አስቴር ኤልያስ
የመንግሥትን የማሻሻያ ፕሮግራም በስኬት ለማስፈፀምና በአጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገት በቀጣይነት ለማረጋገጥ የምሁራን እና የባለሙያዎችን ምክር እንዲሁም ግብረመልስ መቀበሉ ጠቃሚነቱ ይታመንበታል። መንግሥት ይህንንም በመገንዘቡ ገለልተኛ ከሆኑ ምሁራን እና ባለሙያዎች የተውጣጣ የመጀመሪያው የገለልተኛ ብሔራዊ የኢኮኖሚ ምክር ቤት በቅርቡ ማቋቋሙ ይታወቃል።
አገሪቱ ከ2013 እስከ 2022 ዓ.ም ድረስ ባለው የአስር ዓመት የልማት ዕቅዷ ላይ እንዳሰፈረችውም በ2022 ዓ.ም የኢትዮጵያ የነፍስ ወከፍ ገቢ ሁለት ሺህ 201 የአሜሪካን ዶላር እንደሚድግ ይጠበቃል። በዚህም ደግሞ የድህነት ምጣኔው አሁን ካለበት 20 በመቶ በ2022 በጀት ዓመት ወደ ሰባት በመቶ እንደሚቀንስም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የፕላን እና ልማት ኮሚሽን መረጃ ያመለክታል። ይህን ዕቅድ ስኬታማ ለማድረግ ደግሞ የገለልተኛ ብሔራዊ የኢኮኖሚ ምክር ቤት አባላት ሚናም ከፍ ያለ እንደሚሆን ይታሰበል። ይህንን ታሳቢ በማድረግም አዲስ ዘመን ጋዜጣ ከ16ቱ የምክር ቤት አባላት መካከል አንዱ የሆኑትን የፖለቲካ ምሁሩን ዶክተር ዲማ ነገዎን ምክረ ሐሳባቸውንም ሆነ ልምዳቸውን ለማካፈልና ለመሥራት ምን ያህል ዝግጁ ነዎት? በሚለውና በሌሎችም ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ቃለ ምልልስ አድርጎ እንደሚከተለው አቅርቧል። መልካም ንባብ።
አዲስ ዘመን፡– በቅርቡ የገለልተኛ ብሔራዊ የኢኮኖሚ ምክር ቤት አባል ሆነው መመረጥዎ ይታወቃል፤ ጉዳዩ በጥቅሉ ኢኮኖሚ ላይ እንደማተኮሩ ኢትዮጵያ በ2022 የያዘችው ርዕይ ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት ማድረግ የሚል ነውና ለስኬታማነቱ ምን ያህል በቁርጠኝነት ለመሥራት ተዘጋጅተዋል?
ዶክተር ዲማ፡– ምክር ቤቱ ገና አዲስ ሆኖ በመቋቋም ላይ ያለ ነው፤ በእስካሁኑ ሂደትም የተመረጡ ሰዎች የስም ዝርዝራቸው ይፋ ሆነ እንጂ ገና በይፋ ሥራ አልጀመረም። የምክር ቤቱ ዋና አላማ ግን የአገሪቱን የኢኮኖሚ ችግሮችና የዕድገት አቅጣጫ ለመቀየስ መንግሥት የሚያደርገውን ጥረት በሐሳብ መርዳት ነው። ችግር ያለባቸው አካባቢዎች ካሉ ይህ በዚህ ቢስተካከል፤ እዚያ አካባቢ ያለው ችግር ደግሞ በዚኛው ቢቀረፍ በሚልና በጥቅሉ ግን የአገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት አቅጣጫ ምን መሆን አለበት? የሌሎች አገሮችስ ልምድ ምንድን ነው? ከእነሱስ መማር ያለብን የቱን ነው? የእኛስ አገር ሁኔታ ምንድን ነው? ኢትዮጵያ ማደግ የምትችለው ምን ላይ ተመስርታ ነው የተሻለ የኢኮኖሚ ዕድገት ልናስገኝ የምችለው? ህዝባችንንስ በተለይ አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ በድህነት ሥር ያለ ነውና ከድህነት ግብግብ ልናላቅቅ የምንችለው እንዴት ነው? ያለንን የተፈጥሮ ሀብት እንዴት አድርገን ነው ልንጠቀምበት የምንችለው? በሚሉ እና በመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ መንግሥት የሚያወጣቸው ዕቅዶች አሉ።
መንግሥት የራሱ የሆነ የፕላን ኮሚሽን አለው፤ በዚህም የአንድ ዓመት፣ የአምስት እና የአስር ዓመት መሰል ዕቅዶችን ያወጣል። እነዚህን ዕቅዶች መመልከት እዛ ላይ ካለን ልምድና እውቀት ምን አይነት ምክር ነው ልንሰጥ የምንችለው የሚለው ላይ ነው ዋና ሥራችን ትኩረቱን የሚያደርገው።
ስለሆነም እስካሁን ባገኘሁት ልምድ፣ በተማርኩት ትምህርት እና ባደረኩት ምርምር በጥቅሉ ባለኝ ልምድ በተቻለኝ መጠን በቀሪው እድሜዬ የምችለውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ። በዚህ ምክር ቤት ውስጥ የምናበረክተው አስተዋጽኦ ሁሉ ነፃ አገልግሎት ነው።
ግን ሁላችንም በምክር ቤቱ ውስጥ እንድንሳተፍ ስማችን የተጠቀስነው ሁሉ የተማርነው በህዝብ ሀብት ነው። ትምህርት ቤት አስገብቶ ፊደል እንድንቆጥር ዕድሉን ያመቻቸልን እና ውጭም አገር ድረስ ልኮ እንድንማር ያስቻለን ይህ ድሃ ህዝብ ነው። ይህ ያገኘነው እውቀት ይህ ህዝብ ከኑሮው ቀንሶ በማካፈሉ ነው። በመሆኑም የዚህ ህዝብ ኑሮው እንዲሻሻል በሚደረገው እንቅስቃሴ ሁሉ ያለንን አስተዋጽኦ ለማበርከት ግዴታም አለብን ብዬ
አዲስ ዘመን፡– የአንድ አገር ዲፕሎማሲ ተቀባይነት ሊኖረው የሚችለው አንዱ አገሪቱ በኢኮኖሚው ዘርፍ ፈርጣማ የሆነ ማንነት ሊኖራት ሲችል ነውና አገሪቱ አሁን ላይ ያለባትን ውስብስብ የሆነ ችግሯንና ድህነቷንም ለመቅረፍ በምክር ቤቱ አባልነት የተመረጡ ምሁራን ሚና እምን ድረስ ነው ብለው ያስባሉ?
ዶክተር ዲማ፡– ዛሬ ዛሬ ሁሉም ነገር መሠራት የሚኖርበት በእውቀት ነው። ለውጥ ሊመጣ የሚችለው በጉልበት ሳይሆን በጥበብ እና በእውቀት ነው። ከዚህ አኳያ ምሁራኑ ባገኙት እውቀት እና ምርምር መሠረት የአገሪቱን አቅም ማሳደግና ማጎልበት ይጠበቅባቸዋል። አገራቸውንም ሊረዱ የሚችሉት በዚህ በኩል ነው። ይህ የሚሆነው ግን በአንድ ኢኮኖሚ መስክ ብቻ አይደለም። ለአብነት ያህል ብጠቅስልሽ እኔ በውጭ ጉዳይ በተቋቋመ ምክር ቤት የድርሻዬን አበረክታለሁ፤ በዛ ውስጥም ሐሳብ ከመስጠት ጀምሮ አገልግላለሁ። ልክ እንደዚሁ ሁሉ ሌሎችም በምህንድስናው፣ በትምህርቱ፣ በጤናው እና መሰል ዘርፎች የአገሪቱን ሁኔታ እንዴት ነው ማሻሻል የሚገባኝ በማለት ሊንቀሳቀሱ ይገባል ባይ ነኝ።
በአሁኑ ወቅት ማስተዋል የሚችል አካል ካለ የትምህርቱ ሁኔታ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ያለ ነው። አንድ አገር ከአካባቢው ጋር ሊወዳደር የሚችለው በእውቀት ነው። በተመሳሳይ በዓለም ካሉ አገሮች ጋርም መወዳደር የሚቻለው በእውቀት ነው።
እኔ እንደምገምተው አሁን ያለው ሁኔታ አሳሳቢ ነው። ምክንያቱም የትምህርቱ ደረጃ እየወደቀ ነው። አሁን እየወጣ ያለው ትውልድ ግማሽ ትምህርት የተማረ ነው ማለት ይቻላል። ከዚህ አንፃር ይህ ጉዳይ መታየት ያለበት ነው ብዬ አምናለሁ። በትምህርት መስክ እውቀት ያላቸው ምሁራን ይህን የትምህርት ደረጃ ለማሻሻል ጥረት ማድረግ አለባቸው ማለት ነው። ይህ ሊያሳየን የሚችለው ዕድገት የሚመጣው በኢኮኖሚ ብቻ ሳይሆን ሁሉንም አካታች እንደሆነ የሚያመላክት መሆኑን ነው። ኢኮኖሚውንም ሊያሳድግ የሚችለው የተመራማረ እና የሰለጠነ የሰው ኃይል ካለ ብቻ ነው። ነገር ግን የሰው ኃይል በማስተማሩ እና በማስልጠኑ በኩል ያለን ጉድለት ምንድን ነው ብለን መመልከቱ አስፈላጊ ነው።
አዲስ ዘመን፡– የትምህር ጥራት መውደቁን በቅርቡ ከሚታየው ሂደት ኮቪድ 19ኝን ጨምሮ ነው ወይስ ቀደም ሲልም የትምህርት ጥራቱ መውደቁን ነው ያስተዋሉት?
ዶክተር ዲማ፡– ከኮቪዱ 19 ጋር በተያያዘ ብቻ ሳይሆን ባለፉት አምስት አስርት ዓመታት ጀምሮ ነው፤ ድሮ በንጉሠ ነገሥቱ ዘመን የሚማረው የተወሰነ ሰው ብቻ ነው። ደርግ ወታደራዊ ሥልጣን ላይ ከወጣ ጊዜ ጀምሮ የትምህርት ጥራት ቀስ በቀስ እየወደቀ መጥቷል። ይህም አንዱ በደርግ ጊዜ ከፖለቲካ ጋር ግንኙነት ያለው ነበር። በፖለቲካ ታማኝነት ወደከፍተኛ ትምህርት ቤት የሚገባበት ሁኔታ የነበረበት ጊዜ ነው። ባለፉት 30 ዓመታት ደግሞ ከዛ የባሰና የትምህርት ደረጃው በጣም የወደቀበት ሁኔታ ነው የሚታየው።
ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አጠናቀው የሚወጡትን ስናስተውል በቀላሉ የጥራቱ ጉዳይ መውደቁን ማየት ይቻላል። የመምህራኑ የጥራት ደረጃ ሲታይ ምን ያህል ነው የሚለውም አጠያያቂ ነው። የመምህራኑ ጥራት የወደቀ ሲሆን የሚያስተምሯቸውም ሰዎች የጥራታቸው ሁኔታ እንደዚያው ነው የሚሆነው። በመሆኑም ይህ በአግባቡ የሚታይ ነው መሆን ያለበት። ይህ ማለት ግንኙነቱ ከሁሉም ጋር የተያያዘ ነው ማለት ነው። ምክንያቱም የምናስተምረው ኢንጂነሮችን፣ ሐኪሞችን፣ ኢኮኖሚስቶችን እንዲሁም የውጭ ግንኙነት ሥራዎችን የሚሠሩትን እና ሌሎችንም ጭምር በመሆኑ የትምህርት ጥራት ወደቀ ማለት እነዚህ ዘርፎች ሁሉ ወደቁ እንደማለት ነው።
ለምሳሌ የውጭ ቋንቋ ችሎታን በተመለከተ ብቻ ባነሳልሽ ችሎታችን ከድሮ ጋር ስናስተያየው ጥራቱ በጣም የወደቀ ነው። ይህ ደግሞ በተለይ በውጭ ግንኙነት ላይ ተጽዕኖ አለው። ምክንያቱም ከውጭው ዓለም ጋር ግንኙነት የሚፈጠረው በአገር ውስጥ ቋንቋ እንዳልሆነ ይታወቃል። በተለይ ደግሞ ዲፕሎማቶቻችንን የአካባቢ አገሮችን እና የሌሎችንም ዓለም አቀፍ ቋንቋዎች በደንብ ማስተማርና በዛ ቋንቋ የተሻለ ክህሎት ሊኖራቸው የሚገባቸው ናቸው። በሁሉም መስክ ያሉ እንደየ ችሎታቸው አገሪቱን ማገልገል አለባቸው።
አዲስ ዘመን፡– በአሁኑ ወቅት የተቋቋመው ምክር ቤት ገለልተኛ ነው ተብሎ ይታመናል፤ ከዚህ ቀደም ግን መሰል አደረጃጀቶች ገለልተኛ ናቸው ተብለው ቢቋቋሙም ለይስሙላ እንጂ ሥራቸውን በአግባቡ ሲከውኑ አይስተዋሉምና እርስዎ ለሥራችን ፈተና ይሆንብናል ብለው የሚያሰጋዎት ነገር ይኖር ይሆን?
ዶክተር ዲማ፡– እንዳወቃቀሩ ነው፤ አሁን እንደማየው ከሆነ በምክር ቤቱ ውስጥ የተካተቱ ሰዎች የፖለቲካ ገለልተኝነት አለ። በሙያም ቢሆን የተለያየ ሙያ ያላቸው ሰዎች ናቸው። ግማሹ መምህር ገሚሱም ምርምር የሚያደርግ ነው። ስለዚህ በልምዳቸው የሚያበረክቱትም የተለያየ እውቀት፣ ምርምር እና ልምድ በመሆኑ ብዙ አስተዋጽዖ ይኖራቸዋል ማለት ነው።
ትልቁና ዋናው ነገር ግን የፖለቲካ ገለልተኛነቱ ነው። በሥልጣን ላይ ያለው የፖለቲካ ሥርዓት እርሱ የሚፈለገው ብቻ የሚሠራ አካል ከሆነ ዘላቂነት ያለው ሳይሆን ጊዜያዊ ነው ማለት ይቻላል። የአገሪቱን ጥቅምና የወደፊት ዕድገት ለማሟላት ይቸግራል ማለት ነውና መንግሥትም ፕሮፌሽናል የሆኑ ምክሮችን የመቀበል ዝግጁነት ሊኖረው ይገባል።
አዲስ ዘመን፡– በአሁኑ ወቅት እርስዎ የፖለቲካ ምሁርነትዎ እንደተጠበቀ ሆኖ ከየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ግን ነፃ ስለመሆንዎ ይታወቃል፤ ይሁንና አሁን በአገሪቱ ውስጥ እየተካሄደ ያለው የፖለቲካ ትኩሳትን እንዴት ያዩታል?
ዶክተር ዲማ፡– አንዱና ትልቁ ችግር የፖለቲካ አደረጃጀት ችግር ነው፤ በኢትዮጵያ ውስጥ የተረጋጋ እና ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ሥርዓት ለመገንባት ቢያንስ ሁለት ነገሮች ያስፈልጋሉ። አንደኛ ገለልተኛ የሆነ አገሪቱን እና ህዝቡን የሚያገለግል የመንግሥት ሥርዓት፤ ሁለተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት የሚያስችል ምርጫ።
ገለልተኛ የሆነ አገሪቱን እና ህዝቡን የሚያገለግል የመንግሥት ሥርዓት ስንል የአገረ መንግሥቱን ሥርዓት በተለይ ቁልፍ የሆኑ ተቋማት አገርንና ህዝብን የሚያገለግሉ ናቸው እንጂ የማንም የፖለቲካ ቡድን አገልጋይ አሊያም የተወሰነ የህዝብ ወገን አገልጋይ መሆን የለበትም ማለት ነው። መላ አገሪቱንና ህዝቡን የሚያገለግሉ ተቋማት መፍጠር መቻል ያስፈልጋል።
ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት ምርጫ የግድ የሆነ ጉዳይ እና አንዱ አካል ነው። ሰው ለመምረጥ ግን ማን ነው የሚመርጠው የሚለው መጤን አለበት። የፖለቲካ ፓርቲዎች በሥርዓት መገንባት እና መደራጀት አለባቸው።
በእኔ አስተያየት በአገራችን እስካሁን ድረስ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሉም። የፖለቲካ ቡድኖች ሊኖሩ ይችላሉ። ነገር ግን ሰፊውን ህዝብ በአግባቡ ሊያንቀሳቅሱ እና ሊያነሳሱ የሚችሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገና አልተፈጠሩም። ስለዚህም የፖለቲካ ፓርቲዎች መፈጠር መቻል አለባቸው የሚል እምነት አለኝ። ምክንያቱም አንድ የፖለቲካ ፓርቲ መሆን የሚጠበቅበት የሕዝቡን ልዩ ልዩ ጥቅም የሚያንፀባርቅ እንጂ የተወሰነውን ቡድን ስሜት ብቻ የሚከተል መሆን አይጠበቅበትም። ስለዚህ ሰፋ ያለውን የህዝቡን ፍላጎት የሚያፀባርቁ የፖለቲካ ድርጅቶች መፈጠር አለባቸው። እስካሁን ያሉት በቡድን ደረጃ ነው። ስለሆነም ትልቁ የሚቀረን ነገር ቢኖር ይህን ማጠናከር ነው። የተቋማት መገንባት ሰፋ ያለ ፍላጎት ላይ የተመሰረቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያስፈልጋሉ የሚል እምነት አለኝ።
አዲስ ዘመን፡– እርስዎ በውጭ ጉዳይ ውስጥም በማማከሩ ሥራ የሚሠሩም ጭምር እንደመሆንዎ ከዲፕሎማሲው ጋር በተያያዘ በአሁኑ ወቅት መንግሥት በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል በትግራይ ክልል የሕግ ማስከበሩን ሥራ ጀምሮ በድል ማጠናቀቁ ይታወቃል፤ ይሁንና ቀደም ሲል አንዳንድ አካላትም ሆኑ ተቋማት ከቡድኑ ጋር ድርድር አሊያም ሽምግልና እንዲፈጠር ጥረት ሲያደርጉ ነበር፤ በዚህ ላይ የእርስዎ አስተያየት ምንድን ነው?
ዶክተር ዲማ፡– እኔ በእርቅ እና በመግባባት አምናለሁ። አሁን ከሥልጣን ከተባረረው እና በሰሜኑ የአገራችን ክፍል ችግር ይፈጥር ከነበረው ቡድን ጋርም በተለያየ ደረጃ ለዓመታት ውይይት እና ድርድር በማድረግ የተካፈልኩባቸው መድረኮች በርካታ ናቸው።…
አዲስ ዘመን፡– ቀደም ሲል የነበሩበትን የፖለቲካ ድርጅት ወክለው ነው?
ዶክተር ዲማ፡– አዎ! ይህ ቡድን ጉልበተኛ የሆነ ነው። በድርድር እና በመግባባት እንዲሁም ሰጥቶ በመቀበል የሚያምን ቡድን አልነበረም። ይህን ቡድን ካለፉት 30 እና 40 ዓመታት በላይ ከነበረኝ ልምድ ተነስቼ ባህሪውን ያስተዋልኩት ጉዳይ ነው። እናም ባለፉት ሁለት ዓመታት ተኩል ጊዜ ውስጥም ደግሞ አሁን ያለው አመራር ይህን ድርጅት ወደመግባባት ለማምጣት ሙከራ ሲያደርግ የነበረ ይመስለኛል። በአሁኑ ጊዜ ድርድር አድርጉ የሚለው አካሄድ ጊዜው አልፎበታል።
ነገር ግን ይህ ቡድን ቢወገድም ለብዙ ዓመታት በአካባቢው ከፍተኛ ተጽዕኖ ሲፈጥር የነበረ ቡድን ነው። በተለይ በአካባቢው ህዝብ ላይ ለረጅም ዓመታት በደል ሲያደርስ የነበረ መሆኑ እውን ነው። አሁን በትግራይ ውስጥ ያለው ትውልድ ከዚህ በኋላ ሌላ መንግሥትም የሚያውቅ አይደለም። ይህም ህዝብ ከመቶ 85 የሚሆነው ህዝብ ሲሆን፣ አዕምሮው የተሞላው በዚያኛው ቡድን ፕሮፖጋንዳ ነው።
እናም ይህ በመሆኑ የዚህን ቡድን አመለካከት የፖለቲካ ይዘቱንና የመሳሰለውን ከህዝቡ አዕምሮ ማውጣት ያስፈልጋል። በጥቅሉ ቡድኑ እና ህዝቡን መለየት እና ህዝቡም ከለውጡ እና ከሕግ ማስከበሩ ሥራ ተጠቃሚ መሆን ይኖርበታል። ህዝቡ ከሌላው ወገኑ ጋር አብሮ የወደፊቷን ኢትዮጵያ ዕድል ፈንታ የሚወስንበት ሁኔታ ማመቻቸት ያስፈልጋል።
በጥቅሉ እኔ በአገራዊ መግባባት ላይ አምናለሁ። ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ውስብስብ ችግሮች አሉ። የሰላም ማስከበሩ ሁኔታ ራሱ የፈጠረው ችግር ሌላም እንዲኖር ሊያደርግ ይችላል። የርስትና የመሬት ፍልሚያም አለ። ከእነዚህ ጋር በተያያዘ ሌላ ችግር ውስጥ እንዳንገባ ለማድረግ አጠቃላይ የሆነ አገራዊ ምክክር ተደርጎ አገራዊ የሆነ መግባባት ቢኖር ተመራጭ ነው። የአንዱን ችግር ስንፈታ ሌላው ችግር ተከትሎ ደግሞ እንዳይመጣ የታሪክ ሽሚያም እንዳይኖር ያስፈልጋል። ይህ እንግዲህ ወደፊት መመቻቸት ያለበት ሁኔታ ነው።
አገራዊ መግባባትን በተመለከተ ከሌሎች አካላት ጋር እየሠራን ያለነው በዚህ መስክ ነው። እና ወደፊት ምን አይነት አገር ነው የምንፈልገው፤ ለምሳሌ ለመጥቀስ ያህል ይህን ሁሉ የኢትዮጵያን ችግር ያመጣው አሁን ያለው የፌዴራል ሥርዓት ነው የሚሉ ሰዎች አሉ። አይ የፌዴራል ሥርዓቱ መነካት የለበትም የሚሉ አካላት ደግሞ አሉ፤ እንዲያውም ወደነበርንበት የክፍለ አገራት አደረጃጀት መመለስ አለብን ሲሉም የሚናገሩ አሉ። ይህ ሁሉ አመለካከት አንዳች መግባባት ላይ መድረስ እንዲችል በመቀመጥና አብሮ በመሆን መወያየትን የሚጠይቅ ነው።
የሚሻለን ምንስ አይነት የመንግሥት ሥርዓት ነው፤ ወይስ ምን አይነት የመንግሥት ሥርዓት ይኑረን የሚለውን ማጤን ተገቢ ነው። ኢትዮጵያ እንደሚታወቀው ትልቅ አገር ነች። ወደ 120 ሚሊዮን ህዝብ እየተጠጋን ነውና ይህቺን ትልቅ አገር አዲስ አበባ ላይ ብቻ ተቀምጦ መምራት አሊያም ማስተዳደር አይቻልም። ስለዚህ ህዝቡ በአካባቢው በቀበሌ፣ በወረዳ እንዲሁም ከዛም በላይ በሆነ መዋቅር ራሱን የማስተዳደር አቅም አለው። አቅሙም እየጎለበተ መሄድ አለበት።
ሌላው ደግሞ በአገሪቱ ውስጥ የተለያዩ ማንነቶች አሉ፤ እነዚህ ማንነቶች ሁሉ ተከብረው እና ጎልብተው ህዝቡ በአብሮነትና በወንድማማችነት ተሰልፎ ጠንካራ የሆነች አገር ሊኖረን የሚችልበት ሁኔታ መመቻቸት አለበት። እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው ሁልጊዜ መናቆር መሆን የለብትም። ላለፉት ከ50 ዓመታት በላይ (በእርግጥ ከዛ በፊት የፖለቲካ ክርክር አልነበረም) በፖለቲካ ስም እርስ በእርስ የምንባላበት ሁኔታ ነው ያለው፤ በተለይ ይህኛው ርዕዮተ ዓለም ይሻላል፤ እሱ ደግሞ አይሆንም።
ያኛውም አይሆንም፤ ስለዚህ የሚሻለው ሶሻሊዝም ወይም ደግሞ ሊበራል ዴሞክራሲ ነው እያልን ከምንደክም ከዚሁ ሁሉ ንትርክ ይልቅ ተቀምጠን ብንወያይና ብንመካከር ነው የሚሻለን። ሌላው ቀርቶ የአገሪቱን የወደፊት የኢኮኖሚ ዕድገት አቅጣጫስ ምን መሆን አለበት በሚለው እና አጠቃላይ በሆነ አቅጣጫ ሀብት እንኳ እንዴት መከፋፈል እንዳለብን እንዲህም ስል አገራችን ያላት ሀብት ውስን ነውና ይህንን የተፈጥሮ ሀብት እንዴት ነው የምንጠቀምበት፤ ሌላውንስ ሀብት እንዴት አድርገን ነው የምናከፋፍለው የሚለውን ሁሉ በጋራ በመቀመጥ እና በመወያየት አንድ መሰረታዊ የሆነ መግባባት መኖር አለበት ብዬ አምናለሁ።
አዲስ ዘመን፡– ጥቂት የማይባሉ ሰዎች ስለፌዴራለዝም ሥርዓቱ ብዙ ሲሉ ይደመጣል፤ አሁን ያለው ሁኔታ እምብዛም እምነት የሚያሳድር እንዳልሆነም ይናገራልና በእርስዎ አተያይ ይህ ሥርዓት ለኢትዮጵያ ምን ያህል ወሳኝ ነው?
ዶክተር ዲማ፡– አሁን ያለው ሥርዓት የፌዴራል ሥርዓት ነው ብዬ አላምንም። ምክንያቱም ፌዴራሊዝም ከዴሞክራሲ ውጭ ሊኖር አይችልም። ላለፉት 28 ዓመታት ያህል ክልሎች በራስ የመተዳደር ጥያቄያቸው መከልከላቸው ይታወቃል። በራሳቸው ቋንቋ የተከለሉ ክልሎች አምስት ያህል ይመስሉኛል። አሁን በቅርቡ 10ኛ ክልል በመሆን የተመሰረተው ሲዳማ ሲጨመርበት ደግሞ ስድስት ይሆናሉ። ሌሎች ክልሎች ግን በሌላው ቋንቋ ነው የሚገለገሉት።
በእርግጥ ባለፉት ዓመታት የነበረውን ስናስተውል አገሪቱን ያስተዳድር የነበረው አንድ ፓርቲ ብቻ ነበር። ህዝቡ የመረጣቸው ሳይሆኑ ሸገር ላይ ተቀምጠው ሲያስተዳድሩ የነበሩት የአንድ ፓርቲ ካድሬዎች ናቸው። በአንድ ቦታ ብቻ ተቀምጦ ማስተዳደር ስለማይቻል ሁሉም በየራሱ ክልል ሆኖ ህዝቡ ራሱን በራሱ ማስተዳደር መቻል አለበት። ያንን ለማድረግ ደግሞ የፌዴራሊዝም ሥርዓት ጥሩ የሚባል ሥርዓት ነው። በእርግጥ ያለውም ሕገ መንግሥት መሻሻል የሚችል ነው። ሕገ መንግሥቱም ቢሆን ያስኬዳል ወይስ አያስኬድም በማለት ማየቱም መልካም ነው።
እንደሚታወቀው የፌዴራል ሥርዓት ደረጃው ሊለያይ ይችላል። ዋናው ነገር ግን ሰብዓዊ መብትን የሚጠብቅ ነው። የመንግሥት ሥልጣንንም የሚያጋራ ነው። ባህልን እና ቋንቋን ጠብቆ ማስቀጠል የሚያስችል ነው። ስለዚህም ሕገ መንግሥቱን እነዚህን ከመሳሰሉት ጽንሰ ሐሳቦች አኳያ መልሶ ማየት የሚቻል ነው።
ስለዚህ ይህን ሥርዓት ይፍረስ የሚሉ አካላት አገሪቱ ብዙ ማንነቶች እንዳሏት እየታወቀ አንድ አይነት ማንነትን ለመጫን የሚከጅሉ ናቸው የሚል እምነት አለኝ። ከዚህ ቀደም የነበረውን ሥርዓት ማስተዋል ከተቻለ ሲያንፀባርቅ የነበረው አንድ አይነት ማንነትን ነው። እንዲያውም ደግሞ ከዛ በፊት የነበረው ደግሞ ሲያንፀባርቅ የሚስተዋለው አንድ አይነት ቋንቋ፣ ባህል እንዲሁም ኃይማኖትም ጭምር ነው። ይህ አይነቱ አካሄድ ደግሞ በአሁን ሰዓት ጨርሶ የሚቻል አይደለም።
ምክንያቱም አገራችን ትልቅ ናት ብያለሁ፤ ብዙ አይነት ማንነት ያለው ህዝብ የሚኖርባት እንደመሆኗ በአገራችን ውስጥ ደግሞ የህዝብን ማንነት ጨፍልቆ እንደከዚህ ቀደሙ መኖር አይቻልም። ይህ የሚሆን ከሆነ እንደገና ህዝቡን ሌላ ትርምስ ውስጥ መክተት ነው የሚሆነው ማለት ነው። ስለሆነም የሁሉም ማንነት ተከብሮ እና የአገሩ አንድነት ተጠብቆ አንድ ላይ መኖር የሚያስችል ሥርዓትን መግፋቱ የትም ሊያደርስ የሚችል አይደለም።
አዲስ ዘመን፡– አንዳንዶች የፌዴራሊዝም ሥርዓቱን አይተገብረው ይሆናል ሲሉ በብልጽግና ፓርቲ ጥርጣሬ የሚያድርባቸው አሉና ይህ ከምን የመነጨ ነው ይላሉ?
ዶክተር ዲማ፡– ይህ ጥርጣሬያቸው ከምን የመነጨ እንደሆነ በእውነቱ አይገባኝም። ነገር ግን በአንድ ነገር አምናለሁ። ያለፈው አሮጌ ሥርዓት ወይም ማንነትን የማይቀበል ሥርዓት ተመልሶ መምጣት አይችልም። የፈለገው ሰው ይሁን ያንን ሥርዓት መልሶ ማምጣት አይቻለውም።
በእርግጥ የብልጽግናን መርሃ ግብር እንዳየሁት ከሆነ ደግሞ የፌዴራሊዝንም ሥርዓት እንቀይራለን የሚል ጽንሰ ሀሳብ አላገኘሁበትም። ደግሞም ህዝቡ የማይፈለገውን ሥርዓት በግድ ህዝብ ላይ መጫንም አይቻልም። ለአብነት ያህል በቅርቡ 10ኛ ክልል እንደመመስረቱ 11ኛም ክልል የሚቀጥል ስለመሆኑ አመላካች ነው። ይህም የሚያጠራጥር ነገር የለውም። የብልጽግና ፓርቲም ቢሆን ይህን ነገር ባይፈልግ ኖሮ ውሳኔውን ያሳልፍ ነበር።
አዲስ ዘመን፡– ስለሰጡኝ ማብራሪያ ከልብ አመሰግናለሁ።
ዶክተር ዲማ፡– እኔም አመሰግናለሁ።
አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 19/2013
acheter des tablettes au royaume-uni en ligne almus
Limbourg venta de medicamentos en línea en Colombia
acheter des médicaments sans médecin Apofri Katwijk medicijnen: Veiligheid en effectiviteit
каспи магазин караганда,
каспи магазин шымкент суйемин сени песня, гульмира
избасханова – сени суйем скачать uzeyir zordur her sey mp3, qizlar narahat – mp3
skachat түс жору шабдалы көрсе, түс жору әйел адам көрсе
менің отаным қазақстан авторы,
менің отаным қазақстан эссе 4 сынып бірлігі бүтін ел эссе,
бірлігіңнен айырылма бірлікте бар қасиет
эссе электр машиналарын монтаждау,
электр монтаждау құралдары моңғол шапқыншылығы тест жауаптарымен, моңғол шапқыншылығының салдары слайд
hh ru работа юрист удаленно подработка в пятерочке подработка в
молокове когда разрешено проводить ремонтные работы в многоквартирном доме
ферсинол капли инструкция, ферсинол капли отзывы рмс авиация,
утпз авиация ак булак камеры, ак булак горнолыжный курорт пайдаланылған әдебиеттер тізімі информатика,
пайдаланылған әдебиеттер тізімі
педагогика