ዋርካው ትልቅ ዛፍ ነው፡፡ የበቀለው ጉብታ ላይ መሆኑ ደግሞ በሁሉም ዓይን ውስጥ ጎልቶ እንዲታይ አስገድዶታል፡፡ የዋርካው ግንድ እንደሌሎቹ ዛፎች ጥቁር አይደለም፡፡ ግንዱ ነጣ ያለ ሲሆን ፈሳሽ ያወጣል። በግንዱ ዙሪያ ጥቅጥቅ ብለው አግድም የተንሳፈፉ በርካታ ቅርንጫፎች በዋርካው ላይ ይታያሉ፡፡ ቅጥሉ ሰፋፊ ነው፡፡ የዛፉ ስቃይ የጀመረው ሁልጊዜም ዛፍ በመቁረጥ ራሱን የሚያዝናናው ሽማግሌው ዛፍ ቆራጭ የመጥረቢያውን ዛቢያ ትከሻው ላይ ተሸክሞ መጠጋት ሲጀምር ነው፡፡
ዛፍ ቆራጩ በቅድሚያ የዋርካውን ትልቅ ቅርንጫፍ ተጠግቶ ትንሽ ቅጠል በእጁ ገነጠለ፡፡ የገነጠላትን የእጁን መዳፍ የምታክለውን የዋርካውን አካል፤ ትንሽዋን ቅጠል መሬት ጣላት፡፡ የጣላትን ቅጠል በተረከዙ ረገጣት፤ እንደአቅሟ አነባች፡፡ ዛፍ ቆራጩ ሽማግሌ ፈርጣማና የጊዜው ሃያል በመሆኑ የቅጠሏ እንባ አልታየውም፡፡ በጎ ሰው ከበጎ ልቡ በጎ ነገር እንደሚያደርገው ሁሉ፤ እንደዛፍ ቆራጩ አይነት ክፉ ሰው ደግሞ በክፉ ልቡ ክፉ ነገር ያደርጋል፡፡ ዛፍ ቆራጩ አላቆመም መራመድ ጀመረ፤ በሁለት እጆቹ ትከሻው ላይ የነበረውን የመጥረቢያውን ዛቢያ አንስቶ በስለቱ የዋርካው ግንድ ላይ አሳረፈው፡፡
ዛፍ ቆራጩ ሽማግሌ ከኖረበት ዕድሜ በላይ ብዙ ዘመናትን ያስቆጠረ፤ ብዙዎችን አስጠግቶ ያሳረፈው ዋርካ እንደቅጠሏ አነባ፡፡ በተለይ ዋርካው በጣም የተከፋው ዛቢያው የራሱ ወገን በመሆኑ ለዛፍ ቆራጩ አልታዘዝም ማለት ሲገባው በገዛ በራሱ ወገን መቁሰሉ የበለጠ አሳመመው፡፡ የገዛ ወገን የአንዳንዶች መጠቀሚያ ሆኖ ሲጎዳ ልብ ያደማል፡፡ እናም ዋርካው በገዛ ወገኑ መጎዳቱ አንገበገበው፡፡ ገንዘብ ወዳጅ ፍቅር አያውቅም እንደሚባለው፤ ዛቢያው የሰው ላብ የጠማው ሆዳም በመሆኑ፤ የወገን ፍቅር ብሎ ነገር አይገባውም፡፡
ዛፍ ቆራጩ መፍለጫውን ያሳረፈበትን የዋርካውን ግንድ ጠጋ ብሎ በጣቶቹ ለመፈርፈር ሞከረ፤ የዋርካው ግንድ ቢመታም ከቅርፊቱ አልፎ ግንዱን አልነካውም። ዛፍ ቆራጩ ትንሽ ተበሳጨ፤ ተስፋ እንደመቁረጥ አለ። ነገር ግን በዋርካው አካባቢ የነበሩ ሌሎች ዛፎችን እንዴት ከዛፍነት ወደ አመድነት እንደቀየራቸው ሲያስታውስ፤ ተስፋው ለመለመ፡፡ ዋርካውን መቼ እና እንዴት በመፍለጫው ቆርጦ እንደሚጥል እና ከዛፍነት ተራ አውርዶ እንዴት ጉቶ ሊያደርገው እንደሚችል ሲያስብ በደስታ ፊቱ በራ፡፡ ሽምግልናው ቀርቶ እንደጎረምሳ ጡንቻዎቹ ተወጣጠሩ፡፡ ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል ይባል አይደል? ዛፍ ቆራጩም ዋርካውን አመድ ማድረግ እችላለሁ ብሎ አሰበ፡፡
ዛፍ ቆራጩ ህልሙ ዛፎችን በመቁረጥ ተራ እንጨትና አመድ ማድረግ ብቻ አይደለም፤ አካባቢውን ምድረ በዳ በማድረግ ፍላጎቱን ያለተከላካይ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ደጋግሞ ህልሙን የሚያሳካበትን መንገድ በደንብ ማሰብ ጀመረ፡፡ ዋርካው በአንድ ጊዜ የተቆራረጠ እንጨትና ጉቶ የሚሆንበትን መንገድ አውጠነጠነ፡፡ ከጥላው ስር አረፍ ብሎ መፍለጫውን ሳለ፡፡ የዋርካው ወገን ዛቢያው በበኩሉ የሽማግሌው ዛፍ ቆራጭ የእጅ ላብ ጣፍጦታል፡፡ ዛቢያው ማጣጣም ጀምሮ ተደጋግሞ የዋርካው ግንድ እንዲመታ አጥብቆ እየፀለየ ነው፡፡ ዛፍ ቆራጩን እየተለማመጠ ደጋግሞ ቀና ይላል፡፡ መጠቀሚያ ሆኖ የገዛ ወገኑን ዋርካን አመድ የሚሆንበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ቋምጧል፡፡
ሰዎች ለሆዳቸው አድረው የገዛ ወገናቸውን እንደሚያጠፉ፤ የዋርካው ዘመድ ዛቢያ በሽማግሌው ላብ መብለጭለጭ በመፈለጉ ዋርካውን ከጥቃት መጠበቁን ትቶ በተቃራኒው በዛፍ ቆራጩ ሽማግሌ ዋርካው እንዲቆረጥ መገፋፋቱን ቀጥሏል፡፡ ዋርካው በበኩሉ የዛፍ ቆራጩ ተግባር አስከፍቶታል፤ የዛቢያው ሁኔታ አንገብግቦታል፡፡ ነገር ግን በምንም መልኩ እንደማይንበረከክላቸውና እንደተመኙት የተቆራረጠ እንጨትና ጉቶ በመጨረሻም አመድ እንደማይሆንላቸው ለራሱ ቃል ገባ፡፡
ዋርካው መለስ ብሎ የገዛ ወገኑን ዛቢያውንም ሆነ ሽማግሌ ዛፍ ቆራጩን ምን እንዳደረጋቸው? ለምን ይህን ያህል እንደጠሉት ለማወቅ እያወጣና እያወረደ ቢያሰላስልም ማወቅ አልቻለም፡፡ ዋርካው ለራሱ ‹‹ዛፍ ቆራጩ ሸምግሏል፤ ሲሆን ሲሆን እየተንከባከበኝ እኔ ስር ቁጭ ብሎ እንደማረፍ የእኔን መኖር ለምን ጠላ?›› ሲል ራሱን ጠየቀ፡፡ ‹‹በእኔ ስር የተጠለሉ ሰዎችን ከቀትር ፀሐይ ቃጠሎ በመከላከሌ ቅናት ተሰምቶት ይሆን?›› በማለት ለራሱ የሚያቀርባቸውን ጥያቄዎች አከታተለ፡፡ እርግጥ ነው፤ በስሩ የለመለሙት ዕጽዋት ዋርካውን ይበልጥ ያስውቡታል አድገው አካባቢውን ያሳምሩታል የሚል ስጋት እንዳለበት አስታወሰ፡፡ ለራሱ ‹‹አይ ሰው፤ ሰው ክፉ ነው!›› አለ፡፡
‹‹አንበሳ ንጉስ የሆነው ተርቦ ስለሚያድን ነው›› ይባል አይደል? ዛፍ ቆራጩ አንበሳ ሆኗል፡፡ ለአደን የወጣ የተራበ አንበሳ መስሏል፤ ድርጊቱ ይህን ያሳብቃል፡፡ ‹‹የሰዎች መሰብሰቢያ ለአይን የሚማርክ ዘመናትን ያስቆጠረ ዛፍ አይቼ እኔ አያስችለኝም›› የሚል ይመስላል፡፡ የሰዎች መጠለያውን ዋርካውን ካልገነደሰ የሚያርፍ አይመስልም፡፡ ያለ የሌለ አቅሙን ሰብስቦ ዋርካው ላይ ለመዝመት ቀድሞ አንድ መላ መጥቶለታል፡፡ ዛቢያውን የዋርካው ዛፉ ላይ ቢያሰፍረውም እንዳሰበው ዋርካው ላይ ምንም አይነት የመገንደስ ምልክት ሊታይ አልቻለም፡፡ ያው የውጪው ዓለም ኢትዮጵያን በገዛ ልጆቿ ተገዝግዛ እንድትፈርስ እንደሚያሴረው ማለት ነው፡፡
ዛፍ ቆራጩ በዛቢያው በመጠቀም የዋርካውን ግንድ ዙሪያውን በስለቱ ቢሰነዝርም፤ ከቅርፊቱ ማለፍ አልቻለም፡፡ ዛፍ ቆራጩ ግንዱን ከስሩ ለመገንደስ ደጋግሞ ወደ ታች ቢሞክርም አልተሳካለትም፡፡ በዚህ ጊዜ መጠቀሚያ የሆነው ዛቢያ የሽማግሌው ላብ ጣፍጦት ማጣጣሙን ተያይዞታል፡፡ ያው ኢትዮጵያን እያመሷት ከስሯ ሊንዷት እንደሚሞክሩት የልጅ ከሃዲዎች የሚልሱትን ብቻ እንደሚያስቡ የቀን ጅቦች ማለት ነው፡፡ ዛቢያውም ያው እንደነርሱ ዋርካው እንዲፈርስ እየተጋ፤ እርሱ የሚልሰውን ያነፈንፋል፡፡
ሽማግሌው ዛፍ ቆራጭ ላቡን እያፈሰሰ የዋርካውን ግንድ ለመቁረጥ ቢሞክርም አልሆነለትም፡፡ ዋርካው እንደሌሎቹ ዛፎች በቀላሉ የሚቆረጥ አልሆነም፡፡ ዛፍ ቆራጩ እንዳሰበው ዋርካውን በቀላሉ እንጨትና አመድ ማድረግ አልቻለም፡፡ ሌላ መንገድ አሰበ፡፡ ያው የተራበ አንበሳ ግዳይ ሳይጥል አይተኛም፡፡ የተቻለውን መንገድ በሙሉ ከመሞከር አይቦዝንም፡፡ ስለዚህ በሺህ የሚቆጠሩ ዓመታትን ያሳለፈ፤ ለብዙዎች መጠለያ የሆነ፤ ነፍሳትን ያኖረ፤ በመኖሩ ከመጥቀም ውጪ ማንንም ያልጎዳ ዋርካን አንድ ሽማግሌ ዛፍ ቆራጭ ቆራርጦ ለመጣል ከማሰፍሰፍ አልፎ ሌሎችን ለማስተባበር አሰበ፡፡ ያው መቼም ጊዜው የ ‹‹ሃያል ነን›› ባዮች አይደል፡፡ እነአሜሪካንም እንደሽማግሌው ዛፍ ቆራጭ ‹‹አድራጊ ፈጣሪ እኛ ነን፤ እኛ ከፈቀድነው ውጪ ማንም ምንም ዓይነት እድገት ማስመዝገብም ሆነ በሰላም መኖር እንዲሁም የቱንም አይነት እርምጃ መውሰድ አይችልም፡፡›› የሚሉት ለዚህም ነው፡፡
ሽማግሌው ባይገባውም ዋርካው እንደርሱ የተወሰኑ በጣት የሚቆጠሩ አሥርት ዓመታትን ሳይሆን በሺህ የሚቆጠሩ ዘመናትን ያስቆጠረ ነው። በእነዚህ ዘመናትም ከማንም በላይ ሃያልነትን ያየ እና ከሌሎች ዛፎች አንፃር በሃያልነት ወደር የሌለው ነበረ፡፡ ዕፅዋት ከእርሱ ጋር ሲነፃፀሩ ጋን እና ጋን ውስጥ ያለች የአቧራ ብናኝን እንደማነፃፀር ነበር። እና ይህንን ለምድር ለሰማይ የከበደ ዋርካን ለመገንደስ ማሰብን ምን ይሉታል? ኢትዮጵያም ያው ናት፡፡ ሃያል የነበረችሽማግሌው ዛፍ ቆራጭ ላቡን እያፈሰሰ የዋርካውን ግንድ ለመቁረጥ ቢሞክርም አልሆነለትም፡፡ ዋርካው እንደሌሎቹ ዛፎች በቀላሉ የሚቆረጥ አልሆነም፡፡ ዛፍ ቆራጩ እንዳሰበው ዋርካውን በቀላሉ እንጨትና አመድ ማድረግ አልቻለም፡፡ በቀላሉ በማንም የማትፈርስ እና ከማንም ጋር ብትነፃፀር የጋንን እና የአቧራ ብናኝን ያህል ልዩነትን ያላት ሃያል ነበረችሽማግሌው ዛፍ ቆራጭ ላቡን እያፈሰሰ የዋርካውን ግንድ ለመቁረጥ ቢሞክርም አልሆነለትምሽማግሌው ዛፍ ቆራጭ ላቡን እያፈሰሰ የዋርካውን ግንድ ለመቁረጥ ቢሞክርም አልሆነለትምሽማግሌው ዛፍ ቆራጭ ላቡን እያፈሰሰ የዋርካውን ግንድ ለመቁረጥ ቢሞክርም አልሆነለትም። ዋርካው እንደሌሎቹ ዛፎች በቀላሉ የሚቆረጥ አልሆነም፡፡ ዛፍ ቆራጩ እንዳሰበው ዋርካውን በቀላሉ እንጨትና አመድ ማድረግ አልቻለም፡፡ ዋርካው እንደሌሎቹ ዛፎች በቀላሉ የሚቆረጥ አልሆነም፡፡ ዛፍ ቆራጩ እንዳሰበው ዋርካውን በቀላሉ እንጨትና አመድ ማድረግ አልቻለም፡፡ ዋርካው እንደሌሎቹ ዛፎች በቀላሉ የሚቆረጥ አልሆነም፡፡ ዛፍ ቆራጩ እንዳሰበው ዋርካውን በቀላሉ እንጨትና አመድ ማድረግ አልቻለም፡፡ ኢትዮጵያ እንደሌሎቹ በቀላሉ የፈረሱ ሃገራት አይደለችም፡፡ በቀላሉ ወደ አመድነት አትቀየርም፡፡ ምክንያቱም ሃያልነቷ አሁን ባለው የቁስ ሃብቷ ሊታይ ባይችልም፤ ህዝቧ እልሁ እና ንፅህናው እንዲሁም አገር የመውደድ ፅናቱ የዛፍ ቆራጩ ሽማግሌን ህልም የሚያጠፋ ነው፡፡
ዛፍ ቆራጩ በድጋሚ ወደ ዋርካው ስር ጠጋ ብሎ በፈርጣማ እጆቹ የመጥረቢያውን ዛቢያ ግንዱ ላይ አሳረፈው፡፡ ዋርካው እንባውን ከማፍሰስ ውጪ ምንም አላለም፡፡ ኢትዮጵያን ከስሯ ለመገንደስ ቢሞክሩም እንዳልተሳካላቸው የኢትዮጵያ ጠላቶች ሁሉ ዛፍ ቆራጩም የዕለቱ ሙከራ አልተሳካለትም፡፡ ምንም ማድረግ እንደማይችል ሲረዳ ከላይ ከዋርካው አናት ለመጀመር አሰበ፡፡ ነገር ግን የዋርካው ቅርንጫፎች የዋዛ አይደሉም፡፡ ወደ ዋርካው አናት እንዲወጣ አልፈቀዱለትም፡፡ እጁን እና ፊቱን ቆራርጡት፡፡ ዛፍ ቆራጩ ግን ተስፋ አልቆረጠም፤ ሌላ መንገድ ማሰብ ጀመረ፡፡ የተራበ አንበሳ ካልበላ እንደማይተኛው ሁሉ ዛፍ ቆራጩ ሽማግሌም ዋርካውን መገንደስ አልችልም ብሎ ተስፋ ቆርጦ ትቶ ለመሔድ አላሰበም፡፡ ያሉ አማራጮችን በሙሉ ለመሞከር ወሰነ፡፡
በዕለቱ የተራበ ያረጀ አንበሳ አቅቶት እንደሚዝለፈለፈው ሁሉ ዛፍ ቆራጩ ሽማግሌም አቅሙ ከዳው ተዝለፈለፈ፡፡ መጥረቢያውን ቢስልም ያለ የሌለ አቅሙን ቢጠቀምም ግዳይ መጣል አልቻለም፡፡ ዋርካው ቁስሉን እያስታመመ እንዲሰቃይ ከማድረግ ውጪ ገንድሶ ሊጥለው አልቻለም፡፡ አሁንም ተስፋ ያልቆረጠው ዛፍ ቆራጭ የዋርካ ዛቢያ ይዞ በዛፉ ቅርንጫፍ ላይ መፍለጫውን ሲያውል አንድ ተለቅ ያለ ቅርንጫፍ ተገንጥሎ እንዲወድቅ ማድረግ ቻለ፡፡ ለዛሬ ተሳክቶልኛል አለ፡፡ በቀጣዮቹ ጊዜያት ደግሞ አንድ አንድ እያለ ቅርንጫፎቹን ገነጣጥሎ ዋርካውን እርቃኑን ካቆመው በኋላ ለመገንደስ እና ከስሩ ለመንቀል እንደማያዳግተው አሰላ፡፡ እርግጥ ነው፤ የዋርካውን አንዲት ቅርንጫፍ መገንጠል ችሏል። እንደተራበ አንበሳ ያሰፈሰፈው ሽማግሌው ዛፍ ቆራጭ ተረጋጋ፡፡
የኢትዮጵያ ጠላቶች ቅርንጫፎቿ በሙሉ ተገነጣጥለው ትጠፋለች ብለው እንዳሰሉት ዛፍ ቆራጬ ሽማግሌም ዋርካውን ያለ ቅርንጫፍ ለማስቀረት ቀስ እያለም ዋርካውን ወደ አመድነት የሚቀየርበትን መንገድ ማወቁ አበረታው፡፡ አሁን ጊዜው ደርሷል፤ ዋርካው የአንዱ ቅርንጫፉ መገንጠል በእጅጉ አሳዝኖታል፡፡ ያው አካል ሲቆረጥ እንደሚያመው ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ዋርካው ከአንዱ ቅርንጫፍ መገንጠል በላይ የጎዳው ሽማግሌው ዛፍ ቆራጭ መላ ቅርንጫፎቹን ለመገነጣጠል መወሰኑ ስጋት ውስጥ ከተተው፡፡ ሲጨልም ነገን ተስፋ አድርጎ በማግስቱ ዋርካውን እንጨትና ጉቶ ሊያደርገው እንደሚችል አረጋግጦ ዛፍ ቆራጩ ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡
ዛፍ ቆራጩ ወደ ቤቱ ሲሄድ በመንገዱ የተሰበሰቡ ሰዎችን አየ፡፡ ሲጠጋቸው እርስ በእርስ እየተጯጯሁ ነበር፡፡ መጥረቢያውን በቀኝ እጁ ወደ ታች እንዳንከረፈፈ ‹‹ምንድን ነው?›› ብሎ ቢጠይቅም ምላሽ የሰጠው አልነበረም፡፡ ሰው ሊወድቅ ሲል ይኮራል እንደሚባለው ዛፍ ቆራጩ ሽማግሌ ጉዳዩ ሳይገባው ሰዎቹ ምን እንዳላቸውና ምን እንዳሰቡ ሳያረጋግጥ እንደልማዱ ትዕቢቱና ኩራቱ ከደረቱ አልፈው አናቱ ላይ ሲደርሱ በማያውቃቸው ሰዎች ላይ ቁጣ ቁጣ አለው፡፡ ያንከረፈፈውን መጥረቢያ አንስቶ ዛቢያውን ትከሻው ላይ ሲያደርግ ከሰዎቹ መሃል ሁኔታውን አይቶ የተጠራጠረ የእርሱ ቢጤ ትዕቢተኛ፤ ሃያል ነኝ ባዩን እንደተራበ አንበሳ ዋርካውን ለመገንደስ ላቡን ያፈሰሰውን ዛፍ ቆራጭ ቀድሞ በጥይት ደረቱን መታው፡፡ ዛፍ ቆራጩ ከነህልሙ መሬት ላይ ተዘረረ፡፡
ዋርካው በማግስቱ ወደ አመድ ሊቀይረው ያሰበው ሰው ክፉ ነውና እንደማይተወው ተጠራጥሯል፡፡ ነገር ግን በጠዋት ሰዎች ቃሬዛ ተሸክመው ተጠጉት፤ ከዋርካው ሥር መቆፈር ጀመሩ፡፡ እርስ በእራሳቸው ‹‹ካገኘው ጋር በየመንገድ መጣላት መጨረሻው ይኸው ነው›› ሲባባሉ፤ ዋርካው ሰማ፡፡ ከስሩ የተቆፈረው ጉድጓድ ውስጥ የዛፍ ቆራጩ ሽማግሌ አስክሬን ሲገባ አየ፡፡ ዋርካው ቀባሪዎች ባይሰሙትም እንዲህ ሲል ዘፈነ፡፡
“አዬ ግፍ አዬ ግፍ አዬ ግፍ ገፋፊ
ሌቱን አላደረም የዛሬው ተጋፊ”
ዋርካው አገር ነው፡፡ ዛቢያው ደግሞ የእኛው አካል የሆኑት ከሃዲዎቹ ናቸው፡፡ ዋርካን መገንደስ አገርን ማፍረስ ቀልድ አይደለም፡፡ በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ያለች አገርን ማፍረስ እርሷ ከመፍረሷ በፊት ለፈራሽነት ይዳርጋል፡፡ እርግጥ ነው፤ እንደዛፍ ቆራጩ ኢትዮጵያን ለማፍረስ አጥብቀው እንደተራበ አንበሳ እየተጉ ያሉ አሉ፡፡ ነገር ግን ያረጀና የተራበ አንበሳ ሲደክመው ይሞታል፡፡ ኢትዮጵያ ደግሞ በእርሱ ቦታ ሃያልነቷ ይረጋገጣል፡፡ ዋርካው አሁንም ጥላ ነው፡፡ በቀትር ለተጠጉት ሰዎች ፀሐይ ሳያሳልፍ ማረፊያ ሆኖ ያገለግላል፡፡ ዛፍ ቆራጮች አገር ገንዳሾች አይሳካላቸውም፡፡ አመድ የሚሆነው ዋርካው ወይም ኢትዮጵያ ሳትሆን እነርሱ ናቸው፡፡
ምህረት ሞገስ
አዲስ ዘመን ጥቅምት 11/2014