በብዙ ቦታዎች ላይ እንደሚታየው ሻምፓኝ ቅልጥ ባለ የሠርግ ሥነ ሥርዓት ላይ፣ በስፖ ርታዊ ክንዋኔ ማሳረጊያና በልዩ ልዩ ግብዣዎች ላይ በመጠጥነት ይቀር ባል፡፡ በተለይም በስፖ ርታዊ ውድድሮች መጨረሻ ላይ አሸና ፊዎች ሽልማታቸውን ከወሰዱ በኋላ ደስታቸውን ለመግለፅ ሻምፓኝ በመክፈት እርስ በርስ ይራጫሉ፡፡
ኦዲቲ ሴንትራል የተሰኘው ድረገፅ ከሰሞኑ ባወጣው መረጃ ሻምፓኝ ከመጠጥነት በዘለለ ለሌላም አገልግሎት ይውላል ሲል ዘግቧል፡፡
እንደዘገባው ከሆነ ሰዎች ፀጉራቸውን ለመታጥብ ሻምፓኝና ኮንዲሽነር የሚጠቀሙ ቢሆንም በሞስኮ የሚገኝ አንድ ብኩን ፀጉር የማስተካከያ ቤት ግን የምን ሻምፓኝና ኮንዲሽነር በሚል የሰዎችን ፀጉር በሻምፓኝ ማጠብ ጀምሯል፡፡ ለደንበኞች ሻምፓኝን እንደ ፀጉር ማጠቢያ በአማራጭነት በማቅረቡም ዝናው ናኝቷል፡፡
ቪለን ኑዳቬርዲየን የተሰኘው የፀጉር ቤቱ ባለቤት ይህን ዓይነቱን ያልተለመደ በሻምፓኝ ፀጉር የማጠብ አገልግሎት የጀመረው በቅድሚያ በሥራ ባልደረባው ላይ እንደቀልድ በመሞከር ሲሆን፣ከዚህ ጊዜ አንስቶም ለሌሎች ደምበኞችም አገልግሎቱን በማስከፈል ለመቀጠል እንደወሰነ ገልፀዋል፡፡ በዚህም የእርሱ ፀጉር ቤት በእጅጉ ዝና ለማትረፍ በቅቷል፡፡
‹‹ውጤቱ ጥሩ ነው፤ ሰዎች በሻምፓኝ ፀጉራቸውን ሲታጠቡ ቅንጡ ህይወት የኖሩ ያህል ይሰማቸዋል፡፡›› ሲል የፀጉር ቤቱ ባለቤት ቪለን ኬተርስ ኒውስ ለተሰኘው ሚዲያ በሰጠው ቃለምልልስ ገልጿል፡፡ ‹‹አገልግሎቱ ከፍተኛ ተቀባይነትን በማግኘቱ አሁን አሁን አንዳንድ ደንበኞች የራሳቸውን ሻምፓኝ ወደ ፀጉር ቤቱ ይዘው በመምጣት እስከ መጠቀም ደርሰዋል›› ሲልም ጨምሮ ተናግሯል፡፡
ፀጉርን በሻምፓኝ የማጠቡ ሂደት ቀላል መሆኑን በዘገባው የተገለፀ ሲሆን ቪለን በቅድሚያ ለብ ያለ ውሃ በደንበኞቹ ፀጉር ላይ ካፈሰሰ በኋላ በሻምፓኙ ፀጉራቸውን በማሽት እንደሚያጥባቸው ተጠቅሷል፡፡ ሆኖም ሻምፓኙን የደንበኞቹን ፀጉር ካጠበ በኋላ በድጋሚ በውሃ ያለቅልቀው አያለቅልቀው የታወቀ ነገር የለም ሲል ዘገባው አመልክቷል፡፡
አዲስ ዘመን ጥር 7/2011
አስናቀ ፀጋዬ