ተመስገን! በሚያዝያ ወር እና በሰኔ ወር መሃል የሚገኝ ከአስራ ሦስቱ ኢትዮጵያ የወራት አቆጣጠር ውስጥ ዘጠነኛው ወርሀ ግንቦት ላይ ደርሰናልየዛሬ ዓመት በዚህ ወቅት የነበረውን ጭንቀት መቼም አልረሳውምእንኳንስ ዓመት አስቆጥሬ ለዛሬ ልደርስ ይቅርና ውዬ ስለማደሬ አሊያም አድሬ ስለመዋሌ እጅጉን እጠራጠር ነበር እርግጠኛ ሆኜ መናገር የምችለው ይህ የሁሉም ሰው ስሜት ነበርምክንያቱ ደግሞ ሁሉንም በአንድ ቋንቋ ማናገር የቻለው ኮሮና ነው፡፡
የዛኔ የነበረው ጭንቀትና ጥንቃቄ እስከዛሬ ቢቀጥል ዛሬ የሚሞተውን ሰው ቁጥር መቀነስ በቻልን ነበርዳሩ ምን ዋጋ አለው ያ ሁሉ ጭንቀት ከወራት በኋላ ነው ብን ብሎ የጠፋውዛሬ ማስክ ማድረጉ ለህግ ተገዥ መሆንን ለማሳየት እንጂ መቼ በሽታውን ለመካለከል ሆነ፤ ለማንኛውም አንዳንዶቻችን ኮሮናን አምልጠን እነሆ ታላቁ ግንቦት ወር ላይ ደርሰናልወርሀ ግንቦት ከስያሜው ጀምሮ አስደናቂ ነውመረጃዎች አንደሚያሳዩት፤ “ግንቦት” ከግዕዙ “ግንባት” ከሚለው ቃል የተባዛ ነው። የግንቦት ወር የክረምት ጎረቤት ቢሆንም ሞቃታማ፣ ደረቃማ እና ዝንብ የሚበዛበት ወር ነው። በዚህም ጸባዩ ብዙ ምሳሌያዊ አነጋገሮችን አፍርቷል።
አባቶች “በግንቦት አንድ ዋንጫ ወተት” ይላሉ። አቶ ካሕሣይ ገብረ እግዚአብሔር፣ ”ኅብረ ብዕር” በተባለው መጽሐፋቸው፣ ብሂሉ ሰውነታችን ኃይለኛውን የግንቦት ሙቀት መቋቋም ይችል ዘንድ አንጀት የሚያርስ፣ ቆዳን የሚያለሰልስ፣ የጠፋ አቅምን የሚመልስ ወተት ማግኘት አለበት ለማለት ነው፤ ይላሉ፡፡ሌላም ብሂል አለ። “በ ነሐሴ ባቄላ፣ በግንቦት አተላ” የሚለውም ሰው ብቻ ሳይሆን ከብቶችም በደረቃማው ገጽታ ምክንያት በግንቦት ወር ምን ያህል እንደሚጐዱ ያሳያል። በመሆኑም በወሩ አተላ እንደሚወደድ አመልካች ነው።
እግረ መንገዴን ብዬ ( እግረ መንገድ ለጽሑፍ እጂ መንገድ ይባል ይሆን?) እንጂ በጽሑፌ ግንቦትን ለመዘከር አይደለምይልቁንም በወርሀ ግንቦት ካሉት ክዋኔዎች ስለ አንዱ ለማውጋት ነውያው ነገርን ነገር ያነሳው የለወርሀ ግንቦት ልክ እንደ ጥርና ሚያዝያ ድግስ የሚበዛበት ወር ነውየልጃችሁን ለልጃችን ሽምግልናው፣ ሠርጉ፣ መልሱ፣ ቅልቅሉ፣ አክፋዩ፣ ግንቦት ልደታ… እያለን መጥቀስ ይቻላልባለፈው ዓመት ይህ ሁሉ ሁነት በቀድሞው ቁመናው አልነበረም፡፡ዘንድሮ ግን የባለፈውንም ዓመት ለማካካስ ጭምር ሁነቶቹ በዝተዋልየግንቦት ልደታን ‹‹ስለት››ና ሠርጋቸውን ወደዚህ ዓመት ያሸጋገሩ እየተሽቃዳደሙ በመደገስ ላይ ናቸውግንቦት ልደታ ዓመታዊ የመሰባሰቢያ ቀን ሆኗል፤ ይደገሳል፤ልጅ አዋቂው ይደሰታልግን እኮ ዛሬም ኮሮና አልጠፋም ጃል፡፡
ግንቦት ልደታ ከግንቦት አንድ ቀን ጀምሮ በተለይ አንድ አካባቢ ያሉ ሰዎች ተሰብስበው ለዛሬ ዓመት ካደረሰከኝ እንዲህ አደርጋለሁ በማለት ለፈጣሪያቸው ስለት ተስለው በጋራ የሚያከብሩት ማህበራዊ አጋጣሚ ሆኗልሁነቱ ልዩ ክብር አለውድግሱም የዋዛ አይደለምከንፍሮ እስከ ቂጣ ብሎም እስከ እርድ ድረስ ይፈጸምበታልመጠጡም ልዩ ነውበዚህ በዓል ላይ የሚሳሉ ሰዎችም እልፍ ናቸውስለቱ ግን የሚገባው ለዓመታዊው በዓል ዝግጅት ነው፡፡ስለት ሰንል ደግሞ ለፈጣሪ የሚቀርበውን ልመና እንጂ ገጀራውን አይደለምእንግዲህ ስለት አንድ ሰው በእርሱ ላይ ግዴታ ያልሆነበትን ነገር በራስ ተነሳሽነት እራሱ ላይ ግዴታ አድርጎ የሚሳለው ነውስለት የሚባለው ሰዎች እንዲሰጣቸው እንዲደረግላቸው በህይወታችን በጸሎት ፈጣሪያቸውን የሚጠይቁበት፣ ስለቱ ሲሰምርም፤ ለተሳሉት ታቦት የሚያስገቡበት ነው፡፡
በግንቦት ልደታ ወቅት ይህ ዓይነቱ ሁነት በሰፊው ይስተዋላልስለቱ የሚቀርበው ለበዓሉ ማካሄጃ እንዲውል ነውቃል መግባት ማለት ነውአንዳንዶች በመንፈሳዊው ቋንቋ ይሳላሉ፤ አንዳንዶች ደግሞ ቃል ይገባሉ፡፡የስለት ዓይነቶች ይለያያሉግማሹ አረቄ፣ ግማሽ ሥጋ፣ ግማሹ ዳቦ፣ ግማሹ ቢራ የተሳለውን በማስገባት በዓሉን በጋራ በደስታ ያክብሩታልአሁን አሁን በተያዘው ግንዛቤ በዓሉን በመዋጮ ማክበር ማለት ነው፤ የአካሄድ ልዩነት ነው፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ስለት የሚገባበት ሁኔታ አስገራሚ ሆኗል ለቃሉም የሚታመን እየታጣ ነውአንዳንዱ የስለት ማስገቢያው ቀን የማይደርስ እየመሰለው ነው መሰለኝ ከአቅሙ በላይ ሲሳል ታዩታ ላችሁእኛ ሰፈር ውስኪ ከአንድ በግ ጋር ተስሎ ዕለቱ ሲደርስ በጉም ውስኪውም የሉምኧረ እርሱም እቦታው ላይ ድርሽ አይልም፡፡ምናለበት አንደኔ ስቲኪኒ ቢሳልምን ተበልቶ ስቲኪኒ አትሉም፤ ለነገሩ ይሄ ነገር ስለት የሚያስገቡ ሰዎች ሴራ ነውአንዳንዶች ሰዎችን ከአቅም በላይ መጠጥ እንዲጠጡ ያደርጉና ከአቅም በላይ እንዲሳሉ ያደርጓቸዋልሰው ሲሰክር የሚያደርገውን አያውቅም ይባል የለ እውነቴን ነው መጠጥ ብዙ ነገር ያስደርጋል፡፡
እና የኛ ሰፈር ሰዎች ለግንቦት ልደታ ድግስ እልም ያለ ስካር ውስጥ ገብተው ተስለው ሲያበቁ ለዓመቱ እልም ብለው ይጠፋሉ ልላችሁ ነውበእርግጥ ደጋግ ሰዎችም አይጠፉምወስነው ተስለው ወስነው ስለት የሚያስገቡበስካር ሲጦዙ ግን በግ የሚታያቸው አሉለእነርሱ ትንሽ ነገር መሳል ውርደት ይመስላቸዋልበቃ አያስችላቸውም ስለት የሚያስገቡት ሰዎች ደግሞ የክፋታቸው ጥግ ሰውን አስክረው ነው እንዲሳሉ የሚያደርጉትደሞ ማስታወሻ ይይዛሉበዓመቷ ብቅ የምትል፡፡
እርግጥ ነው በኔ አመለካከት መጠጥ በራሱ ክፋት የተሞላበት የተረገመ ነገር አይደለምክፋቱና ደግነቱን የሚወስነው ግን የስካሩ ጊዜ ነውስካር ብዙ ዓይነት ነውየሰከረው ሰው ምን ታፈጥብኛለህ እያለ ከሚጠጣው ጋር ሁሉ የሚጣላ፤ ድሮ የሞተበትን ሠው እያስታወሰ የሚያለቅስ፤ አስተናጋጆችን የማያሳልፍ፣ የተኛ ጓደኛውን ካልጋበዝኩህ ብሎ ወስዶ ሂሳብ የሚያስከፍል፤ ለግንቦት ልደታ ከኔ ሌላ ብሎ ከፍተኛውን ስለት የሚያስለፈልፍ ብቻ ብዙ ስካሮች አሉእኔ ግን እላለሁ በስካር ከመሳል ይሰውረንእንዲህ እንደ ግንቦት ልደታው ዓይነት ስለት ተስሎ ቀኑ ሲደርስ መሸሽ፤ እዳው ገብስ ነውዋናውን ስለት ተስሎ የት ይሸሻል?
አትክልት ተራ የጭነት መኪና ላይ ዕቃ በመጫንና በማውረድ ሞያ የሚተዳደረው የሰፈራችን ወጣት ስሜቱን መቆጣጠር ተስኖት በደስታ መዳፎቹን እየዳበሰ፤ ለዓመቱ በሠላም ካደረሰኝ ለበግ መጥበሻ አምስት ሸክም እንጨት አመጣለሁ ብሎ ነበርና ስለቱን ይዞ ቀረበ በእርሱ እንጨት የሚጠበሰውን በግ የተሳለው ሰው ግን በስካር ልቡ ስለነበር የተሳለው ትዝም አላለውአሁን እንጨቱ ምን ይደረግበት ነው? ምንምእንደተለመደው ለቀጣይ ሰክሮ በግ የሚሳል እየጠበቀ ነው እኔ ግን ስለቴን በታማኝነት አመጣለሁለዓመቱ በሰላም ካደረሰኝ በጉ የሚተሰርበትን ገመድ አቅርባለሁ ሰላም!
አዲሱ ገረመው
አዲስ ዘመን ግንቦት 11/2013