በኢትዮጵያ ለውጥ ከመምጣቱ ከ2010 ዓ.ም በፊት የሀገሪቱ ኢኮኖሚ አጣብቂኝ ውስጥ የገባና በብዙዎች ዘንድ ሊያንሰራራ እንደማይችል ተደርጎ ሲታሰብ የቆየ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ በተለይም የብድር ጫናው፣ የወጪ ንግድ በከፍተኛ ሁኔታ እያሽቆለቆለ መምጣቱ፣ የወጪ እና የገቢ ንግድ አለመመጣጠን የፈጠረው መዛባት ትልቅ መሆን፣ በአገሪቱ የገንዘብ ፖሊሲ ምክንያት የገንዘብ ሥርዓቱ በጣም የቀጨጨ እንዲሁም ቁጠባና ኢንቨስትመንት መካከል ያለው ሚዛንም አስፈሪ ነበር፤ የሥራ አጥነትና የዋጋ ግሽበትን ካየን ነገሮች በጣም ከባድ ነበሩ። በዚህ ላይ ዝርፊያው ተጨምሮበት ሁሉ ነገር በጨለማ ተውጦም እንደነበር የሚታወስ ነው።
እነዚህና መሰል የፖለቲካና የኢኮኖሚ ምስቅልቅሎሽ የፈጠሩት የሥራ አጥነት ችግር በነበረው መንግስት ላይ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞና ብሎም የመንግስት ለውጥ እንዲከሰት ምክንያት ሆነዋል፡፡ ስለሆነም በዶክተር አብይ የሚመራው የለውጥ መንግስት ሀገሪቱን ማስተዳደር ከጀመረ በኋላ በግንባር ቀደምትነት ከወሰዳቸው እርምጃዎች መካከል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ማድረግና ሀገሪቱ ከገባችበት አጣብቂኝ እንድትወጣ ማድረግ ነበር፡፡ በዚህ መነሻነት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ፖሊሲ በማውጣት በውጭ ሀገራት በጎ ፍቃድ ላይ ተንጠልጥሎ የቆየውን የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ፖሊሲ በሀገር ሃብቶችና ጸጋዎች ላይ እንዲመሰረት በማድረግ ዜጎች በአካባቢያቸው ጸጋ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል መሰረት ተጥሏል፡፡
የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ፖሊሲው በሀገሪቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ የመጣውን የስራ አጥነት ችግር በዘላቂነት ለመፍታት አይነተኛ ሚና እንደሚጫወት ይታመናል፡፡ ከ2010 ዓ.ም በፊት በነበረው ሁኔታ አብዛኛው ስራ ዕድል የሚፈጠረው መንግስት ከውጭ ተበድሮ በሚያመጣው ብድር በሚጀመሩ የግንባታ ፕሮጀክቶች አማካኝነት የነበረ በመሆኑ በቂ ገንዘብ በማይገኝ ጊዜ የፕሮጀክት መቀዛቀዝና በዚያው መጠንም ስራ የመፍጠር አቅም ሲዳከም ቆይቷል፡፡ ከዛም አልፎ በብድር ላይ በተመሰረተው ኢኮኖሚ ፖሊሲ ምክንያት የሀገሪቱ ዕዳ እየጨመረ በመምጣቱ ሀገሪቱ ወደ ማትወጣበት የኢኮኖሚ አዙሪት እንድትገባ ምክንያት ሆኖ ቆይቷል፡፡ ለአብነትም በ2010 በጀት ዓመት ለውጭ ዕዳ የተከፈለው ከሀገሪቱ ጠቅላላ በጀት ውስጥ አንድ ሶስተኛ የሚሆነው ነው፡፡
እነዚህን ተጨባጭ ችግሮች ከግምት ውስጥ በማስገባት የተቀረጸው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ፖሊሲ ከጊዜ ወደ ጊዜ ውጤት እያሳየ ነው፡፡ ሀገሪቱ በኮሮና ወረርሽኝ ስጋት ውስጥ በነበረችበት ወቅት ሳይቀር የ6 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት በማምጣትና ቀጥሎ በህግ ማስከበር ዘመቻ ውስጥ በገባችበት ሁኔታ እና በአንበጣ ወረርሽኝ ሳይቀር ይህ ነው የሚባል የኢኮኖሚ መዛነፍ ሳይስተዋል በማለፍ ላይ ትገኛለች፡፡ ለዚህ ደግሞ ባለፉት ስድስት ወራት በመላ ሀገሪቱ የተፈጠረው የስራ ዕድል አንድ ማሳያ ሊሆን ይችላል፡፡
የስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን እንዳስታወቀው በ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ለአንድ ሚሊዮን 692 ሺህ 910 ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር ተችሏል፡፡ ለተፈጠሩት የስራ ዕድሎችም በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ፖሊሲው ላይ በግልጽ እንደተመላከተው በአካባቢያችን ያሉ ሀገር በቀል ጸጋዎች ከፍተኛውን ሚና ተጫውተዋል፡፡
በተለይ ጫማችን ስር ያሉ ጸጋዎች ማለትም እንስሳት ሀብት፤ አትክልትና ፍራፍሬ ልማቶች ላይ ለዜጎች ሰፊ የስራ ዕድል መፍጠር አስፈላጊ ነው፡፡ በኢትዮጵያ በእንስሳትና በዶሮ እርባታ፣ በአትክልትና ፍራፍሬ በከተማም ሆነ በገጠር ለብዙ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር እየተቻለ ሲሆን የበለጠ ለአካባቢ ጸጋዎች ትኩረት በተሰጠ ቁጥርም የበለጠ የስራ ዕድል እየተፈጠረ እንደሚሄድ አሁን እየተመዘገበ ካለው ውጤት መረዳት ይቻላል፡፡
ባለፉት ስድስት ወራት በሶስት የስራ መስኮች ለዜጎች ከዕቅድ በላይ የስራ ዕድል መፍጠር የተቻለ ሲሆን እነዚህም በግብርና ለ505 ሺህ 905፤ በኢንዱስትሪ 437ሺህ 037 እና በአገልግሎት 749ሺህ 968 ዜጎች የስራ ዕድል ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ በኢትዮጵያ ካለው ከፍተኛ የስራ አጥ ቁጥር አንጻርም አሁንም የስራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ መሆኑን ግን አሁንም መዘንጋት የለበትም፡፡ የስራ ዕድል ለዜጎች የኑሮ መሰረት ከመሆኑም ባሻገር ለአንዲት ሀገር መረጋጋት ሁነኛ ዋስትና በመሆኑ የተጀመረውን ስራ ዕድል ፈጠራ ሂደት በማጠናከር ረገድ የበለጠ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል እንላለን
አዲስ ዘመን የካቲት 05/2013
የሥራ ዕድል ፈጠራው ተጠናክሮ ይቀጥል!