አስምረት ብስራት
ልጆች እንዴት ናችሁ? ሰላም ነው? ረጀሙ የእረፍት ጊዜ ተጠናቆ ወደ ትምህርት ቤት ለመግባት በመቻላቸሁ ደስ ብሎኛል። ለስምንት ወራት በቤታቸው ተቀምጠው ያሳለፉት ህፃናት ትምህርት ቤት በመከፈቱ የተነሳ ደስታቸው ወስን እንዳጣ ይናገራሉ።
በሮሆቦት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የአምስተኛ ከፍል ተማሪ የሆነው ኤልሮኢ ኤርሚያስ እንደሚለው ቤት ውስጥ በጣም ሰልችቶት ስለነበር አሁን ትምህርት ቤት በመከፈቱ እጅግ በጣም ደስተኛ ሆኗል።
“አሁን በክፍላችን ውስጥ ልጆችን አራርቆ ማስቀመጥ ስለተጀመረ ኮሮና እንደማይዘን አውቀናል። ከበርም ስንገባ እግራችንን በኬሜካል አፅድተን እጃችንን በደንብ ታጠበን ስለሆን ንፅህናቸንን ከጠበቅን ኮሮና ሳይዘን ትምህርታችንን እንከታተላለን።” ብሏል።
“አንዳንድ ልጆች ኮሮና መኖሩን እየረሱ ሊያቅፉን ይሞከራሉ፤ ሁልጊዜ ብንነግራቸውም ስለሚረሱ፣ እበካችሁልጆች በድጋሚ ቤት እንዳንቀመጥ ርቀታችንን ጠብቀን መማርና መጫወት ይኖርብናል።” ብሎ መክሯቸዋል።
የሂል ሳይድ ትምህርት ቤት ተማሪ ህፃን ዜና አስረስ በበኩሉ:- “በጣም የምወደውን ኳስ መጫወት ብፈልግም ኮሮና ይዞኝ ቤት ከመቀመጥ አይበልጥብኝም ብዬ አቁሜያለሁ” ብሏል:: “ትምህርት በመጀመሩ በጣም ነው ደስ ያለኝ” የሚለው ህፃን ዜና ልጆችን ተራርቃችሁ ተጫወቱ፤ ልጆችን ይህን አድርጉ፣ ይህን አትንኩ እያሉ ሲነግሩኝ በጣም ቢያሰለቸኝም ቤት ከመቀመጥ ትዕዛዝማክበር ይሻላል” ብሏል።
“ከብዙ ወራት በኋላ ጓደኞቼን ሳገኛቸው፣ ቢናፍቁኝም አልሳምኳቸውም” የሚለው ዜና “ኮሮና ቶሎ ከሀገራችን እንዲጠፋ መምህራኖቹ የሚሉትን ምክር መስማት ይኖርብናል” ሲል መክሯቸዋል።
ስለዚህ ልጆች፣ እናንተ ልጆች ስለሆናችሁ ቁጥጥሩ ሊያሰለቻችሁ ይችላል፤ ነገር ግን አሁንም ወረርሽኙ ተባብሶ በድጋሚ ቤታችሁ እንዳትቀመጡ መጠንቀቅ ይኖርባችኋል፤ እሺ?
አዲስ ዘመን ህዳር 27/2013