ማህበረሰብ ተኮር የፋይናንስ ተቋም በመሆኑ ብዙዎቹ አምነውበት ገንዘባቸውን ቆጥበው ከወለድና ከትርፍ ክፍፍል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ አስችሏቸዋል። በርካቶች ከተቋሙ ገንዘብ ተበድረው በተለያዩ የንግድ ስራዎች ተሰማርተው ህይወታቸውን ቀይረዋል። ቤት፣ መኪና እና ቦታ ገዝተዋል፤ ያለባቸውን የጋራ መኖሪያ ቤት ብድርም ከፍለዋል።
ከመነሻው ማህበረሰቡን ሊያገለግልና ሊለውጥ የሚችል ጥቃቅንና አነስተኛ የፋይናስ ተቋም ሊሆን እንደሚችል የተረዱት መስራቾች፤ ተቋሙን ‹‹አዋጭ የቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር›› ሲሉ ሰይመውታል። እውነትም እንደ ስሙ አዋጭ የሆነው ይህ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር የኢንተርናሽናል ኮፕሬቲቭ አልያንስ የመጀመሪያውና ብቸኛው አባል ለመሆንም በቅቷል።
አቶ ዘርይሁን ሸለመ የህብረት ስራ ማህበሩ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ ናቸው። ህብረት ስራ ማህበሩ ከመመስረቱ በፊት በአንድ መንግስታዊ ባልሆነ ድርጅት ውስጥ በሶሻል ወርክና በፕሮግራም አስተባባሪነት ሰርተዋል። በጊዜው ይሰሩበት የነበረው መስሪያ ቤት ለሰራተኞቹ የብድር አገልግሎት የማይሰጥ በመሆኑ፤ እርሳቸውና የስራ ባልደረቦቻቸው እቁብ በማሰባሰብ የሚያገኙትን ገንዘብ ለተለያዩ ፍጆታዎች ያውላሉ። ይሁን እንጂ እንደ ቴሌቪዥንና ፍሪጅ የመሳሰሉ እቃዎችን በእቁብ ተሰብስቦ በሚገኘው ገንዘብ ብቻ ለመግዛት ይቸገራሉ።
አቶ ዘርይሁን የሚሰሩበት የእርዳታ ድርጅት በገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበራት እናቶችንና ወጣቶችን በማደራጀት ተቋቁመውበት ለሌሎች እንዲያስረክቡ የተዘዋዋሪ ፈንድ ይሰጣቸዋል። እርሳቸውም የዚህ ማህበር ሃላፊ ሆነው ሰርተዋል። እነዚህ እናቶችና ወጣቶች አምስትም አስር ብርም እየቆጠቡ አምስትና አስር ሺ ብር ሲበደሩ ይመለከታሉ። ‹‹ወጣቶቹና እናቶቹ ትንሽ ቆጥብው ይህን ያህል ገንዘብ መበደር ከቻሉ ለምን የቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር አላቋቁምም›› የሚል ሃሳብ ይመጣላቸዋል።
በዚህ መነሻነት የስራ ባልደረቦቻቸውን፣ በዙሪያቸው ያሉ ፍቃደኞችንና በእርዳታ ድርጅቱ የቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበሩ ውስጥ መግባት ያልቻሉ እናቶችን በማሰባሰብ አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበርን በመጋቢት ወር 1999 ዓ.ም በአርባ አንድ አባላትና በ15 ሺ ብር መነሻ ካፒታል መስርተዋል። ከማህበሩ በወሰዱት የመጀመሪያ ብድርም ቴሌቪዥን መግዛት ችለዋል።
በመቀጠልም ማህበሩ ፍሪጅ፣ ስቶቭና የመሳሰሉ እቃዎችን ለአባላት ማቅረብ ጀመረ። የግላቸውን ስራ መስራት ለሚፈልጉ ሰዎች ደግሞ እስከ 20 ሺህ ብር የሚደርስ የብድር አገልግሎት መስጠትም ጀመረ። እንዲህ አይነቱ የቁጠባና ብድር አገልግሎት ፈጣንና በተፈለገው ጊዜ የሚገኝ በመሆኑ አባላት ብድርን እንዲደፍሩ ይበልጥ አበረታታቸው። ከተመሳሳይ ማህበራት ገንዘብ መበደር ስለሚቻል ህብረት ስራ ማህበሩ ለአንድ ዓመት ያህል ገንዘብ ከቆጠበ በኋላ ከአንዱ ማህበር 50 ሺ ብር በመበደር ለአባላቶቹ ከአምስት ሺህ እስከ አስር ሺህ ብር ብድር ለማበደር በቅቷል።
በአርባ አንድ አባላትና በ15 ሺህ ብር መነሻ ካፒታል ስራውን የጀመረው አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር በአሁኑ ወቅት ከ27 ሺህ በላይ አባላትን አፍርቷል። ካፒታሉም ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ ደርሷል። በ2003 ዓ.ም አቶ ዘርይሁን ቀደም ሲል ይሰሩ የነበረበትን ድርጅት በመልቀቅ የአዋጭ የቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር ስራ አስኪያጅ በመሆን እስካሁን ድረስ በማገልገል ላይ ይገኛሉ። ማህበሩ በአሁኑ ወቅት እርሳቸውን ጨምሮ 116 ለሚሆኑ ሰዎች የስራ እድል ፈጥሯል። በአስር ቅርንጫፎች አገልግሎቱን በመስጠት ላይ ይገኛል። በአንድ ወር ጊዜ ውስጥም እስከ 80 ሚሊዮን ብር ያበድራል። የማበደር አቅሙም እስከ አንድ ሚሊዮን ብር ደርሷል።
ህብረት ስራ ማህበሩ በአሁኑ ወቅት ከ9 ሺህ በላይ ለሚሆኑ አባላቱ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ሰጥቷል። ይህም እንደ አንድ መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበር ገንዘብ የማበደር አቅሙ ከፍተኛ መሆኑን ይጠቁማል። እነዚህ 9ሺህ ተበዳሪ የማህበሩ አባላት በስራቸው ለሶስት ሰው የስራ ዕድል ፈጥረዋል ተብሎ ቢታሰብ ህብረት ስራ ማህበሩ በተዘዋዋሪ ከ27 ሺ በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ጠቅሟል እንደማለት ነው። አባላት በየግዜው ሳያቋርጡ መቆጠባቸውም የህብረት ስራ ማህበሩን ካፒታል አሳድጎታል።
ህብረት ስራ ማህበሩ በዋናነት የሚሰጠው የቁጠባ አገልገሎት ሲሆን፤ ወደ 800 ሚሊዮን ብር ከአባላቱ በማሰባሰብ የቁጠባ ባህልን በማሳደግና ይህንን ቁጠባ ወደ ኢንቨስትመንት በማምጣት የድርሻውን ተውጥቷል። የልጆች ቁጠባንም በመጀመር ከ3 ሺህ በላይ የሚሆኑ ህፃናት ወደ 6 ሚሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ ቆጥበዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ህብረት ስራ ማህበሩ እስከ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ የብድር አገልግሎት ይሰጣል። አብዛኛዎቹ ተበዳሪ አባላት በጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ የሚሰማሩ ወጣቶችና ሴቶች በመሆናቸው ብድር ከመውሰዳቸው በፊት በመሰረታዊ ንግድ ክህሎት ዙሪያ ስልጠና ይሰጣቸዋል።
በተጨማሪም ህብረት ስራ ማህበሩ ተበዳሪዎች ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ ማህበሩ የተበዳሪውን ዋስትና ወይም ቁጠባውን በእዳ ማካካሻ አይወስድም፤ እዳውም ወደ ቤተሰቡ አይተላለፍም። ለዚህም በብድር ህይወት ዋስትና አገልግሎት መሰረት ከሌሎች ተበዳሪ አባላት ላይ በየዓመቱ አንድ ከመቶ በመቁረጥ እዳውን ይሸፍናል። በዚህ መልኩም እስካሁን ማህበሩ 7 ሚሊዮን የኢንሹራንስ ገንዘብ ሰብስቧል። ይህም ህብረት ስራ ማህበሩን እንዲያድግና በተለይ ሰዎች ብድርን ያለፍርሃት እንዲበደሩ ካደረጉ አገልግሎቶች ውስጥ በዋናነት ይጠቀሳል።
በሌላ በኩል ህብረት ስራ ማህበሩ በማህበራዊ አገልግሎት ላይ በንቃት የሚሳተፍ ሲሆን፤ አንድ የማህበሩ አባል ከሚያገኘው ትርፍ ላይ ወይም ህብረት ስራ ማህበሩ ከሚያገኘው ትርፍ ላይ የተወሰነውን በማስቀመጥ በዓመት ከግማሽ ሚሊዮን ብር ያላነሰ በጀት ለዚሁ የማህበራዊ ግልጋሎት ይያዛል። ለአብነትም ማህበሩ የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ፣ በመፀዳጃ ቤቶች ግንባታ፣ ለህፃናት ተማሪዎች የትምህርት ድጋፍ በማድረግ ስራዎች ላይ ይሳተፋል።
በተጨማሪም መንግስት አስፈላጊ ናቸው ብሎ ባመናቸው አገራዊ ጉዳዮች ላይ በተለይም በአገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መረሃግብር፣ በተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ማሰባሰብ ስራ ላይ በንቃት ተሳትፏል። በአሁኑ ወቅት ደግሞ በአገሪቱ በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለችግረኞች ድጋፍ የሚውል የ100 ሺ ብር የገንዘብ ድጋፍ ለከተማ አስተዳደሩ አስረክቧል። በተመሳሳይም ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እስካሁን ድረስ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የቦንድ ግዢ ፈፅሟል። በዚህ ዓመትም ተጨማሪ የቦንድ ግዢ ለመፈፀም እቅድ ይዟል።
የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበራት ዋነኛ አላማቸው ትርፍ ሳይሆን የአባላቱን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፣ በአካባቢው ላይ ስራዎችን መስራት፣ ማህበረሰቡን ማገዝና በአገሪቱ ምጣኔ ሃብት ላይ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ማድረግ በመሆኑ አዋጭም ከ116 ቅጥር ሰራተኞቹ በወር ከ300 ሺ ብር በላይ በመሰብሰብ ለመንግስት የስራ ግብርና የጡረታ ፈንድ ይከፍላል። ይህም ተጠራቅሞ በዓመት ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ለመንግስት ገቢ ስለሚሆን፤ መንግስት ይህንኑ ገንዘብ መልሶ ኢንቨስት ለማድረግ ያስችለዋል። 116ቱ ሰራተኞች በስራቸው 5 ቤተሰብ ይኖራቸዋል ተብሎ ቢታሰብ እንኳን 500 የሚሆኑ ሰዎችን በተዘዋዋሪ ይጠቅማል እንደማለት ነው።
ማህበሩ ሰራተኞችን የሚቀጥረው በቅድሚያ ከዩኒቨርሲቲ የተመረቁ ተማሪዎችን የስራ ልምድ ሳይጠይቅ አንድ ሺ 500 መቶ ብር የትራንስፖርት እየከፈላቸው ለሶስት ወር በበጎ ፍቃደኝነት እንዲሰሩ ካደረገ በኋላ በመሆኑ ከሌሎች የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበራት ልዩ ያደርገዋል። በአሁኑ ወቅትም በአብዛኛው በማህበሩ ተቀጥረው እየሰሩ ያሉት ከዩኒቨርስቲ ተመርቀው የወጡ ወጣቶችና ሴቶች ናቸው። ህብረት ስራ ማህበሩ ካሉት አጠቃላይ ሰራተኞች ውስጥ 60 ከመቶ ያህሉ ሴቶች መሆናቸውና ለሴት አባላቱም ብድር የሚሰጠው በአነስተኛ የወለድ መጠን መሆኑ ከሌሎቹ ይለየዋል።
ከሌሎች ጥቃቅንና አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት ጋር ሲነፃፀር ማህበሩ ለተበዳሪዎች የሚያስከፍለው የወለድ መጠን አነስተኛ ከመሆኑም ባሻገር የሚከተለው የወለድ አሰራርም የተለየ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ማህበሩ የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ግዜ የብድር አገልግሎት ለአባላት ይሰጣል። ይህም አባላት በአስር
ዓመት ውስጥ የሚከፈል እስከ አንድ ሚሊዮን ብር በመበደር ቤት ለመስራት፣ ለማደስና ሌሎችንም ስራዎች ለመስራት ያስችላቸዋል። በተመሳሳይ በአነስተኛ ቢዝነስ ላይ መሰማራት የሚፈልጉ አባላት በአምስት ዓመት የሚከፈል 5 ሺህ ብር በመበደር የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ።
በፌደራል ደረጃ የሚሰራ ብቸኛውና ከፍተኛ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ መሆኑ አዋጭን ሞዴል ማህበር አሰኝቶታል። በካፒታል መጠኑ፣ በአባላት ቁጥር፣ በሚሰጠው የብድር መጠን ከፍተኛና ዓለም አቀፉን መርህ ተከትሎ ስራውን መስራቱ ህብረት ስራ ማህበሩ ልዩ አድርጎታል። በዚህም ከፍተኛ የሆነውን የብቃት ማረጋገጫ ነጥብ ማስመዝገብ ችሏል። ማህበሩ የህብረት ስራ ማህበራትን አዋጅ ደንብና መመሪያዎችን ተከትሎ መስራቱና የአባላትን ተጠቃሚነት ማረጋገጡም ለተጨማሪ ስኬት አብቅቶታል።
መበደር ከሚችሉ አባላቶች ለግማሽ ያህሉ ብድር መስጠት ችሏል። አንድም ጊዜ ሳያቋርጥ በየዓመቱ ገቢና ወጪውንም ኦዲት አስደርጓል። ይህም የአባላት ቁጥሩን በእጥፍ እያሳደገ እንዲመጣ አስችሎታል። ባለፈው ዓመት የኦዲት ሪፖርት መሰረትም 21 ሚሊዮን ብር አትርፏል። ለእያንዳንዱ አባልም ትላልቅ ባንኮች የሰጡትን ያህል ከ20 በመቶ በላይ የትርፍ ክፍፍል ሰጥቷል። ጥሩ የአስተዳደር ስርዓትና በዘርፉ የሰለጠኑ ትጉህ ባለሙያዎች ያሉት መሆኑ በስኬት ላይ ስኬት እንዲደርብ አስችሎታል። ለዚህም በተለያዩ ጊዜያት የተሸለማቸው ዋንጫዎችና የተበረከቱለት የምስክር ወረቀቶች ይመሰክራሉ።
ህብረት ስራ ማህበሩ በአምስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅዱ መሰረት በቀጣይ በውስጡ የሚሰሩት ሰራተኞች ቁጥር 700 ይደርሳሉ ተብሎ ይገመታል። የካፒታል መጠኑም 17 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። በዛው ልክ የማበደር አቅሙም ከ20 እስከ 30 ቢሊዮን ብር ለማድረስ የታቀደ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት አስፈላጊዎቹን ዓለም አቀፍ መስፈርቶች በማሟላቱ የኢንተርናሽናል ኮፕሬቲቭ አልያንስ ብቸኛውና የመጀመሪያው አባል ለመሆን ችሏል።
አገሪቱ ቀደም ሲል በንጉሱ ጊዜ የአፍሪካ ክሬዲት ኮንፌዴሬሽን መስራች የነበረች ቢሆንም በነበሩ ስርዓቶች ከአባልነቷ ወጥታ ቆይታለች። ይሁንና በአሁኑ ወቅት በአዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር አማካኝነት ተመልሳ የእዚህ ኮንፌዴሬሽን አባል ለመሆን ችላለች። የኮር ባንኪንግና ቴማኖስ 24 የተሰኙ ስርዓቶችንም መከተል ጀምራለች።
አዋጭ እ.ኤ.አ በ2030 በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቁ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር የመሆን እቅድ የያዘ ሲሆን፤ በቀጣይ ህጉ ሲፈቅድ የመጀመሪያውንና ትልቁን የህብረት ስራ ማህበር ባንክ በኢትዮጵያ የመመሰረት እውን ሊሆን የሚችል ህልምን ሰንቀዋል። የአባላትን ቁጥር ከ200ሺህ በላይ ለማድረስም አቅደዋል። የኮር ባንኪንግ ስርዓቱን በመጠቀም የኤ ቲ ኤም አገልግሎት በመጀመር ደምበኞች ገንዘባቸውን ማውጣት፣ መበደርና በሞባይላቸው አማካኝነት ትንንሽ ብድሮችን እንዲበደሩ ቴክኖሎጂውን የማዘመን ስራዎችንም አያይዞ ይሰራል።
ይህ ታዲያ በህብረት ስራ ማህበሩ አቅም ብቻ የሚሰራ ባለመሆኑ የመንግስት አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንዲደረግለት ጥሪውን ያቀርባል። ይህንኑ ድጋፍ የሚያገኝ ከሆነም በአዲስ አበባ ለብዙ ሰዎች የስራ አድል መፍጠር እንደሚችል ይጠቁማል። እኛም አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር አስካሁን እያከናወናቸው ያሉ ስራዎችን እያደነቅን በቀጣይም ተጨማሪ አባላትን በማፍራት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ያለንን ተስፋ እንገልፃለን። ሰላም !!
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 20/2012
አስናቀ ፀጋዬ
የስኬት ጎዳናን የያዘው ህብረት ስራ ማህበር