ሴቶች የህብረተሰቡ ግማሽ አካል እንደመሆ ናቸው በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ የሚኖራቸውም ተሳትፎ በዛው ልክ መሆን እንዳለበት ቢታመንም በተግባር ግን ያላቸው ተሳትፎ በሚጠበቀው ደረጃ አይደለም። በተለይም በአመ ራርነትና በውሳኔ ሰጪነት ላይ የሚገኙት ሴቶች ቁጥር ትንሽ ከመሆኑ ባሻገር በአብዛኛው በፌዴራል ደረጃ ባሉ ተቋማት የተገደበ ነው። ለዚህ ደግሞ የተለያዩ ምክንያቶች የሚጠቀሱ ቢሆንም ተገቢው ድጋፍ አለመደረጉና እድሉን ያለማግኘታቸው ቀዳሚዎቹ ናቸው።
የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር የሴቶችን መብትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በበጀት አመቱ ከያዛቸው እቅዶች መካከል የአመራርነት ክህሎትን ለማሳደግ የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል። በቅርቡም ለመጀመሪያ ዙር የተመረጡ ከዘጠኙ ክልሎችና ሁለቱ ከተማ መስተዳድሮች እንዲሁም ከፌዴራል ተቋማት ለተውጣጡ 140 ሴት አመራሮች በቢሾፍቱ ከተማ የስራ አመራር ኢንሲቲትዩት ስልጠና ሰጥቷል። ስልጠናው እጩ ሴት አመራሮች በውሳኔ ሰጪነትና በኃላፊነት ያላቸውን አቅም በማሳደግ በህግ አውጪውና አስፈጻሚው ደረጃ ተተኪ ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑንና ቀጣይነት እንደሚኖረውም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሴቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ስመኝ ውቤ ተናግረዋል።
እንደ ሚኒስትር ደኤታዋ ማብራሪያ በአሁኑ ወቅት ስልጠናው የተሰጣቸው ሴቶች በተለያዩ የአመራርነት ደረጃ ላይ የሚገኙ ሲሆኑ ወደፊት ለኃላፊነት ሲታጩ ውጤታማ እንዲሆኑ አሰልጥኖ መጠበቅ አስፈላጊ በመሆኑ ነው። በቅርቡ የፌዴራል መንግስት በወሰዳቸው እርምጃዎች በከፍተኛው የስልጣን እርከን ለውጥ ማስመዝገብ ተችሏል። ነገር ግን በመካከለኛው የአስተዳደር እርከንና በክልል፣ በዞንና በወረዳ ያለው የሴቶች ተሳትፎ በአንዳንድ ክልሎች በካቢኔና በቢሮ ሃላፊነት ደረጃ በጣት የሚቆጠሩ ቢኖሩም እንደአጠቃላይ ከአንድ ሶስተኛ በታች ነው። በመሆኑም በውሳኔ ሰጪነት የሴቶችን ተሳትፎ የማሳደግ ስራው በፌዴራል በመካከለኛው ደረጃ አመራርና በክልሎችም እታች ድረስ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።
ሴቶች በአመራርነትና በውሳኔ ሰጪነት መሳተፍ አለባቸው ሲባል ግን ለኮታ መሙያ ብቻ ሳይሆን ብቃቱና ክህሎቱ ኖሯቸው በተግባር እንዲያገለግሉ በማስቻል መሆን አለበት። በመሆኑም የአመራር ክህሎት ባህሪያትን በማዳበር በስራ ወቅት የሚገጥሙ ተግዳሮቶችን እንዴት መሻገር እንዳለባቸው ግንዛቤ ኖሯቸው ወደ ኃላፊነት መቅረብ አለባቸው። ለዚህም በየወቅቱ ወደ አመራርነት የሚመጡትን ሴቶች በትምህርትና በስልጠና መደገፍ ይጠበቃል አሁን የተሰጠው ስልጠናም ይሄን ክህሎት የሚያስጨብጥ ነው። በክልሎች በኩል ሴቶችን ወደ አመራርነት ለማምጣት የበቁ ሴቶች የሉም የሚለው ምክንያት በተደጋጋሚ ሲነሳ ይደመጣል ያሉት ሚኒስትር ደኤታዋ የዚህ ስልጠና መሰጠት ክልሎች እጩ ሴት አመራሮችን ሲፈልጉ በቅርበት የበቁ ሴቶችን እንዲያገኙ ለማስቻል መሆኑንም ተናግረዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተከታታይነት ያላቸው ሴቶችን የማብቃት ስራ የሚሰራ ቢሆንም ካለው የአቅም ውስንነት አንጻር ክልሎችም በተገኘው አጋጣሚ በራሳቸው የመደገፍና የማብቃት ስራ መስራት እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል።
ሴቶች በእናትነት ባህሪያቸው ለሙስናና ለጥቅማ ጥቅም የመጋለጥ እድላቸው ጠባብ በመሆኑ ማብቃትና እድሉን መስጠት ከተቻለ ጥቅሙ ሰፊ እንደሆነ በመጠቆም በመንግስት በኩል በሴቶች ላይ ያለው እምነት እያደገ መምጣቱንም ተናግረዋል። ይሄ እንደተጠበቀ ሆኖ የሴቶች የራሳቸው ጥረትም ወሳኝ በመሆኑ ሁሉም ሴቶች በመንግስት አልያም በየተቋማቸው የሚደረገውን ድጋፍ ብቻ ሳይጠብቁ ባሉበት ደረጃ ራሳቸውን ለማብቃት መስራት እንደሚጠበ ቅባቸውም ሚኒስትር ዴኤታዋ ጨምረው ተናግረዋል።
የሴቶች ስትራቲጂካዊ የልማት ማእከል መሥራችና ሥራ አስኪያጅ አምባሳደር ዶክተር ገነት ዘውዴ በበኩላቸው ሴቶችን በማብቃቱም ሆነ ወደ ስልጣን በማምጣቱ ረገድ እንደ ሀገር ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴዎች ቢኖሩም ብዙ መስራት ይጠበቃል ይላሉ።
አምባሳደር ገነት እንደሚሉት በሚፈለገው ደረጃ ባይሆንም ባለፉት ሀያ ሰባት ዓመታት እንደ ሀገር ተጨባጭ ለውጦችን ማስመዝገብ ተችሏል። ለዚህ ደግሞ ከህገ መንግስቱ ጀምሮ የተቀመጡት የሴቶችን መብቶች የሚያስጠብቁና ተጠቃሚነታ ቻውን የሚያረጋግጡት ህጎች ትልቅ ሚና አላቸው። የኢፌዴሪ ህገ መንግስት እስካሁን ከነበሩት ህገ መንግስቶች በተለየ የሴቶች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የተናጥል መብቶችን አስቀምጧል።
ህገ መንግስቱ እንደ የቡድን መብቶችን ስለሚያረጋግጥ በግለሰብም ደረጃ ሆነ እንደ ቡድን ሴቶች በሴትነታቸው ያለባቸውን ችግር ለመፍታት በር ከፍቷል። ይህንንም ተከትሎ የሴቶችን አቅም ለመገንባትና የሚደርስባቸውን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ የሚያስችሉ ተቋማት በሀገር አቀፍ ደረጃና በየክልሎቹም እንዲሁም በማህበራት ደረጃ በስፋት የተቋቋሙ ሲሆን፤ እነዚህም የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የራሳቸው ድርሻ አላቸው። ሴቶችን ወደ አመራርነት ለማቅረብ ግን ራሱን የቻለ ተከታታይነት ያለው ድጋፍና ክትትል ያስፈልጋል።
በአሁኑ ወቅት በፓርላማው የሴቶች ተሳትፎ 39 በመቶ ደርሷል። ይሄ ደግሞ በአፍሪካ ከሩዋንዳ ቀጥሎ ሁለተኛው ሲሆን ሀገሪቷን በዓለም ከቀዳሚዎቹ አስር ሀገራት ተርታ የሚያስልፋትም ነው። በቅርቡ ደግሞ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የሴቶችን ተሳትፎ ሃምሳ በመቶ ማድረስ ተችሏል። ይሄ እንዳለ ሆኖ በክልል ዞንና ወረዳ ያለው ተሳትፎ ሲታይ ግን በጣም የተራራቀ ሲሆን ይህም በታዳጊ ክልሎች ይበልጥ እየሰፋ ይሄዳል። በክልሎችም በከተማ ደረጃ ብሎም በዞንና በወረዳ ደረጃ ሲታይ ቁጥሩ በእጥፍ እየቀነሰ ይመጣል። በመሆኑም እነዚህን ሁሉ ክፍተቶች ለመሙላት በጥናት ላይ የተመሰረቱ ተከታታይነት ያሏቸው ስልጠናዎችን መስጠት ይጠበቃል።
የሴቶች ጉዳይ የህብረተሰብ፣ የባህልና የአመለካከት ችግር በመሆኑ በመንግስት መዋቅርና ህግ በማውጣት ብቻ የሚፈታ አይደለም። በመሆኑም ሴቶች ራሳቸውን ከችግር ለመከላከል፣ መብታቸውን ለማስከበርና እኩልነታቸውን ለማረጋገጥ በተግባር በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ አሁንም ድረስ የሚገጥሟቸው በርካታ ተግዳሮቶች አሉ። ይህም በጊዜ ሂደት ሴቶች ራሳቸው በውሳኔ ሰጪነትና በአመራርነት ያላቸው ድርሻ እየጨመረ ሲመጣ ችግሮቹን ይቀንሳቸዋል ተብሎ ይታሰባል። ለዚህ ደግሞ ሴቶች እንደሚችሉ ታምኖ ቦታውንና እድሉን እንዲያገኙ ሁኔታዎችን ማመቻቸትና መደገፍ ይገባል ይላሉ።
አምባሳደር ገነት ጨምረው እንደተናገሩት ከቤታቸው ውጪ ስራ የሚሰሩ ሴቶች ወደ ቤት ሲመለሱም በርካታ ስራዎች ይጠብቋቸዋል። አንዳንድ ተቋማት ስብሰባ ሲያካሂዱ በቅዳሜና እሁድ እንዲሁም በምሽት ይሆናል፡፡ እነዚህ ሁሉ ለወንዱ የተመቻቹ ሲሆኑ ለሴቶቹ ግን የራሳቸው ጫና ያለባቸው ናቸው፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ የባህልና የሃይማኖትም ተጽእኖ አለ። በመሆኑም በመንግስት ከሚደረገው የማብቃትና ወደ ኃላፊነት የማምጣት እንቅስቃሴ በተጓዳኝ በቤት ውስጥ ያለባቸውንም ጫና ለመቀነስ እንደ ማህበረሰብም ግንዛቤ በመፍጠሩ ረገድ መሰራት ያለባቸው ነገሮች መኖራቸውንም ጠቁመዋል።
«የሚሰጠው ስልጠና በኃላፊነት ደረጃ ያሉትን ለማሳደግ ብቻ ሳይሆን፤ ወደ ሃላፊነት ማምጣትንም ታሳቢ ያደረገ መሆን አለበት» የሚሉት ደግሞ የስልጠናው ተካፋይ የሆኑት በጋምቤላ ክልል በወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ቢሮ የሰው ሀብት ቡድን መሪ ወይዘሮ ኦጂሉ ሜዶ ናቸው።
ወይዘሮ ኦጂሉ እንደሚሉት እስካሁን በፌዴራልም ሆነ በክልል ስልጠናዎች ሲሰጡ በዝቅተኛ ደረጃም ቢሆን ኃላፊነት የተሰጣቸው ሴቶች ተመርጠው ነው። ይሄ ደግሞ ትንሽ እድል ያገኙትን የበለጠ የሚያሳድግ ሲሆን ከስር ያሉትን አዳዲሶቹን ለማምጣት ግን በር የሚከፍት አይሆንም። በጋምቤላ ክልልም አጠቃላይ የሴቶች ተሳትፎ ዝቅተኛ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ከአስተዳደር ውጪ በተለያየ የስራ ድርሻ ያሉት ሴቶች ራሳቸውን የሚያበቁበት የትምህርትም ሆነ የስልጠና እድል ሲያገኙ አይታይም። በመሆኑም የፌዴራል መንግስት ለእኛ እንዳመቻቸልን ሁሉ የየክልሉ ሃላፊዎችም ከስር ጀምረው በየደረጃው ላሉት ሴቶች ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ተናግረዋል።
በተመሳሳይ የስልጠናው ተካፋይ የሆኑት ከአፋር ክልል ዳሊ ፋጊ ወረዳ በማህበራት ማደራጃ የስራ ሂደት አስተባባሪ የሆኑት ወይዘሮ ፋጡማ አብዲ በበኩላቸው፣ በክልላቸው ያለው የሴቶች የአመራርነት ተሳትፎ እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን ይናገራሉ።
«በአሁኑ ወቅት በስራ ሂደት ደረጃ በወረዳው አመራር ሴት እኔ ብቻ ነኝ» የሚሉት ወይዘሮ ፋጡማ፣ እንደ ክልልም በሴቶች ጉዳይ ላይ ሳይቀር የሚሰሩት በጣት ከሚቆጠሩ በቀር አብዛኛዎቹ ወንዶቹ ናቸው። ለዚህ ደግሞ እንደ ክልል ብዙ የተማሩ ሴቶች አለመገኘት አንዱ ምክንያት ነው።
በክልሉ ጥቂት በትምህርት ላይ ያሉ ሴቶች ቢኖሩም ስራ ከመጀመራቸው በፊት ወይም አቋርጠው ትዳር የሚመሰርቱ በመሆኑ እንኳን በኃላፊነት ደረጃ በመደበኛ ሰራተኝነት የሚገኙትም ቁጥር በጣም ጥቂት ነው። በመሆኑም እንደ ክልል ለውጥ ለማምጣት ከመደበኛ ትምህርት ቤት ጀምሮ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ገብተው እስኪመረቁ ድረስ ተከታታይነት ያለው ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል።
አዲስ ዘመን ጥር 18/2011
ራስወርቅ ሙሉጌታ
commander des tablettes en ligne Landsteiner Beinasco medicijnen zonder
voorschrift verkrijgbaar in Zwitserland
к чему снится шерсть во рту лучшие сериалы про магию и волшебство с высоким рейтингом что если снится известный человек
сон большие алмазы как правильно наблюдать
за солнцем кратко
көшпелілер отырықшы елдерден қандай заттар алып отырды, жартылай көшпелі мәдениет
көкірек аралық анатомиясы,
көкірекаралық топография теле2 мобайл легендс, эмоции mobile
legends машина сбоку, группы грузоперевозок
achat en ligne de médicaments à Bruxelles sandoz Milazzo farmacia que vende medicamentos
I’m truly enjoying the design and layout of your blog. It’s a
very easy on the eyes which makes it much more pleasant for me to
come here and visit more often. Did you hire out a designer to create your
theme? Excellent work!
үш таро картасы бар жағдайға арналған таро орналасуы иә жоқ тасмола мәдениетінің басты ерекшелігі,
тасмола мәдениеті кім зерттеді қазақстанның халықаралық
қауымдастықтағы орны, қазақстан әлемдік қауымдастықта презентация ауызашар уақыты шу, шу кесте ораза 2023
online apotheek in Nederland die medicijnen verkoopt Liomont Magdeburg Acheter médicaments sans prescription en France
ашыған сүт өнімдері, сүт өнімдері пайдасы ашу бар жерде ақыл тұрмайды, сөз қуған пәлеге жолығады жел туралы тақпақ балабақша, жел туралы
жұмбақ ұлттық сана сезім дегеніміз не, ұлттық сана сезімін оятуға үлесі
doxxim – yuragim sen deya mp3 skachat, doxxim – eslama meni mp3 skachat
магистратура өтініш беру, ұлттық тестілеу орталығы өтініш беру қоршаған ортаның денсаулыққа әсері
эссе, қоршаған ортаның ластануы эссе греческий йогурт фудмастер калорийность, греческий йогурт состав
кенесары қайда жерленген, кенесары мінездеме разливное пиво цена
за литр, разливное пиво виды перифериялық
тамырлардағы пульсті анықтау,
пульсті өлшеу алгоритмі сен кімсің мектеп 2015 10 бөлім
қазақша, сен кімсің мектеп 2015 1 бөлім қазақша
аркан дьявол в отношениях
матрица судьбы, как проработать 15 аркан в отношениях сахасрара
физика 18 значение, сахасрара
энергия 10 значение какой аркан
отвечает за отношения
к чему снится выбирать макароны божья матерь неувядаемый цвет молитвы
әдістемелік құрал жасау, оқу әдістемелік құралға қойылатын талаптар қазіргі замандағы
әйел затының қоғамдағы рөлі қандай, әйелдердің қоғамдағы рөлі эссе дара етістік, дара етістік күрделі етістік скачать песни марсель казахстан, ұланғасыр ками скачать песни
Usually I do not learn post on blogs, but I wish to say that this write-up very forced me to take a look at and
do so! Your writing taste has been surprised me. Thank you, quite
nice article.
Comprar medicamentos con entrega rápida Zentiva Vlijmen achat de somnifères à base
de médicaments
работа дома онлайн спб заработать денег 1 рублях
сколько заработать на прогнозах без вложений закрытая система отопления
многоквартирного дома принцип работы