ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የእያንዳንዱ ዜጋ አሻራ ያረፈበት ፤ ወደፊት የሀገራችን ዕድገት ተስፋ ፣ ድህነታችንን እንቀርፍበታለን ብለን በጉጉት የምንገነባው አንጡራ ሀብታችን ነው። ከዛሬ ነገ አለቀ ብለን የምንጠብቀው፣ በገንዘባችንና በእውቀታችን ያለማንም ደጋፊና አጋዥ ኃይል የምንገነባው የዚህ ዘመን የጀግንነት ታሪካችን አንዱ ማሳያ አርማችንም ነው። ይህንን ታሳቢ ባደረገ መልኩ በአሁኑ ወቅት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በተጠናከረ መልኩ እየተሰራ ይገኛል። የሲቪል ኢንጅነሪንግ ሥራው 87 በመቶ ፣ የብረታብረት ሥራዎቹ ከ 31 በመቶ በላይ ፤ የኤሌክትሮ ሜካኒካል፣ የተርባይንና የጀነሬተር ተከላ ሥራዎች አፈጻጸም ደግሞ 45 በመቶ ደርሷል። ይህም አጠቃላይ የፕሮጀክቱን አፈጻጸም 74 በመቶ አድርሶታል።
ይሁን እንጂ በስግብግብነት መንፈስ ተፈጥሮ በለገሰችን ፣ በራሳችን ጥረት ልናሳካውና ልንጠቀምበት የምንገነባውን የህዳሴ ግድብ ግብጽ ለማጨናገፍ ላይ ታች በማለት ላይ ትገኛለች። ኢትዮጵያ 86 ከመቶ ከምታመነጨው ከዚሁ ሀብቷ ተጠቃሚ እንዳትሆን ለማድረግና አሁንም ዕቅዷን ለማደናቀፍ ከምታደርገው የመሰሪነት ተግባሯ አልተቆጠበችም። ይልቁንም የዓለም ሀገራትን በማሳሳት የቀኝ ግዛት ስምምነቶችን መነሻ በማድረግ ለማሳመን ዛሬም ሩጫዋን ቀጥላለች።
አልተሳካላትም እንጂ ግብጽ ከመነሻውም ግድብ የመገንባት አቅም እንዳይኖረን ብዙ ጥራለች፤ ለጋሽ ሀገራት ድጋፍ እንዳያደርጉልን አድርጋለች። በራሳችን አቅምም እንዳንጀምር፣ የጀመርነውን እንዳንቀጥል ለማድረግም ስትወጣ፤ ስትወርድ ቆይታለች። ኢትዮጵያን ማዳከምና ማጠልሸት ዘላቂ ግቧ አድርጋ ስትሰራም ከርማለች ። ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ የተፈጥሮ ሀብቷ ተጠቅማ ሀገሯን እንዳታለማ ፣ ህዝቧን ከድህነት እንዳታወጣ አንዴ ለአሜሪካ ፣ ሲቀጥል ለመንግሥታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ሌ ላ ጊዜ ደግ ሞ ለአረብ ሀገራት በውሸት የተለ ወሰ ውትወታዋን አሰ ምታለች።
ይሁንና ይህ መንገድ የማያዋጣ ነውና ኢትዮጵያ ጉዳዩ አፍሪካዊ መፍትሄ እንዲፈለግለት ነው የምትሻው። የራሳችንን ጉዳይ
በራሳችን የመፍታት የሰለጠነ መንገድ መከተል እንዳለብንም በጽኑ ታምናለች። ሆኖም ግን ግብጽ በአንድ በኩል እየተደራደረች በሌላ በኩል ጉዳዩን ለመንግሥታቱ የጸጥታው ምክር ቤት ለመውሰድ የምታደርገውን ጥረት አሁንም አላቆመችም ። ይሄ ግን የትም ሊያደርሳትና እኛንም ከዓላማችን ዝንፍ ሊያደርገን አይችልም።
ግብጽ አንዴ ግንባታው የጥራት ችግር አለበት ስትልና ይሄም በባለሙያዎች እና በዓለም አቀፍ የቴክኒክ አጥኚዎችና ባለሙያዎች ተፈትሾ ፉርሽ ሲሆንባት አሁን ደግሞ በኃይል እና በጦርነት እንደምትገፉበት በየመገናኛ ብዙሀኑ ዛቻና ማስፈራራቷን ቀጥላለች።
ይሄንን የግብጽ ዛቻና ማስፈራራት ከምንም ሳንቆጥር ዛሬም እንደትናንቱ በአቋማችን ጸንተን መቀጠል አለብን። ኢትዮጵያ ዛሬም እንደትናንቱ ማንንም የመጉዳት ዓላማ ሳይኖራት የጋራ ተጠቃሚነት ላይ ቆማ የግድብ ግንባታውን ታካሂዳለች። የውሀ ሙሌት ሥራዋንም በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንደምታካሂድ ለሁሉም ግልጽ ሊሆን ይገባል።
የናይል ውሃ የጠቅላላው የተፋሰሱ አገራት ውሃ ነው። በተመሳሳይ መልኩ ከኢትዮጵያ የሚመነጨው ጥቁር አባይ የኢትዮጵያ፣ የሱዳን እና የግብጽ ነው። ስለሆነም ውሃውን በጋራና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ መጠቀም አለብን፡፡ ስለዚህ እኛ ኢትዮጵያውያን በአንድ በኩል ለግድቡ ግንባታ ያለንን ድጋፍ እያደረግን፤ በሌላ በኩል ደግሞ በግዛታችን የሚገነባነውን ግድብ እና ከአባይ ውሃ የመጠቀም መብታችን በምንም መንገድ አሳልፈን የማንሰጥ መሆናችን ደግመን ደጋግመን መግለጽ ይጠበቅብናል። ለግብጽ ህዝብም ሆነ ለመላው ዓለም ይህንን ጠንካራ አቋማችንን አስረግጠን ማሳወቅም ይገባል።
በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ የሚቃጣ ማንኛውንም ጥቃት የሚታገስ ዜጋ የለም፤ አይኖርምም። ለበጎ ነገር ጋሻና መከታ እንደሆነው ሁሉ ለመልማት የምናደርገውን ጥረት እና ትጋት ለማደናቀፍ የሚነሳ ኃይል ካለ ዛሬም እንደ ጥንቱ ክተት ሰራዊት ምታ ነጋሪት ብሎ በመነሳት ዳግም ታሪክ እንደምንሰራ መዘንጋት አይኖርበትም።
ይህንን ሃሳባችንን ሙሉ ለሙሉ መሙላትና የግብጽን ሴራ በአንድነት መመከት እና ማሸነፍ የምንችለው ግን የውስጥ አንድነታችንን አጠናክረን መንቀሳቀስ ስንችል ብቻ ነው። በአንድ ሀገር ውስጥ ልዩነቶች በተለያየ መልኩ ይኖራሉ። የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም ልዩነት ድሮም ነበር፤ አሁንም ሆነ ወደፊት ይኖራል። የሃይማኖት፣ የብሄር የመሳሰሉ ልዩነቶችም ተፈጥሯዊ ናቸው።
እነዚህን ልዩነቶቻችንን የምናስተናግደው ደግሞ ሀገር ሲኖርና የሀገር ሉዓላዊነት ሲከበር ነው። የሀገራችንን ሉዓላዊነት በማስከበሩ ረገድ ታዲያ ምንም አይነት ልዩነት ቢኖረን እንኳን እሱን ለነገ አሳድረን ቀፎው እንደተነካበት ንብ በጋራ መነሳት ይጠበቅብናል።
አክቲቪስቱ ፣በውጭ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ፣ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሁሉ ካለ ልዩነት የሀገራችንን ብሄራዊ ጥቅም ለማስጠበቅም ቆርጠን መነሳት አለብን። ይሄ ወቅት እጅ ለእጅ ተያይዘን የምንሻገርበት እና የህዳሴ ግድባችንን ገንብተን በሁሉም አቅጣጫ የሚነሳውን ቀጣዩን ሰላማችንን የምናረጋገጥበት ሊሆንም ይገባል!
አዲስ ዘመን ሰኔ 14/2012
የግብጽን ሴራ ለመመከት ውስጣዊ አንድነታችንን እናጠናክር!