ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ውበቷ፣ በታሪክ፣ በቅርስ፣ በበርካታ ብሔር፣ ብሔረሰቦች መገኛ በቱሪዝም ሀብቶቿ የምትታወቅ አገር እንደሆነች እሙን ነው። ከእነዚህ መካካል ባህል አንዱ እና ዋነኛው ነው። ባህል ሲባል በመሰረቱ እጅግ ክቡር ነው፤ የአንድ ህብረተሰብ ባህል በራሱ የህብረተሰቡ እንክብካቤ መጠበቅ መዳበር መሻሻልና የላቀ ዕድገት ማሳየት እንዳለበት ሳይታለም የተፈታ ነው።
ባህልን የመንከባከብ ኃላፊነት የሚወድቀው ባለው ትውልድ ላይ ሲሆን እንክብካቤ የሚሹ መሆናቸውም እሙን ነው። ማንኛውም የማህበረሰብ ክፍል እንዳይረሳና በሌሎች ተውጦ እንዳይቀር የማንነት መገለጫ የሆነውን ባህሉንና ቋንቋውን እንዲሁም ታሪኩን ጠብቆ ሲያቆይ ነው። ከዚያ ላቅ ሲል ከዘመን ወደ ዘመን የሚያሻጋገረውን ትውልድ መፍጠር ሲችል ነው። ይህንን ማድረግ የሚቻለው ደግሞ ህብረተሰቡ ባህሉና ቋንቋውን የመጠቀም ጽኑ ፍላጎት ሲኖረው እንደሆነ ማመን አለበት።
በራሱ ባህልና ቋንቋውን የመገልገል ማህበራዊ ግዴታውንም መወጣት ይጠበቅበታል። አንድ ህብተሰብ እራሱን የሚያስተዳድርበት ባህላዊ ሥርዓቶችና ደንቦች ቀርፆ በእነዚህ በቀረፃቸው መተዳደሪያ ደንቦች መመራት እና መገልገል ሲጀመር ባህሉንና ቋንቋውን በተገቢው መንገድ መጠበቁን ያመለክታል። ይህ ደግሞ ህብረተሰቡ እየተጠቀመባቸው ያሉት ባህሉንና ቋንቋውን የመጠበቅ ማህበራዊ ግዴታውን ያመለክታል። የሰውን ልጅ የሥልጣኔና የዘመናዊነት ግስጋሴ በየጊዜው ለመገደብ የሚሞክሩ አጋጣሚዎች በተለያዩ ጊዜያቶች ይከሰታሉ።
ከነዚህ መካከል የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ረሃብ፣ የተፈጥሮ አደጋ፣ ጦርነት ጨምሮ ሌሎችም በምሳሌነት ይነሳሉ። ከሁሉም በከፋ ሁኔታ ግን እንደ ተዛማች በሽታ የዚህን ሰብአዊ ፍጡር ህልውና እየተፈታተነ የሚገኝ አይመስልም። ዓለም አቀፍ ወረርሽኝና ቫይረስ የመኖር ህልውናውን በተደጋጋሚ ፈትኖታል። ህልውናው ላይ ጥፋት የሚቃጡ ቫይረሶችን በተሰጠው ጥበብ ተመራምሮ መድሃኒት ከማግኘት ጀምሮ ክፉውን ዘመን አጎንብሶ ሥነ ልቦናውን አደድሮ የሚያልፍበት መላ ከመዘየድ ወደ ኋላ አላለም። ይህ ጥረቱ እዚህ ቢያደርሰውም የተፈጥሮ ለውጥ ደግሞ ተመሳሳይ ፈተናዎችን ከማምጣት አትቦዝንም። ለዚህም ይመስላል አሁንም ዓለምን በአንድ ቀረጢት ውስጥ ከትቶ ከወዲህ ወዲያ የሚያላጋ አዲስ ፈተና የገጠመን።
መረዳዳት ፈተናውን ለማለፍ
ጊዜው ዓለማችን ብሎም ኢትዮጵያ ከባድ ፈተና ውስጥ የወደቁበት ነው። የተከሰተው የኮሮና ወረርሽን ታማሚውንም ሆነ ጤነኛውን አሽመድምዶ በሐኪም ተቋም እና በመኖሪያ ቤት ካዋለ ቆየት ብሏል። ታዲያ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገራት ወረርሽኙን ፍራቻ ቤት በተቀመጠው እና የዕለት ጉሩሱን በሚፈልግ መካካል ችግር መፈጠሩ የማይቀር እየተከሰተም ያለጉዳይ ነው።
ታዲያ እነዚህ አቅም የሌላቸው ሰዎች ከበሽታው ባልተናነሰ በችግር የተቆራመድ ቤተሰብ አያሌ ነው። አገሪቱ ደግሞ እንዲህ ያሉ ክፉ ቀኖችን ለማለፍ የሚረዱ ባህላዊ የመረዳጃ መንገዶች ያሏት ነች። ከእነዚህ ባህላዊ የመረዳጃ ባህላት መካከል የአፋር፣ የጉራጌና፣ በጎንደር አካባቢ የሚገኙት የቤተ እሥራኤላዊያን ማህበረሰቦች ይገኙበታል። ለዛሬ ይህን ድንቅ እሴት እያወጋናችሁ የገጠመንን ፈተና እንዴት በጋራ እንደምንወጣው የመፍትሄ መንገድ ልናመላክታችሁ ወደናል። ችግሩ ከተከሰተበኋላ ከልጅ እስከ አዋቂ፣ መካከለኛ ገቢ ካለው እስከ ባለሀብቱ ለመተጋገዝ የሚያሳየው ቁርጠኝነት እንዲህ ባሉ ባህላዊ እሴቶች ሲታገዙ የሰው ልጅ የገባበትን ግብግብ ለማሸነፍ እድሉ እጅጉን እንደሚሰፋ እናምናለን።
መልዕክቱን ተረድታችሁ የመረዳዳት ባህላችሁን ከነበረው በተለየ መልኩ እንደምታሳድጉም ሙሉ ተስፋ ሰንቀናል። በአፋር ክልል የሚገኘው ባህላዊ መረዳጃ መንገድ እናስቀድም። ከአፋር እሴቶች መካከል “ፈኢማ” ዋነኛው ነው። “ፈኢማ” የብርቱ ወንዶች ስብስብ የቡድን ስም ሲሆን የፈኢማ አባላት ሰላምና ፀጥታን የማስከበር፣ ፍርድን የማስፈፀም፣ የታመመን የመረዳት፣ እንግዳን የማስተናገድ በሰርግና በመሰል በዓላት ሥራ የማገዝ፣ በቀብር ወቅት መቃብሩን የማዘጋጀትና ሥርዓቱን የማስፈፀም ወዘተ ተግባራትን ያከናውናሉ። በእያንዳንዱ ጎሣ በብርታታቸውና ንቃታቸው የተመረጡ ወንድ ወጣቶችና ጎልማሶች ተውጣጥተው “ፈኢማ” ይመሠርታሉ።
‹‹ፈኢማ››
“ፈኢማ” በመባል የሚታወቀው የአፋር ብሔረሰብ ማኅበራዊ የቡድን አደረጃጀት በአንድ ሰው አቅም የማይከናወኑ ሥራዎችን ተጋግዞ ለማቃለል የብሔረሰቡ አባላት የሚጠቀሙበት ባህላዊ አደረጃጀት ነው። ለሥራ ተሳታፊዎች ከሥራ በኋላ በአንድ ላይ መብላትና መጠጣትም ባህላዊ እሴቱ ነው። በችግር ጊዜ የሚፈለገውን በማዋጣት የተለያዩ ችግሮችን ለማቃለል በገንዘብ፣ በጉልበትና በምክር ድጋፎች ማድረግን ያጠቃልላል። ለምሳሌ ያህል ከብሔረሰቡ እጅግ ደሃ ወይም አቅመ ደካማ የሆነውን መልሶ ለማቋቋም በገንዘብና በዓይነት ድጎማ ማድረግን፣ በሰርግ ወቅትም ቢሆን ለጋብቻ የሚዘጋጀው ሰው በቡድኑ ገንዘብ በማዋጣት ችግሩን ለመፍታት የሚያገለግል ነው።
ሴቶችም በተመሳሳይ ፈኢማ ይመሰርታሉ። ይህ ፈኢማ ሴቶች ያለባቸውን የቤት ውስጥ ዕቃና የገንዘብ ችግር ለማቃለል አባላቱ ገንዘብ በማዋጣት እንደ ችግራቸው ቅድሚያ እየተሰጣጡ ሁሉንም በየተራ የሚረዳዱበት ዘዴ ነው። “ፈኢማ” የዕድር አይነት ባህሪ ቢኖረውም የአፋር ብሔረሰብ የመረዳዳት ባህል ከሌሎቹ ብሔረሰቦች ለየት ይላል። የራሱ ባህልና ወግም አለው። በአፋር ብሔረሰብ ውስጥ ፈኢማ ሲባል ወንድና ሴት አይቀላቀልም፤ ሁለቱም የየራሳቸው አደረጃጀት አላቸው።
እስከ ዛሬ ድረስ የአፋር ብሔረሰብን ባህል ዕድሜ የሰጠው ከጥንት አያትና ቅድመ አያቶች ጀምሮ እየተወራረሰ የመጣው የፈኢማ ባህል እንደሆነ የብሔረሰቡ ነዋሪዎች ይገልፃሉ። “ፈኢማ” በአጠቃላይ ጽንሰ ሐሳቡ በመረዳዳት ላይ በመመርኮዝ ችግሮች ሲከሰቱ የሚከናወን ነው። ፈኢማ በአባላቱ ዕውቅና የተሰጠው አለቃ /ሰብሳቢ/ ይኖረዋል። በሰብሳቢው አማካይነት ሥርዓቱን ያልተከተለ አባል ይቀጣል።
ስለዚህ አባላት ለሥርዓቱ ተገዥ ይሆናሉ። በአፋር ብሔረሰብ ብዛት ያላቸው ፈኢማዎች ሲኖሩ ማንኛውም የብሔረሰቡ አባል በመረጠው ፈኢማ የመግባት መብት አለው። ነገር ግን ከነበረበት ፈኢማ ወጥቶ ወደ ሌላ ፈኢማ ለመግባት ከመጀመሪያው ፈኢማ ለምን እንደወጣ በቂ ምክንያት ካላቀረበ ሌላኛው ለአባልነት አይቀበለውም። ቀደም ሲል እንደተገለፀው ፈኢማዎች የወንድና የሴት ከመሆናቸውም ሌላ አንዱን ከሌላው የሚለይበት ሁኔታ የለም።
ሴቶች የራሳቸው ደንብ አላቸው ወንዶችም በተመሳሳይ። የሴቶች ፈኢማ በሰርግና በለቅሶ ጊዜ ምን መልክ እንዳለው እንመልከት። ሰው በሚሞትበት ጊዜ “ፈኢማ” ይጠራል። በዚህም ጊዜ የተለየ የአለባበስ ባህል አለ፤ ወደ ለቅሶ የሚመጡ ሴቶች ሁሉ ፀጉራቸው ላይ ሻሽ ያስራሉ፣ ባዶ እጃቸውን አይመጡም። ይህም የሚደረገው ሀዘንተኛውም ሆነ ዘመዶቹ ምንም ዓይነት ወጭ እንዳያወጡና ፈኢማው ከጎናቸው መሆኑን ለማሳወቅ ነው። ሰርግንም በተመለከተ በፈኢማዎች በኩል ጥሪ ይደረጋል። በሰርግ ጊዜ ብቻ የሚዘፈን ባህላዊጨዋታ ይጫወታሉ። በጭፈራውም ወቅት ፈኢማው ቀድሞ ሳይጫወት ሌላ ሰው መጫወት አይችልም። ቀድሞ የሚጫወት ካለ ይቀጣል። ጨፍረው ከዘመድ አዝማድ የሚገኘውን ሽልማት ከፊሉን ለሙሽራው ወይም ለሙሽራዋ እናት ይሰጣሉ።
ከዚህ በተጨማሪ “ፈኢማ” ከፍተኛ ክብር ስላለው በድግሱ ወቅት ለአባላት የሚዘጋጅላቸው ምግብ የተለየ ነው። የሴቶች ፈኢማ ባህልን ከማስጠበቅ አኳያ ከፍተኛ ድርሻ ስላለው ማንኛውም የአፋር ብሔረሰብ እናት ይቀርበኛል ወይም ይስማማኛል በሚሉት ፈኢማ ይደራጃሉ። ፈኢማ የአፋር ብሔረሰብን ያስተሳሰረና የማንነቱ መግለጫ ስለመሆኑ አብዛኛው የብሔረሰቡ አባላት አጽንኦት ሰጥተው ነው የሚነጋገሩት።
ፀቢያት
ሌላኛው በህብረት በመኖር የሚታወቁት በጎንደር አካባቢ የሚገኙት ቤተ እሥራኤላውያን ናቸው። ቤተ እሥራኤላውያን በአካባቢያቸው ካሉ ማህበረሰቦች ጋር ይተባበራሉ። አንድ ሰው ብቻውን አንድ ነገር ማድረግ ባይችለው ወይም ባይመቸው ሌላውን ጉረቤቱን ወይም በአካባቢው ካለው አንድ ሰውን እርዳታ ይጠይቃል። ያ ሰው ቤተ እሥራኤላዊ ሆነ ሌላ ሰው ከአገዘው እና ለመፈፀም ከቻለ የዚያ ሰው ውለታ አለበት፤ ስለዚህም እርሱም አንድ ቀን በተራው መርዳት ይኖርበታል። ይህ ዓይነቱ መረዳዳት ፀቢያት ይባላል።
“ፀቢያት” በመጠቀም ማህበረሱ በህይወቱ የሚያጋጥመውን የተለያዩ የህይወት ሁነቶችን በመተጋገዝ ለማለፍ ይጠቀሙበታል። በማህበራዊ ኑሮአቸው ማለትም እንደ ቀብር ወይም ሐዘን፣ ሰርግና የደስታ በዓል ወይም ወረርሽኝ የሆነ በሽታ በሚገጥምበት ወቅት፣ በጦርነት በሚነሳበት ወቅት በጋራ በመሆን በመረዳዳት ያላቸውን በማከፋፈል ፈታኙን ጊዜ የሚያሳልፉበት ባህላዊ መረዳጃ ባህላዊ እሴት ነው።
ፈቸት
የጉራጌ ብሔረሰብ ችግር ሲገጥመው ማለትም የተጣሉ ካሉ እርቅ ሰላም እንዲወርድ፣ ሰው ሰራሽ አደጋዎች እንዲቀንሱና ፍቅርና አንድነትን እንዲጎለብት ወደ ፈጣሪ በህብረት በመሆን በአካባቢው ካሉ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ምርቃት በማድረግ ጸሎት የሚያደርጉበት ባህል አለ። ይህ ባህል ፈቸት ይባላል። ማንኛው ሰው ተሰብስቦ ፈጣሪውን ከመጣበት ቁጣ እንዲታደገው የሚለምነበት ነው ስለዚህም ልክ እንደ ጉራጌ ብሔረሰብ የጋራ ጸሎት ማድረጊያ መንገዶችን በመጠቀም ፈጣሪን በቤት ሆኖ መለመን ሌላኛው መፍትሄ ነው።
በፈቸት ዙሪያ ጥናት ያካሄዱት የጉራጌ ባህል ጥናት ባለሙያ አቶ መንግስቱ ሃይለ ማርያም እንደሚሉት በጎሳዎች መካከል የተከሰተ ችግር ካለ፤ በአካባቢው ብሎም በአገር ደረጃ ችግር ከተፈጠረ እሱን ፈጣሪ እንዲመልሰው እና ሰላም እንዲወርድ ጸሎት የሚደረግበት ሥርዓት ነው ።
ጸሎቱ የየትኛውም ሃይማኖት በጋራ የሚያደርገው ሲሆን ከጸሎቱ በኋላ መስዋት የሚቀርበው ከብት ሆነ ሌላ ለምግብነት የሚውሉ ነገሮች እንደየ ሃይማኖቱ ሥርዓት ይዘጋጃል። ጸሎቱ በቤተክርስቲያ አልያም በመስጊድ ከሚካሄዱ ጸሎቶች ይለያል። ጸሎቱ አካታች እና ለወገን ለአገር የሚፀለይ የጋራ ጸሎት በመሆኑ ነው ልዩነቱ። በነገራችን ላይ ፈቸት ከተደረገ በኋላ ያለው ለሌለው በመርዳት አብሮ በመመገብ እና በመደጋገፍ የመጣባቸውን ችግር በህብረት በባህላቸው መሰረት ያሸንፉታል። ይሄ የመረዳዳትና የመተሳሰብ ባህል ታዲያ ዛሬ ሀገራችን በኮሮና ወረርሽኝ ላይ ባለችበትና ህዝቡ በጭንቀትና በሐዘን ላይ ባለበት ወቅት ፈጥኖ መድረስ ይኖርበታል። ርዕስ በርዕስ መረዳዳት ክፉ ነገር ከሀገርና ከህዝብ ላይ እንዲርቅ መፀለይ ያስፈልጋል። ይሄ በሁሉም ባህል ያለ ሥርዓት ቢሆንም አሁን ደግሞ ይበልጥ ልንጠቀምበትና ልናነሳው የግድ ነው፡፡
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 4/2012
አብርሃም ተወልደ
ባህላዊ መረዳጃ ከክፉ ቀን ማምለጫ