በብርሃን የፈካ የኢትዮጵያ ጊዜ ላይ ነን። ብዙ ነገ ሮችን አሸንፈን፣ ብዙ ችግሮችን አልፈን ሊነጋ በከጃጀ ለው ሰማይ ስር ነን። ትላንትና ከነጉድፉ በእያንዳንዳችን ልብ ውስጥ አለ። ያለፉት ጊዜያቶች ለእኛ ለኢትዮጵያው ያን አዳፋ ነበሩ። ሁሉን አልፈን፣ ሁሉን ተሻግረን እነሆ የኢትዮጵያ ጊዜ ላይ ደርሰናል። ዛሬ እንደትላንት አይ ደለም፣ አይሆንምም። ለውጥ በናፈቁ፣ ሰላም በተራቡ ነፍሶች አዲስ ማለዳን አይተናል።
ኢትዮጵያዊነት በሚያስጨንቃቸው አሸናፊ ልቦች አሸንፈናል። የኢትዮጵያ የመነሳት ጊዜ ላይ ነን። ትላን ትን በነበር የምናስታውስበት፣ ችግሮቻችንን ጥለን ወደ ላቀ ሀገራዊ ማንነት የምንሸጋገርበት ትክክለኛ ጊዜ ላይ እንገኛለን። በሰላም ድምጽ የትላንት የታላቅነት ገድላች ንን መልሰን ዳግም ታሪክ የምንሠራበት ጫፍ ላይ ነን። እንደተመኘነው ሆኗል..ኢትዮጵያ በልጆቿ አሸንፋለች። ኢትዮጵያ በሰላም አሸንፋለች፡፡
ከዚህ በኋላ ያለው የከፍታ ዘመን ነው። ስለ ኢትዮ ጵያ የሚያወጉ ድምጾች በዓለም ዙሪያ እየተሰሙ ነው። የአፍሪካ ኅብረትን ጨምሮ የተባበሩት መንግሥታትና የአውሮፓ ኅብረት ስለ ኢትዮጵያ ሰላማዊ ምክክር ደስታ ቸውን ገልጸዋል። አሁን ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት እየ ሄደባቸው ያለውን ሀገራዊ ስትራቴጂ የሚያደንቁና የሚ ያበረታቱ ሀገራት በዝተዋል።
የኢትዮጵያን ጥቅምና ሉዓላዊነት በማይነካ መልኩ የተራመድንባቸው የሰላምና የድርድር ሂደቶች ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ አድርገዋል። የኢትዮጵያ ማሸነፍ የመላው ሕዝብ ማሸነፍ ነው። ስለሀገራችን ክብርና ሉዓላዊነት በአንድ ባንቆም ኖሮ በነዛ ሁሉ ጣልቃ ገብ ሀገራት ተከበን ቀና አንልም ነበር።
የአፍሪካ ጉዳይ በአፍሪካውያን እንዲፈታ ያደረ ግነው ጥረት ፍሬ አፍርቶ እነሆ ሀገራችን ወደምትናፍ ቀው ሰላሟ ተመልሳለች። መንግሥት ከሕዝብ ጋር አብሮ በሁሉም መስኮች እየወሰዳቸው ያለው አመርቂ ውጤቶች ስለሀገራችን ምን ያክል እንደምንቆረቆር የሚ ያሳይ ሆኖ አልፏል፡፡
ይሄ የማሸነፍ ስነልቦና ሀገራችን ለያዘችው የለው ጥና የብልጽግና ጉዞዋ ወሳኝ ነው፤ በበረታ መንፈስ ልን ቀጥለው ይገባል። ወደፊት ተባብረን የምናሸንፋቸው የድ ህነትና የኋላቀርነት ነውሮች አሉብን። ከሰላም ውጪ በምንም የማይረቱ በርካታ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ እን ዲሁም ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶች አሉብን። መፍትሔአ ቸው ሰላምና መነጋገር፣ አንድነትና ወንድማማችነት የሆኑ ብዙ ሀገራዊ አጀንዳዎች አሉን።
ከሰላምና ከእርቅ ውጪ ሊታደጋቸው የማይችል እልፍ ነቀርሳዎች በዙሪያችን አሉ። እናም በአንድነት ያመ ጣነው የአሁኑ የሰላም ጸሐይ ለነገይቱም ኢትዮጵያ እን ዲበቃ በችግሮቻችን ላይ መነጋገርን እናስቀድም። እርቅና ሀገራዊ ተግባቦትን እናስቀድም። ያለፍናቸው ሁለት ዓመታት ሰላም አጥተን በብዙ ነገር ላይ የባከነባቸው ናቸው። ካለፈው ተምረን መጪውን ጊዜ መልካም ለማድረግ በሰላም ማሸነፍን፣ በአንድነት ማሸነፍን መለ ማመድ አለብን፡፡
ኢትዮጵያን ነጻ ላወጡ..ባሉበት ቦታ ሁሉ ስለሀገራ ቸው ለጮሁ ለነዛ ነፍሶች ክብር ይግባቸው። ለጠላቶቿ ንክሻ ላልተዋት የቁርጥ ቀን ልጆቿ ምስጋና ይገባል። ባዕድ ሆነው ወዳጅ ለሆኑንም እንደ ቻይናና ሩሲያ ላሉ ሀገራትም ክብር አለን። መቼም የማንረሳቸው የኢትዮ ጵያ የመከራ ወዳጆች ናቸው። ኢትዮጵያ በምታደርጋ ቸው ማናቸውም ሀገራዊና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ከፊት በመሆን ሲተባበሩን ያሉ ሀገራት ናቸው። ኢትዮ ጵያ ሀገራችን ውለታ አትረሳም።
ለነዚህ ሀገራት ያላትን ክብርና ምስጋና በተለያየ ጊዜ ገልጻለች.. አሁንም ልታመሰግናቸው ትፈልጋለች። በህዳሴ ግድባችንም ሆነ መንግሥት በትግራይ ክልል እየወሰደ በነበረው የሕግ ማስከበር ሥራ ላይ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሚደርሱብንን ጫናና ጣልቃ ገብነት ሲኮንኑና ሲከላከሉልን ነበር። ያኔ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ሙሉ በሙሉ ማክበር እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተው ሲከራከሩልን ነበር፡፡
ትንሳኤያችን ከዚህ በኋላ ነው። የኢትዮጵያ ጊዜ ላይ ነን። የኢትዮጵያ ጊዜ ላይ እንደመሆናችን ብዙ የምንሰማቸው የክብርና የከፍታ ድምጾች ይኖራሉ። የሰላምን ጣዕም አውቀንዋል። ሰላም ርቆን በሰነበትን ባቸው ዓመታት ውስጥ የሰላምን ዋጋ ተረድተናል ። አሁንም ከሰላም ውጪ ምንም ክብርና ከፍታ እንደሌ ለን በማመን በአንድ ሀገር ላይ አንድ ሆነን መኖር የመ ጨረሻ ምርጫችን ይሆናል።
እስከዛሬም የራሳችን ጠላቶች ራሳችን ነበርን። አሻጋሪ በሌለበት የሰላም ድልድያችንን ሰብረን ለመሻ ገር ስንዳክር ኖረናል። ጥቅም በሌለበት ስንሞትና ስን ገዳደል ኖረናል። ጨለማ ውስጥ ሆነው ብርሃን ስንጠ ብቅ ብዙ ጊዜ አልፎናል። አሁን ይበቃናል..እኛም ሆንን ሀገራችን ብርሃን የምታይበት ጊዜ ነው። ባጣነው ሰላም ልክ፣ ባጣንው ወንድማማችነት ልክ ሁሉንም የምናገኝ በት ጊዜ ነው። መጪው ጊዜ በብርሀን ውስጥ የምንመ ላለስበት የክብር ጊዜ ይሁንልን፡፡
ለሀገራችን ሙሴን እንሁን። ለመከራዋ ተጨማሪ መከራ ሳይሆን ችግሯን የምትሻገርበትን መላ እንፍጠር። ሙሴ አንድ ሆኖ ብዙዎችን ከባ ርነትና ከግዞት ያወጣ ሰው ነው። ሰላም ወዳድ የፍቅር ሰው ከሆንን ሙሴን መሆን አይቸግረንም። ሙሴነት በሰላም የሚመጣ ነው። ሙሴነት ፍቅርን ከማወቅ የሚጀምር ነው። ሙሴነት በአንድነትና በመተባበር የሚገኝ ነው፡፡
እያንዳንዳችን ሰላም ወዳድ በሆነ ልብና ፍቅርን በሚያመልክ ማንነት ሙሴን መሆን እንችላ ለን። ለከእንግዲኋ ኢትዮጵያ እንደ ሙሴ ያለ ሀገር ወዳድና ሰላም ናፋቂ ነፍስ ነው የሚያሻት። ለብዙ ጊዜ ሰላም አጥታ ፍቅር ርቋት ኖራለች አሁን ግን ሙሴን የምንሆንበትና ሀገራችንን ከኋላቀርነት የም ናላቅቅበት ጊዜ ነው። ትላንት በብዙ ምስቅልቅል ውስጥ ነበርን። ሙሴን የመሰለ..እንደ ሙሴ የሆነ ባህር አሻጋሪ አጥተን ተስፋ እየናፈቅን፣ ከባህሩ ወዲህ ማዶ ቆመን ከባህሩ ወዲያ ማዶ ያለውን ከንዓንን ስንናፍቅ ነበር። ዛሬ ወደናፈቅነው ከነዓን መጥተናል። ዛሬ ወደናፈቅንው ሰላምና እርቅ ተሸጋ ግረናል። መጪው ጊዜ እንደዚህ ሆኖ እንዲቀጥል ሙሴነታችንን እንዳናጣ መትጋት አለብን፡
የኢትዮጵያ ጊዜ ላይ ነን። በፈካና ተስፋ በተሞላ እውነት ውስጥ። የምንናፍቀውን አግኝ ተናል። ግን ገና ነን..ብዙ የምንናፍቃቸው ነገሮች አሉ። ደስ የሚለውና የሚያኮራው ደግሞ እነዛ የም ንናፍቃቸው ብዙ ነገሮች በሰላም ውስጥ መገኘታ ቸው ነው። ዋናውን ከያዝን አያሳስብም..ዋናው ነገር ሰላም ነው። ሰላም ባለበት ቦታ ሁሉም ነገር አለ። የምንናፍቃቸው ነገሮች የእኛ እንዲሆኑ ሰላማ ችን መቀጠል አለበት።
መጪውን ጊዜ በሰላምና በሀገራዊ ተግባቦት ውስጥ ማለፍ ግድ ይለናል። ብዙ ተስፋ የሰነቅን ሕዝቦች ነን። እንዲሆንልን የምንፈልገው ብዙ ነገር አለ። እንደ ሀገር እንደ ዜጋ የሚያምረን ብዙ ነገር ነው። እኚህ ሁሉ መንግሥታዊና ሕዝባዊ ተስፋዎ ቻችን እውን እንዲሆኑ ይቅር ባይ ልብ ያስፈልገ ናል። ችግሮቻችንን በሰላማዊ መንገድ መፍታትን ባህል ማድረግ ይጠበቅብናል። የሀሳብ ልዩነት፣ የፖለቲካ ልዩነት ሲፈጠር ጦር መማዘዝ ሳይሆን በአንድ ሀገር ላይ ስለ አንድ ሀገር እያሰብን እንደሆነ በመረዳት ልዩነቶቻችንን በምክክር ማጥበብን እንል መድ። በትናንት ስህተቶቻችንም እንማር ።
ባጣንው ልክ የምናገኝበት፣ በወደቅንው ልክ ቀና የምንልበት፣ በከሰርነው ልክ የምናተርፍበት ቀናት ከፊታችን አሉ ። ትላንት ብዙ ዋጋ አስከፍ ሎናል ..በብዙ ነገር ልባችንን ተሰብሯል። አንድና አንድ የሚያስፈልገን ሰላም እንደሆነ ከሁሉም በላይ አስተምሮናል። አሁን ከትናንት ተምረን ስለ ሰላም ተጠንቅቀን የምንኖርበት ጊዜ ነው። አሁን በተረዳንው ሐቅ ውስጥ የምንቆምበት ጊዜ ነው፡፡
ሰላም ያጣንባቸውን እነዛን የመከራ ጊዜያቶች እያሰብን ሰላማችንን ላለማጣት ተጠንቅቀን የምንኖ ርበት ጊዜ ላይ ነን። ሰላም አንድ ጊዜ ከእጅ ከወጣ ዋጋ ሳያስከፍል አይመለስም። ያለፉት ሁለት ዓመታት ሰላማችን ከእጃችን ወጥቶ ምን ያክል ዋጋ እንዳስከፈለን እኛው ምስክር ነን። እንደ ሀገር ብዙ የልዩነት ሀሳቦች ሊኖሩብን ይችላሉ።
እንደ ሀገር ብዙ ፈተናዎችን እያስተናገድን ሊሆን ይችላል ሰላም ካለንና ለሰላም ቅድሚያ ከሰጠን ችግሮቻችን አይበልጡንም። አሁን ላይ ችግር የሆነብን በችግሮቻችን መበለጣችን ነው። ሁሉም ችግሮቻችን ሰላም የሚያሳጡን፣ የሚያገፋ ፉን መሆናቸው ነው። ካለፈው ተምረን ችግሮቻች ንን ለሰላም ማጣት ሳይሆን ሰላማችንን ለችግሮቻ ችን እንጠቀም፡፡
ለሀገር ሰላም መንግሥት እንደ መንግሥት የሚ ሠራው አለ። እያንዳንዱ ዜጋም እንደ ዜጋ የሚያ ደርገው የማይተካ አስተዋጽዖ አለ። ሁላችንም ባለን እውቀትና በተሰጠን መክሊት በመጠቀም ለሀገራችን ምርጡን በማድረግ የመንጋቷን ዘመኗን ማፍጠን እንችላለን።
ሰላም የአንድ ወገን ብቻ የቤት ሥራ አይደ ለም። ሰላም ከመንግሥት ብቻ የሚጠበቅም አይ ደለም ። ከዚህ ይልቅ ከአጠቃላይ ሕዝባችን ማኅ በረሰባዊ ስብዕና የሚጠበቅና በዚሁ ላይ የሚመሠ ረት ነው ። እንደ ሀገር የሰላማችን ፈጣሪዎችና ጠባ ቂዎች እኛ ነን። ምሽት ላይ ቆመው በሌሎች የተፈ ጠረን ንጋት መጠበቅ አደራ በልነት ነው። እውቀታ ቸውን ሸሽገው በሌሎች ጥበብ የተፈጠረን ብርሃን ማንጸባረቅ ነውር ነው። ለሀገራችን መንጋት ሁላች ንም አስተዋጽዖ ማድረግ ከቻልን የጋራችንን የማይ መሽ ቀን መፍጠር እንችላለን፡፡
ያለነው በለውጥ ወቅት ነው ፣የፈተናዎች ብዛት የወቅቱን ባህሪ አይለውጡትም ። ለዚህ ቀድሞ ችግሮችን በንግግር ለመፍታት የሚደረጉ ጥረቶ ችና የሚገኙ ተስፋ ሰጭ ውጤቶች ለውጡን የማ ስቀጠል ወሳኝ አቅም ናቸው። ሀገር በጥቂት ሰዎች ኃይልና ብርታት አትለወጥም። ለውጥ የብዙኃኑን ፍቃድ ይፈልጋል። በአንድ ወገን ፍቃድ ብቻ ንጋት የለም።
በጀመርንው የሰላም መንገድ ከተጓዝን ንጋታ ችን ሩቅ አይሆንም። ገና ከፍ እንላለን። ገና ከዚህም በላይ ዓለም ያውቀናል። ገና በጠላቶቸችን ላይ ከፍ ብለን የምንታይበት ጊዜ ይመጣል። ከፊታችን ሰላምን የለበሱ በርካታ የመንጋት ዘመኖች አሉ። የህዳሴ ግድባችን ኃይል ማመንጨት ጀምሯል። ከድህነትና ከኋላ ቀርነት ሊያወጡን የሚችሉ ትልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ነው።
በዛ ላይ እርቅ ወርዷል..ወደ ሰላማችን ተመል ሰናል። እነዚህ ሁሉ የከፍታችን ማሳያዎች ናቸው። ያለምንም ጥርጥር በኢትዮጵያ ጊዜ ላይ ነን። ዳግም ጥፋት እንዳይመጣ መትጋት ይኖርብናል። ለሀገራ ችንም ሆነ ለሚመጣው ትውልድ አዲስ ነገር ለመ ሥራት አሁን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ምቹ ሁኔታ ላይ እንገኛለን።
እጆቻችንን ለሥራ፣ አዕምሯችንን ለበጎ ሀሳብ በማሰልጠን ብሩህ ነጋችንን መገንባት እንጂ ጊዜ ባለፈበት ለየትኛውም ወገን በማይጠቅም ጦርነ ትና ንትርክ ጊዜን ማባከን ለዚህ ዘመን የማይመ ጥን ተግባር ነው፡፡
እውቀታችንን እና መክሊታችንን በመጠቀም የተጀመረውን የሰላም ጥረት ውጤታማ ለማድ ረግ የያንዳንዱ ዜጋ ኃላፊነት ከፍ ያለ ነው ፣ይህን ኃላፊነት መወጣት የተጀመረውን ለውጥ በማስቀ ጠል ሀገራዊ ብልጽግናን እውን ለማድረግ አቅም የመሆን ያህል ነው ።ለመጪው ትውልድ የጠሸለች ሀገር ለማስረከብ የሚያስችል የመሠረት ድንጋይ የማኖር ጭምር ነው ።
እኔ የሚጠበቅብኝን ሁሉ እንደ አንድ ዜጋ ለማበርከት በዝግጅት ላይ ነኝ። እናተም የሚጠ በቅባችሁን በማድረግ ለራሳችሁም ሆነ በእናንተ በኩል ለሚመጣው ትውልዳችሁ መልካም ቤትን መሥራት ይጠበቅባችኋል ። ይሄ ሲሆን ብቻ ነው ሰላም የሚመጣውና የመጣውን ሰላም ማስቀጠል የምንችለው፡፡
ጥሩዋና መልካሟ ኢትዮጵያ ያለችው በጥሩ ውና በመልካሙ እኔና እናንተ ውስጥ ነው። ዘመ ናዊቷና ስልጡኗ ኢትዮጵያ ያለችው ሰላም ወዳድ በሆነ ሕዝቦቿ ጉያ ውስጥ ነው። ከትላንት እስከ ዛሬ ለሀገራችን እንዲህ መሆን ተጠያቂው እኛው ነን። ልቡን ከፍቅር፣ እጆቹን ከልማት፣ አዕምሮ ውን ከሰላም አሽሽቶ ታላቅ ሀገር የመሰረተ ሕዝብ የለም ።
ሁላችንም እንደ ዜጋ የሚጠበቅብንን መወጣት በሚያስችል ሁለንተናዊ ቁመና ላይ ከተገኘን አይ ደለም ለራሳችን ለሌላውም የሚተርፍ አቅምና ሞራል ያለን ሕዝቦች ነን። ወደጀመርነው ፤ወደ ቀደመው የተስፋ ዝማሪያችን የምንመለሰውና መጭውን ትውልድ የተሻለ ሀገር ተረካቢ ልናደ ርገው የምንችለው በይቅርታ መንፈስ ለተደረሰ በት የሰላም ስምምነት አቅም መሆን ስንችል ነው። ለዚህ ደግሞ መንፈሳዊና ማኅበራዊ እሴቶችችን ትላልቅ ጉልበቶቻችን ናቸው ። ሰላም እንሁን፣ ሰላም እናድርግ፡፡
በትረ ሙሴ (መልከ ኢትዮጵ)
አዲስ ዘመን ጥቅምት 29/ 2015 ዓ.ም