ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ በሻህ፣ ኑሯቸውን ያደረጉት በአገረ አሜሪካ በሰሜን ካሮላይና ነው፡፡ ሙያቸው የፖለቲካል ሳይንስ ዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ኢንተርናሽናል ጆርናሊዝም ሲሆን፣ በሰሜን ካሮላይና በኤ ኤንድ ቲ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የፖለቲካል ሳይንስና የጋዜጠኝነት መምህር ናቸው፡፡ በዛው በአሜሪካ በተለያዩ ሲቪክ ድርጅቶች ውስጥ በኢትዮጵያ ጉዳይ በንቃት ይሳተፋሉ፡፡ በብዙ ድርጅቶች ውስጥ ኤክስኪዩቲቭ ኮሙዩኒቲ አባልና አማካሪም ናቸው፡፡ ቀደም ሲልም ዲፕሎማት በመሆን በምክትል አምባሳደርነት በአውሮፓ፣ በዩናይትድ ኔሽንና በአሜሪካም በኢትዮጵያ ኤምባሲ ውስጥ ሰርተዋል፡፡ እኚህ ፕሮፌሰር በአሜሪካ የዲያስፖራ የሰላም ጓድ ሰብሳቢ ሲሆኑ፣ ሰሞኑን ከአሜሪካ ዘጠኝ ያህል አባላት የያዘውን ልዑክ በመምራት ወደትውልድ አገራቸው ኢትዮጵያ መጥተዋል፡፡ አዲስ ዘመን የሰላም ጓዱ ወደኢትዮጵያ ስለመምጣቱ ጉዳይና ሰሞነኛውን የኢትዮጵያና የአሜሪካንን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ከእርሳቸው ጋር ቆይታ አድርጎ እንደሚከተለው አጠናቅሮታል፡፡ መልካም ንባብ ይሁንልዎ፡፡
ብቻ ነው ወይስ ለተራቡ ወንድምና እህት ለሆነው ለትግራይ ወገኖቻችን ነው ይህን የሚያደርገው የሚል ጥያቄ እንድንጠይቅ የሚያደርግ ነው፡፡ እኛ ለትግራይ ህዝብ እናዝናለን፡፡ ምክንያቱም የዚህ ግጭት ገፈት ቀማሹ እሱ ነውና፡፡ ስለዚህም በዚህ መልክ ግልጽ የሆነ ሪፖርት አለማድረጋቸው አሳዝኖናል፤ እንዲሁም እኛንም ሆነ ሌሎችንም ጥርጣሬ ውስጥ አስገብቶናል፡፡
በአብዛኛው ያኔ የሚወራው ከጥቅምት 24 በኋላ ትኩረት ያደረጉት መንግስት ላይ ነበር፡፡ ይህን ሲያደርጉ የነበረው እውነታው ተይዞ ሳይሆን እስከ ጸጉር መሰንጠቅ ድረስ የዘለቀ ትኩረት ነበር በማድረግ የተጠመዱት፡፡ እያንዳንዷን ኩንታል የት ገባች በማለት እስከመቆጣጠር ድረስ ነበር፡፡ እሺ ይሁን፤ ያድርጉትም፤ ነገር ግን አሁን ለምንድን ነው እንደዛ የማያደርጉት፡፡ አሁንስ ህዝቡ ዘንድ ድጋፉ ስለመድረስ አለመድረሱ ምን ማረጋገጫ አለ፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኛም ጋብዞ ሄደው እንዲያዩት በማድረግ በኩል የበኩሉን ሲወጣ ነበር። ስለዚህም የምዕራባውያኑም ጋዜጠኞች ያለውን እውነታ ቆፍረው ማውጣት ነበረባቸው፡፡ ይህንን ባለመደረጋቸው እናዝናለን፡፡
የአሜሪካ መንግስት እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ የኢትዮጵያና የአሜሪካንን መንግስት የቆየ ግንኙነት የሚያላላና የሚያሻክር እንጂ የሚያዋድድ፣ የሚያጠናክር ብሎም ከበፊቱ የበለጠ ተጣጥሞ የሚሄድ ግንኙነት አለመሆኑን እያየን ነው፡፡ ይህ በመሆኑ ደግሞ እናዝናለን። ይሁንና ተስፋ ሳንቆርጥ በመስራት ላይ ነን፡፡
ለጊዜውም ቢሆን እዛ ያሉት የድሮው ስርዓት አቀንቃኞች ባላቸው ሀብትና ገንዘብ በብዙ መንገድ እየታገሉ ይገኛሉ። ይሁንና እኛ በርከት ያልን ኢትዮጵያ ውያን በመሆናችን እየታገልናቸው እንገኛለን። እኛ ጥረታችን ይህን የተሳሳተ የአሜሪካን ፖሊሲ እንዲታረም ነው፡፡
አዲስ ዘመን፡– የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳ ንት ዶናልድ ትራምፕ ስለህዳሴ ግድቡ በቅጡ ካለመረዳታቸው የተነሳ በአንድ ወቅት ግድቡን ግብጽ ታፈነደዋለች እስከማለት ደርሰው ነበር፤ የእርሳቸው አስተዳደር አብቅቶ የጆባይዳን አስተዳደር እንዲተካ በአሜሪካ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ጥረት አድርጋችኋል፤ ይሁንና ያንን ጥረታችሁን ከግምት ባለማስገባት በተመሳሳይ በኢትዮጵያ ላይ ጫና እያሳደሩ ይገኛሉ፡፡ ይህን ለማስተካከል እየጣራችሁ ያላችሁት በምን አግባብ ነው?
ፕሮፌሰር ብሩክ፡– ይህን ለማስተካከል እየተንቀሳቀስን ያለነው በተለያየ መንገድ ነው። አንደኛ የአሜሪካ ዜጋ በመሆናችን ድምጽ እንሰጣለን። እያንዳንዷ ድምጽ ደግሞ ዋጋ ታስከፍላለች፡፡ ስለዚህም ክብደት አላት፡፡ እኛ ባለፈውም እኤአ በ2016 ምርጫ ፕሬዚዳንት ትራምፕን አልመረጥናቸውም፡፡ ነገር ግን ቀኝ አክራሪ የሆኑት መርጠዋቸዋል፡፡
በመሆኑም እኛ አራት ዓመት ሙሉ የጠበቅነው በትዕግስት ነበር፡፡ እርሳቸው ደግመው እንዳይመረጡ ትልቅ እንቅስቃሴ አድርገን ባይደንና ዴሞክራቶች እንዲመረጡ ከፍተኛ ሚና ተጫውተናል፡፡ ሴኔት በተለይ 48 ለ50 ሆነው በጣም አጣብቂኝ ውስጥ በመግባት ልክ እንደማራቶን ሩጫ ማን ቀደመ፤ ማንስ ወደኋላ ቀረ የሚለውን መለየት እስከሚከብድ ድረስ እኔ የምኖረው ሰሜን ካሮላይና ነውና ጆርጂያ ካሉ ወገኖቼ ጋር በመሆን ዘመቻውን በመቀላቀል እሰራ ነበር፡፡
በተለየ ሁኔታ ሁለት ሴናተር የጆርጂያ ወንበሮች እንደሚታወቀው እያንዳንዱ ስቴት ሁለት ሁለት ሴናተር ነው በህገ መንግስት መሰረት የተቀመጠውና ሁለቱንም ልናሸነፍ ችለናል፡፡ ይህም ማለት ዴሞክራቶች እንዲያሸነፉ ረድተናል፡፡ 30 እና 40 ሺህ ድምጽ ሲታይ አነስተኛ ይመስላል፤ ነገር ግን ሚዛኑን መድፋት የሚያስችል ድምጽ ማስገኘት ተችሏል፡፡ በመሆኑም በኛ ድምጽ ዴሞክራቶች እንዲያሸንፉ ማድረግ ስለቻልን በዚህ ጉዳይ እነርሱም በጣም ደስተኞች ናቸው፡፡
ነገር ግን ፕሬዚዳንት ባይደን ጥር ላይ ስልጣን ከተረከቡ በኋላ ይዘዋቸው የመጡት የውጭ ግንኙነትና የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ሰዎች የቀድሞው ፕሬዚዳንት ኦባማ አስተዳደር ውስጥ የነበሩ፤ ያለፈው ስርዓት ወዳጅና የዚያም አቀንቃኝ የሆኑ 27 እና 30 ዓመት እንደ ጓደኛ አድርገው የሰሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ይህንንም ጠንቅቀን እናውቃለን። ለእነሱ ነው ስልጣን የሰጧቸው። ስልጣን እንዳገኙም የወጡት ፈረስ ላይ ነው፡፡ በቀጥታ ጸረ ኢትዮጵያ ፖሊሲ ማራመድ ነው የተያያዙት። በዚህ በጣም ነው ያዘነው፡፡ መቼም ሰውዬው አንዴ ተመርጠዋል፡፡ ወደኋላ መመለስ አይቻልም፡፡ስለዚህ አራት ዓመት መጠበቅ የግድ ይለናል፡፡
ነገር ግን የሚሰሩት ስራ የኢትዮጵያና የአሜሪካን ግንኙነት እንደሚጎዳ መረዳት አለባቸው፡፡ ኢትዮጵያ በሰላምና በጸጥታው በኩል ያላት ተሳትፎ ከፍተኛ ነው። የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ያለው ሰላም በማስጠበቁ በኩል ድርሻዋ ጉልህ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን አልሻባብንም ሆነ ሌላውን ሰላም አደፍራሽ ኃይል በመዋጋት ረገድ አስተዋጽኦችን በርካታ ነው፡፡ ሽብርተኛውን በመጋፈጥም ትልቅ ስራ የምንስራ ነን፡፡
ኢትዮጵያ ማለት ተራ የአፍሪካ አገር አይደለችም፤ እንዲህ ስል ግን ሌሎቹን የአፍሪካ አገራት በመናቅ ወይም ዝቅ በማድረግ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ከ115 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላት አገር ናት፡፡ አቀማመጣችንና የጂኦፖለቲካል አቅጣጫችን እንኳን የአፍሪካን ቀንድ ይቅርና እስከ ቀይ ባህር ጀርባ ብሎም እስከ የመን እና ኦማን ድረስ ተጽዕኖ መፍጠር የሚችልና ትልቅ ጫናን መፍጠር የሚችል ነው። ይህ ሆኖ አገራችን ቀውስ ውስጥ ከገባች ይህን ሁሉ ስጋት መውሰድ ስላለባቸው እኛ ትግላችንን እንቀጥላለን፡፡ከሰሞኑም የቲውተር ዘመቻችን ከቀናት በፊት እስከ 20ኛ ድረስ ሄዷል፡፡
አዲስ ዘመን፡– ከአሜሪካ ከተለያዩ ስቴቶች ተውጣጥታችሁ የመጣችሁ የሰላም ጓደኞች ወደኢትዮጵያ የመምጣታችሁ ዋና ዓላማ ምንድን ነው?
ፕሮፌሰር ብሩክ፡– እርግጥ ነው ከአሜሪካ ከተለያዩ ስቴቶችና ክልሎች ተሳባስበን የመጣን ነን። በተለያየ የሙያ ዘርፍ ላይ ያለን ሰዎችም ነን፡፡ በወቅቱ አሜሪካ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ስንሆን ወደአገር ቤት የመምጣችን አንዱ ዓላማ ከህዝባችን ጋር ለመገናኘት ነው፡፡ በተጨማሪም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ኢኮኖሚያዊም ሆነ ማህበራዊ እንቅስቃሴ ለማየትም ጭምር ሲሆን፣ በሰላም ዙሪያ እየተሰራ ያለውን መሰረታዊ የሆኑ ስራዎችንም ለመከታተል ጭምር ነው፡፡
በተጨማሪም በአገሪቱ በተፈጠረው ግጭት ሳቢያ በተለያዩ አካባቢዎች ያሉትን ተፈናቃይ ወገኖቻችንን በአካል ወደእነርሱ በመሄድ አይዟችሁ፤ አለን ልንላቸው ስለወደድንም ጭምር ነው፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን በውጭ አገር የምንኖር ብንሆንም እንደማንረሳቸው ለመግለጽና የነበረንንም ቃል ኪዳን ለማደስም ጭምር ነው የመምጣታችን ምስጢር፡፡
ከዚህ ሌላ በባህላችን ወደአንዱ ቤት ሲኬድ ባዶ እጅ አይኬድምና አቅማችን በሚፈቅደው ልክ ሁላችንም ለፍቶ አዳሪዎች እንደመሆናችን ከምናገኘው ገንዘብ ቆጠብንና እርዳታም አሰባስበን የተለያዩ ቁሶችን ይዘን መጥተናል። እዚህ ከመጣን በኋላም ብርድ ልብሶችን ገዝተን እዛ ድረስ ሄደን አስረክበናል፡፡ እንዲሁም የሴቶች ንጽህና መጠበቂያም በርከት አድርገን በማምጣትን ለተፈናቃይ እህቶቻችን አስረክበናል፡፡
አዲስ ዘመን፡– ከሰሞኑን ወደትግራይ ህዝብ መድረስ የሚገባው እህል የጫነ በርካታ ተሽከርካሪ አፋር አካባቢ በጁንታው አላሳልፍም ባይነት መቆሙ ይታወቃል፤ ይሁንና ይህ አግባብነት የሌለው አካሄድ ነው በሚል አንድም የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ነኝ የሚል አካል ምንም አለማለቱን እንዴት ያዩታል?
ፕሮፌሰር ብሩክ፡– ይህ ጉዳይ እኛን በጣም ያሳዘነን ነው፡፡ በተለይ ያዘንበት ነገር አንደኛ በተለያዩ ምክንያቶች ከአገራችን ወጥተን አሜሪካንን ሁለተኛ አገራችን አድርገን የምንኖር ኢትዮጵያውያን ነን፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እኛ ለአሜሪካን መንግስት ታክስ ከፋዮች ነን፡፡ በመሆኑም በአሜሪካ ምርጫ ሂደት ውስጥም እንሳተፋለን፡፡ በአገራችን ጉዳይ ደግሞ እንደ ዲያስፖራ ህብረት ፈጥረን ሁሌ እንገናኛለን፡፡
ያነሳሽው ጉዳይ ልብ ሰባሪ ነገር ሆኖ ነው ያገኘሁት። ምክንያቱም መንግስት ወርቃማ የሆኑ እድሎችን ሰጥቶ ከዚያ ሲያልፍ ደግሞ ወደ አላስፈላጊ ጦርነት ተገብቶ ህዝቡ ሲቸገር ደግሞ እህሉን ሳያቋርጥ መንግስት አቅርቦ እያለ፤ ከተለያየ ቦታ የተገኘውን ድጋፍ ደግሞ አላሳልፍ ማለቱ አሳዛኝ ጉዳይ ነው፡፡ የቀረበው እህል ወደስፍራው አለመድረሱ እየታወቀ እንኳ ለህዝብ መድረስ አለመድረሱ ላይ እንቅስቃሴ አለመደረጉ በጣም ያሳዝናል፡፡
አንድም ምዕራባውያን ሚዲያዎችም ሆኑ የተባበሩት መንግስታት ሰዎች በቅጡና ኃላፊነት በተሞላበት አካሄድ አለመጠየቃቸው አስገራሚ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ ይህ አመጸኛው ቡድን እህሉ እዛ ድረስ ቀርቦለት በምን ሁኔታ አስልቶ እንዳያልፍ ማድረጉ ግልጽ አይደለም፡፡ ለራሱ ብቻ ነው ወይስ ለተራቡ ወንድምና እህት ለሆነው ለትግራይ ወገኖቻችን ነው ይህን የሚያደርገው የሚል ጥያቄ እንድንጠይቅ የሚያደርግ ነው፡፡ እኛ ለትግራይ ህዝብ እናዝናለን፡፡ ምክንያቱም የዚህ ግጭት ገፈት ቀማሹ እሱ ነውና፡፡ ስለዚህም በዚህ መልክ ግልጽ የሆነ ሪፖርት አለማድረጋቸው አሳዝኖናል፤ እንዲሁም እኛንም ሆነ ሌሎችንም ጥርጣሬ ውስጥ አስገብቶናል፡፡
በአብዛኛው ያኔ የሚወራው ከጥቅምት 24 በኋላ ትኩረት ያደረጉት መንግስት ላይ ነበር፡፡ ይህን ሲያደርጉ የነበረው እውነታው ተይዞ ሳይሆን እስከ ጸጉር መሰንጠቅ ድረስ የዘለቀ ትኩረት ነበር በማድረግ የተጠመዱት፡፡ እያንዳንዷን ኩንታል የት ገባች በማለት እስከመቆጣጠር ድረስ ነበር፡፡ እሺ ይሁን፤ ያድርጉትም፤ ነገር ግን አሁን ለምንድን ነው እንደዛ የማያደርጉት፡፡ አሁንስ ህዝቡ ዘንድ ድጋፉ ስለመድረስ አለመድረሱ ምን ማረጋገጫ አለ፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኛም ጋብዞ ሄደው እንዲያዩት በማድረግ በኩል የበኩሉን ሲወጣ ነበር። ስለዚህም የምዕራባውያኑም ጋዜጠኞች ያለውን እውነታ ቆፍረው ማውጣት ነበረባቸው፡፡ ይህንን ባለመደረጋቸው እናዝናለን፡፡
የአሜሪካ መንግስት እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ የኢትዮጵያና የአሜሪካንን መንግስት የቆየ ግንኙነት የሚያላላና የሚያሻክር እንጂ የሚያዋድድ፣ የሚያጠናክር ብሎም ከበፊቱ የበለጠ ተጣጥሞ የሚሄድ ግንኙነት አለመሆኑን እያየን ነው፡፡ ይህ በመሆኑ ደግሞ እናዝናለን። ይሁንና ተስፋ ሳንቆርጥ በመስራት ላይ ነን፡፡
ለጊዜውም ቢሆን እዛ ያሉት የድሮው ስርዓት አቀንቃኞች ባላቸው ሀብትና ገንዘብ በብዙ መንገድ እየታገሉ ይገኛሉ። ይሁንና እኛ በርከት ያልን ኢትዮጵያ ውያን በመሆናችን እየታገልናቸው እንገኛለን። እኛ ጥረታችን ይህን የተሳሳተ የአሜሪካን ፖሊሲ እንዲታረም ነው፡፡
አዲስ ዘመን፡– የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስለህዳሴ ግድቡ በቅጡ ካለመረዳታቸው የተነሳ በአንድ ወቅት ግድቡን ግብጽ ታፈነደዋለች እስከማለት ደርሰው ነበር፤ የእርሳቸው አስተዳደር አብቅቶ የጆባይዳን አስተዳደር እንዲተካ በአሜሪካ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ጥረት አድርጋችኋል፤ ይሁንና ያንን ጥረታችሁን ከግምት ባለማስገባት በተመሳሳይ በኢትዮጵያ ላይ ጫና እያሳደሩ ይገኛሉ፡፡ ይህን ለማስተካከል እየጣራችሁ ያላችሁት በምን አግባብ ነው?
ፕሮፌሰር ብሩክ፡– ይህን ለማስተካከል እየተንቀሳቀስን ያለነው በተለያየ መንገድ ነው። አንደኛ የአሜሪካ ዜጋ በመሆናችን ድምጽ እንሰጣለን። እያንዳንዷ ድምጽ ደግሞ ዋጋ ታስከፍላለች፡፡ ስለዚህም ክብደት አላት፡፡ እኛ ባለፈውም እኤአ በ2016 ምርጫ ፕሬዚዳንት ትራምፕን አልመረጥናቸውም፡፡ ነገር ግን ቀኝ አክራሪ የሆኑት መርጠዋቸዋል፡፡
በመሆኑም እኛ አራት ዓመት ሙሉ የጠበቅነው በትዕግስት ነበር፡፡ እርሳቸው ደግመው እንዳይመረጡ ትልቅ እንቅስቃሴ አድርገን ባይደንና ዴሞክራቶች እንዲመረጡ ከፍተኛ ሚና ተጫውተናል፡፡ ሴኔት በተለይ 48 ለ50 ሆነው በጣም አጣብቂኝ ውስጥ በመግባት ልክ እንደማራቶን ሩጫ ማን ቀደመ፤ ማንስ ወደኋላ ቀረ የሚለውን መለየት እስከሚከብድ ድረስ እኔ የምኖረው ሰሜን ካሮላይና ነውና ጆርጂያ ካሉ ወገኖቼ ጋር በመሆን ዘመቻውን በመቀላቀል እሰራ ነበር፡፡
በተለየ ሁኔታ ሁለት ሴናተር የጆርጂያ ወንበሮች እንደሚታወቀው እያንዳንዱ ስቴት ሁለት ሁለት ሴናተር ነው በህገ መንግስት መሰረት የተቀመጠውና ሁለቱንም ልናሸነፍ ችለናል፡፡ ይህም ማለት ዴሞክራቶች እንዲያሸነፉ ረድተናል፡፡ 30 እና 40 ሺህ ድምጽ ሲታይ አነስተኛ ይመስላል፤ ነገር ግን ሚዛኑን መድፋት የሚያስችል ድምጽ ማስገኘት ተችሏል፡፡ በመሆኑም በኛ ድምጽ ዴሞክራቶች እንዲያሸንፉ ማድረግ ስለቻልን በዚህ ጉዳይ እነርሱም በጣም ደስተኞች ናቸው፡፡
ነገር ግን ፕሬዚዳንት ባይደን ጥር ላይ ስልጣን ከተረከቡ በኋላ ይዘዋቸው የመጡት የውጭ ግንኙነትና የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ሰዎች የቀድሞው ፕሬዚዳንት ኦባማ አስተዳደር ውስጥ የነበሩ፤ ያለፈው ስርዓት ወዳጅና የዚያም አቀንቃኝ የሆኑ 27 እና 30 ዓመት እንደ ጓደኛ አድርገው የሰሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ይህንንም ጠንቅቀን እናውቃለን። ለእነሱ ነው ስልጣን የሰጧቸው። ስልጣን እንዳገኙም የወጡት ፈረስ ላይ ነው፡፡ በቀጥታ ጸረ ኢትዮጵያ ፖሊሲ ማራመድ ነው የተያያዙት። በዚህ በጣም ነው ያዘነው፡፡ መቼም ሰውዬው አንዴ ተመርጠዋል፡፡ ወደኋላ መመለስ አይቻልም፡፡ስለዚህ አራት ዓመት መጠበቅ የግድ ይለናል፡፡
ነገር ግን የሚሰሩት ስራ የኢትዮጵያና የአሜሪካን ግንኙነት እንደሚጎዳ መረዳት አለባቸው፡፡ ኢትዮጵያ በሰላምና በጸጥታው በኩል ያላት ተሳትፎ ከፍተኛ ነው። የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ያለው ሰላም በማስጠበቁ በኩል ድርሻዋ ጉልህ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን አልሻባብንም ሆነ ሌላውን ሰላም አደፍራሽ ኃይል በመዋጋት ረገድ አስተዋጽኦችን በርካታ ነው፡፡ ሽብርተኛውን በመጋፈጥም ትልቅ ስራ የምንስራ ነን፡፡
ኢትዮጵያ ማለት ተራ የአፍሪካ አገር አይደለችም፤ እንዲህ ስል ግን ሌሎቹን የአፍሪካ አገራት በመናቅ ወይም ዝቅ በማድረግ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ከ115 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላት አገር ናት፡፡ አቀማመጣችንና የጂኦፖለቲካል አቅጣጫችን እንኳን የአፍሪካን ቀንድ ይቅርና እስከ ቀይ ባህር ጀርባ ብሎም እስከ የመን እና ኦማን ድረስ ተጽዕኖ መፍጠር የሚችልና ትልቅ ጫናን መፍጠር የሚችል ነው። ይህ ሆኖ አገራችን ቀውስ ውስጥ ከገባች ይህን ሁሉ ስጋት መውሰድ ስላለባቸው እኛ ትግላችንን እንቀጥላለን፡፡ከሰሞኑም የቲውተር ዘመቻችን ከቀናት በፊት እስከ 20ኛ ድረስ ሄዷል፡፡
እያዳንዱን የኮንግረንሱን አባልና ሴናተሮችንም በተከታታይ በስልክ እናገኛለን፡፡ ኢ-ሜይል በመላክም እንከታተላለን፡፡ ሁላችን በየስቴቱ ቅንጅት ፈጥረን የእያንዳንዳችንን ተወካይ ምክር ቤት አባላችንን (ሴናተሩ በስቴት ደረጃ ነው፡፡ የምክር ቤት አባል ደግሞ 900 ሺህ የሚሆን የአሜሪካ ህዝብ በአንድ ምርጫ አውራጃ ይዋቀራል።) ሁላችንም ጠንክረን ይዘን በመከራከር ላይ ነን።
ይህ መልዕክቱ ምንድን ነው ብትይኝ ባይደን የውጭ ጉዳይ ሰዎችን ሲሆን ሲሆን እንዲያነሳቸው፤ አለበለዚያ ግን አደብ እንዲገዙ ወይም ደግሞ ከተሳሳተው መንገድ እንዲመለሱ፤ ኢትዮጵያ ላይ ትልቅ ጫና እያሳደራችሁ ነው፤ ኢትዮጵያን አትግፉ፤ እያደረጋችሁ ያለው ትክክል አይደለም፡፡ የተጠቃው የኢትዮጵያ ህዝብ ነው፡፡ ህገ ወጥ በሆነ መንገድ ስልጣን ላይ መመለስ የሚፈልግ አካል አለ፡፡ በህዝባችን ላይ ጦርነት ያወጀ አካል አለ። ከዚህ አካል ጋር በመሄድ የኢትዮጵያውያኑን ግንኙነት የሚጎዳ እንዲሁም በጎ ነገር የማያመጣ እንደሆነ ነው የምንነግራቸው፡፡ ይህንኑ እንድትረዱ እና ትክክለኛውን መንግስት እንዲያውቁት ነው ግፊት የምናደርገው፡፡
አዲስ ዘመን፡– የአሜሪካ መንግስት ይህን ያህል በኢትዮጵያ ላይ እንዲህ ያመረረበት ምክንያት ምን ይሆን?
ፕሮፌሰር ብሩክ፡– በቀላሉ ለመመለስ ታዛዥ መንግስት በመፈለጋቸው ነው፡፡ እዚህ ላይ ማስመር የምፈልገው ይህ ሁኔታቸው የተኮላሸና ኩራት የሌለው፣ በነጻነቱ የማይመካና ጠንካራ መንግስት በኢትዮጵያ እንዲኖር አይፈልጉም ወደማለቱ ያደርሳል፡፡ ባለፈው 27 ዓመት ውስጥ የነበረው መንግስት በደንብ ይታዘዝ ነበር፡፡
በአሁን ወቅት ባለው በኢትዮጵያ መንግስት ታዛዥነት ላይ ትልቅ ጥርጣሬ አላቸው፡፡ አሁን ኢትየጵያ ውስጥ ያለው መንግስት ሁሉን አገር በእኩል አይን የሚያይ፤ አሜሪካ አሜሪካ ስለሆነች ለየት ባለ ሁኔታ የማያደገድግ፤ የራሱ የሆነ ኩራት ያለው፤ አብሬ ከአሜሪካ ጋር እሰራለሁ የሚል፤ ግልጽ የሆነ አቋም ያለው ነው፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያን ጥቅምና ክብር የሚነካ ነገር ሲመጣ የኢትዮጵያ መንግስት ላስብበት ማለት ጀምሯልና ይህ ነው ያልተመቻቸው። ይህ ሁኔታ እነርሱን ቅር ያሰኘና ያላስደሰታቸው አካሄድ ሆኖ አግኝተውታል። ሲጠሩት ‹አቤት› የሚል መንግስትን ነው ማየት የሚፈልጉት፡፡ ፍላጎታቸውን የሚያሳካ አካል ባለመኖሩ ነው ይህ ሁሉ ጫና እየደረሰ ያለው፡፡ ነገር ግን እኛ አሜሪካ ውስጥ ያለነው አሜሪካውያን ኢትዮጵያውያን የአሜሪካንን መንግስት እንደምናከብር ሁሉ እነርሱም የእኛ ህዝብ ማክበር ይጠበቅባቸዋል ባዮች ነን፡፡
አዲስ ዘመን፡– በቅርቡ እርስዎም እንደሚያውቁት የኢትዮጵያ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ በአሜሪካ የጸጥታው ምክር ቤት ተገኝተው በግብጽ ከሳሽነት ለቀረበው ጥያቄ ማብራሪያ በመስጠታቸው የሕዳሴ ግድቡ ጉዳይ ወደአፍሪካ ህብረት እንዲመለስ ተደርጓል፤ ኢትዮጵያ ነጥብ ባለመጣሏ ግን ብዙዎቹ ስለምን በዛ ልክ ተንጫጩ ይላሉ?
ፕሮፌሰር ብሩክ፡– ያነሳሽው የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ኢትዮጵያን አጀንዳ በማድረግ ግብጾች ከሰውና የአረቡን አገር አስተባብረው ነበር የመጡት፡፡ ይሁንና የቱንም ያህል ደባ ቢኖር በጸጥታው ምክር ቤት ባቀረብነው ማብራሪያ አሸናፊ ሆነን ልንወጣው ችለናል፡፡ እኛ ይህን ተፈጥሮን የሰጠን እግዚአብሄር ነው፡፡ የአባይ ወንዝን በተፈጥሮ ብንቸረውም ቀደም ሲል ለአንድ ሰከንድ እንኳ ስለሱ እንዳናስብም ብሎም እንዳንጠቀምበት ተደርገናል፡፡ ዜሮ በመቶ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ እንደ ግብጽ አይነት አገሮች ወንዙን በትዕቢት ተነሳስተው የእኛ ነው የሚሉበት እና አንድ ነገር ታደርጉና ዋ! እየተባልን እየተፎከረብን የኖርን ነን፡፡ የአሁን መንግስት ስራውን ይጀምረው እንጂ ባለፉት መንግስታት ዘንድ ሐሳቡም ሆነ ፕላኑ መኖሩ የሚታወቅ ነው፡፡ ነገር ግን በአጼ ኃይለ ሥላሴም ሆነ በደርግ ፍላጎቱ ቢኖርም የአቅም ጉዳይ በመሆኑ መላወስ አልተቻለም ነበር፡፡
ባለፈው መንግስት የተጀመረው የህዳሴ ግድብ አሁን ላይ በመቋጨት ላይ ይገኛል፡፡ ይበልጥ ወደማጠናቀቂያው በተቃረብን ቁጥር ደግሞ ተቃው ሞውም የዚያን ያህል እየበረታ ነው፡፡ በመሆኑም ግብጾች ጉዳዩን ወደአሜሪካ፣ ወደተባበሩት መንግስታት፣ ወደአውሮፓውያን ብሎም ወደአረብ ሊግ ለመውሰድ ሙከራ ቢያደርጉም ሩጫቸው ከሽፏል፡፡ ጉዳዩ አፍሪካዊ ይዘትና አፍሪካዊ ጉዳይ ያለው ስለሆነ በአፍሪካ ህብረት ብቻ እንዲቋጭ በሚል ነው ስብሰባው የተደመደመውና ይህ ለእኛ ትልቅ ድል ነው፡፡
በጸጥታው ምክር ቤት በአባልነት ካሉት አገራት መካከል ከእኛ ጋር የቆሙ ለምሳሌ ቻይና፣ ራሽያና ሌሎችም አሉ፡፡ ስለዚህም የተጠነሰሰብን ደባ ከሽፏል። ግብጾች የተማመኑት የምዕራቡን ዓለም በተለይ እንግሊዝን እና አሜሪካንን ይዘን ኢትዮጵያ ላይ ጫና በመፍጠር ስራዋን ማስተጓጎል ብቻ ሳይሆን እንዲቆምና በውሃው ላይ ድርድር እንዲጀመር እናደርጋለን በሚል ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ ሐሳባቸው ውሃ የሚቋጥር ካለመሆኑም በተጨማሪ ተቀባይነት ያለው አይደለም፡፡
እኤአ በ2015 የመርህ ስምምነት የሚለው ሰነድ በሱዳን የተፈራረምነው አለ፤ እኛ ውሃውን እየሞላን ያለነው በዛ ስምምነት መሰረተ ነው፡፡ በዚህ መሰረት ኢትዮጵያ የዓለም ህግ የሚጠይቀውን በሙሉ ያሟላች ናት፡፡ አስቀድሞ በማሳወቅ ቢባል፤ ያጠናቻቸውን ጥናቶች ለሁለቱ አገራትም ሆነ ለታዛቢዎች በማቅረብ በኩል ቢባል በግልጽ ስታሳይ ቆይታለች፡፡ በዚያም መሰረት ነው ሁለተኛውን ዙር ውሃ መሙላቷን አሳውቃ ያጠናቀቀችው፡፡ በዚህ ሁሉ መሃል ደግሞ የኢትዮጵያ አምላክ አልተለየንም፡፡ በዚህም ወደጸጥታው ምክር ቤት ሄዶ የነበረውም ክስ ከሽፏል፤ ብዙዎቹ የአፍሪካ አገሮችም ከእኛ ጋር በመሆን ላይ ናቸው። እኛ የአባይን ውሃ ያውም ኃይል አመንጭተን የምንለቀው እንጂ በእሱ የምንጠቀመው መስኖ እንኳ የለንም። ግብጾች ወዲህ ወዲያ ብለው ፎክረው ቢደክማቸውም እኛ ዛሬም ቢሆን የሰውን አገር መብት አልነካንም፤ በቀጣይም እናከብራለን፡፡ በነጻነታችን የሚመጣን አገር ግን አንቀበልም።
አዲስ ዘመን፡– ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ባለው ሁኔታ ግጭቱ አይሏል፤ ይህ ጉዳይ እንዲረግብ በቀጣይ ኢትዮጵያውያኑም ሆኑ ዲያስፖራው ምን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ይላሉ?
ፕሮፌሰር ብሩክ፡– እንዳልሽው የእርስ በእርሱ ጦርነት ብቻ ሳይሆን የውጭ ጠላቶች ሁሉ ኢትዮጵያ ላይ ተነስተውባታል፡፡ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድባችንም ተግባራዊ እንዳይሆን ሌት ተቀን የሚጥሩ አሉ፡፡ የእኛም ውስጣዊ ጠላቶች ከግብጽ ጋር የማበር ሁኔታ አለ። ተቃዋሚ ድርጅችን መሳሪያ በመስጠት የማስታጠቅና ገንዘብ የመስጠት ሁኔታም አለ፡፡ በሚዲያም በኩል ፕሮፖጋንዳውን የበለጠ በማስፋፋት ሽፋን የሚሰጥም አለ።
ስለዚህ ከዲያስፖራው ምን ይጠበቃል ለሚለው የመጀመሪያው ህብረት በመፍጠር አንድ መሆን፤ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ አለማመቻመች፤ እኛ አሜሪካ አገር ያለነው ኢትዮጵያዊያን ኢትዮጵያዊነታችንን ሁሌም በልባችን ላይ አንጠልጥለን ነው የምንኖረው፡፡ ስለዚሀ ህብረታችንን አጠናክረን ለኢትዮጵያ ጠበቃና አምባሳደር ሆነን በሁሉም መድረክ ሚዲያን ጨምሮ በኢትዮጵያ ላይ የሚነዛውን የተሳሳተ መረጃ እንዲስተካከል ጥረት እናደርጋለን፡፡ ህዝባችንን በተጣመመ ፖሊሲ እንዳይጎዳ ማድረግ፤ ለአረቡ ዓለም የህዳሴ ግድብ ጎጂ አለመሆኑን ማስረዳት ይበልጥ ይጠበቅብናል፡፡ ከግብጾች ጋር ያለውን ሁኔታ ስናስተውል ግብጾች የምትከራከርላቸው አሜሪካ አለችላቸው፡፡ ከእነርሱ ጋር ትግል ገጥመናል፡፡
አረብኛ ቋንቋ አለመማራችን ይጎዳን ነበር፡፡ እኔ ራሴ ጋዜጠኝነትንም ስለማስተምር ከፖለቲካል ሳይንስ ባሻገር በፕሮፌሰርነቴም የማስተምረው የጋዜጠኝነቱን ትምህርት ስለሆነ ሁሌም አዝንበትና ሐሳብም ስሰጥበት የነበረው ነገር የአረብኛ ክፍለ ትምህርት ማቋቋም እንዳለብንና አረብኛ የሚናገሩ ኢትዮጵያውያንን አሰባስበን ስለእውነታው ለመግለጽ ነው የምንሰራው። ግብጻውያን በጣም በርካታ ሚዲያ አላቸው፡፡ መካከለኛው ምስራቅ አለ፤ እስከ ኒውርክና ለንደን ድረስ ደግሞ ውጭ አገር ያሉ አረቦች የሚጠቀሙ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ፕሮግራም አለና እሱ ላይ መጋደል አለብን፡፡
ሌላው ይቅርና እናንተና እናንተን የመሰሉ ሚዲያዎች የምትዘግቡት ስራ እየተተረጎመ ቶሎ ባስቸኳይ በአረብ ኛውም እንዲቀርብ በማድረግ መታገል አለብን፡፡ ቋንቋን የሚችሉ ወገኖቻችን ቅን የሆኑና ኢትዮጵያን የሚያስቀድሙ እንዲሁም የሚወዱ ልክ እንደ መሃመድ አላሩሲ አይነቶች 30 እና 40 ሆነው የኢትዮጵየያን ጉዳይ ገትረው ይዘው እንዲሟገቱ ነው እቅዳችን፡፡
በተለይ የግብጽ ህዝብ ልክ ኢትዮጵያ እንደም ታጠፋቸው ጠላት ተደርጎ የተነገራቸውን የሀሰት ትርክት በእውነት በመግለጽ ሐቁን በማድረስ ስራ መስራት ጫናውንም ያሳንሰዋል፤ እንዲሁም ደግሞ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱም ይዳብራል። ኢትዮጵያውያኑም መልማት አለባቸው፤ ውሃውም ይበቃናል እንዲሉ እና የእኛን የኢትዮጵያውያንን መብት እንዲያከብሩ ነው መስራት የሚጠበቅብን፡፡ ለዚህ ደግሞ በሁሉም የዓለም ክፍል ያለው ዲያስፖራ ህብረት ፈጥረን መንግስትንና ህዝባችንን ማገዝ አለብን፡፡
አዲስ ዘመን፡– በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ከድህነት በመውጣት ወደብልጽግና ለመንደርደር በምታደርገው የመጀመሪያው ጉዞ ሌሎች አገሮች ተጽዕኖ እያሳደሩባት ነው፤ ባስ እያለ የመጣው ደግሞ እውነታው መሬት ላይ እያለ የሚያወሩት ሌላ ነውና ለምዕራባውያኑ የሚያስተላልፉት መልዕክት ምንድን ነው?
ፐሮፌሰር ብሩክ፡– ለምዕራቡ ዓለም የማስተላ ልፈው መልዕክት ኢትዮጵያን በቅጡ ቢያውቋት ጥሩ ነው። እኛ የሚያውቋት መስሎን ነበር። ይህቺ ቅኝ ተገዢነትን የተዋጋች፣ ምዕራብ አገሮችን ያሸነፈች፣ ነጻነቷን አክብራ ለሺህ ዓመታት የኖረችን አገር በቅጡ ሊያውቋት ያስፈልጋል። ኢትዮጵያዊ ነጻነቱን የሚወድና ፈሪሃ እግዚአብሔር ያለው ነው፡፡ በአስተያየቱም ሚዛናዊ ነው፡፡ ስለዚህ እኛ እንድምናከብራቸው እኛንም ማክበር አለባቸው። ምዕራባውያኑ እኛን በገፉ ቁጥር እንደብረት የምንጠነክር ህዝቦች መሆናችንን ሊረዱ ይገባል፡፡ ኢትዮጵያን ገፍቶ ያሸነፋት አካል እንደሌለ ምዕራባውያኑ ቢያውቁ መልካም ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮጵያን ማጣት ምን እንደሆነ መረዳት መቻል አለባቸው፡፡ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ሰላምን በማምጣት ሚናዋ የጎላ አገር ስለመሆኗ ሊዘነጉት አይገባም፡፡ በምስራቅ አፍሪካ አካባቢ እየከፈለች ያለውን መስዋዕትነትና ለወደፊቱም ቢሆን የእርሷ ጣልቃ ገብነት ወሳኝ እንደሆነ ሊያስታውሱት ይገባል፡፡ ለአካባቢው መረጋጋት አስተዋጽኦዋ ላቅ ያለ በመሆኑ እኛን ማጣት እንደሚጎዳ ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ ኢትዮጵያን መንካት ማለት የራሳቸውን ጥቅም እንደማሳጣትና የራሳቸውን አፍንጫ እንደመቁረጥ ነው፡፡ እኛን የቱንም ያህል ቢገፉን አንድ አንበረከክም፤ ሁለትም አያሳካላቸውም። ስለዚህ ከእኛ ጋር ተከባብረው እና አክብረውን መራመድ ለእነሱም ለእኛም የሚበጅ ነው፡፡ በአሮጌ ስርዓት ለመሄድ ባይሞክሩ መልካም ነው፡፡ ያ አሮጌ ስርዓት ላይመለስ አልፏል። የኢትዮጵያን ወድቀት የሚመኙ አካላት አሁን ያለው መንግስት እንደሻማ ቀልጦ የሚያልቅና በነኩት ጊዜ የሚፈርስ መስሏቸው ከሆነ ተሳስተዋል፡፡
አዲስ ዘመን፡– ለአሸባሪው ህወሓት የሚያስተ ላልፉት መልዕክት ይኖርዎት ይሆን?
ፕሮፌሰር ብሩክ፡– ለእነሱ ያለኝ መልዕክት መንገዳችሁን ስታችኋል የሚል ነው፡፡ ከመጀመሪያም ጀምሮ የመጡበት ዓላማ አገራችንን ጦስ ውስጥ ከቷታልና ቆም ብለው ቢያስቡበት እላለሁ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ለሁሉም ጊዜ እንዳለው መዘንጋት የለባቸውም፤ በኢትዮጵያ ውስጥ አመራር በመሆን የ27 ዓመታት ወርቃማ ጊዜን አልተጠቀሙበትም፡፡ ዴሞክራሲውን በሰፊው አልሄዱበትም፡፡ በኢኮኖሚያዊ ሁኔታም ሲስተዋል እነርሱ ወደዘረፋና መሰል ጉዳዮች በመግባታቸው ህዝቡን አሳዝነውታል፡፡ ህዝቡን መዝብረውታል። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያውያኑን በእጅጉ ያሳዘነው ጉዳይ ሆኗል። የኢትዮጵያ ህዝብ ጥሩ ግንዛቤ አለው፡፡ 27 ዓመታት ቆይተው ምን እንደሰሩ እና በቆይታቸው ውስጥ ድክመታቸው ምን እንደሆነ በአግባቡ ተረድተዋል፡፡
አሁን ደግሞ በአዲስ ጉልበት አዲስ አበባ እንገባለን እያሉ ነው፡፡ የትግራይ አርሶ አደር ልጆች በጦርነቱ ይማገዳሉ። የእነርሱ ልጆች ደግሞ በአሜሪካ ቤት ገዝተውላቸውና አንደላቀዋቸው በማስተማር ላይ እንደሆኑ የምናስተውለው ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የግፍ ግፍ ነው እላለሁ፡፡ እስኪ እውነት እንነጋገር ከተባለ የሚያደርጉት ሩጫ ለህዝብ ከሆነ በሩጫቸው ለማሳተፍ የራሳቸውን ልጆች ከበለጸጉ አገሮች አምጥተው የትግራይ ድሃው ህዝብ እየማገዱበት ወደላው ጦርነት ያስገቧቸው፡፡
ለዚህ ለተሳሳተ ፖለቲካ አካሄዳቸው ግን የሚማግዱት የደሃውን ህዝብ ልጅና ራሱን ደሃውን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሆነ ያለፈውን ጊዜ ከደርግ አይብስም በሚል አልተሞከሩምና መከላከል ባለመቻሉ አሁን ግን እሱ እድል ዳግም አይመጣም፡፡ ዜሮ ነው፡፡ ተዋውቀናል፤ ህዝቡም አሳምሮ አውቋቸዋል፡፡ ስለዚህም የትግራይን ድሃውን ህዝብ ባያስጎዱት መልካም ነው፡፡
ያም የተሰጣቸው የይቅርታም የጥሞናም ጊዜ አልፎ በሽብርተኝነት በመፈረጃቸው ተጠያቂ የሚሆኑበት ጊዜ ነው እየመጣ ያለው፤ የመነጋገሪያውና የመወያያ ጊዜው ያለፈም ይመስለኛል፡፡ እያደረጉ ያለው ጥፋትም ይህ ነው የማይባል ነውና ነገ ዋጋ የሚያስከፍላቸው ነው፡፡ እኛም በጥንቃቄ የትግራይ ህዝብና አሸባሪውን የህወሓት ድርጅት እየለየን የህዝቡን ህሊና እንዳንጎዳ መጠንቀቅ አለብን፡፡
አዲስ ዘመን፡– ለሰጡኝ ማብራሪያ ከልብ አመሰግናለሁ።
ፕሮፌሰር ብሩክ፡- እኔም ስለተሰጠኝ እድል አመሰግናለሁ፡፡
አስቴር ኤልያስ
አዲስ ዘመን ሐምሌ 23/2013