ዳንኤል ዘነበ
ድንገተኛ የሕፃናት ሞት እና ሌሎች ከእንቅልፍ ጋር የተዛመዱ የሕፃናት የሞት አደጋን ለመቀነስ ሕፃናት ከተወለዱ አንስቶ እስከ 1 ዓመት ድረስ ከእንቅልፍ ጋር ተያይዞ ለሞት ተጋላጭ ይሆናሉ። በየአመቱ ከእንቅልፍ ጋር በተገናኘ በአሜሪካን ውስጥ ወደ 3 ሺህ 500 እድሜያቸው ከአመት በታች የሆኑ ሕፃን ሲተኙ ይሞታሉ። ከነዚህም በእንቅልፍ እያሉ ከሞቱት ሕፃናት ውስጥ አብዛኛዎቹ ይህ ሲከሰት የተገኘባቸው ነገሮች ስንመለከት፤ ከሕፃን አልጋ ውጭ በሆነ ቦታ የተኙ ናቸው፤ ከወላጆቻቸው፣ ከአያቶቻቸው ወይም ከሌሎች ተንከባካቢዎች ጋር አብረው የተኙ ናቸው፤ ከወንድማቸው፣ ከእህታቸው ወይም ከሌሎች ልጆቻቸው ጋር ተኝተው የተገኙ ሲሆኑ እነዚህን አሳዛኝ የሞት አደጋ ለመከላከል፣ ለልጅዎ በእንቅልፍ ወቅት ሊወሰዱ ስለሚገቡ ጥንቃቄዎች በቀን ሆነ ማታ ማረጋገጥዎን አይዘንጉ። ለመሆኑ ደህንነቱ የተጠበቀ የሕፃናት እንቅልፍ ኤቢሲ ምንድ ናቸው?
ኤቢሲ የሕፃናት እንቅልፍ ደህንነቶች ኤ
ህፃናት ሲያስተኙ ሁሌም በእራሳቸው አልጋ ወይም ባሳኔት ውስጥ ብቻቸውን መተኛት አለባቸው። ህፃናትን ከሌሎች ልጆች ወይም ጎልማሶች ጋር እንዲተኙ አያድርጉ። ይህም በአጋጣሚ የህፃኑ አፍ ላይ በመተኛት ህፃን ማፈን ወይም አፍንጫ ወይም በእንቅልፍ ጊዜ በእነሱ ላይ የመንከባለል አደጋ ሊፈጥር ስለሚችል ነው።
አልጋ ውስጥ ሲተኙ ሁሉንም ለስላሳ ዕቃዎች ከህፃኑ ያርቁ ለምሳሌ የሕፃናት አሻንጉሊት፣ ትራሶች ወይም ለስላሳ ዕቃዎች አብሯቸው መተኛት የለባቸውም እነዚህ ለስላሳ ዕቃዎች በአጋጣሚ በሕፃን ፊት ላይ በመምጣት የማፈን አደጋ ሊያስከትሉ ይችላሉ። ለነሱ የተዘጋጁ መተኛዎች ወይም ብርድ ልብስ ህፃኑን በሚተኛ ጊዜ እንዲመቸው ያደርጋሉ። ህፃኑን ከመጠን በላይ ሊያሞቁ የሚችሉ ከባድ ብርድ ልብሶችን ወይም መተኛዎች መጠቀም ከሚፈለገው በላይ ሙቀት በመፍጠር የህፃኑን ምቾት ይቀንሳሉ።
ኤቢሲ የሕፃናት እንቅልፍ ደህንነቶች ቢ
ሕፃናትን በጀርባቸው እንዲተኙ ያድርጉ። በጀርባቸው ላይ የሚተኙ ሕፃናት ከእንቅልፍ ጋር በተያያዙ የድንገተኛ የሕፃናት ሞት አደጋ የመሞት ዕድላቸው በከፍተኛ መጠን ይቀንሳል። በአቅራቢያዎ ያሉ እናቶችን፣ አያቶችን እና እርስዎን የሚንከባከቡትን ሁሉ ያስተምሯቸው ህፃን ሲያስተኙ በጀርባ እንዲያስተኙ። በጀርባ ማስተኛት ”የሕፃንን የመታፈን
አደጋ ወይም ትንታን ሊጨምር ይችላል ብለው ለደቂቃ እንዳይሰጉ ።
ኤቢሲ የሕፃናት እንቅልፍ ደህንነቶች ሲ
የህፃናት አልጋ እና ካቢኔቶች ለህፃናት መተኛ ከየትኛውም ስፍራ በጣም አስተማማኝ ስፍራዎች ናቸው። በህፃን አልጋዎች ላይ ትራሶች፣ ባምፐሮች፣ የተለያዩ መጫወቻዎች፣ ብርድ ልብሶች መኖር የለባቸውም ምክንያቱም በአጋጣሚ የሕፃኑን ፊት
በመሸፈን የማፈን አደጋ ሊያመጡ ይችላሉ። የሕፃን የአልጋ ፍራሽ ጠንካራ እና የማይሰረጉድ መሆን አለበት። ባዶ ቦታ ሳይኖር በጥሩ ሁኔታ የሚስማማ መሆኑን ያረጋግጡ:: ሕፃኑን ጡት አጥብተው ከጨረሱ በኋላ ሁል ጊዜ ልጅዎን ወደራሱ አልጋ መመለስዎን አይዘንጉ ሲሉ የህፃናት ሐኪም ዶክተር መሐመድ በሽር ምክረ ሀሳባቸውን ይለግሳሉ።
ምንጭ- ከኢትዮ ጤና ቴሌግራም ገጽ
አዲስ ዘመን ጥር 20/2013