በአክሱም ዘመነ መንግሥት ጥንታዊው የንግድ መስመር በምጽዋ ተጀመረ። በመካከለኛው ዘመን የንግድ መስመሩ ወደ አራት አድጓል። ኢትዮጵያ ከ18ኛው ክፍለ ዘመን በፊት በቀይ ባህር መስመር ህንዶችና ግሪኮች የንግድ ግንኙነት ያደርጉ እንደነበር ታሪክ ያስረዳናል። በሌላ በኩል ደግሞ ግብጾች የዓባይን ወንዝ ተከትለው ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የንግድ ልውውጥ ያደርጉ ነበር። በኢትዮጵያ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ዳግም በአንሰራራው የረዥም ርቀት ንግድ የሲራራ ነጋዴዎች መጠሪያ ስያሜ ጀበርቲ (Jabarti) እና አፍካላ (Afkala) ይባሉ ነበር። ጀበርቲ ተብለው የሚጠሩት በሰሜን ኢትዮጵያ ይኖሩ የነበሩ ሙስሊም ሲራራ ነጋዴዎችን ሲሆኑ አፍካላ ደግሞ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የነበሩ የኦሮሞ ሲራራ ነጋዴዎች መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ።
ረዥም ርቀት ንግድ ይካሄድ የነበረው ግትልትል ግመሎች (Caravan) በሚጠቀሙ ነጋዴዎች ነበር። እነዚህ ነጋዴዎች ደግሞ ሲራራ ይባላሉ። በዘመኑ ዘራፊዎችና የየድንበሩ የተለያዩ አስተዳዳሪዎችና ገዥዎች ከፍተኛ የሆነ ቀረጥ በማስከፈል ሲራራ ነጋዴዎችን ያማርሯቸው ነበር። እነዚህን ችግሮች ለመፍታትም ነጋዴዎቹ በቡድን ሆነው በመጓዝ ረጅም ርቀት ይነግዱ ነበር። በቡድን ሆነው የሚሄዱትን ነጋዴዎች የሚያስተባብርና የሚመራ አንድ ሰው ይሾማሉ፤ መጠሪያ ስያሜውም «ነጋድራስ» ይባላል። በወቅቱም ዘመናዊ መገናኛና መጓጓዣ ስላልነበረ ብዙ ፈተናዎች የሚያጋጥማቸው ቢሆንም ያንን ተቋቁመው ነበር የሚነግዱት። ሲራራ ነጋዴዎቹ ወደ ውጭ ከሚልኩት ሸቀጦች መካከልም ወርቅ ፣ዝባድ ፣ ቆዳ ፣ሌጦ ፣እጣንና ቡና ይገኙባቸዋል።
ወደ ሀገር የሚያስመጡት ደግሞ መዳብ ፣ቅመም ፣ልብስ፣ ዶቃዎች፣ ሃርና ሌሎች ሸቀጦች ይገኙባቸዋል። ዋነኛ የገበያዎቹ ማዕከል ደግሞ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ የተዘረጉ የንግድ መስመሮች ናቸው። ለአብነት ያህል እናርያ፣ ቦንጋ በከፋ ፣ ሂርማታ በጅማ ፣አሰንዳቦ በወለጋ ፣ባሶ በጎጃም ፣ በጎንደር መተማ፣ ሱዳን ተሻግሮ ወደ ግብጽ ሲያቀና ሌላው መስመር ደግሞ በጎንደር፣ ዓድዋ ፣አዶሊስ /ምጽዋ ዋነኛ የንግድ መስመር ነበሩ። ምጽዋ የሀገሪቱ የሰሜኑ ክፍል መዳረሻ፣ የንግድ ኬላና ወደብ ሆና ለረጅም ጊዜ አገልግላለች። በምስራቅ ምዕራብ የንግድ መስመር ደግሞ ሶዶ በጉራጌ ፣አንኮበር እና አልዩ አምባ በሰሜን ሸዋ፤ድሬዳዋና ሐረር በሐረርጌ ይገኙበታል። በዚህ መስመር የዜይላና በርበራ መዳረሻ ወደቦች ሆነው አገልግለዋል።
ይህ ረዥም ርቀት የንግድ መስመር የሀገራችንን ህዝቦች ኢኮኖሚያዊ ታሪክ ይጠቁመናል። አጼ ምንሊክ ዛሬ ያለችውን ኢትዮጵያ አንድ አድርገው ከማስተዳደራቸው በፊት ይብዛም ይነስም የሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል በጌምድር፣ ጎጃም፣ ትግራይና የሸዋ አካባቢዎች የራሳቸው ነጻ ግዛት ነበሩ። ሌላው ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍል ደግሞ ከፋ፣ ጅማና ወለጋ ራሳቸውን የቻሉ ግዛቶች እንደነበሩ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት ምሁሩ ዶክተር ብርሀኑ ደኖ ያወሳሉ። ይህንን መሰረት አድርጎ አንደኛ ከቦንጋ ጀምሮ በሶዶ አድርጎ አልዩ አምባ ደርሶ በሐረር አቋርጦ በዘይላና በበርበራ ወደብ ወደ መካካለኛ ምስራቅ አገሮች መዳረሻውን ያደረገ የንግድ መስመር ነበር። ሁለተኛው የንግድ መስመር ደግሞ ጅማ ፣ሲቃ-አሰንዳቦ-ሆሮ ጉድሩ(ምዕራብ ወለጋ) ባሶ በሚባለው አካባቢ አቋርጦ በጎንደር- በመተማ አድርጎ ወደ ሱዳን የሚሄድ የንግድ መስመር ነው። ሦስተኛው ደግሞ ጅማ ፣ሲቃ-አሰንዳቦ-ሆሮ ጉድሩ (ምዕራብ ወለጋ) ባሶ በሚባለው አካባቢ አቋርጦ በጎንደር አልፎ በዓድዋ አድርጎ ወደ ምጽዋ ይሄድና ወደ ውጭ ይወጣል። የሰሜንና የደቡብ ምዕራብ ግዛቶች አንድ አይነት የፖለቲካ አስተዳደር ስርም ባይሆኑም ያን ጊዜም ቢሆን ለረጅም ጊዜ በንግድ የተሳሰሩና የሚተዋወቁ ነበሩ። እነዚህ የንግድ መስመሮችም ለዘመናዊው ንግድ መሰረትና አመላካች ናቸው።
ለረጅም ጊዜና ከ23 ዓመት በፊትም በምጽዋ ነበር የወጪና የገቢ ንግድ የሚካሄደው። (አሁንም ግንኙነቱ ተሻሽሎ መጠቀም ልንጀምር ነው) ።ሌላው መስመር ቀደም ሲል የነበሩት የንግድና የወደብ መስመሮች ታጁራ፣ በርበራና ዘይላም አሁን እየተጠቀምንበት ካለው በጅቡቲ ወደብ መልካም ስነ ምድራዊ አቀማመጣቸው ቅርበት ያላቸው ናቸው። ቀደም ሲል በመተማ በኩል ወደ ሱዳን የሚሄደው የንግድ መስመርም አሁንም ነዳጅና አንዳንድ ዕቃዎች የሚገቡበት ነው። በጥቅሉ የአየር ትራንስፖርትን ሳይጨምር አሁንም ብዙ የገቢና የወጪ ንግዶች የሚካሄዱት ቀደም ሲል በነበሩት መስመሮች አቅራቢያ ነው። ከዋና ዋና የንግድ ሸቀጦች መካካልም የከብት ቆዳ፣ ወርቅ፣ ቡና፣ የአውራሪስ ቀንድ፣ ዕጣን፣ ዝባድና አቡጀዴ ልብስ ይገኙበታል። በመካከለኛው ዘመን ዕቃ በዕቃ ከመለዋወጥ ጎን ለጎንም በኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ አሞሌ ጨው ዋነኛው የመገበያያ ገንዘብ ሆኖ አገልግሏል። በአጼ ምንሊክ ዘመነ መንግሥት ደግሞ ንጉሱ ከኦስትሪያ መንግሥት ጋር በፈጠሩት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በንግሥት ማሪያቴሬዛ ስም የታተመው የማሪያ ቴሬዛ ብር በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የወረቀት መገበያያ ገንዘብ ሆኖ ማገልግል ጀመረ። በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቋቋመው አቢሲንያ ባንክም የውጭ ገንዘብ ነበር የሚጠቀመው። ቀስ በቀስ የባንክ ሥራ እየተስፋፋ ሲመጣ በአጼ ኃይለስላሴ ዘመነ መንገሥት ኢትዮጵያ የራሷን ገንዘብ አሳትማ ሥራ ላይ አውላለች። «ንግዱ በሚፈለገው መልኩ ተስፋፍቷልና አድጓል ማለት አይቻልም» የሚሉት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት ምሁሩ ዶክተር ብርሀኑ፤ በእጅ ሙያተኞች ለምሳሌ ሸማኔው፣ ሸክላ ሰሪውና ነጋዴው የተለያዩ አሉታዊ ስያሜ የሰጣቸው ስለነበር በሚፈለገው መልኩ ንግዱ አድጓል ማለት እንደማይቻል ያስረዳሉ።
በመሆኑም ከውጭ የሚገቡ ምርቶችም በአገር ውስጥ የሚመረቱ ምርቶች እንዳይስፋፉ ጫና አሳድሯል። የትምህርት አለመስፋፋት፣ ባህላችንና የፖለቲካ ስርዓቱ የአገር ውስጥ ምርቶችን የሚያጥላላ ስለሆነ ንግዱ ረጅም ዘመን እንደማስቆጠሩ የተስፋፋ እንዲሆን አላስቻለም። ይህም የመፍጠር ችሎታንም እንዲቀጭጭ አድርጎታል። በትንሽ የእጅ ሥራ ሙያ የተጀመረው የአገር ውስጥ ንግድ ሥራ ተስፋፍቶ ለማደግ ዕድል ስላላገኘ ከውጭ የመጣው ሸቀጥ ነው ዘመናዊ የሚባለው። በዓለም ላይ ዘመናዊ ንግድ ተጀመረ የሚባለው ከሁለተኛ የዓለም ጦርነት በኋላ ነው። የእንጨት፣ የመጠጥ፣ ልብስ፣ የቆዳ ውጤቶች ድንበር አቋርጠው ይሸጡ ነበር። ጥንት መካከለኛው ምስራቅ የነበረው የንግድ መዳረሻ ዛሬ ከመካከለኛው እስያ አገራት ወደ አውሮፓና አሜሪካ አቅጣጫውን ቀይሯል። ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን ብዙዎቹ የአፍሪካ አገሮች ፊታቸውን ወደ አሜሪካ፣አውሮፓና ሩቅ ምስራቅ እስያ ማድረጋቸውን ምሁሩ ይተነትናሉ። የኢትዮጵያ ምርቶች የግብርና ምርቶች ስለሆኑ ንግዱ ወደ እነዚህ አገራት እያዘነበለ ነው።
በአሁኑ ጊዜ መካከለኛ ምስራቅ አገራት ብዙ የኢንዱስትሪ መስፋፋት አይታይም። ሰላምና መረጋጋትም የለም። የኢትዮጵያን እሴት ያልተጨመረባቸው የግብርና ምርቶች በብዛት የሚፈልጉት ቻይና፣ ምዕራብ አውሮፓና ሰሜን አሜሪካ ናቸው። በዚህ ምክንያት ብዙ አገራት ፊታቸውን ወደእነዚህ አገራት አዙረዋል። ኢትዮጵያም የዚሁ አካል ናት። ምክንያቱም የዓለም አቀፍ የንግድ መዳረሻዎች የሚወሰኑት ጉዳዮች አንዱና ዋነኛው ፍላጎት ነው። አሁንም በዘመናዊ ዓለም የንግድ መዳረሻንና የሚላኩ ምርቶችን አይነት ማስፋፋት ያስፈልጋል። አልዩ አምባ እስከ ዘይላ ወደብ ድረስ ተዘርግቶ ለነበረው የሲራራ ንግድ ማዕከል ነበረች። በ1834 እና 1835 ዓ.ም በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው የቀረጥ ውል የተፈረመው በአልዩ አምባ ገበያ መሠረት ነው።
በአጼ ምንሊክ ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ የቀረጥ መሥሪያ ቤት ሲከፈት በአልዩ አምባ የጉሙሩክ ጽሕፈት ቤት ሥራውን እንዲጀምር ተደርጎ ነበር። በዚህም መሠረት በዘይላ ወደብ የንግድ መስመር በኩል ወደ ሀገራችን በሚገቡ የንግድ ዕቃዎች ላይ የቀረጥ ክፍያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጀመረባትና የኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ የጉሙሩክ ከተማ አልዩ አምባ ሆነች። ከአንድ ሺህ 500 እስከ አንድ ሺህ 700 የሚጠጉ ግመሎች የአገር ውስጥ ሸቀጦችን ወደ ውጭ ያጓጉዙባት እንደነበርም ይነገራል። በተጨማሪ አልዩ አምባ ከተማ በ19ኛው ከፍለ ዘመን የሲራራ ንግድ ማዕከል ነበረች ። በከተማዋ ከፐርሽያ፣ ከህንድና ከዓረብ አገሮች የሚመጡ በርካታ የውጭ ዜጎች ይኖሩባት እንደነበርም ጎብኝዎች ጽፈውላታል። በአጼ ምንሊክ ዘመነ መንግሥት የታክስ ስርዓት ቢኖርም በገቢና በምርት ላይ የተጣሉት ዘመናዊ የታክስ ስርዓት ተግባራዊ የሆነው ግን በአጼ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግሥት ነው። ይህ የታክስ ስርዓት እየተሻሻለ ሄዶ ዛሬ ላይ ደርሷል።
አዲስ ዘመን የካቲት 16/2011
ጌትነት ምህረቴ
Online apotheek voor medicijnen in Leiden Teva Dübendorf farmaci disponibili in Italia
acheter médicaments Maroc avec indication médicale Liomont Mons (Bergen) medicijnen bestellen voor
een comfortabel leven
Heya i am for the first time here. I came
across this board and I find It really useful & it helped
me out much. I am hoping to give one thing again and help others such as you helped
me.
большой сонник миллера – толкование снов, сонник толкование снов бесплатно колдуны и ведьмы контакты к чему сниться мыть длинные волосы
приснилось что меня хотят задушить
к чему если снится что парень
в тюрьме
medicijnen kosten in Nederland hexal Cartagena Günstiger Medikamente-Kauf in Österreich
популярные близнецы по гороскопу к чему
снится черный дракон мужчине порча на тоску как ее снять
расклад карты таро на парня приснилась вошь в голове у себя
найти подработку в находке
подработка педагог уфа найти работу недалеко от дома
как заработать денег в гта 5 онлайн чит