ታምራት ተስፋዬ
የኖቭል ኮሮና ቫይረስ /ኮቪድ19/ ወረርሽኝ ደሃ ሃብታም ፣ አዋቂና ታዋቂ፣ መሪና ተመሪን ዘርንና የቆዳ ቀለምን ሳይለይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሚሊየኖችን በማጥቃትና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩትን ሕይወት በመቅጠፍ ጨካኝ መሆኑን ማስመስከሩን ይቀጥላል።
አገራት አስከፊው ቫይረስ ድንበራቸውን አቋርጦ እንዳይገባ ከገባም ጉዳቱን ለመቀነስ በርካታ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራዎችን ከመከወን ላይ ተጠምደዋል ።የጤናው ዘርፍ ጠቢባን ብሎም የምርምር ተቋማትም የሰው ልጅ የመኖርና ያለመኖር ጥያቄ ውስጥ ለከተተው ወረርሽኝ መድኃኒትና ክትባት ፍለጋ ሌት ተቀን ደክመው በመጨረሻ ተሳክቶላቸዋል።
ተመራማሪዎቹ ከዚህ
ስኬት
ለመብቃትም
ውድ
ህይወታቸውን
ከመስጠት
ባለፈ
ብርቱ
ትግል፣
ጥናት
እና
ምርምሮችን
ስለማድረጋቸው
በርካቶች
ይስማሙበታል።ከቀናት
በፊት
ይፋ
የሆኑ
መረጃዎችም
በዓለም
ዙሪያ
ያሉ
ተመራማሪዎች
ኮቪድ
19 ከተከሰተ
ጀምሮ
እስካለፈው
የፈረንጆቹ
ዓመት
ጥቅምት
ወር
ድረስ
ከ87
ሺህ
በላይ
የሚሆኑ
በወረርሽኙ
ዙሪያ
የተሰሩ
ጥናታዊ
ጽሁፎችን
ማቅረባቸውን
አስነብቧል።ተመራማራዎችን
ጨምሮ
በርካቶችም
በዚህ
አጭር
ጊዜ
ውስጥ
ይህን
ያክል
የምርምር
ውጤት
መታተሙ
አስደናቂ
መሆኑን
ገልፀዋል።
በዩናይትድ ስቴትስ ኦሃዩ ስቴት ዩኒቨርሲቲ በጆን ግሌን ኮሌጅ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ካሮሊን ዋግነር ፣ቁጥሩ በጣም አስገራሚ እና በሳይንስ ታሪክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ነው››ብለዋል።ክስተቱም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሳይንስ ማህበረሰብ አባላትና ተመራማሪዎች ትኩረታቸውን ወደ ወረርሽኙ ማዞራቸውን እንደሚያመላክትም አስገንዝበዋል።
ተመራማሪዎቹ ከጥር ግማሽ እስከ ሚያዚያ 2020 አጋማሽ ድረስ 4ሺ 875 የጥናት ውጤቶች ወይም አርቲክሎች መታተማቸውን አረጋግጠዋል።ይህ ቁጥር እስከ ሐምሌ ግማሽ 2020 ድረስ ወደ 44 ሺህ 13 በጥቅምት ወር መጀመሪያ ደግሞ ወደ 87 ሺህ 515 ከፍ ማለቱን አውቀናል ብለዋል።
ተባባሪ ፕሮፌሰር ካሮሊን ዋግነርም፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ ላይ የተካሄዱ ጥናቶችና ለጉዳዩ የተሰጠውን ትኩረት እኤአ በ1990ዎቹ ዋነኛ የሳይንስ ጥናት ማጠንጠኛ ማዕከል ከነበረው ከናኖ ስኬል ሳይንስ ጋር አነፃፅረውታል ።በዚህ አብይ ጉዳይ ላይ የተሰሩ 4ሺህ የሳይንስ አርቲክሎች 90 ሺህ ለመድረስ ከሁለት አሥርት ዓመታትን መውሰዳቸውን የጠቆሙት ፕሮፌሰሯ፣ የኮሮና ቫይረስ ጥናቶች በአንፃሩ 90 ሺህ ለመድረስ አምሥት ወራትን ብቻ ማስቆጠራቸውን አስገንዝበዋል።
ተመራማሪዎቹ በወረርሽኙ ጅማሮ ወራት በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለይ ዩናይትድ እስቴትስ እና የቻይና ከፍተኛ ጥናት እና ምርምር በማድረግ የጎላ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ይፋ አድርገዋል።ይሑንና በተለይ ቻይና የወረርሽኙ ስርጭት እና ጉዳት እየቀለላት መምጣቱን ስትመለከት የጥናት እና ምርምር ስራዎችን በእጅጉ መቀነሷን አስታውቀዋል።እንደ መረጃው ከጥር 1 እስከ ሚያዚያ 8 በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተሰሩት ጥናቶች መካከልም የቻይና ሳይንቲስቶች ሚና 47 በመቶ ድርሻን ወስዷል።
በተመሳሳይ መልኩ የወረርሽኙ ስርጭት እየቀለላቸው መምጣቱን ተከትሎ ሌሎች አገራትም የጥናት አስተዋፆዋቸውን ቀንሰዋል።ተባባሪ ፕሮፌሰር ካሮሊን ዋግነርም፣‹‹ይሕ መመልከታችንም በጣም አስገርሞናል ››ብለዋል።የዚህ ምክንያት ሊሆን የሚችለው ወረርሽኙ ትልቅ ስጋታችን አይደለም በሚል መንግሥታት ለጥናት እና ምርምር የሚሰጡ ትኩረት እና በጀት መቀነሳቸው መሆኑን ጠቁመዋል።
የዩናይትድ እስቴትስ ሳይንቲስቶችም በተለይ በወረርሽኙ ክስተት የመጀመሪያ ወራት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተካሄዱ ጥናቶች 2 በመቶ ድርሻን ተወጥተዋል።ከሐምሌ እስከ ጥቅምት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ደግሞ የ33 በመቶ ድርሻን ተወጥተዋል።
መረጃው ጨምሮ እንዳስነበበውም፣በጥናት እና ምርምር ፕሮጀክት ላይ ተሳታፊ የነበሩ ተመራማሪዎች የቡድን ቁጥርም ዝቅተኛ መሆኑ ተመላክቷል።ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ካሮሊን ዋግነርም ‹‹ይህን ያልተጠበቀ›› ብለውታል።
እርሳቸውም ሆነ የጥናት አጋሮቻቸው የወረርሽኙ አቅም እና ጉልበት እየጨመረ በተጓዘ ቁጥር፣ የጥናት ቡድኖች ቁጥርም ከፍ እንደሚል ጥርጥር እንዳልነበራቸው ያስታወሱት ፕሮፌሰሯ፣ ይሁን ካገኙት መረጃ መረዳት የቻሉት ግምታቸው ስህተት እንደነበር መሆኑን አስረድተዋል።
ዓለም አቀፍ ትብብሩም ቢሆን ቀስ በቀስ እየተቀዛቀዘ መምጣቱ ተጠቁሟል።በተለይ የጉዞ ማእቀቦች ተመራማሪዎች ተቀራርበው እና ተገናኝተው እንዳይሰሩ ማድረጉም ለዚህ ውስንነት በምክንያትነት ቀርቧል። እንደ ተባባሪ ፕሮፌሰሯ ገለፃ ግን ከጉዞ ክልከላ ባሻገር ተባብሮ ለመስራት ያልተቻለው በፖለቲካ ሽኩቻም ጭምር ነው። በተለይ ቻይና እና ዩናይትድ እስቴትስ በጋራ መስራት እንዳይችሉ ያደረገው ፖለቲካዊ ፉክክር ነው።
ይህን አይነት የተናጥል ፉክክር ድምር ውጤቱ ዜሮ ስለመሆኑ ያመላከቱት ፕሮፌሰሯ፣በተለይ ለሳይንሳዊ ምርምር ግኝቶች እጅ ለእጅ መያያዝ እና የጋራ መፍትሄ መስጠት የግድ ስለመሆኑ አፅእኖት ሰጥተውታል።በድህረ ኮሮና ወቅትም በሳይንሳዊ ምርምር ይበልጥ ተቀራርቦ መስራትን ለማጎልበት አማራጭ መንገዶችን ሁሉ መቃኘት እንደሚያስፈልግም ሳይጠቁሙ አላለፉም።ምንጫችን ኒውስ ዋይዝ ነው።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተሰሩት ጥናቶች መካከልም የቻይና ሳይንቲስቶች ሚና 47 በመቶ ድርሻን ወስዷል፤
አዲስ ዘመን የካቲት 30/2013