የኢትዮጵያን ነጻነት ተከትሎ ግንቦት 1933 ዓ .ም አዲስ ዘመን የሚል ስያሜ የተሰጠው ጋዜጣ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያው ጊዜ ለህትመት በቃ። ጋዜጣው ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 79 ዓመታት በተለያዩ የመንግሥት ስርዓቶች ውስጥ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን በመዘገብ፣ ተዐማኒ መረጃዎችን በማቅረብ፣ ቋንቋና ስነ ጽሁፍን በማሳደግና በኢትዮጵያ የጋዜጠኝነት ታሪክ የራሱን ጉልህ አሻራ በማሳረፍ ለአገር እና ለህዝብ ባለውለታ ሆኖ እነሆ ዛሬ 79ኛ ዓመቱን ደፍኗል። እንኳን አደረሳችሁ እንኳን አደረሰን!
በጎም ይሁን ክፉ አሳዛኝም ሆነ ደስ የሚያሰኝ የየዕለቱን ሁነት በመዘገብም በየዘመኑ ያለውን የትውልድ ታሪክ እየሰነደና፣ ለጥናት አጥኚና ተመራማሪዎችም የተሟላ መረጃን እያቀረበ አዲስ ዘመን ጋዜጣ የኢትዮጵያን ታሪክ በመሰነድ ያለምንም መቆራረጥ ለ79 ዓመታት ተጉዞ ዛሬ ላይ ደርሷል።
ለኢትዮጵያ ሥነ ጽሁፍ መዳበር እና ለቋንቋ እድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ማበርከቱም አዲስ ዘመን ለአገር ካበረከተው ፋይዳ የሚደመር ነው፡፡ በዚህም ከጋዜጣው ምስረታ ከ1933 ዓ.ም ጀምሮ በርካታ ሥነ ፅሁፍ እንዲጻፉና ለአንባብያን እንዲደርሱ በማድረግ ለአገራችን ስነጽሁፍ ዕድገት ሚናውን ተወጥቷል፡፡ አንጋፋዎቹ የአገራችን ደራሲዎች በዓሉ ግርማ፣ ስብሃት ገብረእግዚአብሄር፣ ብርሃኑ ዘሪሁን ሙሉጌታ ሉሌ ወዘተ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትና የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ፍሬዎች ናቸው።
ጋዜጣው ከ1970 እስከ 1971 ዓ.ም ደግሞ ‹‹ የባህል መድረክ›› የሚል ገጽ በመክፈት ባህልን ለህዝብ ብቻ ሳይሆን ለዓለም ያስተዋወቀ ባለውለታ ነው፡፡ ከዚያ አለፍ ሲል በኪነ ጥበብ ዘርፉ በርካታ መጽሐፍት፣ ተውኔቶች እንዲተቹ አድርጓል። በዚህም ደራሲያንና ተደራሲያን እንዲማማሩ ጭምር አስተዋጽኦ አድርጓል። በዚህም ሥራው ‹‹ የክፍለ ዘመኑ የኢትዮጵያ ሥነ ጽሁፍ ጀግና›› ለመባል በቅቷል፡፡ በ1994 ዓ.ም የአገሪቱ ደራሲያን ማህበር የእድሜ ልክ የክብር አባልነትን ሰጥቶታል፡፡
አንጋፋው አዲስ ዘመን ከ1933 ዓ.ም ጀምሮ ለ18 ዓመታት በሳምንት አንድ ቀን ከዛም ቀጥሎ ከሰኞ በስተቀር ዕለታዊ ሆኖ ሲወጣ ቆይቶ ከ1993 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ ሰኞ ዕለትን ጨምሮ ሳምንት ሙሉ የሚወጣ ዕለታዊ ጋዜጣ በመሆን ለአንባብያን በርዕሰ አንቀጹ፣ በዜና፣ በሀተታ እና በአምድ ሥራዎች መረጃን በማቅረብ አስተዋጽኦ አድርጓል።
ጋዜጣው በራሱ ባለሙያዎች ከሚያወጣቸው መረጃዎች በተጨማሪም የህዝብ በሆነውና ህዝብን ለማገልገል በተቋቋመው ነፃ የአስተያየት አምዱ ዜጎች በነፃነት እንዲጽፉና ሃሳባቸውን እንዲያንጸባርቁ ሰፊ እድል በመስጠትም የዜጎችን ህዝባዊ ተሳትፎ አረጋግጧል።
ይሁን እንጂ ጋዜጣው በየስርዓቱ ለነበረው መንግሥት የወገነ ፣በተለይም በደርግ ሥርዓት ቅድሚያ ምርመራ (ሳንሱር) የመሳሰሉትን ሙያውን የሚገዳደሩ ችግሮችን ያስተናግድ እንደነበር ይታወቃል። ሆኖም በየዘመኑ የነበሩ ችግሮችን ተቋቁሞ ቀጥሏል። ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በተወሰነ መልኩ ነጻነት አግኝቶ ቅድመ ምርመራ ቆሟል። ሆኖም የፖለቲካ እና የባለስልጣናት ጣልቃ ገብነት በመኖሩ ከመንግሥት አቋም ውጪ የህዝብ ወገንተኝነቱ በአብዛኛው ዳግም ጥያቄ ውስጥ ገብቷል፡፡
አዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደ ህዝብ መገናኛ ብዙሀን የተሻለ ሥራ የሰራው በምርጫ 97 ወቅት ነበር ቢባል ማጋነን አይሆንም።በዚህ ወቅት በተቻለ መጠን ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሀሳባቸውን በነጻነት እንዲገልጹ ሀሳባቸውን ከማስተናገድ ጀምሮ የነጻ ሀሳብ አምዶችን በመክፈት በሚዛናዊነት ህዝብንና አገርን አገልግሏል፡፡ ይሁንና ይህ ሥራው በቂና ምሉዕ ስላልነበር ህዝብንና መንግሥትን በሚፈለገው መንገድ አገልግሏል ማለት አይቻልም።
አሁን በአገራችን ከፈነጠቀው ለውጥ ጋር ተያይዞ ግን ለመድብለ ፓርቲ ስርዓት ማበብ፣ ለዴሞክራሲ ስርዓት መጎልበት፣ለልማት እና ብልጽግና ግንባር ቀደም ሚናውን የመወጣት ዕድል ተከፍቶለታል ። ከዚህም ጋር ተያይዞ የህትመቶቹን ተነባቢነትና ተጽእኖ ፈጣሪነት ከፍ የሚያደርጉ የሪፎርም ሥራዎችን በሁሉም ጋዜጦች ላይ በመተግበር በቅርጽና በይዘት የሚታይ ለውጥን አስመዝግቧል። በዕቅድ ላይ የተመሰረቱ ኤክስክሉሲቭ ሥራዎችን በመስራትም ለሌሎች መገናኛ ብዙሃን ምንጭ በመሆንም ብዙ ርቀት ተራምዷል።
የመልካም አስተዳደር ችግር የደረሰባቸውን ዜጎች ችግር በሚዛናዊነት ይፋ በማድረግም ለብዙዎች ባለውለታ በመሆን ላይ የሚገኝ ሲሆን በደረሰባቸው ችግር አስከፊ ኑሮን የሚገፉ ዜጎችን ህይወት በማስቃኘትም ድጋፍ የሚያገኙበትን ዕድል ለማመቻቸት የተለያዩ ሥራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል። ከህትመቶቹ መሻሻል ጋር ተያይዞም በርካታ እውቅ ጸሐፍትና ምሁራን ለጋዜጣው ጽሁፍ በማበርከትና በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
ይሁንና የተሰራው ሥራ መስራት ከነበረብን አንጻር ብዙ እንደሚቀረው በጽኑ እንገነዘባለን። ለዚህም ይረዳው ዘንድ ድርጅቱ ከየት ተነስቶ የት መድረስ እንዳለበት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ፍኖተ ካርታ አዘጋጅቶ ወደተግባር ገብቷል። በዚህም መነሻነት በቀጣይ ያሉበትን እጥረቶች በመቅረፍ ህብረተሰቡ በሰላም፣በልማት እና በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ በባለቤትነት እንዲሳተፍ ፣ተዓማኒነት ያላቸው የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር መረጃዎች የማድረስ ተግባሩን አጠናክሮ ይቀጥላል። በረጅም ጊዜ ደግሞ በመረጃ የበለጸገ ማህበረሰብ በመፍጠር፣ ንቁ ፖለቲካዊ ተሳትፎ የሚያደርግ ፣ በማህበራዊ አገልግሎት የሚሳተፍ፣ ለልማት ትጉ የሆነ እንዲሁም በእኩልነት የሚያምን እና ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ያለው ህዝብ ለመፍጠር በአዲስ መልኩ መረጃ እየሰጠ፣ ሁነትን እየዘገበና ታሪክን እየሰነደ ይቀጥላል።
አዲስ ዘመን ግንቦት 30/2012
የየዕለቱን ሁነት እየዘገብንና ታሪክን እየሰነድን እንቀጥላለን !