እ.ኤ.አ. በ1997 የተረቀቀው ዓለም አቀፍ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ኮንቬንሽን ድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን አስመልክቶ የተፈረመ ብቸኛ ስምምነት ነው። ስምምነቱ እ.ኤ.አ. ከነሐሴ 17 ቀን 2014 ጀምሮ ተፈጻሚ ሆኗል። በስምምነቱ የማርቀቅ ሒደት የውኃ መብትን በተናጠል ዕውቅና ስለመስጠት ክርክር ተደርጓል። ብዙ አገሮች ለግለሰቦች መብት የሚሰጠውን የውኃ መብት ስለአገሮች መብትና ኃላፊነት በዋነኛነት በሚደነግግ ስምምነት ውስጥ ማካተት ተገቢ አይደለም ብለው ተከራክረው ነበር። ነገር ግን አገሮች የዜጐቻቸውን ብቻ ሳይሆን ውኃውን በጋራ የሚጠቀሙ አገሮችን የውኃ መብት ለማክበር ተስማምተዋል። አገሮች የውኃ ክፍፍል ሲያደርጉ ለተፋሰሱ አገሮች ነዋሪዎች መሠረታዊ ፍላጐቶች ቅድሚያ መስጠትን ግንዛቤ ውስጥ እንዲከቱም ተስማምተዋል። ይኼም በኮንቬንሽኑ አንቀጽ 10(2) ላይ በግልጽ ተቀምጧል።
የውኃ መብት የፖለቲካ መብት ሳይሆን የሰብዓዊ መብት ነው። የሕይወትና የሰዎች ኑሮ ሁኔታን የሚመለከት ነው። በዓለም አቀፍ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ስምምነትም ሆነ በልማዳዊ ዓለም አቀፍ ሕጐች ገዥ የሆነው መርህ ፍትሐዊና ምክንያታዊ የውኃ አጠቃቀም መርህ ነው። ይህ መርህ ተግባራዊ ሲደረግ ሁሉም የተፋሰሱ አገሮች በእኩልነት ይታያሉ። አገሮች በአንድ ላይ ተሰባስበው ለመጠጥና ለንፅህና አገልግሎት የሚውል ውኃን ማቅረብ ተቀዳሚ አጀንዳ ካደረጉ፣ በመካከላቸው እምነት ለማሳደር መነሻ ነጥብ ሊሆን ይችላል። ይህም አገሮች መቼ ውኃን ለግብርና፣ ለአካባቢ ጥበቃ፣ ለቱሪዝምና ለኢንዱስትሪ መጠቀም እንዳለባቸው እንዲደራደሩ ሁኔታዎችን ያመቻቻል። በአገሮች መካከል የጋራ እምነት በማሳደር ስምምነት ለመፍጠርም ያግዛል።
እውነታው ይህ ቢሆንም ከዓባይ ተፋሰስ አንፃር የወንዙን ውሃ አገሮች በእኩልነት እየተጠቀሙ አይደለም። ግብፅ፣ ሱዳንና ኡጋንዳ ብቻ ናቸው በተሻለ በቂ የሚባል ውኃ ለዜጐቻቸው የሚያቀርቡት። ኢትዮጵያና ሌሎች የተፋሰሱ አገሮች ግን ለዜጐቻቸው በቂ የመጠጥና ለንፅህና አገልግሎት የሚውል ውኃ በማቅረብ በኩል ዝቅተኛ ቦታ ላይ ነው የሚገኙት። የኤሌክትሪክ አጠቃቀም ልዩነቱም የሰማይና የምድር ያህል የተራራቀ ነው። ይህን ጉዳይ የበለጠ አስገራሚና አሳዛኝ የሚያደርገው ደግሞ አገራችን ኢትዮጵያ ከዓባይ ውሃ ከ86 በመቶ በላይ የሚሆነው አመንጪ ሆና አጠቃቀሟ ግን ከማንም በታች መሆኑ ነው።
በውሃ በተለይ በድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ጉዳይ የከፍተኛ ዕውቀት ባለቤቱ ኢትዮጵዊው ፈቅ አህመድ ነጋሽ አንደሚናገሩት በግብጾች በኩል ኢትዮጵያ በቂ ውሃ መጠን አላትና ዓባይን ለመጠቀም ማሰብ የለባትም ሲባል የሚነሳው ሃሳብ ፍጹም ውሸትና መሬት ላይ ያለውን እውነታ የደፈጠጠ ነው። እንደ አቶ ፈቅ አሀመድ ነጋሽ ገለጻ በኢትዮጵያ ያሉ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ካላቸው የውሃ መጠን 92 በመቶው ወደ ውጪ አገር የሚሄድ ነው። ስለሆነም ኢትዮጵያ ያላትን ወንዝ በመቁጠር በቂ ውሃ አላት የሚለው ብሂል ተቀባይነት የሌለው ነው።
አሁን ላይ ያለፉ የተዛቡ ታሪኮችን በመተረክ የሚቆዘምበትና በዘፈንና በዜማ ዓባይን እየረገሙና እየገዘቱ መጓዝ ዘመን አልፎበታል። ምክንያቱም ኢትዮጵያ ፍትሃዊ የውሃ አጠቃቀም መርህን ጠብቃና የታችኞቹን ተፋሰስ አገራት አለመጎዳት ከግንዛቤ አስገብታ ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ወደ ፍጻሜ እያቃረበች ነውና! ታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አገራችንን በሌለ አቅሟ ገንብታ ለራሷና ለተፋሰሱ አገራት ያበረከትችው መልካም የወዳጅነት ገጸ በረከት ነው የሚባለውም ለዚህ ነው።
ይህ በሆነበት ሁኔታ የውሸት ትርክት እየፈጠሩና ዘመን ያለፈበት ኢፍትሃዊ ስምምነትን የሙጥኝ ብለው ግድቡን ለማደናቀፍ መሞከር ተራራን በገመድ እንደመጎተት ይቆጠራል። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ በሠጡበት ወቅት የታላቁ ሕዳሴ ግድብን አስመልክቶ “ግድቡን በመስራታችን የምንጎዳው ነገር የለም፤ እያልን ያለነው መብራትና ውሃ የማያገኙ ዜጎቻችን ይጠቀሙ ነው፤ ይሄ ደግሞ ከማንም የማንለምነው መሰረታዊ መብታችን ነው ” ሲሉ መናገራቸውም ከላይ ለገለጽነው እውነት ጥሩ ማስረጃ ነው።
በአጠቃላይ ታላቁ የህዳሴ ግድብንና የዓባይ ወንዝ አጠቃቀምን በተመለከተ አገራችን ኢትዮጵያ የምትከተለው መርህ ማንንም አንጎዳም መብታችንን ደግሞ ለማንም አሳልፈን አንሰጥም የሚል ነው። በዚህ መርህም ታላቁ የህዳሴ ግድብን በፍጥነት በማጠናቀቅ ለኢትዮጵያም ሆነ ለጎረቤት አገራት የኤሌክትሪክ ኃይል ምንጭ የምንሆንበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም!
አዲስ ዘመን ሰኔ 4/2012
ማንንም አንጎዳም፤ መብታችንንም ለማንም አሳልፈን አንሰጥም!