በተዛቡና አግባብነት በሌላቸው የፈጠራ ትርክቶች በተፈጠረ ፍርሐት ሁለንተናው በጠላትነት መንፈስ የተሞላን፣ ይህንን መንፈስ አሸንፎ ለመውጣት ሌት ተቀን የሚዳክር ወዳጅን ከመታደግ የተሻለ በጎነት አይኖርም። ይህን ወዳጅ አስከ መጨረሻው ከፍርሐቱ ነፃ ለማውጣት ያለው አንድና አንድ አማራጭ ደግሞ ፍርሐቱን ከምንጩ ማድረቅ ነው። ለችግሩ አልፋና ኦሜጋ መፍትሔውም ይሄው ነው። ከዚህ ውጪ የሚወሰዱ የመፍትሔ ዕርምጃዎች ፍርሐቱን ከፍ በማድረግ ጠላትነትን ከማሳደግ ያለፈ ፋይዳ አይኖረውም።
እኛ ኢትዮጵያውያን እንደ ሀገር እንደ ህዝብም ከግብፅ የቤተ መንግሥት ሰዎች ጋር በዘመናት መካከል እያጋጠመን ያለው ተግዳሮት ከዚህ የተለየ አይደለም። በአንድ በኩል “የዓባይ የግብፅ የፈጣሪ ስጦታ ናት። ያለ አባይ ግብፅ አትኖርም” የሚል የተሳሳተ ትርክት የፈጠረው የወንዙን ውሃ የመጠቀም ብቸኛ ባለመብት የመሆን መነሳሳት እና መነሳሳቱን አካል ለማልበስ በግብፅ በኩል ለተሄደባቸው የክፋት መንገዶች እኛ ኢትዮጵያውያን እንደ ሀገር እንደ ህዝብም ብዙ ዋጋ ከፍለናል።
በዚህ ብዙ ታሪክና ስልጣኔ ባለቤት የሆነውን የግብጽን ህዝብ ብቻ ሳይሆን ፈጣሪን በሚያሳንስ የተሳሳተ አመለካከት አዕምሯቸው የተያዘው የግብፅ የቤተ መንግሥት ሰዎች፤ ትውልዶችን በዚህ አስተሳሰብ ለመቅረጽ የሚያደርጉት ጥረት በሀገራቱ ህዝቦች መካከል ለዘመናት የቆየ ያልተገባ አለመተማመን ፈጥሯል። ይህ አለመተማመን ደግሞ ወደ ለየለት ጠላትነት እንዲያመራ ቀን ተሌት እየተጉ ይገኛሉ።
በሌላ በኩል ደግሞ በተፈጠረው የተሳሳተ የጥላቻ መንፈስ በመነዳት በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያውያን ላይ ዘመናት ያስቆጠሩ የጥፋት ተግባራትን ሲያከናውኑ ቆይተዋል። ዛሬም ቢሆን በዚሁ ተግባራቸው እንደገፉ ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ ሀገሪቱንና ህዝቦቿን በተደራጀ መልኩ ጥላሸት ሲቀቡ ውለው ያድራሉ።
በሀገሪቱ ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖር፤ ከሰላምና መረጋጋት ልማት እንዳይመጣ ፣ ከልማት ወደ ብልጽግና እንዳንሸጋገር የአባይ ውሃ ጉዳይ ትልቁ ተግዳሮታችን ሆኗል። ሰላም ካገኙ ወደ ልማት ይሄዳሉ፣ ልማት ከጀመሩ ወንዞቻቸውን ይጠቀማሉ፣ ወንዞቻቸውን ከተጠቀሙ እኛ እና የኛ ስግብግብ ፍላጎት አደጋ ውስጥ ይገባል በሚል ስጋት የምናልማቸውን ሕልሞች ቅዠት ለማድረግ ዘመናት ያስቆጠሩ የአመጽና የክፋት ሥራዎችን በራሳቸው እና በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ለዚህ እኩይ ተግባራቸው መሳሪያ በሆኑ ኃይሎች ሲጠቀሙ ቆይተዋል። ዛሬም ለመጠቀም ላይ ታች እያሉ ነው።
ከአብዛኞቹ የሀገራችን የጦርነትና የግጭት ታሪኮቹ በስተጀርባ የግብፅ የቤተመንግሥት ሰዎች ረጃጅም እጆች ለማየት ብዙ የሚያስቸግር
አይደለም። ነገሮችን በተረጋጋና በሰከነ አዕምሮ ለመመርመር ዕድሉን ላገኘ ኢትዮጵያዊ ደግሞ የበለጠ ግልጽ ነው።
ትልቁ ተግዳሮት ግን ኢትዮጵያውያን እውነታውን በሰከነና በተረጋጋ አዕምሮ ማየት እንዳይችሉ ዘመናችንን በሙሉ ባለመረጋጋትን በሁከት እንዲሞላ ማድረጋቸው፤ ይህንን እንደ አንድ ትልቅ ታሪክ ባለሀብት እንደሆነ ህዝብ መረዳት አለመቻላችን ነው።
በተሳሳተ ትርክት ጠላት የሆኑትን የጠላቶቻችንን ስውርና ግልጽ ሴራ ቆም ብለን ከማየት ይልቅ እነሱም በሚፈጥሩልን የሁከትና ያለመረጋጋት ማእበል ውስጥ ዋና ተዋናይ በመሆን በራሳችን ዛሬዎችና ነገዎች ላይ ፍጹም በሆነ መሳት በአመጻ መሰለፋችን እና በዚህም ብዙ ትናንቶችን ለመኖር መገደዳችን ነው።
በእርግጥ የግብፅ የቤተ መንግሥት ሰዎች ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያውያንን ጠላት አድርጎ በመሳልና ከዚያም በላይ በመስበክ የሄዱበት መንገድ ረጅም ከመሆኑ፤ እስከ ዛሬ ያስገኘላቸውም ውጤት በእነሱ መመዘኛ ውጤታማ ተደርጎ ቢወሰድም በሀገራቱ ህዝቦች መካከል ከፈጠረው አለመተማመንና አለመተማመኑ ከፈጠረው ጥላቻ አንጻር ትልቅ ኪሳራ እንደሆነ መጪው ዘመን ምስክር ሊሆን እንደሚችል መገመት የሚከብድ አይሆንም።
ይህን በዘመናት ውስጥ የደነደነና አካል ለብሶ የቆመን የሳተ አስተሳሰቡ ከግብፃውን እና ከግብፅ ቤተ መንግሥት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ እና በሰላም ለመኖር ግብፃውያንን ከፍርሐታቸው መታደግ የኛ የኢትዮጵያውያን በተለይም ደግሞ የዚህ ትውልድ ታላቅ ኃላፊነት ነው።
ባልተገባ ፍርሐትና ቀውስ ውስጥ ያለን ወንድምህን ነፃ በማውጣት የተገባለትን ነፃ ህይወት እንዲኖር ከማስቻል የበለጠና የተገባ የወዳጅነት ውለታ የለም። በተለይም እኛ ኢትዮጵያውያን ካለን ትልቅ የሞራል ልእልና አንጻር በብዙ ልንተጋበት የሚገባ እውነታ ነው።
ለዚህ ደግሞ የጀመርነውን የህዳሴ ግድብ እንደ ጀመርነው በትጋትና በአርበኝነት ስሜት መጨረስ ይጠበቅብናል። ይህንን በማድረግም ግብፃውያን ውንድሞቻችን ዘመናት እንቅልፍ አጥተው የሄዱበትን የጥፋት መንገድና መንገዱ በወንድሞቻቸው ላይ የፈጠረውን ውስብስብ ችግር ተረድተው ንሰሐ የሚገቡበትን እውነተኛ ዕድል መፍጠር እንችላለን።
በጠላትነት መንፈስ ከሚፈጠር ስጋት የተነሳ በዘመናት መካከል የባከነውን አቅማቸውንና እውቀታቸውን ሀገራቸውን የተሻለች ሀገር ለማድረግ፤ ከዚህም ባለፈ በወንድማማችነት የትብብር መንፈስ ለዘመናት ያጣነውን የትብብር ትሩፋቶችን ለማግኘት እና ለማጣጣም የሚያስችል ይሆናል።
የግብፅ ቤተ መንግሥት ሰዎችን ይህ የተሳሳተ ትርክት የፈጠረውን የጠላትነት መንፈስ የፖለቲካ አቅም ከማድረግ ወጥተው ለእውነተኛው የግብፅ ህዝብ ፍላጎት ራሳቸውን አስገዝተው፤ ለግብፃውያን ወንድሞቻችን አዲስ የፖለቲካ ስርዓት ለመፍጠር የተሻለ ዕድል ይፈጥርላቸዋል። በዚህም የግብፅ ወንድሞቻችን የተሻሉ ዛሬዎች ባለቤት ይሆናሉ።
ከዚህ ተጨባጭ አውነታ በመነሳት ለራሳችን ሰላምና መረጋጋት፤ ከዚህም በላይ ለግብፃውያን ወንድሞቻችን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ለመክፈት የታላቁን የህዳሴግድብ ግንባታ በቁርጠኝነት መጨረስ፤ ለዚህ የሚሆን አቅምና ጉልበታችንን ያለስስት ማበርከት ይጠበቅብናል፡፡ ለመጪው ትውልድም ያለን የከበረ ስጦታም ይሄው ነው!
አዲስ ዘመን ሰኔ 15/2012
ኑ አባይን በመገደብ ሰላምና ብልጽግናችንን እናጽና!