አብዛኛዎቻችን በህይወታችን የራሳችንን ውሳኔዎች እናስተላልፋለን ተብሎ ይታሰባል፡፡ አንዳንዴ ግን የተሳሳቱ ውሳኔዎችን ልንወስን፣ አልፎ አልፎም ለውሳኔ አስቸጋሪ የሆኑ ሁኔታዎች ሊያጋጥሙንና መንታ መንገድ ላይ ልንቆም እንችላለን፡፡ ሆኖም አማራጮቹ ሁሉ በማየትና የምናሳልፈው ውሳኔ ያለውን ጠንካራና ደካማ ጎን በመፈተሽ ትክክለኛውን መምረጥ ደግሞ የእኛ ሃላፊነት ይሆናል፡፡ ይህም ካልተቻለ ግን ሰዎችን አማክረን ተገቢውን ውሳኔ ማሳለፍ እንችላለን፡፡
እዚህ ላይ ግን አንዳንድ ሰዎች በግል ህይወታቸው ሌሎችን ጣልቃ አስገብተው እንዲወስኑላቸው መፍቀዳቸው የሞት ሞት መስሎ ሊታያቸው ይችላል ፤ ከሰሞኑ ኦዲቲ ሴንትራል የተሰኘው ድCረ ገፅ ይዞት የወጣው መረጃ ግን ይህን ማድረግ ምንም ማለት እንዳልሆን የሚያረጋግጥ ነው፡፡
እንደ ድCረ ገፁ ዘገባ እንግሊዛዊቷ ወይዘሮ ባለፈው አንድ —መት ያሳለፈቻቸው ውሳኔዎች በአብዛኛው ስህተት የተሞላባቸውና ዋጋ ያስከፈሏት በመሆኑ ከዚህ በኋላ ትክክለኛ ወሳኔ ለመወስን ያስችላት ዘንድ መላ ዘይዳለች፡፡
ስሟ ያልተጠቀሰውና በእንግሊዝ ብሪስቶል የምትኖረው ይህችው ወይዘሮ በባ˜ድ ሃገር እያለች ያመነችው ሰው ከድቷት ያለገንዘብ መናዋን ቢያስቀራትና ከእርሱ ጋር የነበራት የፍቅር ግንኙነት መርዛማ እንደነበር ስታውቅ በተሳሳተ ውሳኔ እዚህ ጉዳይ ውስጥ እንደገባች ትረዳለች፡፡
ይህንንም በመገንዘብ ለአንድ ወር ያህል መንፈሳዊ መመሪያና የህይወት አቅጣጫ እንዲሁም በእርሷ ቦታ ሆኖ ትክክለኛ ውሳኔዎችን በመወሰን ወደ ትክክለኛ የህይወት መስመር የሚመልሳት ሊቅ በ 2 ሺህ ፓውንድ ወይም 2ሺህ 600 የአሜሪካን ዶለር ለመቅጠር ወስናለች፡፡
ሴትየዋ ‹‹ከደረሰብኝ ችግር አኳያ በኔ ቦታ ሆኖ ውሳኔዎችን የሚያሳልፍልኝን አማካሪ ሰው መፈለጌ አይደንቅም»፤ ስትል አድ ኦን ባርክ በተሰኘው ድህረ ገፅ ፅፋለች፡፡ ‹‹ ከመንፈሳዊ ህይወቴም እርቄ በመቆየቴ ይህንን ጉዞዬን የሚመራልኝና ትክክለኛ ውሳኔ እንድወስን የሚረዳኝ አማካሪም እፈልጋለሁ›› ስትል ተደምጣልች፡፡
‹‹ህይወቴን ወደ ነበረበት ሁኔታ ለመመለስ ከአማካሪዬ ጋር አንድ ወር መቆየት ለኔ በቂ ቢሆንም ነገሩ በርግጥም ለውጥ የሚያመጣ ከሆነ እቀጥልበታለሁ››ስትልም አክላለች፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ ሴትየዋ ቀደም ሲል ከወንድ ጋር በነበራት የፍቅር ግንኙነት መጥፎ ግዜያትን ያሳለፈች በመሆኑ እርዳታ ከምትፈልግባቸው የውሳኔ አይነቶች ውስጥ ይህ አንዱ ሲሆን በዚህ ውስጥ ደግሞ ከወንዶች ጋር ቀጠሮ ይዞ ማውራት ይገኝበታል፡፡
በሴትየዋ ቦታ ሆኖ ውሳኔዎችን ለመወሰን ለስራው የተመረጠው ሊቅም ደንበኛው ለምትጠይቀው ማንኛውም አገልግሎት በየትኛውም ጊዜና ቦታ ላይ ሆኖ አፋጣኝ ምላሽ መስጠት እንደሚጠበቅበትም በዘገባው ተጠቅሷል፡፡
የአድ ኦን ባርክ ድህረ ገፅ መስራች ካይ ፌለር ሴትይዋ በድህረ ገፁ የለቀቀችው መልዕክት ከእስካሁኖቹ ሁሉ እንግዳ መሆኑን ጠቅሰው ‹‹ሰዎች ገንዘባቸውን ለመቆጣጠር እንዲያስችላቸው የፋይናንስ አማካሪ እንደሚቀጥሩ ሁሉ እርሷም የዘመናዊ አኗኗር ዘዴ ጫና የህይወት አማካሪ ለመቅጠር የሚያስገድድ መሆኑን ሳትረዳ አልቀረችም›› ሲሉ ገልፀዋል፡፡
‹‹ዘመናዊ አኗኗር ጫና የበዛበት መሆኑን ተከትሎ ሰዎች በሚያስተላልፏቸው የቀን ተቀን ውሳኔዎች ስህተቶችን ቢሰሩም የራሳቸውን ህይወት እንዲመሩላቸውና ውሳኔዎች እንዲያስተላለፉላቸው አማካሪዎችን መቅጠር ግን ተገቢ ነው የሚል እምነት የለኝም›› ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል፡፡
አዲስ ዘመን የካቲት 5/2011
በአስናቀ ፀጋዬ