በአለም ላይ ከ3000 በላይ የእባብ ዝርያዎች ይገኛሉ።
• እባቦች ከአውስትራሊያ አህጉር ውጪ በሁሉም አህጉሮች የሚኖሩ ተሳቢ እንስሳት ናቸው።
• እባቦች አፋቸውን እስከ 150 ዲግሪ መክፈት ይችላሉ። ይህ ደግሞ የራሳቸውን አካል ከ75 እስከ 100 እጥፍ የሚሆን ነገርን ለመዋጥ ያስችላቸዋል።
• እባቦች ምግቦችን የሚመገቡት እንደማንኛውም እንስሳት ሳይሆን በቅድሚያ ውጠው በማበስበስ ሂደት ነው።
• እባቦች በመደበኛነት ምላሳቸውን እንደመተንፈሻ አካል ይጠቀሙበታል።
• እባቦች እንደ ሰው እና እንደ ሌላ እንስሳት ሳይሆን አካላቸውን በቆዳ የሚሸፍኑት በሂደት ነው።
• አንዳንድ እባቦች በከፊል በቆዳቸው የሚተነፍሱ ሲሆን፤ ይህም በውሃ ውስጥ ጠልቀው እንዲገቡ ያግዛቸዋል።
• በምድራችን ላይ ከ700 በላይ መርዛማ እባቦች የሚኖሩ ሲሆን፤ መርዛቸውን በዋናነት እራሳቸውን ለመከላከል ይጠቀሙበታል።
• በአለም ላይ በርካታ ሰዎች እባብን የሚፈሩ ቢሆንም በየአመቱ በእባብ ተነድፈው ከሚሞቱ ሰዎች ይልቅ በንብ ተነድፈው የሚሞቱት ሰዎች ይበዛሉ።
• 70 በመቶ የሚሆኑት የእባብ ዝርያዎች እንቁላል በመጣል የሚራቡ ሲሆን፤የተቀሩት 30 በመቶው ደግሞ ዘራቸውን የሚተኩት በመዋለድ ነው።
• በአለም ላይ ፈጣን የእባብ ዝርያዎች በመባል የሚታወቁት ጥቁር ማምባ የሚባሉት ሲሆኑ፤ በሰዓት እስከ 20 ኪሎ ሜትር መሮጥ ይችላሉ።
• በአለም ላይ አጭር የእባብ ዝርያዎች በራሚኒ ብሊንድ በመባል የሚታወቁት ሲሆኑ፤ ቁመታቸው ሁለት ኢንች ብቻ ነው።
• በብራዚል አንድ ደሴት ውስጥ በአንድ ስኩዌር ሜትር መሬት ላይ በአማካኝ አምስት እባቦች ይገኛሉ።በዚህም የተነሳ ወደዚህ ደሴት ማንኛውም ሰው እንዲሄድ አይፈቀድለትም።ቦታውም አደገኛ ቦታ በመባል ተፈርጇል።
• ባለ ሁለት ራስ እባብ ዝርያዎች በምድራችን ላይ የመከሰት እድላቸው አነስተኛ ነው።ምንም እንኳን የጋራ አካል ቢኖራቸውም ምግብ በሚመገቡበት ጊዜ ከባድ የሚባል ድብድብ ያደርጋሉ።
አዲስ ዘመን ሀምሌ 19 ቀን 2012 ዓ.ም
በሞገስ ፀጋዬ