በዓለም ላይ የተለያዩ አባባሎች አሉ። አባባሎቹ ከሰው ልጅ አኗኗር ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ይገናኛሉ። በተጫማሪም ከሀይማኖታዊ አስተምሮትና ከባህላዊ ወጎች ጋር ትስስር አላቸው።
አባባሎች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ለሰው ልጅ አቅጣጫ በመጠቆም ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያበረክታሉ። ለተለያዩ ችግሮች የመፍትሄ አቅጣጫ ያስቀምጣሉ። ወደፊት የሚከሰቱ ነገሮችን ይተነብያሉ። ህዝብን ያስተሳስራሉ። ታሪክን ያወሳሉ። ማንነትን ይገልፃሉ። ሌሎችም ጠቅሜታዎች አሏቸው።
በሀገራችን በጣም ብዙ አባባሎች አሉ። የቀድሞ አባባሎች ካላቸው ጠቀሜታ ዘመን ተሻግረው ዛሬ ላይም ከፍተኛ ተቀባይነት አላቸው። አብዛኞች አባባሎች ሀገር-በቀል ሲሆኑ አንዳንዶች መጤ ናቸው። ሀገር-በቀል አባባሎች ይዘታቸውን ጠብቀው ሲቀጥሉ መጤዎች ከሀገራዊ ለዛ ጋር ተዋህደዋል።
አንዳንድ ሀገርኛ አባባሎች በዘፈቀደ የተፈጠሩ በመሆናቸው እምብዛም ትርጉምና ጠቀሜታ አይገኝባቸውም። አንዳንዶች ደግሞ ጊዜና ወቅትን ያላገናዘቡ ይሆናሉ። ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸውም የጎላ ይሆናል። መጥፎ ትርክቶችን ከትውልድ ወደ ትውልድ ያስተላልፋሉ። ፆታዊ እኩልነትን የሚጎዱ ይሆናሉ። የሰው ልጅን ስብዕና ይጎዳሉ። የሰው ለሰው ግንኙነትን ያበላሻሉ። በአጠቃላይ አሉታዊነታቸው ያመዝናል። በሌላ መልኩ ደግሞ አንድ አባባልን ያለቦታው መጠቀም የራሱ የሆነ ጠንቅ ይኖረዋል።
እናት ሀገራችን ኢትዮጵያ በአባባሎች የተሞላች ባህር ናት። ከእነዚህ አባባሎች መካከል የሰው ፊት የሚባለው አባባል ይገኝበታል። የሰው ፊት ማለት ሰዎች የሚያደርጓቸውን ነገሮች ሌሎች ሰዎች በማይሰሙና በማያዩት ሁኔታ እና የሌላን ሰው ስሜትና ክብር በማይጎዳ መልኩ መፈፀም ነው።
የሰው ፊት የሚባለው አባባል ቀጥታ ተያያዥነቱ የሚፈፀመው
ድርጊትና የሚያዳምጠው ወይም የሚመለከተው ሌላ ሰው ጋር ይገናኛል። ይህም ማለት አንድ ድርጊት ፈፃሚ የሚፈፅመውን ድርጊት ሳይሆን የሚመለከተውን ሌላ ሰው እንዲጠነቀቅ ያደርገዋል። ለምሳሌ፦ አንድ ግለሰብ ሲጋራ ከማጬስ ከሚመጣው ጉዳት ይልቅ ሲጋራ ሲያጬስ የሚመለከተው ሌላ ሰው የሚታዘበውን እንዲያተኩር ያደርጋል። በመጓጓዣ መንገድ ላይ ሌላ ሰው የሚያየው ከሆነ የውሃ ሽንት አለመሽናት ካልሆነ ግን መሽናት። በአጠቃላይ መጥፎ ድርጊቶች ከሰው ዕይታ ውጪ ሲሆኑ መፈፀም ካልሆኑ ደግሞ አለመፈፀም ይገኝበታል።
በእኔ አስተሳሰብ መጥፎ ድርጊቶች በሰው ዕይታ ቢሆኑም ባይሆኑም ተገቢ ባለመሆናቸው መፈፀም የለባቸውም። ጥፋቱ ሊሆን የሚገባው ሰው ከማየቱ ሳይሆን ድርጊቱን ከመፈፀሙ ትክክለኛ መሆን አለመሆን ጋር መያያዝ አለበት። ነገር ግን ብዙ ሰዎች ከሰው ዕይታ መራቅን ይመርጣሉ። ከክፉው ተግባር ግን አይርቁም። ሲጋራ በማጬስ የሚመጣው የሳንባ ካንሰር ይልቅ በሌላ ሰው እገሌ ያጬሳል የሚባለውን መጥፎ ስም ብዙ ሰዎች ይፈራሉ። አንድ ሰው አንድን ነገር ህሊናው ሲያምን ማድረግ ብቻ ይኖርበታል። ሲቀጥል የሌላ ሰውን ሕሊና መጠበቅ ከተቻለ ይኖርበታል። ድርጊት ከራስ ተነሳሽነት የሚመነጭ ስለሆነ በመጀመሪያ የራስ ህሊና ሊያምን ይገባዋል። ሰውየው እራሱ ያመነበትን ነገር ብቻና ብቻ ሊያደርግ ይገባል። ይህ ሲሆን ሰዎች የሚያምኑትን ነገርና ተገቢ የሚሉትን ነገር ይፈፅማሉ።
በታክሲ መጓጓዣዎች ላይ ይህ አጋጣሚ በስፋት ይታያል። የትራፊክ ፖሊሶች ሲኖሩ ብቻ ትርፍ አለመጫን ነገር ግን ከሌሉ አግበስብሶ መጫን የተለመደ ተግባር ነው። ትርፍ ከመጫን የመጀመሪያው ተጎጂ ሹፌሩ ነው። ሲቀጥል ተሳፋሪዎች ናቸው። ለሚደርሰው ጉዳት የካሳ ከፋይ የመኪናው ባለሀብት
ነው። ሹፌሩና ባለመኪናው ትርፍ ከመጫን የሚደርሰውን ጉዳት ተካፋይ በመሆናቸው ትርፍ መጫንን አብዝተው ሊቃወሙ ይገባ ነበር። የትራፊክ ፖሊስ ፊት ሰላማዊ መስለው ዞር ሲሉ ትርፍ የሚያግበሰብሱ ሹፌሮች ትርፍ መጫን ማንን እንደሚጎዳ የተረዱት አይመስለኝም።
በአዲስ አባባ ከተማ ብዙ ነዋሪዎች የቤት እጣቢዎች በመንገድ ላይ ይደፋሉ። ሊደፉ ሲሉ የመጀመሪያ የሚጠነቀቁት ነገር ቢኖር የሚያይ ሌላ ሰው መኖር አለመኖሩ ነው። የሚያይ ሰው ከሌለ በፍጥነት ይደፋሉ። እጣቢዎችን መድፋት ሳይሆን ሲደፉ ሌላ ሰው ማየቱን እንደ መጥፎ ተግባር ያያሉ። ይህ ተግባር በሌሎች ቦታዎችም በስፋት ይታያል።
የሰው ልጅ ተገቢ ነው የሚለውን ነገር በመለየት ያለማንገራገር ማድረግ ይኖርበታል። ተለምዷዊ ገሮችን በመመርመር ጠቃሚ ሲሆን መውሰድ ሳይሆን ደግሞ መተው አስፈላጊ ነው። ነባር የሆኑ ነገሮች ሁሉ በቀድሞው ዘመን ሰዎች የተፈጠሩ በመሆናቸው ለቀድሞው ዘመን የሚመቹ ናቸው። በአብዛኛው የቀድሞ ነገሮች ደግሞ ሳይንሳዊና ተጨባጭ አይደሉም። ምናባዊ ናቸው። ምንም ነገር በሰዎች ዘንድ ትክክለኛ ተቀባይነት እንዲኖረው ተገቢና ትክክለኛ ሊሆን ይገበዋል። ብዙ ተቀባይነት ያላቸው ነገር ግን ትክክለኛና ተገቢ ያልሆኑ ነገሮች ጊዜ ሊፈጅ ቢችል እንጂ አንድ ቀን ተገቢ አለመሆናቸው ይጋለጥና የውሃ ሽታ ሆነው ይቀራሉ። በአጠቃለይ ከሰው ፊት ይልቅ ነውርን እልፍ እላለሁ!
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 24/2012
በላይ አበራ ከአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ
መፍራት ያለብን ነውርን ወይስ የሰው ፊትን?