ በተለየ ግለሰብ፣ ቤተሰብ፣ አሳድጋና አስተምራ አሁን ለሚገኙበት ደረጃ ያበቃች አገር ጭምር የመሰዳደቢያና መበሻሸቂያ አጀንዳ መሆኗ ነው። ይህ ደግሞ እኛ ጋር እንጂ በሌላው ዓለም ስለመኖሩ እንጃ። እውነት ለመናገር እንደዚህ አይነት ግለሰቦች በስደት አገር ጥለው፣ ባህር ተሻግረው በባዕድ አገር የሚኖሩበትን ምክንያት ስተዋል። በርካታ ኢትዮጵያውያን በፖለቲካ ምክንያት መሰደዳቸው ባይካድም እጅግ ብዙ የሆኑት በኢኮኖሚ ችግር ሌት ተቀን ለፍተው የራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ሕይወት ለመለወጥ ነው። በማህበራዊ ሚዲያው ለስድብ የሚቀድሙትም እኚሁ መሆናቸው ነው አስገራሚው።
ከተማ መኖርና የከተማ ሰው መሆን ይለያያል። የሰለጠነ ዓለም መኖርና ስልጡን መሆንም እንደዛው። በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የማህበራዊ ሚዲያ ብሽሽቅ የምንታዘበው ነገር ግራ ያጋባል። በየትኛውም ጉዳይ ላይ መሰዳደብ ሃሳብን በነፃነት መግለፅ ተደርጎ እስከመቆጠር፣ እርስበርስ ከፍ ዝቅ ተደራርጎ መዘላለፍ እስከ ድብድብ እስካልደረሰ መብትና የስልጣኔ መገለጫ እየተደረገ ተለምዷል። ከአገር ርቄያለሁ ብሎ እትብቱ የተቀበረበትን አገርም ይሁን ግለሰብ ከጥላቻም የዘለለ የፈለጉትን መናገር ነፃነትን እንደማጣጣም ተደርጓል።
ነፃ ንግግር ማለት የጥላቻ ንግግር ማለት እንዳልሆነ በሰለጠነ ዓለም እየኖሩ መዘንጋቱ ይበልጥ አስገራሚ ነው። ነፃነት ሌሎችን መስደቢያ ወይም ማሸማቀቂያ ፍቃድ አይደለም። ነፃነት ከባድ ኃላፊነት ነው። ነፃነት ስድነት አይደለም። ነፃነት ገደብ የሌለው እንዝላልነትም አይደለም። ነፃነት ገደቡም ሆነ ኃላፊነቱ ሕሊናዊ ነው። ነፃነትን በአግባቡ ለመጠቀም እውቀት ይፈልጋል፤ ስነምግባር ግድ ይላል።
በነፃነት ስም ሌሎችን የሚያጥላላና ማንነታቸው ላይ የስድብ ናዳ ማውረድ የነፃነትን እውነተኛ ትርጉም መሳት ነው። ዘመኑ የዕውቀት ነውና የሃሳብ ልዩነትን በሃሳብ ፍልሚያ ብቻ መታገል የስልጣኔ ምልክት ነው። እኔ ብቻ ነኝ ልክ፣ እኔ ብቻ አንደኛ፣ እኔ ብቻ ልጠቀም፣ ሌላው የራሱ ጉዳይ የሚል ራስወዳድ አስተሳሰብ ያልበሰለ ሃሳብ ነው። ብዝሀ ሃሳብን ማክበርና የሌሎችን ማንነት መቀበል የዘመናዊነት ምልክት ነው። አውሮፓውያን ከጨለማው ዘመን ወደ ሕዳሴው ዘመን የተሸጋገሩት ለብዝሀ ሃሳብ እውቅና በመስጠት ነው። ከጥላቻ ምንም እንደማይገኝ በመረዳታቸው ነው አሁን ለደረሱበት ሥልጣኔ ብዝሀ ሃሳብን በነፃነት የሚያንሸራሽሩት። በሃሳብ ተከራክረው፣ ተጨቃጭቀውና ተፋልመው ተቃቅፈውና ተጨባብጠው የሚለያዩት ሰውየው ላይ ሳይሆን ሃሳቡ ላይ በማተኮራቸው ነው።
ፍቅር የጥላቻ መድኃኒት ነች። ሌላውን የሚጠላ ራሱን አይወድም። ራሱን የሚጠላ እንዴት ሌላውን ሊወድ ይችላል? ፍቅር በማድረጉ፣ ለሌሎች ቅን በማሰቡ፣ ደግ ሥራ በመስራቱ የሚደሰት እንጂ የሚፀፀት ማንም የለም። ሌሎችን እንደራስ ማየት የሚያረካ እንጂ አያስቆጭም። ሰው ጥሪው ለፍቅር እንጂ ለጥላቻ አይደለም። የጥላቻ ንግግር ጠላትን ያበዛል፣ ሰላምን ይነሳል እንጂ ወዳጅን አያተርፍም፤ ፍቅርንም አያመጣም።
ሌሊሳ ግርማ መጋቢት 2011 ዓ.ም. በታተመው በፍትህ ቁ.21 መፅሔት ላይ ስለነፃነት ሲናገር እንዲህ ይለናል፡-
‹‹ነፃነት ነፃ አይደለም። የዕውቀትን ዋጋ ያስከፍላል። ዕውቀት መዳረሻ አይደለም። ዕድሜ ልክ የሚደረግ ጉዞ ነው። ሰው የመሆን ጉዞ!››
አዎ! ነፃነት እውቀት ይፈልጋል። አለበለዚያ ነፃነት ራሱ ነፃ አይሆንም። ነፃነት መዳረሻው ሰው መሆን ነው። ሰው መሆን ደግሞ ከዘረኝነት፣ ከጥላቻ ንግግር አስወጥቶ ከሰብዓዊነት የሚያገናኝ መሠረት ነው። ሰው ‹‹እውነተኛ ሰው›› ከሆነ ሌላውን እንደራሱ ያያል እንጂ በጥላቻ ንግግር ሰውነቱን አያበላሽም። ሰው ክቡር ሆኖ ሳለ እንስሶችን መምሰል የለበትም። ወዳጆች ሃሳብ ላይ እንጂ ማንነት ላይ አናተኩር! ነፃነትን ለበጎ ነገር እናውለው። የጥላቻ ንግግር ለሰዳቢውም ለተሰዳቢውም አይጠቅምም። ቴክኖሎጂውን ለበጎ ነገር ከተጠቀምንበት ሃሳብን የሚያሳድግ፣ ሕሊናን የሚያበስል፣ ወደፊት የሚያራምድ መልካም ትምህርት ልናገኝበት እንችላለንና።
ከተማ መኖርና የከተማ ሰው መሆን ይለያያል። የሰለጠነ ዓለም መኖርና ስልጡን መሆንም እንደዛው። በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የማህበራዊ ሚዲያ ብሽሽቅ የምንታዘበው ነገር ግራ ያጋባል። በየትኛውም ጉዳይ ላይ መሰዳደብ ሃሳብን በነፃነት መግለፅ ተደርጎ እስከመቆጠር፣ እርስበርስ ከፍ ዝቅ ተደራርጎ መዘላለፍ እስከ ድብድብ እስካልደረሰ መብትና የስልጣኔ መገለጫ እየተደረገ ተለምዷል። ከአገር ርቄያለሁ ብሎ እትብቱ የተቀበረበትን አገርም ይሁን ግለሰብ ከጥላቻም የዘለለ የፈለጉትን መናገር ነፃነትን እንደማጣጣም ተደርጓል።
ነፃ ንግግር ማለት የጥላቻ ንግግር ማለት እንዳልሆነ በሰለጠነ ዓለም እየኖሩ መዘንጋቱ ይበልጥ አስገራሚ ነው። ነፃነት ሌሎችን መስደቢያ ወይም ማሸማቀቂያ ፍቃድ አይደለም። ነፃነት ከባድ ኃላፊነት ነው። ነፃነት ስድነት አይደለም። ነፃነት ገደብ የሌለው እንዝላልነትም አይደለም። ነፃነት ገደቡም ሆነ ኃላፊነቱ ሕሊናዊ ነው። ነፃነትን በአግባቡ ለመጠቀም እውቀት ይፈልጋል፤ ስነምግባር ግድ ይላል።
በነፃነት ስም ሌሎችን የሚያጥላላና ማንነታቸው ላይ የስድብ ናዳ ማውረድ የነፃነትን እውነተኛ ትርጉም መሳት ነው። ዘመኑ የዕውቀት ነውና የሃሳብ ልዩነትን በሃሳብ ፍልሚያ ብቻ መታገል የስልጣኔ ምልክት ነው። እኔ ብቻ ነኝ ልክ፣ እኔ ብቻ አንደኛ፣ እኔ ብቻ ልጠቀም፣ ሌላው የራሱ ጉዳይ የሚል ራስወዳድ አስተሳሰብ ያልበሰለ ሃሳብ ነው። ብዝሀ ሃሳብን ማክበርና የሌሎችን ማንነት መቀበል የዘመናዊነት ምልክት ነው። አውሮፓውያን ከጨለማው ዘመን ወደ ሕዳሴው ዘመን የተሸጋገሩት ለብዝሀ ሃሳብ እውቅና በመስጠት ነው። ከጥላቻ ምንም እንደማይገኝ በመረዳታቸው ነው አሁን ለደረሱበት ሥልጣኔ ብዝሀ ሃሳብን በነፃነት የሚያንሸራሽሩት። በሃሳብ ተከራክረው፣ ተጨቃጭቀውና ተፋልመው ተቃቅፈውና ተጨባብጠው የሚለያዩት ሰውየው ላይ ሳይሆን ሃሳቡ ላይ በማተኮራቸው ነው።
ፍቅር የጥላቻ መድኃኒት ነች። ሌላውን የሚጠላ ራሱን አይወድም። ራሱን የሚጠላ እንዴት ሌላውን ሊወድ ይችላል? ፍቅር በማድረጉ፣ ለሌሎች ቅን በማሰቡ፣ ደግ ሥራ በመስራቱ የሚደሰት እንጂ የሚፀፀት ማንም የለም። ሌሎችን እንደራስ ማየት የሚያረካ እንጂ አያስቆጭም። ሰው ጥሪው ለፍቅር እንጂ ለጥላቻ አይደለም። የጥላቻ ንግግር ጠላትን ያበዛል፣ ሰላምን ይነሳል እንጂ ወዳጅን አያተርፍም፤ ፍቅርንም አያመጣም።
ሌሊሳ ግርማ መጋቢት 2011 ዓ.ም. በታተመው በፍትህ ቁ.21 መፅሔት ላይ ስለነፃነት ሲናገር እንዲህ ይለናል፡-
‹‹ነፃነት ነፃ አይደለም። የዕውቀትን ዋጋ ያስከፍላል። ዕውቀት መዳረሻ አይደለም። ዕድሜ ልክ የሚደረግ ጉዞ ነው። ሰው የመሆን ጉዞ!›› አዎ! ነፃነት እውቀት ይፈልጋል። አለበለዚያ ነፃነት ራሱ ነፃ አይሆንም። ነፃነት መዳረሻው ሰው መሆን ነው። ሰው መሆን ደግሞ ከዘረኝነት፣ ከጥላቻ ንግግር አስወጥቶ ከሰብዓዊነት የሚያገናኝ መሠረት ነው። ሰው ‹‹እውነተኛ ሰው›› ከሆነ ሌላውን እንደራሱ ያያል እንጂ በጥላቻ ንግግር ሰውነቱን አያበላሽም። ሰው ክቡር ሆኖ ሳለ እንስሶችን መምሰል የለበትም።
ወዳጆች ሃሳብ ላይ እንጂ ማንነት ላይ አናተኩር! ነፃነትን ለበጎ ነገር እናውለው። የጥላቻ ንግግር ለሰዳቢውም ለተሰዳቢውም አይጠቅምም። ቴክኖሎጂውን ለበጎ ነገር ከተጠቀምንበት ሃሳብን የሚያሳድግ፣ ሕሊናን የሚያበስል፣ ወደፊት የሚያራምድ መልካም ትምህርት ልናገኝበት እንችላለንና።
ለምለም መንግሥቱ
አዲስ ዘመን ሰኞ መጋቢት 18 ቀን 2015 ዓ.ም