አፍሪካውያን ዓለም አቀፉን ወረርሽኝ ለመቆጣጠር ከሚፍጨረጨሩት መንግሥ ቶቻቸው ጋር ኩኩሉ እየተጫወቱ ነው። ኮሮና ቫይረስ አፍሪካውያን ደጅ አርፍዶ በመድረሱ ሳይሆን አይቀርም ቁጥራቸው ቀላል የማይባል አፍሪካውያን ትከረት አልሰጡትም።በአጉሪቱ አታድርጉ የሚባለውን የሚያደርጉ ፤ ተው የተባሉትን አጥብቀው የሚይዙ “ስልጡኖች” በርክተዋል።ተራው ዜጋ በጎ ተጽዕኖ መፍጠር የሚችሉ ዝነኞችና የጸጥታ ኃይሎች ፈጸሙት እየተባለ በየዕለቱ የሚሰማው ነገር ጆሮን ጭው ያደርጋል።እስኪ አለፍ አለፍ እያልን የተወሰኑትን እንመልከት።
በአክራ በልደት በዓል ላይ 50 ሰዎች ተገኝተው ሌሎቹ ሲያመልጡ ስድስት ሰዎች ተይዘው ፍርድ ቤት ቀርበው 2000 ዶላር ቅጣት ተላልፎባቸዋል።የተጣለባቸውን የገንዘብ ቅጣት መክፈል የማይችሉ ከሆነም አምስት ዓመት እንዲታሰሩ ተወስኖባቸዋል። የሞሮኮ ፖሊስ በ24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ የወጡ ሕጎችን የተላለፉ ሶስት ሺ ሰዎችን አሥሯል።
ከሳምንት በፊት የአዲስ አበባ ፖሊስ በአንድ ቦታ በመሰብሰብ ጫት ሲቅሙ የነበሩ 31 ሰዎችን መያዙን አስታውቋል። ከሁለት ቀን በፊትም በአዲስ አበባ 116 ሰዎች ተሰብስበው ሺሻ ሲያጨሱ በቁጥጥር ስር ውለዋል።የናይጄሪያ ዜና ኤጀንሲ (NAN) እንደዘገበው 30 የእግር ኳስ ተጫዋቾች የእንቅስቃሴ ገደቡን በመተላለፍ ውድድር አዘጋጅተው በግዛቲቱ የተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር የተጫወቱ ሲሆን፤ ደጋፊዎቻቸውም ተሰብስበው ሲመለከቷቸው ነበር። ይባስ ብለው በማህበራዊ መገናኛ ብዙኃን ድርጊታቸውን የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል አጋርተዋል።
ከሁሉ የሚገርመው ደግሞ ለተከታ ዮቻቸው መልካም አርዓያ በመሆን ራሳቸውን ከቫይረሱ እንዲከላከሉ መስበክ የሚገባቸው ተጽእኖ ፈጣሪዎች መጥፎ ምሳሌ ሆነው መገኘታቸው ነው።በሞዛምቢክ አንድ ፓስተር የተጣለውን የመሰብሰብ እገዳ በመተላለፍ ከ 300 ሰዎች በላይ የተሳተፉበት ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት በማካሄዳቸው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል።ጨቋኝ የአፓርታይድ አገዛዝ ወቅትን በመታገል ስመ ጥር የሆነችው የነፃነት ታጋይና ሙዚቀኛዋ ማሪያ ማኬባ “ፓታ ፓታ” የተሰኘው ሙዚቃ ላይ አዳዲስ ግጥሞችን በመጨመር ከኮሮና ጋር ለሚደረገው ትግል ያዋለችው ደቡብ አፍሪካ ኮሚኒዩኬሽን ሚኒስትር ከቤት አትውጡ የተባለውን ሕግ ተላልፈው በቀድሞ የሥራ ባልደረባቸው ቤት ተገኝተው ምሳ ሲበሉ በመታየታቸው
ፕሬዚዳንት ራማፎዛ ተቆጥተዋቸው የሁለት ወር አስገዳጅ ረፍት እንደሰጧቸው ተሰምቷል።
የማራቶን ክብረ ወሰን ባለቤት የነበረው ኬንያዊው አትሌት ዊልሰን ኪፕሳንግ፤ መንግሥት የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ያስተላለፈውን ሰዓት እላፊ ተላልፎ ከሌሎች ዘጠኝ ሰዎች ጋር ፑል እየተጫወተ እና እየጠጣ ተገኝቶ በቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ አንድ ምሽት በእስር ቤት አሳልፎ በ5ሺህ የኬንያ ሽልንግ በዋስ ተለቋል። በኢትዮጵያ አማራ ክልል ሰሜን ሸዋ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ያወጣውን “በርካታ ሰው በአንድ ላይ እንዳይሰበሰብ” የሚከለክል ሕግ በመጣስ ሰርግ የደገሱ የፖሊሰ አባል በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል፡፡
ዓለም በቫይረሱ ለደረሰበት ጉዳት ጆሮ ዳባ ልበስ ማለትን የመረጡ ልጆቿ የበረከቱባት አፍሪካ ከፍተኛ ጉዳት ተጋርጦባታል።የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የኮሮና ቫይረስ በአፍሪካውያን ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት በመገምገም ከሁለት ሳምንት በፊት በሰጠው መግለጫ 300 ሺህ አፍሪካውያን በኮሮና ምክንያት ህይወታቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ ገልጿል።ኮሚሽኑ ወረርሽኙ የአህጉሪቷን ምጣኔ ሀብት እያሽመደመደው በመሆኑ በዚህ ዓመት በሶስት ነጥብ ሁለት በመቶ ያድጋል ተብሎ የተገመተ የአህጉሪቱ ምጣኔ ሃብት በአንድ ነጥብ ስምንት በመቶ ብቻ ሊያድግ ይችላል ብሏል።ይህም 27 ሚሊዮን አፍሪካውያንን ለረሃብ እንደሚያጋልጥ ጠቅሷል።
የዓለም ምግብ ፕሮግራምም በዚህ ዓመት በከፍተኛ ደረጃ በረሃብ ይጠቃሉ ብሎ ከለያቸው አምስት የዓለማችን አገራት መካከል ሁለቱ አገራት የሚገኙት በአፍሪካ ነው።ድርጅቱ በቫይረሱ ስርጭት ምክንያት ሰዎች ከቤት እንዳይወጡ በመደረጉና በሌሎች ተደራራቢ ምክንያቶች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ያላቸው እነዚህ ሁለት አገራት ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎና ኢትዮጵያ ናቸው፡፡
የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ከፋይናንሻል ታይምስ ጋር ባደረጉት ቆይታ አፍሪካ ቫይረሱ የሚያስከትለውን ጫና ለመቋቋም ከበለጸጉ አገራት ቢያንስ የአንድ መቶ ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድም ቀደም ብለው ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ አፍሪካ ከሚደርስባት ጉዳት ማገገም እንድትችል የቡድን ሃያ አገራት የ 150 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ እንዲያደርጉላት ጥሪ አቅርበው ነበር፡፡
“በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ” እንዲሉ የዓለም ጤና ድርጅት ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በወባ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ ሊጨምር ይችላል ሲል አስጠነቅቋል። ድርጅቱ ባጠናው አዲስ ጥናት በዚህ ዓመት የመከላከያ አጎበርና የመድኃኒት አቅርቦት ላይ መደናቀፍ ከተፈጠረ 760 ሺ ሰዎች ሊሞቱ ይችላሉ ብሏል።
በሌላ በኩል የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር መንግሥታት ያወጧቸውን ክልከላዎች ለማስፈጸም በሚል የጸጥታ ኃይሎች በሚፈጽሙት የሰብዓዊ መብት ጥሰት በርካታ አፍሪካውያን ህይወታቸውን እያጡና አካላዊ ጉዳት እየደረሰባቸው ነው።ዛሬ በቫይረሱ ተጠቂዎች 1337 ደርሰው 44 ዜጎቿን በሞት የተነጠቀችው ናይጄሪያ ገና 12 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ በሞቱበት ወቅት ፖሊስ የቤት መቀመጡን መመሪያ ለማስፈፀም በወሰደው እርምጃ 18 ሰዎች መግደሉን የአገሪቱ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አስታውቆ ነበር።በሩዋንዳ መንግሥት የጣለውን የእንቅስቃሴ ገደቡን በመጣስ ከመኖሪያ ቤታቸው ወጥተው መንገድ ላይ የተገኙ ሁለት ግለሰቦች በጥይት ተመተው ተገድለዋል።የእንቅስቃሴ ገደቡን ለማስፈጸም የተሰማሩ አምስት የአገሪቱ ወታደሮች በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተከሰዋል።
በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል አዴት ወረዳ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ የወረዳው የፖሊስ አባል በመጠጥ ቤት የተሰበሰቡ ወጣቶችን ለመበተን በወሰደው እርምጃ አንድ ወጣት በጥይት ተመትቶ ሕይወቱ አልፏል። በፀጥታ ኃይል አባላት ጥቃት ደረሰብን የሚሉ ሰዎች መሰማታቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ቢቢሲ ላቀረበለት ጥያቄ “የፌዴራልም ሆነ የክልል መንግሥት የሚወስዱት የአስቸኳይ ጊዜ እርምጃ በሕገ መንግሥቱና በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ግዴታዎችና መርሆዎች መሰረት የተመራ ሊሆን ይገባል” የሚል ምላሽ ቢሰጥም ሰሚ ጆሮ ያገኘ አይመስልም።
የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ተከትሎ እየተባባሰ የመጣው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ያሳሰባቸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ከትናንት በስቲያ “የአስቸኳይ ጊዜ ሥልጣናት ሊሠሩ የሚገባቸው ወረርሽኙን በተሳካ ሁኔታ ለመጋፈጥና ለመቆጣጠር ጉዳይ ብቻ ነው ሊሆን የሚገባው፤ አንዲት ነቁጥ ወደፊት፣ አንዲት ነቁጥ ወደኋላ ሊንፏቀቅ ጨርሶ መፈቀድ የለበትም።መንግሥታት ተቃውሞን እንዲጨፈልቁ፣ ሕዝብን ጨምድደው እንዲቆጣጠሩ፣ ወይም ሥልጣን ላይ ለመቆየት ከጅለው የሚጠቀሙበት መሣሪያ ሊሆን ከቶ አይገባም” ብለዋል።ምን ተሻላት አፍሪካ ?
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 21/2012
ትናየት ፈሩ
ምን ተሻላት አፍሪካ ?