በፊንላንድ ሄልሲንኪ ከተማ እኤአ በ1983 የተጀመረው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና የዓለማችን ትልቁ የአትሌቲክስ መድረክ በመሆን ያለፉትን አርባ ዓመታት አሳልፏል። እኤአ በ1987ና 1991 በአራት ዓመት ልዩነት የጣሊያኗ መዲና ሮምና የጃፓኗ ቶኪዮ ይህን ታላቅ ውድድር ያዘጋጁ አገሮች ናቸው። ከቶኪዮ ወዲህ ግን ውድድሩ በሁለት ዓመት ልዩነት ነው እየተካሄደ የሚገኘው። የጀርመኗ ስቱትጋርት፤ የስዊድኗ ጉተንበርግ፤ የግሪኳ አቴንስ፤ የስፔኗ ሴቪሊ፤ የካናዳዋ ኤድመንተን፤ የፈረንሳይ መዲና ፓሪስ፤ የፊንላንዷ ሄልሲንኪ (ለሁለተኛ ጊዜ) የጃፓኗ ኦሳካ፤ የጀርመኗ በርሊን፤ የደቡብ ኮሪያዋ ዴጉ፤ የሩሲያዋ ሞስኮና የቻይናዋ ቤጂንግና የእንግሊዟ ለንደን ቻምፒዮናውን በሁለት ዓመት ልዩነት በቅደም ተከተል መድረኩን አዘጋጅተውታል።
የዘንድሮ ተረኛዋ የካታሯ ዶሃ ስትሆን የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ትኩረት ቢነፍጓትም ከአምስት ወራት በኋላ ለሚጠብቃት ታላቅ የስፖርት ድግስ ሽርጉድ ማለት ጀመራለች። የአሜሪካዋ ዩጂንም ቀጣዮን ቻምፒዮና ለማዘጋጀት ወረፋ ይዛለች። ኢትዮጵያም ቻምፒዮናው ከተጀመረ አንስቶ በመሳተፍ ላይ ትገኛለች። የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና አሁን ያለውን መልክ ይዞ መካሄድ ከመጀመሩ በፊት እኤአ በ1913 የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ማህበር ኦሊምፒክ እንደ ዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ያገለግላል ብሎ አምኖበት ነበር። ይህም ለሃምሳ ዓመታት ያህል አገልግሎ 1960ዎቹ ውስጥ በርካቶቹ የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ማህበር አባል አገሮች «የራሳችን የሆነ ውድድር ይኑረን» ብለው ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት እኤአ በ1976 ፑርቶሪኮ ላይ በተደረገ ዓመታዊ የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ማህበር ስብሰባ ላይ የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ከኦሊምፒክ ተለይቶ ራሱን የቻለ ውድድር እንዲያካሂድ ተወሰነ። በእዚህን ወቅት የመጀመሪያውን ውድድር ለማስተናገድ የምዕራብ ጀርመኗ ስቱትጋርትና የፊንላንዷ ሄልሲንኪ ጥያቄ አቀረቡ። እኤአ በ1952 ኦሊምፒክን ያስተናገደችው ሄልሲንኪ እድሉን አገኘች።
የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በውድድር አይነትና በተሳታፊዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በርካታ ለውጦችን አስተናግዷል። እኤአ በ1983 ከመቶ 54 አገራት የተውጣጡ1 ሺ 300 አትሌቶች ተሳታፊ ነበሩ። ይህ ቁጥር እኤአ 2003 ፓሪስ ላይ ተካሂዶ በነበብቻ ሳይሆን በተለያዩ የውድድር አይነቶችም በርካታ ለውጦች ታይተዋል። በተለይም ወንዶች በሚወዳደሩባቸው የውድድር አይነቶች ሴቶችም ተካፋይ እንዲሆኑ መደረጉ የቻምፒዮናው ትልቅ ለውጥ ነው። አሁን ላይ በዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ወንዶች የሚወዳደሩበት ለሴቶች ያልተፈቀደ የሃምሳ ኪሎ ሜትር የርምጃ ውድድር ብቻ ነው።
እኤአ በ1987 የሴቶች አስር ሺ ሜትር ሩጫና አስር ኪሎ ሜትር ርምጃ ውድድር የዓለም ቻምፒዮናን የተቀላቀለ አዲስ የውድድር አይነት ነው። ከስድስት ዓመት በኋላም የሴቶች ስሉስ ዝላይ የውድድሩ አካል ሆኗል። እኤአ በ1995 የሴቶች አምስት ሺ ሜትር ሩጫ የሦስት ሺ ሜትርን ወክሎ የውድድር አካል ሆነ። እኤአ በ1999 ደግሞ የሴቶች ምርኩዝ ዝላይና መዶሻ ውርወራ የውድድር አካል ከመሆናቸው በተጨማሪ የሴቶች አስር ኪሎ ሜትር ርምጃ ውድድር በሃያ ኪሎ ሜትር ርምጃ ውድድር ተተካ። እኤአ በ2005 የሴቶች ሦስት ሺ ሜትር መሰናክል ውድድር ተጨመረ። የለንደኑን ቻምፒዮኗ ሳይጨምር ባለፉት 15 ረው ቻምፒዮና ከሁለት መቶ ሦስት አገሮች የተውጣጡ 1 ሺ 907 አትሌቶች አሻቅቧል። በዓለም ቻምፒዮና የተሳታፊዎች ቁጥር የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮናዎች 98 አገራት የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ የገቡ ሲሆን፣ 2036 ሜዳሊያዎች (670 የወርቅኸ 685 የብርና 681 የነሐስ) ለአሸናፊዎች ተበርክተዋል፡፡
ከ16ኛው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በፊት የምንጊዜም የሜዳሊያ ስብስብ ደረጃን በድምሩ 323 ሜዳሊያዎች (143 የወርቅ፤ 96 የብርና 84 የነሐስ) በመሰብሰብ አሜሪካ አንደኛነቷን አስጠብቃለች፡፡ ሩሲያ 172 ሜዳሊያዎች (55 የወርቅ ፤ 60 የብርና 57 የነሐስ)፤ ኬንያ 128 ሜዳሊያዎች (50 የወርቅ፤ 43 የብርና 35 የነሐስ) ፤ ጀርመን 108 ሜዳሊያዎች (33 የወርቅ፤ 35 የብርና 40 የነሐስ)፤ ጃማይካ 110 ሜዳሊያዎች (31 የወርቅ፤ 44 የብርና 35 የነሐስ)፤ ታላቋ ብሪታኒያ 89 ሜዳሊያዎች (25 የወርቅ፤ 30 የብርና 34 የነሐስ)፤ ሶቭዬት ህብረት 77 ሜዳሊያዎች (22 የወርቅ፤ 27 የብርና 28 የነሐስ) እንዲሁም ኢትዮጵያ 72 ሜዳሊያዎች (25 የወርቅ፤ ቦልትን ያክል በዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በርካታ ሜዳሊያዎችን የሰበሰበ አትሌት የለም። ቦልት አስራ አንድ የወርቅና ሁለት የብር በማጥለቅ ቀዳሚ ነው።
አሜሪካዊው ካርል ሌዊስ ስምንት የወርቅ፤ አንድ የብርና አንድ የነሐስ ሜዳሊያዎች በማጥለቅ ተከታይ ነው። በተመሳሳይ አሜሪካዊው ሚካኤል ጆንሰን ስምንት የወርቅ ሜዳሊያ በማጥለቅ ሦስተኛ ነው። ሌላኛው አሜሪካዊ ላሻውን ሜሪት ስድስት የወርቅና ሁለት የብር ሜዳሊያ በመውሰድ አራተኛ ነው። የረጅም ርቀት ነጉሱ ኃይሌ ገብረስላሴ አራት የወርቅ ሁለት የብርና አንድ የነሐስ ሜዳሊያ በማጠለቅ አምስተኛ ደረጃ ላይ ይቀመጣል። የቀድሞ የምርኩዝ ዝላይ ባለ ክብረወሰኑ ዩክሬናዊው ሰርጌ ቡካ ስድስት የወርቅ ሜዳሊያዎችን በዓለም ቻምፒዮና መድረክ በማጥለቅ ኃይሌን ይከተላል። አሜሪካዊው ጃርሚ ዋሪነር አምስት የወርቅና አንድ የብር ሜዳሊያ ይዞ ሰባተኛ ነው።
የአስርና አምስት ሺ ሜትር ባለ ክብረወሰኑ ቀነኒሳ በቀለ በአምስት የወርቅና አንድ የነሐስ ሜዳሊያ ይከተላል። በሴቶች የረጅም ርቀት ንግስቷና የአምስትና22 የብርና 25 የነሐስ) በማስመዝገብ እስከ 7 ያለውን ደረጃ አከታትለው ይዘዋል፡፡ ጃማይካዊው የአጭር ርቀት ንጉስ ዩሴን አስር ሺ ሜትር የዓለም ክበረወሰን ባለቤቷ ጥሩነሽ ዲባባ በዓለም ቻምፒዮና መድረክ አምስት የወርቅ ሜዳሊያ ብታጠልቅም፣ ከአንድ እስከ አስር ባለው ደረጃ ውስጥ አትካተትም። ጃማይካዊቷ ማርሌን ኦቴይ ሦስት የወርቅ፤ አራት የብርና ሰባት የነሐስ ሜዳሊያ በመሰብሰብ በአስራ አራት ሜዳሊያዎች ቀዳሚ ነች።
አሜሪካዊቷ አሊሰን ፌሊክስ ስምንት የወርቅ፤ አንድ የብርና አንድ የነሐስ በማጥለቅ በአስር ሜዳሊያዎች ሁለተኛ ነች። ሌላኛዋ አሜሪካዊት ጄርል ሚልስ ክላርክ በአራት ወርቅ፤ ሦስት ብርና ሁለት ነሐስ ትከተላለች። ጃማይካዊቷ ቬሮኒካ ካምቤም ብሮውን ቀጣዩ ደረጃ ላይ ትገኛለች። በዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ታሪክ በበርካታ ቻምፒዮናዎች ላይ በመካፈል ፖርቹጋላዊቷ የአስርና የሃያ ኪሎ ሜትር ርምጃ ተወዳዳሪ ሰሳን ፌተር እኤአ ከ1991 እስከ 2011 ድረስ በአስራ አንድ ቻምፒዮናዎች በመሳተፍ ትልቅ ታሪክ አላት። ስፔናዊው የሃምሳ ኪሎ ሜትር ርምጃ ተወዳዳሪ ጂሰስ ኤንጅል ጋርሺያም እኤአ ከ1993 እስከ 2013 ድረስ በአስራ አንድ ቻምፒዮናዎች በመካፈል ተመሳሳይ ታሪክ አለው።
አዲስ ዘመን የካቲት 7/2011
ቦጋለ አበበ