የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በኦሪጎን የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ተሳታፊ የሚሆነውን የመጨረሻውንና ጠንካራውን ብሔራዊ ቡድኑን አሳውቋል። ቡድኑ ከዚህ ቀደም ከነበረው መጠነኛ ልዩነት የታየበትም ነው።
ከጥቂት ቀናት በኋላ በአሜሪካዋ ኦሪጎን የሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ተሳታፊ የሚሆኑ አገራት ዝግጅታቸውን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ። በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በተካሄደው የሰዓት ማሟያ መሠረትም በዕጩነት የተያዙ አትሌቶች ልምምዳቸውን ሲያደርጉ ቆይቷል። አሁን ደግሞ የመጨረሻዎቹንና በቻምፒዮናው ላይ አገርን የሚወክሉ አትሌቶችን ማንነት ፌዴሬሽኑ ይፋ አድርጓል። ቡድኑ በሁለቱም ጾታ ከ800 ሜትር እስከ ማራቶን ድረስ ከነተጠባባቂዎቻቸው 47 አትሌቶችን በመያዝ ወደ አሜሪካ የሚያቀና ይሆናል።
ፌዴሬሽኑ ከዚህ ቀደም ካሳወቃቸው የቡድኑ አባላት የሚሳተፉባቸው ርቀቶች ላይ ወቅታዊ አቋማቸውን ተከትሎ መጠነኛ ማስተካከያዎችን ማድረጉም ታውቋል። በዚህም መሠረት በሴቶች 1ሺ500 ሜትር ሴቶች የዶሃው ዓለም ቻምፒዮና የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤቷ ጉዳፍ ጸጋይ የሚመራ ይሆናል። አትሌቷ በ5ሺ ሜትርም በተጠባባቂነት ተይዛለች። ሌላኛዋ ጠንካራ አትሌትና በዶሃው የዓለም ቻምፒዮና እንዲሁም በቶኪዮ ማራቶን 10ሺ ሜትር የብር እና ነሐስ ሜዳሊያ ባለቤቷ ለተሰንበት ግደይም በ5ሺ እና 10ሺ ሜትር ርቀቶች እንደምትሮጥ ተረጋግጧል።
በተመሳሳይ በወንዶች በኩል ወጣቶቹ አትሌቶች ሰለሞን ባረጋ እና በሪሁ አረጋዊ በ5ሺ እና 10ሺ ሜትር አገራቸውን እንደሚወክሉ ታውቋል። የቶኪዮ ኦሊምፒክ የ10ሺ ሜትሩ ቻምፒዮን እንዲሁም የዶሃው የዓለም ቻምፒዮና 5ሺ ሜትር ባለብር ሜዳሊያው ሰለሞን አሁን ካለበት ወቅታዊ አቋም አንጻር በሁለቱም ርቀቶች የሜዳሊያ ባለቤት የሚሆንበት ዕድል የሰፋ እንደሚሆን ይጠበቃል። በቡድን ሥራ እና ለአገሩ ልጆች ምቹ ሁኔታን በማመቻቸት ተመስጋኝ የሆነው አትሌት በሪሁ አረጋዊም በቻምፒዮናው ከፍተኛ ሚናን ከመወጣት ባለፈ የሜዳሊያ ሰንጠረዡ ከሚጠበቁ አትሌቶች መካከል ይካተታል።
ኢትዮጵያ ውጤታማ ከሆነችባቸው ርቀቶች መካከል አንዱ በሆነው ማራቶንም የመጨረሻዎቹ ዕጩዎች ታውቀዋል። በዚህም መሠረት በወንዶች የዓለም ቻምፒዮናው ሌሊሳ ዴሲሳ፣ የለንደን ዓለም ቻምፒዮና የብር ሜዳሊያ ባለቤቱ ታምራት ቶላ እንዲሁም በዶሃ ዓለም ቻምፒዮና የብር ሜዳሊያ ያጠለቀው ሞስነት ገረመው እንደሚሮጡ ታውቋል። በሴቶች በኩል ደግሞ ጎይቶም
ብርሃን ፈይሳ
አዲስ ዘመን ሰኔ 30/2014