“ሃገር በሰላም ሠርቶና ተኝቶ እንዲኖር አንድ የመከላከያ ሠራዊት የአንበሳ፣ የንስር፣ የላምና የጉንዳን ባህሪ ያለው እንዲሆን ይጠበቅበታል፡፡ ዊኒስተን ቸርችል ሌሊት በሰላም ተኝተን የምናነጋው እኛን ሊጎዱ የሚመጡትን ሁሉ ለመቋቋም ዘወትር ዝግጁ የሆኑ የሰራዊት አባላት ስላሉን ነው” እንዳሉት፡፡
አንድ የመከላከያ ሰራዊት እንደ አንበሳ የማይበገርና ጀግና መሆን አለበት፡፡ ለኢትዮጵያ ወታደር መቼም ስለጀግንነት አይነገርም፡፡ ጀግንነት ጀብደኝነት አይደለም፡፡ ለምን? ማንን? እንዴት? እንደሚዋጉ ከማወቅና ከማመን የሚመጣ ቆራጥነት ነው ጀግንነት የሚባለው፡፡ ንስር ከአዕዋፍ ሁሉ እጅግ የላቀ እና የመጠቀ ነው፡፡ ሰራዊታችን እንደንስር ነው ስንል በእውቀት፣ በክህሎት፣ በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂና በስልጠና ከሚፈለገው ደረጃ በላይ የላቀ ነው ማለታችን ነው፡፡ ሃገራችንን፣ ህዝባችንንና ጥቅሞቻችንን ሁሉ በሚፈለገው ልክ ለማስጠበቅ የሚችል ሰራዊት እንዲኖረን ልህቀት አንዱ መለያችን መሆን አለበት፡፡
በወታደራዊ ሳይንስና ዲስኘሊን የታነፀ፤ ከፍተኛ ህዝባዊ ወገንተኝነት የተላበሰ፤ በአወቃቀሩ የሁሉም የሃገራችን ህዝቦች አሻራ ያረፈበት፤ ህገ-መንግስቱንና የሃገር ሉዓላዊነት በመጠበቅ ረገድ ሙሉ እምነት የሚጣልበት ጠንካራ የመከላከያ ኃይል ለመፍጠር ስንተጋ የቆየነው ይህንን ልህቀት ለማምጣት ነው፡፡ የመከላከያ ኃይላችን በእውቀት፣ በመሣሪያ፣ በክህሎት፣ በአደረጃጀት፣ በዘመናዊነት፣ በንቃትና በብቃት የላቀ፤ ከሚገጥሙት ችግሮች በላይ የመጠቀ ከሆነ ችግሮቹን እንደንስር ከላይ ወደታች እንጂ ከታች ወደ ላይ አያያቸውም” የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር መምሰል ያለበትን አስመልክቶ ይህን አባባል የተናገሩት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶክተር ዓብይ አህመድ ናቸው።
እውነት ነው ሰላም ወጥተን ሰላም የምንገባው፣ የአገራችን ሉዓላዊነትና ድንበር ታፍሮና ተከብሮ የኖረው፣ ታላቁ የህዳሴ ግድባችንም ሆነ ሌሎች አጓጊ የመሰረተ ልማት አውታሮቻችን ያለምንም ስጋት እየተቀላጠፉ ያሉት ላብ ሳይሆን ደማቸውን ለመለገስ ቆርጠው በተሰለፉና ይህንን በተግባር ባረጋገጡ ውድና ብርቅ የመከላከያ ሰራዊት አባላቶቻችን አኩሪ መስዋዕትነት ነው።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የአገሪቱን ድንበር ከማንኛውም ጥቃትና ወረራ በመጠበቅ፣ ማናቸውም
ተፈጥሯዊም ሆነ ሰው ሰራሽ አደጋ በዜጎቻችን ላይ በደረሱ ጊዜ አስተማማኝ ክንድ በመሆን፣ እንደ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ባሉ አገር የሚለውጡ ፕሮጀክቶች ላይ በቦንድ ግዥም በሌሎችም ድጋፎች ቀዳሚ ተዋናይ በመሆንና ከአገርም አልፎ የአፍሪካዊ ወንድም እህቶቻችን ደህንነት አደጋ ላይ ሲወድቅ ፈጥኖ ደርሶ በመታደግ በደም የተጻፈ አኩሪ ገድል ያለው አንጸባራቂ ሰራዊት ነው።
የአድዋና የተለያዩ የነጻነት ትግሎችና ድሎች መንፈስ የወለደው የመከላከያ ሰራዊታችን በዘመናት ቅብብሎሽ ውስጥ የራሱን አኩሪ አሻራ እያስቀመጠና ራሱን እያደሰ የመጣ ሰራዊት መሆኑ ከማንም ሊደበቅ አይችልም። ለዚህ አኩሪ ታሪክ የበቃው ደግሞ መሰረቱን ሕዝባዊ በማድረጉና በየጊዜውም እንደየሁኔታው ራሱን እያሻሻለና እያዳበረ በመምጣቱ ነው። ይህ አኩሪ ገጽታው አሁንም በለውጡ ዘመን ተጠናክሮ ቀጥሏል።
የመከላከያ ሰራዊቱ አመራርና አባላት በሁሉም ረገድ ተልዕኳቸውን የተረዱ፤ ኃላፊነታቸው ለመላው ህዝባቸው መሆኑን የተገነዘቡ፤ ከሙስና፣ ከዘረኝነትና ከግላዊ ጥቅም የራቁ፤ አርዓያዎች የሆኑ፤ በእውቀት፣ በክህሎት፣ በብቃት፣ በጀግንነትና በዲስፕሊን የላቁና ጠንካራ ዲስፕሊን ያለው ሠራዊት ማፍራትን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የሪፎርም ስራዎችን በመካሄድ ላይ ይገኛል። ሪፎርሙም እጅግ ስኬታማ እንደሆነና የሰራዊቱን ግዳጅ የመፈጸም አቅም በከፍተኛ መጠን እያሳደገው ስለመሆኑ የሰራዊቱ አመራሮችና አባላት በየጊዜው እየገለጹት ያለ እውነታ ነው።
ይሄው የሪፎርም ሥራ አሁንም በጠነከረ መልኩ ቀጥሎ የአገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ ያገናዘበና አለምአቀፋዊ ዝማኔን መሰረት ያደረገ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ግንባታ ስትራቴጂ ሰነድ መዘጋጀቱ ተገልጿል። ሰነዱም ተቋሙ ህግና ስርዓትን የሚያስጠብቅ እንደመሆኑ ዘላቂነት ባለው መልኩ ለየትኛውም አካል ሳይወግን ገለልተኛ ሆኖ እንዲያገለግል የሚያግዘውም ነው። መከላከያ ሰራዊቱ በሕብረ ብሄራዊነት ላይ ይታይበት የነበረውን እንከን ለማስተካከልም ዕድል የሚሰጥና ዓለም አቀፋዊ ዝማኔን የሚያጎናጽፈው ነው።
በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ እየተሰሩ ያሉ አጠቃላይ የሪፎርም ሥራዎች ሠራዊቱ እውነተኛ የኢትዮጵያ ወኪልና ከአገር ውጪ ለማንም የማይወግን እንዲሆን፣ ዓለምአቀፋዊ ብቃትን በመጎናጸፍም ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ልዕልና ወሳኝ ክንድ ያደርገዋል!
አዲስ ዘመን ሰኔ 16/2012
የዘመነና ጽኑ መከላከያ ለኢትዮጵያ ልዕልና!