የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን እ.ኤ.አ በ2020 ቶኪዮ ኦሊምፒክ ለመሳ ተፍ የመጀመርያ የማጣርያ ጨዋታውን የፊታችን መጋቢት 25 ከዩጋንዳ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጋር በአዲስ አበባ ስታ ዲየም ያከናውናል። ብሔራዊ ቡድኑ ከፊት ለፊቱ ለሚጠብቀው የማጣሪያ ጨዋታ ከመጋቢት 12 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ልምምድ ያካሂዳል። የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለማሰልጠን ባሳለፍነው ሳምንት ከስምምነት የደረሱት አሰልጣኝ ሠላም ዘርዓይ ብሔራዊ ቡድን ከፊቱ ለሚጠ ብቀው የኦሎምፒክ ማጣሪያ ጨዋታ ለ30 ተጫዋቾች የመጀመርያ ጥሪ አድርገዋል።
በአሰልጣኝ ሰላም ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ግብ ጠባቂ የመከላከያዋ ማርታ በቀለ፣ ታሪኳ በርገና ከጥረት ኮርፖሬት፣ ከሀዋሳ ከተማ አባይነሽ ኤርቄሉ እንዲሁም ምህረት ተሰማ ከጌዴኦ ዲላ እግር ኳስ ክለብ ናቸው። በተከላካይ ክፍል ከአዳማ ከነማ አራት ተጫዋቾች ጥሪ የተደረገላቸው ሲሆን መስከረም ካንኮ፣ እፀገነት ብዙነህ፣ ናርዶስ ዘውዴ፣ ነፃነት ፀጋዬ ናቸው። ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገነሜ ወርቁ፣ ታሪኳ ደቢሶ፣ ብዙዓየሁ ታደሠ ሲሆኑ ከመከላከያ መሠሉ አበራ፣ ከጥረት ኮርፖሬት አሳቤ ሙሶ፣ ትዕግስት ኃይሌ ደግሞ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
በአማካይ ስፍራ ትዕግስት ያደታ፣ አሰልጣኝ ሠላም ዘርዓይ ብርቱካን ገብረክርስቶስና ሕይወት ዳንጊሶ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ ከመከላከያ እግር ኳስ ክለብ አረጋሽ ከልሳ እና እመቤት አዲሱ፤ ብርሃን ኃይለሥላሴ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ሰናይት ቦጋለ ከአዳማ ከተማ፣ ዓለምነሽ ገረመው ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እንዲሁም ዮርዳኖስ ምዑዝ ከመቐለ 70 እንደርታ በምርጫው የተካተቱ ተጫዋቾች ሆነዋል። በአጥቂ ስፍራ ደግሞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንኳ ረሃማ ዘርጋው፤ የአዳማ ከተማ ተጫዋች የሆኑት ሎዛ አበራ፣ሴናፍ ዋኩማ ፣ ሰርካዲስ ጉታ የተካተቱ ሲሆን፤ ምርቃት ፈለቀ ከሀዋሳ ከተማ፣ ሔለን እሸቱ ከመከላከያ እንዲሁም፤ ምስር ኢብራሂም ከጥረት ኮርፖሬት እግር ኳስ ክለብ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል። በብሔራዊ ቡድን ጥሪ ከተደረገላቸው 30 ተጫዋቾች መካከል 29 ተጫዋቾች ከአንደኛ ዲቪዝዮን ሲጠሩ የመቐለ 70 እንደርታዋ ዮርዳኖስ ምዑዝ ብቸኛዋ ከሁለተኛ ዲቪዝዮን የተመረጠች ተጫዋች እንደሆኑም ታውቋል።
ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ ጨዋታዎች አትሌቲክስን ተጠቅማ ብዙ ታሪክ ብታስ መዘግብም በእግር ኳስ ግን ተሳትፋ አታው ቅም። እ.አ.አ በ2016 በሪዮ ዲጄንየሮ እንዲሁም በ2012 በለንደን በተስተናገደው ውድድር ማጣርያዎች ላይ ያልተሳተፈች ሲሆን በ2008 የቤይጂንግ ኦሎምፒክ እስከ ምድብ ማጣርያ ደርሳ ከደቡብ አፍሪካ ጋር በሜዳዋ አቻ ከተለያየች በኋላ በወቅቱ በፊፋ በተጣለባት እገዳ ምክንያት ከጋና እና ናይጄርያ ጋር ጨዋታ ሳታደርግ ከውድድሩ መውጣቷን መረጃዎች ያመለክታሉ።
የእድሜ ገደብ የሌለው የሴቶች እግር ኳስ ላይ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በሪዮ 2016 ማጣርያ ላይ አልተሳተፈም። በቀደመው (ለንደን 2012) ደግሞ በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ 3ለ0 ድምር ውጤት ተሸንፎ ከመጀመርያው ዙር ተሰናብቷል። የማጣርያው አካሄድ ያልታወቀበት ይህ ውድድር ላይ ኢትዮጵያ ስለመሳተፏ የታ ወቀ ነገር የለም።
አዲስ ዘመን መጋቢት 12/2011
ዳንኤል ዘነበ