የኮሮና ቫይረስ በዓለም መከሰቱን ተከትሎ እያስከተለ ያለውን መጠነ ሰፊ ጉዳት ታሳቢ በማድረግ በሽታው አገር ውስጥ እንዳይገባ፤ ከገባም ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ መጠነ ሰፊ ሥራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል። ቫይረሱ ሀገር ውስጥ መግባቱን ተከትሎም የመከላከል ጥረት በከፍተኛ ሁኔታ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው።
በአንድ በኩል ስለበሽታው በዓለም አቀፍ ደረጃ የታወቁ ባህሪዎቹን ለህዝብ በማሳወቅ ስለ በሽታው የተሻለ ግንዛቤ ለመፍጠር፤ በሌላ በኩል የበሽታውን ወረርሽኝ ማስቆም የሚያስችሉ የተለያዩ የመከላከል ሥራዎች በስፋት ተከናውነዋል። ከዚህም ባለፈም በበሽታው የሚጠቁ ዜጎችን ህይወት ለመታደግ የሚያስችሉ የለይቶ ማቆያና ማከሚያ ማዕከላትን የማደራጀቱም ሥራ ትኩረት ተሰጥቶት በከፍተኛ ጥንቃቄ ሲሠራ ቆይቷል።
ይህ ሁሉ በሆነበት ሁኔታ ወረርሽኙን በመከላከል ሄደት ውስጥ እየተመዘገበ ያለው ውጤት ጥረትና ልፋቱን የሚመጥን አልሆነም። ስለበሽታው አስከፊነት የተሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በህዝባችን ውስጥ ከሚታየው መዘናጋት አንጻር ተስፋ የሚጣልበት አልሆነም። ዜጎች በሽታው ምን ያህል ዋጋ ሊያስከፍለን እንደሚችል መረዳት አለባቸው ቢባልም የተረዱትን ያህል እራሳቸውን ሲጠብቁ አይታይም።
ስለበሽታው አስከፊነት በስጋት ውስጥ ሆኖ ከማውራት ባለፈ ከበሽታው ራስን መከላከል ለሚያስችሉ የጥንቃቄ መርሆዎች፤አካላዊ ርቀትን መጠበቅ ፣ እጅን በተደጋጋሚ በውሃና በሳሙና መታጠብ፣ አስገዳጅ ካልሆነ በቤት ውስጥ መቆየት፣ ከቤታችን ወጥተን ስንንቀሳቀስ አፍና አፍንጫ መሸፈኛ /የፊት ማስክ / መጠቀም ለሚሉት ዛሬም በአግባቡ መገዛት አልቻልንም።
ዛሬም የአፍና የአፍንጫ ማስክ ሁሉም ሰው እንዲያደርግ፣ እርቀቱን ጠብቆ እንዲንቀሳቀስ እና አስገዳጅ ሁኔታ ካልገጠመው በስተቀር ከቤቱ አይውጣ የሚል ጥብቅ መመሪያ ከመንግሥት ቢወጣም በተግባር የሚታየው ግን በተቃራኒ ነው። አብዛኛው ህዝብ የአፍና የአፍንጫ ማስክ ቢያደርግም ህግ ለማክበር እንጂ በሽታውን ከመከላከል አንጻር በተገቢ ጥንቃቄ አይደለም።
እርቀቱን ጠብቆ የመንቀሳቀሱ ሁኔታ ደግሞ የከፋ ነው። በተለይ በገበያ እና በትራንስፖርት አገልግሎት ስፍራዎች የሚታየው እውነታ ስለ በሽታው ያለው መዘናጋት የቱን ያህል የከፋ እንደሆነ በተጨባጭ አመላካች ነው። በየቡና ቤቱ፣ ሬስቶራንቱ እና ካፌዎች የሚታየው ደግሞ ከሚባለውም የከፋ ነው።
በአሁኑ ወቅት ከጤና ሚኒስቴር የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከ300 ፐርሰንት በላይ እየጨመረ ይገኛል። የሟቾች ቁጥርም እያሸቀበ ነው። በትናንትናው ዕለት ብቻ በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 27 ሆኗል። የስርጭቱ አድማስም መላ ሀገሪቱን ያማከለ ሆኗል።
የቫይረስ ስርጭት ምን ያህል አሳሳቢና ሳይታሰብም ከቁጥጥር ውጪ ሊወጣ እንደሚችል የሌሎች ሀገሮችን ልምድ አይተናል። በሺዎች የሚቆጠሩ በቀን ሲረግፉ ባናይም የመርገፋቸውን ዜና ከንፈራችንን እየመጠጥን በስጋትና በድንጋጤ ውስጥ ሆነን ሰምተናል። ከዚህ ሁሉ በኋላ እንደ ሀገር ከሌሎች መማር የቻልን አይመስልም። የመማር አለመቻላችንም ምስጢር ግራ አጋቢ ነው።
የበሽታው ወረርሽኝ በሀገራችን እየተስፋፋ ቢሆንም አሁን እየታየ ያለው የመከላከል እና የጥንቃቄ ደረጃ ከመቸውም ጊዜ በላይ እጅግ አስደንጋጭ ነው። ቫይረሱ ወደ ሀገራችን መግባቱን የጤና ሚኒስቴር ባስታወቀበት ወቅት በህብረተሰቡ ዘንድ የነበረው መደናገጥና ለጥንቃቄ ይደረግ የነበረው ርብርብ ሁሉ አሁን የለም።
የችግሩ ስጋት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እንድናውጅ ቢያስገድደንም፤ የጥንቃቄ ዕርምጃዎችን ከመተግበር አንጻር አሁንም የጎላ ክፍተት አለ። በተለይም በገበያ ስፍራዎች፣ በትራንስፖርት አካባቢ፣ በእምነት ተቋማት እና ባህላዊ ክዋኔ(ሠርግና ለቅሶ) በሚከናወንባቸው ስፍራዎች መዘናጋቱ የከፋ ነው። ይሄ መዘናጋት አሁን እየተባባሰ ከመጣው የቫይረሱ ስርጭት ጋር ተዳምሮ የማንወጣው አደጋ ውስጥ ሊከተን እንደሚችል ለመገመት የተሻለ እውቀት አይጠይቅም።
አሁን በያዝነው ለአዕምሮ በሚከብድ መዘናጋት ታላላቅ የዓለም መንግሥታት በማንኛውም መልኩ ያልተቋቋሙትን የቫይረስ ስርጭት እንቋቋመዋለን ብሎ ማሰብ ሞትን እንኳን ደኅና መጣህ ብሎ የመቀበል ያህል ዕብደት ነው። ከዚህ እብደት ፈጥነን ካልወጣን መዘናጋት የከፋ ዋጋ ሊስከፍለን ከደጃችን ነው !
አዲስ ዘመን ሰኔ 1/2012
መዘናጋት የከፋ ዋጋ ሊስከፍለን ከደጃችን ነው !