ሌቦች ለስርቆት አላማ በርካታ የማጭበርበሪያ መንገዶችን ይጠቀ ማሉ። አንዳንዴ ለማጭበ ርበሪያነት የሚጠቀሙባቸው ስልቶች ግን ወጣ ያሉና ፈገግታም የሚያጭሩ ናቸው፡፡
ሮይተርስ ከሰሞኑ ከወደ ኬንያ ያወጣው መረጃም ይህንኑ ያመለክታል። እንደ መረጃው ከሆነ፤ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታን በመመሰል አንድን ታዋቂ የንግድ ሰው ከ10 ሚሊዮን የኬንያ ሽልንግ በላይ አጭበርብረዋል ባላቸው ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ መመስረቱን የኬንያ ፍርድ ቤት አስታውቋል፡፡
የታየር ፈርም ሳመር ድርጅት ኃላፊ ናውሻድ ምራሊና እና የፋይናንስ ዳይሬክተራቸው አኪፍ በት የተባሉትን ጨምሮ ሰባት ተጠርጣሪዎች ፕሬዝዳንት አሁሩ ኬንያታን በመመሰል አንድን ታዋቂ የቢዝነስ ሰው መሬት እንዲሸጥላቸው መጠየቃቸውን የፍርድ ቤቱ የክስ ፋይል ያመለክታል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በናይሮቢ ፍርድ ቤት ቀርበው ጥፋተኛ አለመሆናቸውን ያስረዱ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ በቀጣዩ መጋቢት ወር ጉዳያቸውን እስከሚመለከት ድረስም የዋስ መብታቸው ተጠብቆ እንዲለቀቁ ጠይቀዋል፡፡
ከሰባቱ ተጠርጣሪዎች መካከል አንደኛው የፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታን ድምፅ በማስመሰል አጭበርብሯል በሚል ተጠርጥሯል፡ ፡ ሁለተኛው ደግሞ በቅንጡ መኪና ሙሉ ልብስ ለብሶ ገንዘብ ለመቀበል ወደ ነጋዴው መጥቷል ሲል ፖሊስ ገልጸዋል፡፡ ሜራሊ የተሰኘው ተጠርጣሪየሃገሪቷ ርእሰ ብሄርን እንዳናገረና ክፍያውን ከዚሁ ሰው እንዲቀበል ለፋይናንስ ዳይሬክተሩ ትእዛዝ እንዳስተላለፈ የክሱ መዝገብ አመልክቷል፡፡
ስታር የተሰኘው የኬንያ ጋዜጣ እንዳስነበበው፤ ፕሬዝዳንት አሁሩ ኬንያታን በማስመሰል ከተጠረጠሩት ውስጥ ጆሴፍ ዋሳዋ የተሰኘው ሌላኛው ተጠርጣሪ ቅንጡ መኪናዎችን፣ ሄሊኮፕተሮችንና የግል ጠባቂዎችን ይጠቀማሉ፡ ፡
ጉዳዩ ትንሽ አዝናኝ ቢሆንም በምስራቅ አፍሪካ ሙስና ምን ያህል እየተንሰራፋ እንደመጣእንደሚያመለክት የኬንያ የጸረ ሙስና ካይ አካላት ተናግረዋል፡፡ የኡሁሩ ኬንያታ መንግሥት በጤናው ዘርፍ፣ በብሄራዊ የወጣቶች አገልግሎትና በግንባታ ዘርፍ ስምምነት ዙሪያ በሙስና ቅሌት በተደጋጋሚ ነቀፌታ እንደሚቀርብበት መረጃው ጠቁሟል፡፡
ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች እና የንግድ ሰዎች ከብሄራዊ ወጣቶች አገልግሎት ጋር በተያያዘ በፈፀሙት የ100 ሚሊየን ዶላር የሙስና ወንጀል ባለፈው ግንቦት ወር ክስ እንደተመሰረተባቸውም አስታውሷል።
አዲስ ዘመን የካቲት 26/2011
በአስናቀ ፀጋዬ