ልጆች ክረምቱን እንዴት ልታሳልፉ ነው?

ልጆችዬ፣ እንዴት ናችሁ? በሳለፍነው ሳምንት የስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና መውሰዳቸው ይታወቃል። ተፈታኝ የነበራችሁ ልጆች ፈተናው ጥሩ እንደነበር ምንም ጥርጥር የለኝም። ልጆችዬ በሀገራችን የዘመን አቆጣጠር አራት ወቅቶች እንዳሉ ታውቃላቸሁ አይደል? እነርሱም መኸር፣ በጋ፣ ጸደይ (በልግ) እና ክረምት ናቸው። ከሰኔ አጋማሽ ጀምሮ ያለው ወቅት ደግሞ የክረምት ወቅት ይባላል። በዚህ ጊዜ ለተማሪዎች መደበኛ የትምህርት መርሃ ግብር ተጠናቆ ትምህርት ቤቶች ለጥቂት ወራት ዝግ ይሆናሉ። ታዲያ አንዳንድ ልጆች ይህንን የክረምት ወቅት በምን መልኩ ማሳለፍ እንዳለባቸው አያውቁም። ስለዚህ ዛሬ እንዴት ማሳለፍ እንዳለባቸው የሚጠቁም መረጃእናቀርብላችኋለን።

እንደምታስታውሱት የበጋውን ወቅት በሚገባ ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ ጥሩ ውጤት ለማምጣት ስትሞክሩ የነበረበት ወቅት ነው። በዚህም ጥሩ ውጤት እንደምታመጡ ምንም ጥርጥር የለኝም። በትምህርታችሁ ጥሩ ውጤት ያለመጣችሁ፤ ወይም ደከም ያለ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች ደግሞ የክረምት ትምህርት በመማር አልያም ታላላቆቻችሁን እየጠየቃችሁ ለቀጣዩ የትምህርት ዓመት ዝግጅት ለማድረግ የሚረዳችሁ በመሆኑ ወቅቱን በአግባቡ ተጠቀሙበት እንላለን።

የክረምት ወቅት ለእናንተ የልጆች የእረፍት ጊዜ መሆኑን ተከትሎ የተለያዩ ሥልጠናዎች ይዘጋጃሉ። ለምሳሌ ለመጥቀስ ያህል የእጅ ሥራ፣ የሥዕል፣ የሙዚቃ፣የቋንቋ፣ የኮምፒውተር እና ከቴክኖሎጂ ጋር የተያያዙጉዳዮች ላይ ሥልጠና ይሰጣሉና እናንተ ዝንባሌያችሁን በመለየት፤ እንዲሁም ከቤተሰቦቻችሁ ጋር በመነጋገርሥልጠናዎችን በመከታተል የክረምት ጊዜያችሁን

በአግባቡ ማሳለፍ ትችላላችሁ።ልጆችዬ፣ እዚህ ጋር ማወቅ ያለባችሁ ነገር ምንምመሰላችሁ? አንዳንዶቹ ሥልጠናዎች የግድ ትምህርትቤት ገብቶ መማርን የማይጠይቁ በመሆናቸው

ወላጆቻችሁን፣ ታላላቆቻችሁን እና ለእናንተ የቅርብቤተሰብ የሆኑትን በመጠየቅ ብትማሩ ብዙ ነገሮችን እንድታውቁ ይረዳችኋል።እስቲ ልጆችዬ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ? የደንአለመኖር ምን ሊያስከትል ይችላል? የዝናብ እጥረት፣የአፈር መሸርሸር፣ እና ሌሎች ችግሮች እንዲፈጠርያደርጋል ብላችሁ እንደመለሳችሁ ምንም ጥርጥርየለኝም። ስለዚህም በክረምት ወቅት ችግኞች እንዲተከሉይመከራል። በአሁኑ ወቅት በሀገራችንም በተለያዩ

ቦታዎች የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በተለያዩ ቦታዎችለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተመልክታችኋልብለን እናስባለን። እናንተም የደን አለመኖር በምድራችንላይ የሚያደርሰውን ችግር በመገንዘብ ችግሩን ለመፍታት ከወላጆቻቸሁ ጋር በመሆን የተለያዩ ችግኞችንበመትከል፤ መትከል ብቻ ሳይሆን እንዲጸድቁመንከባከብም ይኖርባችኋል። እናም ልጆችዬ እነዚህንበሚገባ ካደረጋችሁ የክረምት ወቅቱን በሚገባ አሳለፋችሁማለት አይደል?

ከነዚህ በተጨማሪም የተለያዩ ጨዋታዎችንከወንድሞቻችሁ፣ እህቶቻችሁና ከጓደኞቻችሁ ጋርበመጫወት ጥያቄ እና መልስ በማዘጋጀት ማሳለፍትችላላችሁ። ታዲያ ልጆችዬ ሰፊ ጊዜ አገኘን ብላችሁሁል ጊዜ በሞባይል ወይም በታብሌት ጌም መጫወትወይም ፊልም በማየት ጊዜያችሁን አላግባብ ማሳለፍየለባችሁም። አስተማሪ የሆኑ ነገሮችን ማየት እንኳን

ካለባችሁ ከቤተሰቦቻችሁ ጋር በምታወጡት ፕሮግራምመሠረት መሆን አለበት እሺ ልጆች።ልጆችዬ፣ ትምህርታችሁን በጥሩ ውጤትለማጠናቀቅ የተለያዩ የትምህርት እና አጋዥ መጻሕፍትንስታነቡ እንደነበር ተስፋ አደርጋለሁ። የክረምቱን ወቅትደግሞ እንደ ፍላጎታችሁ እና እንደዝንባሌያችሁ ዓይነትወላጆቻቸሁን አልያም የቅርብ ቤተሰባችሁን በማማከር

የተረት፣ የታሪክ፣ የልብ ወለድ፣ የሳይንስ የቴክኖሎጂ እናሌሎች መጻሕፍትን ብታነቡ ብዙ እውቀት ለማግኘት ያስችላችኋል። የማንበብ ልምዳችሁም ያድጋል።ሌላው ደግሞ ልጆችዬ የክረምቱ ወቅት ከወላጆቻችሁ ጋር ጥሩ ጊዜ ለማሳለፍ፣ ቤተሰብ ለመጠየቅእና ወላጆቻችሁን በምትችሉት አቅም ለማገዝ ጥሩ አጋጣሚ ነው። ታዲያ ልጆችዬ አጋጣሚውን በመጠቀምከወላጆቻችሁ ጋር በጋራ እያነበባችሁ፣ እየተረዳዳችሁ፣

እየተመካከራችሁ እና እየተወያያችሁ በደስታ ለማሳለፍአልተዘጋጃችሁም? ሌላም ጥቆማ አለን። ሀገራችን የብዙ ባህል፣ ቅርስ፣እና ታሪክ ባለቤት እንደሆነች በሚገባ ታውቃላችሁ። ታዲያ እንዲህ ያሉትን ቦታዎች ለመጎብኘት ጊዜያስፈልጋል አይደል? ክረምቱን ነጻ የሆናችሁ ልጆች በምትኖሩበት አካባቢም በርካታ ታሪካዊ ቦታዎች ካሉእነርሱን በመጎብኘት መጀመር ትችላላችሁ።የክረምት ወቅት እናንተ ልጆች ከትምህርት ርቃችሁዕረፍት ላይ የምትሆኑበት ጊዜ ነው። ታዲያ በዝናብአማካኝነት ከሚደርሱ አደጋዎች ራሳችሁን መከላከልእና መጠበቅ ይኖርባችኋል። ለምሳሌ በዝናብ ወቅት አለመጫወት፣ የውሃ መውረጃ ትቦዎች ባሉባቸው አካባቢዎችም ይሁን ወንዝ አካባቢ በፍጹም መገኘት የለባችሁም፤ እሺ ልጆች። ወቅቱ በጣም ቀዝቃዛ ስለሆነ ይህንን ታሳቢ ያደረገ አለባበስ ማድረግ ይኖርባችኋል። ልጆችዬ፣ የዛሬው ርዕሰ ጉዳያችን ክረምቱን እንዴት ማሳለፍ እንዳለባችሁ በሚገባ ይጠቅማችኋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። እናንተም ተግባራዊ እንደምታደርጉት ተስፋ አደርጋለሁ። ለዛሬው በዚህ ብንሰነባበትስ? ሳምንት በሠላም ለመገናኘት ያብቃል። መልካም የክረምት መግቢያ ወቅት ይሁንላችሁ።

እየሩስ ተስፋዬ

አዲስ ዘመን እሁድ ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓ.ም

Recommended For You