ቦታው ለመልሶ ልማት በሚል በቆርቆሮ ታጥሮ ለግል ባለሀብቶች የተሰጠ ቢሆንም፣ አንድም የልማት እንቅስቃሴ ሳይታይበት በፍርስራሽ ተሞልቶ፣ ዳዋ ለብሶ፣ የመጸዳጃ እና የቆሻሻ መጠያ ስፍራ ሆኖ ኖሯል፡፡ ካዛንቺስ ኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል ፊት ለፊት የሚገኘው ቦታ፡፡
ዛሬ ግን ይህ መገለጫው ተቀይሯል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወደ ልማት ያልገቡ ቦታዎችን ወደ መሬት ባንክ በመመለስ በጊዜያዊነት ልማት እንዲካሄድባቸው ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ስፍራው ሙሉ በሙሉ ተጠርጎ፣ ተደልድሎ ቀይ አሸዋ ተደርጎበት በማህበር የተደራጁ ወጣቶች የመኪና ፓርኪንግ አገልግሎት እየሰጡበት ይገኛሉ፡፡
ታላቁ ቤተ-መንግሥት ወይም ግቢ ገብርኤል አካባቢ የሚገኘው ቦታም እንደዚሁ ለዓመታት ታጥሮ ምንም ዓይነት ጥቅም ሳይሰጥ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ የእዚህ ቦታ አጥርም እንዲፈርስ ተደርጎ መሬቱ በሚገባ ተደልድሎ እና ቀይ አሸዋ ፈሶበት ለመኪና ፓርኪንግ አገልግሎት እንዲውል ተደርጓል፡፡ የአካባቢው ወጣቶችም ቦታውን ለመኪና ማቆሚያነት በማዋል ተጠቃሚ መሆን ጀምረዋል ፡፡
ወጣት ዳኛቸው አበራ ካዛንቺስ አካባቢ ተወልዶ እንዳደገ ይናገራል፡፡ በዚሁ አካባቢ እንደብዙዎቹ ወጣቶች የተለያዩ ሥራዎችን ለመሥራት ጥረት ሲያደርግ እንደቆየ ያስታውሳል፡፡ ሆኖም የሚያገኘው ገቢ ከእለት ጉርሱ አያልፍም ነበር፡፡ በዚህ የተነሳም ተስፋ ቆርጦ ሥራ አጥ ሆኖ እንደቆየ ያስረዳል፡፡
ወጣት ዳኛቸው ካዛንችስ አካባቢ በሚገኘው ኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል አካባቢ ነው የሚኖረው፡፡ በአቅራቢያው ለዓመታት ታጥሮ የቆየው ቦታ በቅርቡ ፀድቶ ለአካባቢው ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠሩን ይገልጻል፡፡ እርሱም ከሌሎች ወጣቶች ጋር በማህበር በመደራጀት በመኪና ፓርኪንግ አገልግሎት ሥራ መሰማራት ጀምሯል፡፡
ወጣት ዳኛቸው ቦታው ላይ ሁለት ማህበራት ተደራጅተው የፓርኪንግ አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ይገልጻል፡፡ የወረዳው ጥቃቅንና አነስተኛ ፅህፈት ቤት ግን ተጨማሪ ማህበራትን በማደራጀት በቦታው ላይ እንዲሰሩ መወሰኑን ጠቅሶ፣ ይህ ግን ከቦታው ጥበት አኳያ እርሱ የሚሰራበት ማህበር ገቢ እንዲቀነስ ያደርጋል የሚል ስጋት አሳድሮበታል ፡፡
እርሱና ሌሎች የማህበሩ አባላት የአካባቢው ነዋሪ መሆናቸውን በመግለጽም ተገቢውን ጥቅም ማግኘት እንዳለባቸውም ይናገራል፡፡ ከመንግሥት ተበድረው ቦታውን ያፀዱበትን ገንዘብ ለመመለስ ከፓርኪንግ አገልግሎቱ በቂ ገንዘብ ማግኘት እንደሚገባቸውም ይጠቁማል፡፡
የካዛንቺስ ግቢ ገብርኤል አካባቢ ነዋሪው ወጣት ጥላሁን ጌታሁን ቀደም ሲል ሥራ አልነበረውም፡፡ እርሱ በሚኖርበት አካባቢ ለዓመታት ታጥሮ የኖረው ከቤተ መንግሥት ፊት ለፊት የሚገኘው ቦታ ምንም አይነት ጥቅም ሳይሰጥ መቆየቱን አስታውሶ በቅርቡ መንግሥት ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ ቦታው ጸድቶና ተደልድሎ ለፓርኪንግ አገልግሎት እንዲውል መደረጉን ይናገራል፡፡ በእዚህ ቦታ ላይም እርሱና የአካባቢው ወጣቶች በማህበር በመደራጀት የፓርኪንግ አገልግሎት መስጠት እንደ ጀመሩ ይገልጻል፡፡
በቦታው ላይ መጀመሪያ የእነርሱ ማህበር ብቻ ተደራጅቶ እንዲሰራ የወረዳ 8 ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ፅህፈት ቤት መወሰኑን ወጣት ጥላሁን አስታውሶ፣ ፅህፈት ቤቱ ቆይቶ ተጨማሪ ሦስት ማህበራት በቦታው ላይ ተደራጅተው ተመሳሳይ የፓርኪንግ አገልግሎት እንዲሰጡ ውሳኔ ላይ መድረሱን ያመለክታል፡፡ ይህም እርሱና ሌሎች የማህበሩ አባላት ገቢያቸው እንዳይቀነስ ያደርጋል ሲል ስጋቱን ይናገራል፡፡
ወጣት ዳንኤል ፍፁም በየካ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው የመሪሳ ሰፈር አካባቢ ነዋሪ ነው፡፡ ከሌሎች 10 ወጣቶች ጋር በማህበር በመደራጀት ቤተመንግሥት ፊት ለፊት ባለው ቦታ ላይ የመኪና ፓርኪንግ አገልግሎት መጀመራቸውን ያስረዳል፡፡ በቦታው ላይ ወረዳው አደራጅቶ በተጨማሪነት እንዲሰሩ ከፈቀደላቸው ማህበራት መካከል እርሱ ያለበት ማህበር አንዱ እንደሆነም ይናገራል፡፡
‹‹በቦታው ላይ ተጨማሪ ማህበራት ገብተው ቢሰሩ ቦታው በቂ በመሆኑ እኩል ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡›› የሚለው ወጣት ዳንኤል፣ መኪናዎች በአብዛኛው አስፓልት ዳር የሚቆሙ መሆኑ ብዛት ያላቸው መኪናዎች በቦታው ላይ እንዳይገቡ የሚያደርግ መሆኑን ይጠቁማል፡፡ ይህም በማህበራቱ ገቢ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳደር ተናግሮ፣ የሚመለከተው አካል መኪናዎቹን ወደ ተዘጋጀው ፓርኪንግ ስፍራ እንዲገቡ ማድረግ እንዳለበት ያስገነዝባል፡፡
ይህም የማህበራቱን ገቢ ከፍ ማድረግ እንደሚያስችል የሚገልጸው ወጣት ዳንኤል፣ ቦታውን የመኪና እጠበትና መሰል አገልግሎቶች የሚሰጡበት ማድረግ እንደሚገባም ነው የጠቆመው፡፡ ይህ ሲሆን ሁሉም ማህበራት እኩል ገቢ የማግኘት ዕድል ይኖራቸዋል ይላል፡፡
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀትና ክትትል ሥራ ሂደት ቡድን መሪ አቶ ቶሎሳ መርጋ በሁለቱ ቦታዎች ላይ የአካባቢው ወጣቶች በማህበር ተደራጅተው የመኪና ፓርኪንግ አገልግሎት እንዲሰጡ የከተማ አስተዳደሩ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ወጣቶቹ የነዋሪነትና የሥራ አጥ መታወቂያ በመያዝ እንዲመዘገቡ ተደርጓል ይላሉ፡፡ ከወረዳው ውጪ የመጡ ወጣቶችም ከሚኖሩበት ወረዳ ወደ አካባቢው መጥተው ለመስራት እንደሚፈልጉ የሚገልፅ ደብዳቤ በማቅረብ መመዝገባቸውንም ይናገራሉ፡፡ በዚህም መሰረት ሁለት ኢንተርፕራይዞች በሁለቱ ቦታዎች ላይ ተደራጅተው በመኪና ፓርኪንግ አገልግሎት መሰማራታቸውን ይጠቅሳሉ፡፡
ቀደም ሲል በሁለቱ ቦታዎች ላይ ሁለት ማህበራት ብቻ እንደነበሩ የቡድን መሪው ጠቅሰው፣ ሌሎች ወጣቶችንም በሥራ እድል ፈጠራው ተጠቃሚ ማድረግ በማስፈለጉ 7 አዳዲስ ተጨማሪ ማህበራት በቦታው ላይ ገብተው እንዲሰሩ አቅጣጫ ተቀምጧል ይላሉ፡፡
በዚህም መሰረት ግቢ ገብርኤል አካባቢ በሚገኘው ቦታ ላይ 3 ማህበራት እንዲገቡ መወሰኑን ይጠቁማሉ፡፡ ይህን አቅጣጫ ተከትሎ የፓርኪንግ አገልግሎቱን ለመስጠት በማህበራቱ መካከል መግባባት ሊፈጠር እንዳልቻለ ተናግረው፣ አንድ ማህበር ለብቻው፣ ሁለት ማህበራት ለብቻቸው ወይም ሁሉም ማህበራት በአንድ ላይ የፓርኪንግ አገልግሎት እንዲሰጡ ወረዳው አማራጮችን ማቅረቡን ያብራራል፡፡
የቡድን መሪው ማህበራቱ ከቀረቡላቸው አማራጮች ውስጥ ሁለተኛውን መምረጣቸውን ጠቅሰው፣‹‹ከየትኛው ማህበር ጋር ተጣምረው መስራት እንደሚፈልጉ ባለመወሰናቸው ዳግም መግባባት ሊፈጠር አልቻለም፡፡›› ይላሉ፡፡ ከየትኛው ማህበር ጋር ተጣምረው መስራት እንደሚፈልጉ የማይወስኑ ከሆነ ወረዳው በእጣ ለይቶ እንደሚያሳውቅ ይጠቁማሉ፡፡
ኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው ቦታ ላይም ወደ ሥራ የገባው አንድ ማህበር ብቻ እንደነበር የሚጠቅሱት ቡድን መሪው፤ ቦታው ብዙ መግቢያ ስላለውና በቂ በመሆኑ 4 ማህበራት እንዲጨምሩ መደረጉን ይገልጻሉ፡፡ የማህበራቱ መጨመር በገቢ ላይ ተፅዕኖ እንዳለው በተለይም የቀደሙት የማህበሩ አባላት ቅሬታቸውን ለወረዳው ማቅረባቸውን ጠቅሰው፣የወረዳው ፕላን ኮሚቴ ባካሄደው ጥናት ቦታው ለአምስቱም ማህበራት በቂ መሆኑን አረጋግጦ በቦታው ላይ እንዲሰሩበት ውሳኔ ማሳለፉን ይገልጻሉ፡፡
በሚፈለገው መጠን መኪናዎች በቦታው ላይ እየገቡ ባለመሆኑና ቦታውም ገና ስላልተለመደ የማህበራቱ ገቢ ዝቅተኛ ሊሆን እንደሚችል ቡድን መሪው ገልፀው፤ ይህንኑ ከግምት ውስጥ በማስገባት ከትራፊክ ጽሕፈት ቤት ጋር በመነጋገር መንገድ ዳር የሚቆሙ መኪናዎች በቦታው ገብተው እንዲስተናገዱና የትራፊክ ፍሰቱም እንዲሳለጥ ወይይቶች መካሄዳቸውን ያብራራሉ፡፡ መኪናዎቹ ወደ ቦታው ሲገቡ ወጣቶች ከፓርኪንግ አገልግሎቱ የሚያገኙት ገቢ ከፍ እንደሚልም ይጠቁማሉ፡፡
አዲስ ዘመን ጥር 7/2011
በአስናቀ ፀጋዬ
Keep up the amazing work!
Your ideas and insights are unique and thought-provoking I appreciate how you challenge your readers to see things from a different perspective
Drop a link to your favorite blog post of yours in the comments below, I’d love to read more.
Your blog has quickly become one of my favorites I am constantly impressed by the quality and depth of your content
Keep up the amazing work! Can’t wait to see what you have in store for us next.
Hi there to all, for the reason that I am genuinely keen of reading this website’s post to be updated on a regular basis. It carries pleasant stuff.