አዲስ አበባ:- በአገራችን የሚገኙ ሬዲዮ ጣቢያዎች የሚጠበቅባቸውን ሰላምና ፀጥታን የማስፈን፣ በህዝቦች መካከል የነፃ ውይይት ባህልን የማዳበርና መቻቻልን የማስገንዘብ ተግባራትን በአግባቡ እየተወጡ አለመሆኑን የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ገለፀ።
የባለሥልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ገብረጊዮርጊስ አብረሃ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስረዱት፤ ኢትዮጵያ ከ1983 ዓ.ም በፊት ከውጭ ዜጎች የተወረሰውን ጨምሮ ሁለት ጣቢያዎች ብቻ ነበሯት። በአሁኑ ሰዓት ግን አስር የመንግሥትና አስራ ሁለት የግል ሬዲዮ ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን፤ ክልሎች በራሳቸው ቋንቋ ለራሳቸው ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የሚጠቀሙባቸው ያካባቢ ሬዲዮ ጣቢያዎችን ጨምሮ የ ግርማ መንግሥቴ
አዲስ አበባ:- በአገራችን የሚገኙ ሬዲዮ ጣቢያዎች የሚጠበቅባቸውን ሰላምና ፀጥታን የማስፈን፣ በህዝቦች መካከል የነፃ ውይይት ባህልን የማዳበርና መቻቻልን የማስገንዘብ ተግባራትን በአግባቡ እየተወጡ አለመሆኑን የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ገለፀ።
የባለሥልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ገብረጊዮርጊስ አብረሃ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስረዱት፤ ኢትዮጵያ ከ1983 ዓ.ም በፊት ከውጭ ዜጎች የተወረሰውን ጨምሮ ሁለት ጣቢያዎች ብቻ ነበሯት። በአሁኑ ሰዓት ግን አስር የመንግሥትና አስራ ሁለት የግል ሬዲዮ ጣቢያዎች
ሁሉም ክልሎች ድምር 48፤ ባጠቃላይ በመላ አገሪቱ 70 የሬዲዮ (እና 27 የቴሌቪዥን) ጣቢያዎች አሉ ሲሉ ገልፀዋል።
በርግጥ መቶ አስር ሚሊዮን ህዝብ አካባቢ ባለበት ሀገር ይህ በቂ ነው ማለት አይደለም የሚሉት ኃላፊው፤ ክፍተቶችን በመለየት ለማስፋፋት የሚያስችሉ ሥራዎች እየተሠሩ መሆናቸውንና በአሁኑ ሰዓትም 20 የሚሆኑ የሬዲዮ ሞገድ ሥራዎችን ለማስፋፋት ፈቃድ ተጠይቆ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል። ወደፊት በየአካባቢውና በየክልሎች የተሻሉና ህብረተሰቡን የበለጠ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሬዲዮ ጣቢያዎች ይኖሩናል የሚል እምነት አለኝ ሲሉም አክለዋል።
ሰላም፣ መቻቻልና ዴሞክራሲያዊ ውይይትን ከማዳበር አኳያ ጣቢያዎቻችን ብዙ ሠርተዋል ለማለት የኛ ዳኝነት ብቻ ሳይሆን ሁሉም የሚያየው ነው የሚሉት አቶ ገብረ ጊዮርጊስ፤ የነበረው ሁኔታ ቃላት መወራወር፣ የተሳሳቱ ዘገባዎችን ማቀበል፣ የራስን ፍላጎት ብቻ ማራመድ እንጂ፤ በእቅድ ይዞ ለሰላም፣ ለህዝብ መልካም ግንኙነት፣ ስለመቻቻል የመሥራት ሁኔታ ነበር ለማለት ያስቸግራል በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በየእለቱ የሚተላለፉ የተለያዩ የሬዲዮ ፕሮግራሞች ቋሚ አድማጭ የሆኑት አቶ ተስፋዬ መብራቱ እንደሚሉት፤ ሬዲዮ ጣቢያዎቻችን በጣም ይቀራቸዋል። ለህዝብ ትክክለኛውን መረጃ በማቀበል በኩል በሚገባ እየሠሩ አይደለም። የአየር ሰዓታቸውን ባብዛኛው የሚያውሉት አገለግለዋለሁ ለሚሉት ህዝብ ሳይሆን ለታዋቂና ስፖንሰር ለሚያደርጋቸው አካል ነው። በፕሮግራሞቻቸው ሰፊውን ሰዓት የሚይዙት ሙዚቃዎች፣ ቀልዶችና ሌሎች ከማህበራዊ ሚዲያው የተወሰዱ ወሬዎች ናቸው።
አቶ ተስፋዬ እንደሚሉት፤ አብዛኞቹ ሬዲዮ ጣቢያዎቻችን የአየር ሰዓታቸውን የሚሰጡት ለደሀው፣ ለታፈኑ ድምፆች፤ ብሶት ለደረሰባቸውና ለተበደሉ ዜጎች፤ ወይም ለዴሞክራሲ፣ ፍትህና ሰብዓዊ ጉዳዮች አይደለም። በማህበራዊ ሚዲያው መወናበድ ሁሉ የሚመጣው እነሱ ተገቢውን ሙያዊ ሥራ ባለመሥራታቸው ነው።
እንደ አስተያየት ሰጪው ከሆነ፤ አንዳንድ ጊዜ የሚቀርቡት ሀሳቦችም ሆኑ አቅራቢዎቻቸው ከሚዲያው ሥነምግባር ውጪ ሲሆኑ፤ መስማት እንግዳ ነገር አይደለም። በመሆኑም ይላሉ አቶ ተስፋዬ ይህ መታረም አለበት።
ህብረተሰቡ ከሬዲዮ ማግኘት ያለበትን ጥቅም አግኝቷል ብዬ አላስብም የሚሉት የሬዲዮ አድማጩ አቶ ተስፋዬ፣ የእውቀት ማነስ፣ የመረጃ እጥረት ባለበት አገር ይህን መሙላት ከሬዲዮኖቻችን የሚጠበቅ ሲሆን፤ ሲደረግ ግን አይታይም።
እየተከበረ ያለውን የዓለም የሬዲዮ ቀን “ውይይት፣ መቻቻል እና ሰላም” የሚለውን መሪ-ቃል ከአገራችን ሁኔታ ጋር አያይዘን ላቀረብንላቸው ጥያቄም፤ ሬዲዮ ጣቢያዎቻችን የሰላም መሳሪያ መሆን ነው የሚጠበቅባቸው፤ ህብረተሰቡ ሰላሙ በእጁ እንዳለ፣ የሰላሙ ተጠቃሚም እሱ ራሱ እንደሆነ፤ ሰላም፣ ፍቅር፣ መቻቻል አስፈላጊ ጉዳዮች መሆናቸውን ማሳወቅ ላይ ጣቢያዎቻችን ይቀራቸዋል። ይህ ወደፊት ይስተካከላል ብዬ አስባለሁ በማለት መልእክታቸውን አጠቃልለዋል።
የብሮድካስት ባለሥልጣን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው የሬዲዮ ጣቢያዎቻችን ወደፊት ሰላማዊ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ከመፍጠርና ለሰላም፣ ለአንድ ህዝብ፣ ለአንድ ኢትዮጵያ ከመሥራት አኳያ የተሻሉ እንዲሆኑ እንመኛለን፤ መልእክታችንም ይሄው ነው በማለት አብራርተዋል።
አዲስ ዘመን የካቲት 6/2011
በግርማ መንግሥቴ