በአገራችን በኤችአይቪ/ኤድስ ዙሪያ የህዝብ ንቅናቄ ስራው ችላ መባሉን ተከትሎ ከነበረው ልምድና ተሞክሮ በመነሳት እስትራቴጂ ተነድፎ ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡ ከዚህም ውስጥ በቅንጅት በመስራት ኤችአይቪ/ኤድስን መከላከልና መቆጣጠር አንዱ ነው፡፡ በዚህ ረገድ አገራችን ትልቅ ተሞክሮ አላት ባለፉት ዓመታት ኤችአይቪን በመከላከል ረገድ የተቀመጡትን የልማት ግቦች ከማሳካት አንጻር ትልቁን ሚና የተጫወተው በቅንጅት መስራት ነው፡፡ በቅንጅት ከተጓዝን ኤችአይቪ/ኤድስን መከላከልም ሆነ መቆጣጠር አያቅተንም፡፡ ጉዳዩ የጋራ በመሆኑም የቅንጅት ጉዞ ግድ ይለናል፡፡ ይሁንና በቅንጅት መጓዙ አሁንም ቢሆን ችግር ላይ ነው፡፡ ምክንያቱም እኩል ዕየተራመድን አይደለምና ለአብነት ጥር 15 ቀን 2011 የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ_የመከላከል እና የመቆጣጠር ሁኔታ ምን እንደሚመስል መረጃ ለማግኘት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አራት ኪሎ ሳይንስ ፋኩልቲ ተገኝቼ ነበር። በሰዓቱ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ዳይሬክቶሬት ይኖር እንደሆን ጠየቅኩ ለማግኘት አልቻልኩም፤ በኋላም የስርዓተ-ዖታና የኤች. አይ.ቪ/ኤድስ ጉዳይ የሚል ታፔላ በመመልከት ወደዚያው አቀናሁ።
የስርዓተ ጾታ አገልግሎት ብቻ መኖሩንኤች.አይ.ቪ/ኤድስን በተመለከተ አገልግሎት የሚሰጥ ቢሮ በግቢው አለመኖሩን እና መቅረቱን ከስርዓተ-ዖታ ቢሮ ያገኘኋቸው_እናት ነገሩኝ። በዚህም ሁኔታ_ያልተጠበቀ እና መዘናጋት መኖሩን_ በመገረም_መታዘብ ቻልኩ። ምክንያቱም በግቢው ተማሪዎች እስካሉ ድረስ፣ የተለያዩ ማህበራዊ ግንኙነቶች እንደመኖራቸው መጠን ፣የኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ ሁኔታ በየከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አሳሳቢ መሆኑ በተደጋጋሚ ስለሚገለጽ ምንም አይነት በጉዳዩ የሚመክር ቢሮ አለመኖሩ ሊታሰብበት የሚገባ ይመስለኛል። በመሆኑም የኤችአይቪ/ኤድስ ዳይሬክቶሬት ያለዉ የአዲስ አበባው ዋና ካምፓስ ከአራት ኪሎ ሳይንስ ፋኩልቲ ጋር በቅንጅት ቢሰራ መልካም ነው ማለት ፈልጋለሁ፡፡
_ በመቀጠልም በግቢው የሚሰጠውን የኤች.አይ.ቪ ምርመራ አገልግሎት ሁኔታ ለማወቅ ወደ ተማሪዎች ክሊኒክ አመራሁ። በዚያም በነበረው የምርመራ አገልግሎት ዙሪያ መረጃ ለማግኘት ሲስተር አልማዝ ሜኖታ እና ሲስተር ያብሰራ ታምሩን አነጋግርኳቸው። በክሊኒካል ቢኤስሲ ነርስ የሆኑት ሲስተር አልማዝ ሜኖታ__በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አራት ኪሎ ሳይንስ ፋኩሊቲ የተማሪዎች ክሊኒክ ሀላፊ በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ።_በተማሪዎች መካከል ተመርምሮ የራስን ሁኔታ_ለማወቅ ያለውን ተነሳሽነትን በተመለከተም፣ ተማሪዎች ለሌላ ህክምና ሲመጡም የማነሳሳት ስራ መኖሩ፣ በተማሪዎቹም ጥሩ ተነሳሽነት እንዳለ ገልጸዋል። ነገር ግን በክሊኒኩ የመሳሪያ አቅርቦት ባለመኖሩ እየተመረመሩ እንዳልሆነና እጥረቱም ከጤና ቢሮ እገዛ ባለመደረጉ፣ሄልፕ ፕሮጀክት የሚባለውና በስድስት ኪሎ መቀመጫውን ያደረገውም ቢሮውን በመዝጋቱ፣ በግል አጋዥ ድርጅቶችም እገዛ እያገኙ እንዳልሆነም አክለዋል።
ሲስተር አልማዝ ሜኖታ_፣ “ስልጠናም እገዛም እያገኘን አይደለም፤ ኪትም የለንም፤ የተቀየረም ኪት አልመጣም፤ ስልጠናም አልወሰድንም” ሲሉ_ ገልፀዋል።_እንዲሁም አዲስ አይነት ኪት ሲመጣ አዲስ ስልጠና ስለሚያስፈልግ፤ አሁን ላይ ከሁለት ዓመት በላይ ኪት ሳይመጣ ቆይቷልም ብለዋል።_
አሁንም የምርመራ ሂደቱን በዘመቻ መልክ _ለመስራት_አጋዥ የግል ድርጅቶችን _ኪት እንዲሰጡን፣ በስልጠናም እንዲያግዙን፣ ስልጠና ባይሰጡንም እስክንሰለጥን እራሳቸው ሰራተኞ ቻቸውን አምጥተው በዘመቻ መልክ ተማሪዎችን እንዲመረምሩ የተለያዩ እርዳታ ድርጅቶችን _በመጠየቅ ላይ ነንም ብለዋል።
ሲስተር አልማዝ ሜኖታ__አክለውም፣ የቫይረሱ ሁኔታ ለማወቅ የሚቻለው ምርመራ በማድረግ ብቻ ስለሆነ ስርጭቱ ከፍተኛ ቢሆንም እንኳን አገልግሎቱን በግቢው መስጠት አልተቻለም። ተማሪዎቹን ከማስተማር ውጪም የምርመራ አገልግሎት መስጠት አልቻልንም ነገር ግን የምርመራ ኪት ባለመኖሩ እንዲሁም ስልጠናም ባለመሰጠቱ የተነሳ ከዚህ በፊት እንደሚደረገው ምርመራ እየተደረገ ባለመሆኑ የመዘናጋቱ ሁኔታ ኤችአይቪ የሌለ እያስመሰለው ነውም ብለዋል።
__ሲስተር ያብስራ ታምሩ _በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አራት ኪሎ ሳይንስ ፋኩልቲ የተማሪዎች ክሊኒክ ውስጥ በነርስነት ያገለግላሉ። _በተመሳሳይ በሰጡን መረጃ በግቢው በኤችአይቪ ዙሪያ ምንም እየተሰራ እንዳልሆነ፤ በምርመራ ኪት ዙሪያም ምንም አይነት ስልጠና እንዳልተሰጣቸው ገልጸዋል። እንደ ኬር ኢትዮጵያ፣ ዲኬቲ_ባሉት በኩል እገዛ ለማግኘት ብንጠይቅም ማግኘት አልቻልንም ብለዋል። በተለይ ዲኬቲም ካምፓስ ላይ የሚሰራውን ካምፓስ ላይፍ የሚባል ፕሮግራም ነበራቸው፤ ብንደውልላቸውም ካምፓስ ላይፍ ስላቆምን_ትንሽ ታገሱን ብለው እስካሁን መልስ አላገኘንም ብለዋል።
የተማሪዎቹን ተነሳሽነት በተመለከተም እኛበሰጠናቸው ልክ ለመመርመር ስለሚዘጋጁ፤ ወጣቶች እንደመሆናቸው መጠን ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ ስለሚሆን ተመርምረው ራሳቸውን ለማወቅ የግድ ሊነቃቁ እና የኛን እገዛ ይፈልጋሉ ብለዋል።
በመሆኑም በክሊኒኩ በኩል ባሉት ተግዳሮቶች ምክንያት ክሊኒኩ ቢኖርም የምርመራ እቃዎች፣ የኤች.አይ.ቪ ምርመራ ማድረጊያ ኪት ባለመኖሩ እንዲሁም በዚህ ዙሪያ የሰለጠነ ባለሙያም ባለመኖሩና የምክርና የምርመራ አገልግሎት መስጠት እንዳልተቻለም ገልጸዋል።
በቅርቡም_የኤችአይቪ/ኤድስ ቫይረስ በደማቸው የሚገኝ ሰዎች ላይ የሚሰራ__ቅድመ ኢትዮጵያ የተባለ የግል ድርጅት _ስልጠና ሰጥተውን በነሱ እገዛ ኪት አግኝተን፣ስልጠና ሰተውን፣__አብረናቸው ሰርተን፤ እንዲሁም በተንቀሳቃሽ ድንኳን ተደርጎ ምርመራ ለማድረግ ከክሊኒክ ይልቅ ምቹነት ይኖረዋል በሚል ማቴርያልም ድጋፍ ለማግኘት ሞክረን አልተሳካም ብለዋል።_
ሲስተር ያብስራ ጨምረው እንደነገሩን፣ የሳይኮሎጂ_ባለሙያዎችን በማማከርና ህብረ-ቀለማዊ በሆኑ ድንኳኖች በመጠቀም አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅቱ ቢኖርም የበጀት አለመኖር_ ሊገድበን ችሏል። አክለውም ለቅድመ ኢትዮጵያ ያለብንን ችግር ብናሳውቅም ይሄንን ማድረግና መርዳት እንደማ ይችሉ፣ የድንኳን ካምፒንኑን ሰርተንላችሁ ሪፖርት ለኛ መላክ ግን ይጠበቅባችኋል መባላቸውን። በክሊኒኩ ደግሞ ሪፖርት ማድረግ የሚጠበቅባቸው ለአራዳ ክፍለ ከተማ በመሆኑ ምክንያት እገዛ አላገኘንም ብለዋል። ይህም ሆኖ እገዛውን አድርጉልን ብንላቸውም እንደውላለን ብለው እስካሁን ምላሽ አልተገኘም_ብለዋል።
_ ኪት ባለመኖሩ የተነሳ ተማሪዎች መጥተው እንዲመረመሩ የማድረግ እንቅስቃሴ ምንም የለም፤ነገር ግን አንዳንድ ኬዞችን የምንጠራጠር ከሆነ የካቲት ሪፈር እንጽፍላቸዋለን። ይህ ቢሆንም እንደባለሙያ በካምፓሱ ሁሉም ተማሪ ኤችአይቪ እንዲመረመሩ ማበረታታት ተገቢ እንደሆነ ግልጽ ቢሆንም ግን ኪትም ስልጠናም ባለመኖሩ ይህ ሳይሆን ቀርቷልም ሲሉ ተናግረዋል።_
_ በቀጣይም ፍቃደኛ የሆኑ ኤንጂኦዎችን በማነጋገር ላይ ነን፤በኤችአይቪ ዙሪያ በዘመቻ መልክ ካምፒንግ አድርገን ለመስራት ሀሳብ አለን፤ በግቢው ያሉት ተማሪዎች ወጣቶች እንደመሆናቸውም በጤና ትምህርት ግንዛቤው ላይ እንዲሁም በምርመራውም ላይ ለመስራት ዝግጅቱም ተነሳሽነቱም አለን ብለዋል።
ሪፖርተራችን ውብሸት ሰንደቁ ጥር 16/5/2011 በጤና አምድ ላይ ባጠናቀረው መረጃ መሰረት የጤናው ዘርፍ ላይ ከቀረቡት ፖሊሲዎች መካከል የመድኃኒት አቅርቦትና የህክምና ቴክኖሎጂን ማሻሻል፣ የጤና ቁጥጥር ሥርዓት ማጠናከር፣ የጤና ክብካቤ ገንዘብ ምንጭ እና አጠቃቀም ማጎልበት፣ የጤና ሥርዓት አመራርና አስተዳደር ማጠናከር የሚሉት ይገኙበታል። በተጨማሪም የፖሊሲ አቅጣጫዎቹ በዋናነት የማህበረሰብ ባለቤትነትን ማረጋገጥ፣ ፍትሀዊና ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት መስጠት እንዲሁም የህብረተሰብ ጤና አደጋዎችና መሰል ክስተቶችን የሚቋቋምና ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ የጤና ሥርዓት ማጠናከር የሚሉ ይገኙበታል።
ሆኖም የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ብቻ ሳይሆን የሰው ሃይል አቅም በማዳከም አሉታዊ ተፅእኖ የሚያደርሱ እንደ ኤች.አይ.ቪ ያሉ ማህበረሰባዊ ጠንቆችን መከላከል እና ቫይረሱ ደርሶበት ከነበረው የወረርሽኝነት ደረጃ በሂደት ዝቅ ማድረግ እንዲሁም በኤች.አይ.ቪ የሚሞቱና የሚያዙ ወገኖችን መቀነስ ከምንም በላይ አስፈላጊ ነው።
የኤች አይ ቪ/ኤድስ ምርመራ አድርጎ ራስን ማወቅ አስፈላጊነትም በተለያዩ መድረኮች ሲነገር ቆይቷል፤ በህብረተሰቡ ውስጥም ግንዛቤው አለ ተብሎ ይታመናል። መመርመር ነፃ ከሆኑ ራስን አጥብቆ ለመጠበቅ፤ ኤች.አይ.ቪ በደም ውስጥ ከተገኘ ደግሞ አስፈላጊውን የህክምና ምክርና ተግባር በመፈፀም ከቫይረሱ ጋር ለረጅም ዓመት ኑሮን መምራት እንደሚያስችል መገንዘብ አስፈላጊ ነው።
የኤች.አይ.ቪ ቫይረስ በደሙ ውስጥ እንዳለ የተረዳ ሰው ራሱን አረጋግቶና ችግሩን እንደ ማንኛውም የጤና ችግር አይቶ ቫይረሱ የሚያስከ ትለውን ጉዳት ለመቀነስ እና ለመከላከል መወሰን ይኖርበታል። ቫይረሱ የሚያስከትለውን ጉዳት መቀነስና መከላከል የሚቻለው በህክምና እና በአመጋገብ እንዲሁም በባህርይ ላይ አስፈላጊ የሆኑ ለውጦችን በማምጣት ጥሩ ህይወት በመኖር ነው።
ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝ ወገኖች በሽታ የመከላከል አቅማቸውን በማጠናከር በሰውነታቸው የሚገኘውን የኤች አይ ቪ የቫይረስ መጠን መቀነስ አለባቸው። ይኸውም የአካል ብቃት እንቀሰቃሴ አዘወትሮ በማድረግ፣ አልኮል፣ ሲጋራ፣ ጫት የመሳሰሉ ጎጂ ሱሶችን ማስወገድ፣ የግልና የአካባቢ ንፅህና መጠበቅ፣ ጤና መጠበቂያ ምግቦች በአግባቡ መመገብ፣ በቂ እንቅልፍ መውሰድ አስፈላጊዎች ናቸው።
በተመሳሳይ ለአባለዘር በሽታዎች እና ለኤች አይቪ በድጋሚ ላለመጋለጥ ጥንቃቄ ማድረግ እና ስለሚገጥሙ የጤና ችግሮችም ከጤና ባለሙያዎች ጋር በግልጽ መነጋገር ተገቢ ነው።
በማጠቃለያም በየከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱና ዩኒቨርሲቲ ካምፓሶች በሚገኙ የተማሪ ክሊኒኮች የሚሰጠው የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መቆጣጠርና ክትትል ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ግልጽ ነው። በአራት ኪሎ ሳይንስ ፋኩልቲ የተማሪዎች የምርመራ አገልግሎት አለመኖር፤ በሌሎችም ተመሳሳይ ችግር ባለባቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የኤች አይ ቪ ምርመራ አገልግሎት እና አቅርቦቶች እንዲሁም ተያያዥ ድጋፎች ቢኖሩ በተሻለ በቅርበት የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ስለሚያግዝ የሚመለከተው አካል ትኩረት ሰቶ ሊሰራበት ይገባል እንላለን።
አዲስ ዘመን ጥር 19/2011
በኃይሉ አበራ