በጤና ተቋማት የሕክምና ምርመራ ቤተ ሙከራዎች (ላቦራቶሪዎች) በበቂ ደረጃ እንዳልተሟሉ በርካታ ጥናቶች ያሳያሉ። በተለይም በገጠራማው የአገሪቱ ክፍል ችግሩ ይብሳል። ጥራት ያላቸው ላቦራቶሪዎች መኖር ጥራት ያላቸው የጤና ተቋማትን እንደሚፈጥሩም ይነገራል።
በመሆኑም የተጠናከረ የሕክምና ምርመራ የላቦራቶሪ ጥራት ቁጥጥርና ክትትል ሥርዓትን መዘርጋት ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የላቀ ሚና አለው። የአገሪቱ የሜዲካል ላቦራቶሪ ሥርዓት የዘመነ ባለመሆኑ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ የሚፈለገውን ያህል ለውጥ ለማምጣት ተግዳሮት እንደሆነም ጭምር የዘርፉ ባለሙዎች ይናገራሉ።
በዚህ ወረርሽኝ የተነሳ የአገሪቱ የሜዲካል ላቦራቶሪ ሥራዎች እንደ አዲስ ትኩረት አግኝተው ማቆጥቆጣቸውን የሚናገሩት የሜዲካል ላቦራቶሪ ባለሙያው አቶ ዘሪሁን ወልደ ሰንበት ፤ በኮሮና ምርመራ ሂደትም ሆነ በማንኛውም የላቦራቶሪ አገልግሎት ውጤታማ ለመሆን የበርካታ አካላት ቅንጅት አስፈላጊ ነው ይላሉ። ተግባሩ በበቂ ግብዓት፣ ክህሎትና መሰል ጉዳዮች የተደራጀ ባለመሆኑም በኮሮና ወረርሽኙ ባለሙያዎች ጭምር ተጋላጭነታቸው እንዲጨምር አድርጓል ባይ ናቸው።
አቶ ዘሪሁን ሲያብራሩ፤ በኮሮና ምርመራ የሚገኘው ውጤት አስተማማኝ እንዲሆን በተገቢው ናሙና ሊወሰድ ይገባል። ለዚህም የሰለጠኑ ባለሙያዎች መሆን አለባቸው። ከበሽተኛው ናሙና ሲወስዱ የራሱ የሆነ ናሙና መውሰጃ ቁሳቁስ መኖር አለበት። የባለሙያውን ተጋላጭነት መቀነስ የሚያስችሉ መከላከያ ቁሳቆሶች ሊቀርቡለት እንደሚገባ ያስረዳሉ።
ተገቢውን ናሙና መውሰድ የሚችል የሰለጠነ ባለሙያ ካልሆነ ለውጤቱ መበላሸት ቀጥተኛ አስተዋጽኦ አለው። ናሙና ከበሽተኛው መወሰድ ያለበት ራሱን የቻለ ደረጃ አለው፤ ከተያዘ (ከተጠረጠረበት) ቀን ጀምሮ ከስድስት
እስከ ዘጠኝ ቀናት ባሉት ሊሆን ይገባል። የናሙና አወሳሰዱ መዘግየትና መፍጠን ለምርመራ ውጤቱ ፋይዳ አለው።
የናሙና ማጓጓዙ ሂደት ራሱን የቻለ ፋይዳ ያበረክታል። ናሙናው ከተወሰደ ከሁለተኛው ቀን እስከ ስምንተኛው ቀን ባለው ጊዜ ላቦራቶሪ መድረስ ይኖርበታል። በላቦራቶሪ ሂደት ላይም በጥቅም ላይ የሚውለው ‹‹ሪኤጀንት›› ወሳኝነት አለው። ላቦራቶሪ መሰራት ብቻ ሳይሆን ሂደቱን በተገቢው ተከታትሎ ውጤት ማስገኘት ይገባል። የምርመራውን ውጤት እስከ 70 በመቶ ድረስ ውጤታማ ለማድረግ እያንዳንዱ ሂደት የራሱ የሆነ አስተዋጽኦ ያበረክታል። ያ ካልሆነ ውጤታማነቱን ይቀንሰዋል፤በመሆኑም የጤና ስራ ያለ ቅንጅት አይታሰብም ብለዋል አቶ ዘሪሁን።
ባለፉት ጊዜያት የላቦራቶሪ ሥራ የተረሳ ነበር። ባለሙያዎቹም አስተዋሽ አልነበራቸውም ያሉት ሌላኛው የሜዲካል ላቦራቶሪ ባለሙያ አቶ ጥኡመልሳን ወልደገብርኤል ናቸው። እርሳቸው እንደሚሉት የኮቪድ 19 ወረርሽን በመከሰቱ የተነሳ የላቦራቶሪ ምርመራ ምንድን ነው? የመመርመር አቅም ማለትስ ምንድን ነው? የሚለውን ብዙ ሰዎችና ባለስልጣናት መረዳት ችለዋል። ከዚህ በኋላ የሚመለከታቸው አካላት እንደ አገር ሥርዓቱን የሚፈትሹና ለማጠናከር የሚሰሩ ይመስለኛል። ምክንያቱም
የመመርመር አቅሙን አይተዋል። ቁሳቁሶቹ የተሟሉና የተጠናከሩ ሆነው አጠቃላይ የጤና ሥርዓቱ እንዲሻሻል ብዙ ሊሰራ እንደሚገባ ተናግረዋል።
በኮሮና ምርመራ ሂደት የሪፖርት ሥርዓቱስ ምን ይመስላል? የሚለውን አቶ ዘሪሁን ሲያስረዱ፤ የውጤት አገላለጽና አተረጓጎም የራሱ ሙያዊ ቋንቋ አለው። የሚታወቁ ሁለት ውጤቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ‹‹ነጌቲቭ›› ማለት በምርመራው ጊዜ ቫይረሱ የለበትም ይሆናል፤ ቫይረሱ ለመለየት በሚያስችልበት ደረጃ ላይ አልደረሰ ሊሆንም ይችላል። ሙሉ ለሙሉ ተጠንቶ ያለቀ ባለመሆኑ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል። ‹‹ፖዘቲቭ›› ነው ማለት ቫይረሱ ተገኝቶበታል ማለት ነው። ሶስተኛው ደግሞ ‹‹ፔንዲንግ›› ይባላል። ይህ ማለት ምርመራውን ይድገም፤ በመካከል ላይ ሆኖ ለመለየት አዳጋች ሆኗል ማለት ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ የምርመራ ውጤቶች ከ80 በመቶ በላይ ውጤታማ መሆን እንዳለባቸው ይታመናል። አሁን ግን አማራጭ ባለመኖሩ እየተሰሩ ያሉ የኮቪድ ምርመራዎች እስከ 60 በመቶ ውጤታማ ቢሆኑ ነው። እነዚህ መቀነሶች የሚፈጠሩት በናሙና አወሳሰድ፣ ማጓጓዝ፣ የመጠቀሚያ ኪት ጥራት፣ ጋር የሚያያዝ ነው። የውጤት አገላለጽ ሂደት በጣም ጥንቃቄና ከፍተኛ ሃላፊነት የሚጠይቅ ነው። ያለበትን ታማሚ ውጤት ሲገለጽ የለበትም ቢባል የሚያስከትለው ችግር ቀላል አይሆንም። ውጤቱ አጠራጣሪ ከሆነ እንደገና ከሰባት እስከ ስምንት ቀን የሚወስድ ምርመራ ሊደረግለት ይገባል፤ በለይቶ ማቆያ ሆኖ።
አቶ ዘሪሁን በበኩላቸው፤ ከአጀማመሩ ለማሳየትም ኢትዮጵያ በኮቪድ 19 ቫይረስ ምርመራ ስትልክ የነበረው ደቡብ አፍሪካ ነው። በመሆኑም ለመዘግየትና ለከፍተኛ ወጪ የሚዳርግ ነበር። ኢትዮጵያ እንዲህ አይነት ሁኔታዎችን ታሳቢ አድርጋ አላጠናከረችውም ነበር። በዚህ የተነሳ ከ500 እስከ 700 ብር ሊወስድ ይችላል። ለኢንፍሎዌንዛ ምርመራ በሚል ቀደም ሲል የተዘጋጀና እየተንገዳገደ የነበረ የላብራቶሪ ክፍል በዚህ ወረርሽኝ በእግሩ መቆም ችሏል። የላቦራቶሪን አቅም መገንባት
የጤና ሥርዓቱን እንደመገንባት መቆጠር እንዳለበት አስገንዝበዋል።
በዓለም ላይ የተጠናከረ የጤና ሥርዓት ያላቸው አገራት መጀመሪያ መሰረታቸውን የጣሉት በላብራቶሪ ግንባታና ማደራጀት ላይ ነው። ዘመኑ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ሕክምና የሚከወንበት ነው። የሰው ልጅ በሽታዎች በየጊዜው በእጅጉ እየጨመሩ ይገኛሉ። ስለዚህ እነዚህን መቆጣጠርና መከላከል የሚቻለው የጤና ተቋማትን አቅም በመገንባት ነው። የጥናትና ምርምር አቅምን ማሳደግ ሲቻል ነው። ተገፍቶ ያለው ባለሙያ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። አቅሙን ሊያሳድግ ይገባል። ዩኒቨርሲቲዎችና ክልሎች የተጠናከረ የላቦራቶሪ የምርመራ አቅም ማጎልበት አለባቸው።
ላቦራቶሪዎች በኮሮና ቫይረስ ምርመራ ገና ብዙ የሚጠበቅባቸው ተግባር አለ። ቫይረሱን ማወቅ፣ ቫይረሱ ያለበትን ሰው አለበት ወይም የለበትም ብሎ ማሳወቅ አለባቸው። የምርመራ አቅማችን ለምን አነስተኛ ሆነ ለሚለው አሁን እየተጠቀምንባቸው ያሉት የምርመራ ማሽኖች ዓለም ከደረሰበት አንጻር ሲታዩ እጅግ ኋላ ቀር ናቸው። በአንድ ጊዜ እስከ 96 ናሙናዎች መስራት ይችላሉ። ዘመናዊ የሆኑት ማሽኖት ውድ ናቸው። አሁን ባለው አሰራር በቀን በአማካይ ከ200 ሰዎች አይበልጡም። በሽታው የሚለየው ብዙ በመመርመር ነው። ሁኔታው እየጨመረ ከመጣ በእነዚህ ፒሲአር ማሽኖች መርምረን እንዘልቀዋለን ወይ ለሚለው ሌላ መፍትሄ ያስፈልጋል። ሲሰላ ከአንድ ሚሊዮን 45 ሰው ነው አሁን እየመረመርን ያለነው።
ማሽኖቹ አነስተኛ ናቸው። እየተሰራ ያለው በማኑዋል ነው። ስለዚህ የምርመራ አቅምን ማሳደግና የሚባክነውን ሪኤጀንት መቀነስ ይገባል። አንድ ዙር ለመስራት አራት ሰአት ይወስዳል። ስለዚህ የማሽን ብዛትን ማሳደግን ይጠይቃል። ከተቻለ ዘመናዊ ማሽኖችንም ማፈላለግ ይገባል። በዚህ ዘገምተኛ የምርመራ ሂደት ችግሩ እየሰፋ ከመጣ ማህበረሰቡም፣ ባለሙያዎቻችን በከፍተኛ ደረጃ ሊጎዱ ስለሚችሉ የመከላከያ ጥንቃቄዎችን መተግበር እንደሚገባ አቶ ጥኡመልሳን አሳስበዋል።
አዲስ ዘመን ሰኔ 12/2012
ሙሐመድ ሁሴን
የጤና ሥርዓቱና የመመርመር አቅም