የሁለት ወረራዎች ወግ
ከጠቅላላ ሕዝቦቿ መካከል ወደ መቶ ፐርሰንት የሚጠጉት ልጆቿ “ሃይማኖተኞች” መሆናቸውን ኢትዮጵያ ለዓለም ማሕበረሰብ የምታውጀው በኩራት ብቻ ሳይሆን የመከባበርና የመቻቻል ምሳሌ መሆኗን ጭምር አፏን ሞልታ እየመሰከረች ነው።
በእርግጥም እውነታው ሲፈተሽ ከበርካታ ቅርንጫፎቻቸውም ጋር ቢሆን ሦስቱ ታላላቅና ቀደምት የእኛም ሆኑ የዓለም ሃይማኖቶች (ክርስትና፣ እስልምና እና የአይሁድ እምነቶች) እና ሌሎች በርካታ ነባር ሀገራዊና ባህላዊ እምነቶች በጠንካራ ማሕበራዊ ትስስርና መስተጋብር የሚኖሩባት ሀገር ያለ ምንም ትምክህት ይህቺው የእኛይቱ ኢትዮጵያ ስለመሆኗ ባንመሰክር ባዕዳንና የሩቅ ታዛቢዎች በአደባባይ እያወጁላት ስለሆነ ሊታዘቡን ይቻላሉ። ይህ ማለት ግን በሃይማኖቶቹና በአማንያኑ መካከል እርስ በእርሳቸውም ሆነ ከሌሎች ጋር አልፎ አልፎ መጎሻሸምና መኮራኮም አልነበረም፣ ወይንም የለም፣ ወደፊትም በፍፁም አይኖርም ብሎ ለመካድ መሞከር አይቻልም።
እውነታውን እንካድ ወይንም እናድበስብስ ቢባል እንኳ ከታሪክና ከህያዋን ምስክሮች መላተም ይሆናል። እንኳንስ በአይነኬ ቀኖናና ዶግማ በሚለያዩና ግዙፍ ቁጥር ባላቸው የሃይማኖት ቤተሰቦች መካከል ቀርቶ በጣት በሚቆጠሩ የአንድ ቤተሰብ አባላት መካከልም እንኳ ቢሆን የጠብ ይዘት ያለው እንካ ሰላንትያና አንዳንዴም ከረር ያለ እሰጥ አገባ መኖሩ የተለመደ ተፈጥሮአዊ ክስተት ነው።
ብዙ ጊዜ ደጋግሜ የተጠቀምኩበትን አባባል ማስታወሱ አግባብ ይመስለኛል። “ከታሪክ እንክርት ላይ አመዱን ከመጫር ይልቅ ፍሙን ማጋጋል በእጅጉ ስለሚበጅ” በቁርሾ የተቦኩ ታሪኮቻችንን ማስታወሱ እርባና የለውም። “ሃይማኖት የግል ሀገር የጋራ” የሚለው ዘመን ያሸበተው አባባል በተግባር የተፈተነባቸውን በርካታ ሀገራዊ ታሪኮቻችንን ወደ ኋላ ዞር በሎ ማስታዋስ ይቻላል።
ወደ ኋለኛው ዘመን ተንፏቀን የታሪክ ሰነዶችን ብናገላብጥ የየሃይማኖቱ መሪዎችና ብዙኃኑ ምዕመናን የእምነታቸው መሠረት እንዳይናጋ በመጠንቀቅ በሀገራዊ የጋራ ጉዳዮች የተባበሩባቸውን በርካታ ክስተቶች ማስታወስ ባይገድም ለትውስታ እንዲረዳ ብቻ ከዛሬ አራት አስርት ዓመታት በፊት የተፈፀመን አንድ የቅርብ ታሪክ ከአራት ቀናት በፊት ከተፈፀመ አጋጣሚ ጋር ጎን ለጎን በማስተያየት ምስስላቸውን በወግ ትርክት ለመቃኘት እሞክራለሁ። የጽሑፌን ርዕስም የተዋስኩት ከዚያው ከአርባ ዓመቱ ታሪካችን መሆኑን ልብ ይሏል።
ቀዳማይ ወግ፤
ሚያዝያ 4 ቀን 1969 ዓ.ም የደርጉ ሊቀመንበር የነበሩት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም በምሥራቁ የሀገራችን ክፍል የዚያድ ባሬ ተስፋፊ የሶማሊያ ጦር የከፈተብንን ወረራ ለመመከት ለሕዝቡ የክተት ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል። በተስፋፊነት እብደት የሰከሩት የጎረቤት ሱማሊያዋ የወቅቱ መሪ ኢትዮጵያን በተደራጀ የጦር ኃይል የወረሩት “ታላቋን ሶማሊያ”ን ለመመስረት በሚል ቅዠት መሆኑ የቅርብ ጊዜ የሀገራችን የመከራ ታሪክ ነው። በዚህ “ታላቅነት ባሰከረው” የወረራ ዕቅድ ውስጥ ለማጠቃለል የተቃዠባቸው አገራት በዋነኛነት ኢትዮጵያና ጅቡቲ ሲሆኑ በተለይም “በታላቋ ሶማሊያ” ካርታ ውስጥ እንዲካተቱ የተሟረተባቸው የሀገራችን ክፍሎች በዋነኛነት ሐረርጌ፣ ባሌ፣ አርሲና ሲዳሞ ነበሩ። የወራሪው ሠራዊትም እጅግ በተደራጀ የዘመናዊ የጦር መሣሪያዎች በመታገዝ ሉዓላዊነታችንን በመዳፈር 700 ኪሎ ሜትሮችን ዘልቆ በመግባት ያደረሰውን ግፍና የተፈፀመብንን ውድመት ያልመሸበት ታሪካችን እየተከዘም ቢሆን ያስታውሰናል።
በዚህ ወቅት ነበር የሀገር መልኳ መናጋቱ፣ የጦርነቱ ዕሳት መንቀልቀሉ ያስቆጣቸው የሀገራችን የእምነት ተቋማት መሪዎች “በጋራ የሀገር ጉዳይ ሃይማኖት አይለያየንም” በሚል መርህ በአንድነት ተሰባስበው ወረራውን ለመቀልበስ ለሚደረገው የሉዓላዊነት ማስከበር ፍልሚያ ምእመናኖቻቸውን በማስተባበር አጋርነታቸውን ለመግለጥ ግንባር የፈጠሩት። ጀግኖቹ የመደበኛ ጦሩና የሚሊሺያው ሠራዊት አባላት ጦርነቱን በድል እስኪወጡ ድረስም ከየሃይማኖቶቹ ተውጣጥቶ የተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ ድል ከሚያበስረው ጀግና ሠራዊት ጎን እንደማይለይ በአንድነት በአደባባይ ቃል ገቡ። በተለይም ከመጋቢት 19 – 21 ቀን 1970 ዓ.ም ለሦስት ቀናት የቆየ ሴሚናር በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት አዳራሽና በመማክርት ሸንጎ የመሰብሰቢያ አዳራሽ (ፓርላማ) ውስጥ ካካሄዱ በኋላ አቋማቸውን በይፋ ገለጡ።
በስብሰባው ላይ የተገኙት ተሳታፊዎች ብዛት 1200 ያህል ሲሆን ተሰብሳቢዎቹም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፣ ከእስልምና ምክር ቤት፣ ከካቶሊክና ከፕሮቴስታንት ቤተ እምነቶች የተወከሉ ዋና ዋና መሪዎች ነበሩ። በወቅቱ መንግሥትን ወክለው ሴሚናሩን በንግግር የከፈቱት የደርጉ አባል የነበሩት ሻለቃ እንዳለ ተሰማ ሲሆኑ፤ የክርስትና ቤተ እምነቶችን በሙሉ በአንድነት በመወከል መልዕክት ያስተላላፉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ ከእስልምና ምክር ቤት ሐጂ መሐመድ ሳኒ ሐቢብ ነበሩ። አባቶቹ በባለ ዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ ያስተላለፉት ዋነኛ መልዕክት በየቤተ እምነቱ የታቀፉ ምዕመናን በትጋት ለሀገራቸው ህልውና መከበር ቅድሚያ ሰጥተው አስፈላጊውን ሁሉ የዜግነት ግዴታ እንዲወጡና ወረራውን ለመቀልበስ ለሚደረገው ፍልሚያ ደጀን እንዲሆኑ የሚያሳስብ ነበር።
በጉባዔው ላይ የተለያዩ የጥናት ወረቀቶች ቀርበው ውይይት ከተደረገ በኋላ በሰሚናሩ ማጠቃለያ ላይ የጋራ መግለጫው ተነቦ ሲያበቃ “በሀገር ጉዳይ ሃይማኖት አይለያየንም” የሚለውን መርህ ለማስፈፀም ከሃይማኖቶቹ መሪዎች መካከል የተመረጡት አስተባባሪዎች ተግተው ተግባራቸውን እንዲያከናውኑ አደራ ተጥሎባቸው ሴሚናሩ ተጠናቋል። በውሳኔው መሠረትም እያንዳንዱ ቤተ እምነት ወረራውን ለመቀልበስ እንዲያግዝ አቅሙ የፈቀደውን ያህል ገንዘብ እንዲያጣ የተደረገ ሲሆን ከጥሬ ገንዘብ በተጨማሪም ልዩ ልዩ የማቴሪያል ድጋፎችና ጌጣጌጦች ሳይቀሩ እጅግ በሚያስገርም ብዛትና ዓይነት ተሰባስበው ለብሔራዊ ዘመቻ አስተባባሪ ግብረ ኃይሉ እንዲሰጡ ተደርጓል።
ከተቋማዊ ድጋፍ ጎን ለጎንም የየቤተ እምነቱ ምዕመናን እንደ አንድ ዜጋ በሀገራቸው ሉዓላዊነት ላለመደራደር በመጨከን ከመሪዎቻቸው የተሰጣቸውን ትዕዛዝ፣ መመሪያና የፀሎት ድጋፍ በማክበር የማቴሪያል ድጋፍ ብቻ ሳይሆን ወራሪውን ጠላት ለማንበርከክ በተደረገው ፍልሚያ ውስጥ የሕይወት መስዋዕትነትም መክፈላቸው ተመዝግቧል። ለውጤታማ ሀጋራዊ አስተዋጽኦአቸውም ለየሃይማኖቶቹ ቤተ እምነቶች መንግሥት ተገቢውን እውቅና የሰጠ ሲሆን በጀግኖቹ የሠራዊታችን አባላትና በመላው ሕዝብ ድጋፍ ጦርነቱ በድል ከተጠናቀቀ በኋላ “በሀገር ጉዳይ ሃይማኖት አይለያየንም” የሚለውን ብሔራዊ ኮሚቴ ሲመሩ የነበሩት የየሃይማኖቱ መሪዎች ከተስፋፊው የሶማሊያ ወራሪዎች ነፃ የወጡትን ካራማራና ጅጅጋን የመሳሰሉ ቦታዎችን እንዲጎበኙ ተደርጓል። ይህ ሁሉ መልካም ድርጊት ተከናውኖ የምሥራቁ ወረራ በድል ከተጠናቀቀ በኋላ ግን በኮሚኒስታዊ ክህደት ያበደው የደርግ መንግሥት የጭካኔ ተግባሩ አገርሽቶበት በርካታ የእምነት ተቋማትን የዘጋ ሲሆን አልፎም ተርፎ በሺህዎች የሚቆጠሩ ምዕመናንን እምነታቸውን ምክንያትበማድረግ ብቻ በግፍ አስሮ አሰቃይቷቸዋል፣ ነፍሳቸውን ነጥቋል። የተከበሩ ታላላቅ የሃይማኖት አባቶች ሳይቀሩ በግፍ መገደላቸውም አይዘነጋም። የዚያን ዘመን ዝርዝር ታሪክና በዚህ ጽሑፍ ውስጥ የተጠቃቀሱትን ቁንጽል ሐሳቦች በተብራራ ሁኔታ የሚተርከው እኔው ራሴ ሰፊ ጥናት አድርጌ “ኤሎሄና ሃሌሉያ፤ በጌታቸው በለጠ፤ 1992 ዓ.ም) በሚል ርዕስ ያሳተምኩትን ዳጎስ ያለ መጽሐፍ ማንበብ ይቻላል።
ዳግማዊ ወግ፤
“የትላንቱ ነገር ይኸው ሆነ ዛሬ
ዕድሜ ለትዝታ ድሮን አየሁ ቆሜ
እንዲሉ ልክ በ42ኛው ዓመት፤ በተመሳሳይ የመጋቢት ወር 2012 ዓ.ም፤ የኢትዮጵያ የእምነት ተቋማት ሌላ የከፋ ወረራ በጋራ ለመግታት በመሰባሰብ “በሀገር ጉዳይ ሃይማኖት አይለያየንም” የሚለውን መሰል መርህ ሲደግሙ አስተውለን ልባችን ሃሴት አድርጓል። የተከበሩ የሃይማኖት አባቶች የሀገሪቱን ክብርት ፕሬዚዳንትና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችን ከፊት ለፊት አስቀምጠው በአንድ መድረክ ላይ ቆመው ለፈጣሪያቸው ጸሎት፤ ለየቤተ እምነታቸው ምዕመናን ተማጽዕኖ ያቀረቡት መጋቢት 28 ቀን ከምሽቱ 3 – 4 ሰዓት በሸራተን ሆቴል ነበር።
በሀገራችን ታሪክ በተበታተነ መልኩ ሳይሆን የአንዱ ቤተ እምነት የአምልኮ ሥርዓት ሲፈፀም የሌሎች ቤተ እምነት መሪዎች አክብረው በመቆም በቀጥታ የተላለፈው ይህ መርሐ ግብር በሀገራችን ታሪክ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ነበር ማለት ይቻላል። የአባቶች ተማጽኖና ጸሎት ያስፈለገበት ዋነኛው ምክንያት እንደ ካሁን ቀደሙ ታሪካችን የጦር መሣሪያ የታጠቀ ሠራዊት ሉዓላዊነታችንን ለመዳፈር ድንበራችንን ጥሶ ስለገባ “ታጠቅ! ዝመት! ተዋጋ!” የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ አይደለም።
ይህ ጦርነት የከፋ ብቻ ሳይሆን በዘመናዊ የጦር መሣሪያ ሊመለስ የማይችለው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ነው። ረቡዕ መጋቢት 30 ቀን 2012 ዓ.ም በዚሁ ጋዜጣ ቋሚ አምዴ ላይ ለመዘገብ እንደሞከርኩት ዛሬ ሀገራችንን የተፈታተነው ወራሪ ኃይል እንደ ዓድዋው ወይንም እንደ ፋሽስት ኢጣሊያ ጦር፣ ወይንም እንደ ተስፋፊው የቀድሞ የሶማሊያ ወራሪ ዘመናዊ መሣሪያዎች፣ ታንኮችን፣ ተዋጊ አውሮፕላኖችንና ሄሊኮፕተሮችን ታጥቆ የዘመተብን አይደለም። ጦርነቱም እየተካሄደ ያለው በሁለት ኃያላን ሠራዊቶች መካከልም አይደለም።
እንደ ካራማራ በጠላት ወራሪዎች ተይዞ የነበሩ ገዢ መሬቶችን አስለቅቆ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ የሚውለበለብበትም አይደለም። የተፋላሚዎቹ የሠራዊት አባላትን ነፍስ ብቻ አጥፍቶ፣ አካል አጉድሎና ለምርኮ ዳርጎ የሚጠናቀቅ የጦር ሜዳ አሰቃቂ ትርዒትም አይደለም። ጦርነቱ የሁለት፣ የሦስት ከከፋም በቡድን የተሰባሰቡ ጥቂት ኃያላን ሀገራት “በይዋጣልን ጀብድ እየፎከሩ” እንደ ዓለም ጦርነቶች ሻምላ የሚማዘዙበት፣ አረር የሚወናጨፉበት፣ ቁስለኛና ምርኮኛ የሚለዋወጡበት የጦርነት ማጠናቀቂያ ፕሮቶኮልም አይደለም።
ይህ ዛሬ ሀገራችንን የገጠማት አስከፊ ጦርነት ጥይት ሳይተኮስ ሚሳኤል ሳይወነጨፍ ኃያላን አገራት ሳይቀሩ የተንበረከኩበት፣ የታላላቅ አገራት መሪዎች ሳይቀሩ ተሸንፈው አልጋ ላይ የዋሉበት፣ “ከእኛ ወዲያ ላሣር” በማለት በሀብታቸውና በሥልጣኔያቸው ሲቀናጡ የነበሩ አገራት ፈዘው ግራ የተጋቡበትና ረዳት የተማፀኑበት የኮቬድ 19 ጦርነት ነው። የትኛውም አገር በምንም የኢኮኖሚ አቋም ላይ ቢሆን ወራሪውን ወረርሽኝ ለጊዜው ሊቋቋም አልቻለም። የታላቅነትን ክብር ለራሷ ያጎናፀፈችው፣ ሌሎች አገራትም ታላቅነቷን አጽድቀው የፍፃሜያቸው ማረፊያ እንድትሆንላቸው ቀን ከሌት የሚያልሟት፣ ፅንስ የተሸከሙ እናቶች ሳይቀሩ ልጃቸውን ለመገላገል የሚመኟት፣ ምድሯን ለመርገጥ፣ ለመማርና የነዋሪነት ዜግነት ለመቀዳጀት በመሃላ እጃቸውን ከፍ የሚያደርጉላት ገናናዋ አሜሪካ ሳትቀር ለዚህ ወራሪ ተሸነፍኩ ብላ በአደባባይ እየመሰከረች መሆኗን ስናስብ ወራሪው ወረርሽኝ ምን ያህል አሰቃቂ እልቂት እየፈፀመ እንዳለ እንረዳለን።
በሀገሩ ተሰሚነት ያለው አሜሪካዊ ይህንን የኮሮና ቫይረስን ጥቃት በተመለከተ የአገሩን ሁለት ታሪኮች በማስታወስ ያነፃፀረበትን አንድምታ በርካታ የዓለማችን ሚዲያዎች ተቀብለው እየጠቀሱት ይገኛሉ። አንደኛው ማነፃፀሪያ በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ዲሴምበር 7 ቀን 1941 ዓ.ም ጃፓኖች Pearl Harbour በመባል የሚታወቀውን የአሜሪካ የባህር ኃይል መደባቸውን በዘመናዊ የጦር ጀቶች ድንገት ሳይዘጋጁ እየከነፉ በመብረር የዶግ አመድ ያደረጉበትን ታሪክ ሲሆን፤ በዚሁ ወረራ በአንድ ቅጽበት ከ3000 በላይ የባህር ኃይል አባላትና ሲቪሎች እንዳለቁ በታሪክ ተመዝግቧል። ቁስለኞችም በመቶዎች የሚቆጠሩ ነበሩ።
የንብረቱን ወድመት ግን ለማሰብም ሆነ ለመዘርዘር ይከብዳል። ቀዳሚው አንድምታ ይህ ነበር። ሁለተኛው ማነፃፀሪያ በሴፕቴምበር 2011 ዓ.ም አሸባሪዎች በኒዮርክ ከተማ መንትያ ህንጻዎችና በፔንታጎን ላይ ያደረሱትን ጥፋት የሚያስታውስ ነው። በዚሁ ቅጽበታዊ በሆነ አሰቃቂ ጥቃትም 3000 የሚገመቱ ንፁሐን ዜጎች ከመቅጽበት ትንፋሻቸው ተነጥቋል። ከኮረና ቫይረስ ወቅታዊ ውድመት ጋር እነዚህ ሁለት ማነፃፀሪያዎች ለአሜሪካ ብቻ ሳይሆን ለተቀሩት አገራትም ቢሆን ተገቢና ትርጉም የሚሰጡ ማሳያዎች ናቸው።
የሀገራችን ቤተ እምነት መሪዎች በዚሁ በመጋቢት ወር መጨረሻ ተሰብስበው ለምህላና ምዕመናንን ለጥንቃቄ ለመምከር የወሰኑት የዚህን ወረርሽኝ ድንበር አይከለከሌነትና አውዳሚነት በመረዳት ስለሆነ ለአባቶቻችን ክብር ልንሰጥም ልንታዘዛቸውም ይገባል። የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ የሚገታው በጠቢባን ሳይንሳዊ የምርምር ውጤት በሚገኝ መድኃኒት ብቻም ሳይሆን ከፈጣሪ በሚገኝ የምህረት ፀጋ ጭምር መሆኑንም በሚገባ ሕዝባችን እንዲረዳም ጭምር ነው። የእምነት መሪዎቻችን የሰጧቸው ምክሮችና የንስሐ መልዕክቶችም በተግባር ሊተረጎሙ ይገባል።
ከዚሁ ጎን ለጎን ለአንድ ወር የታወጀው የፆምና የጸሎት አዋጅም እንደ የእምነቱ ቀናኖና ዶግማ በምዕመናን ዘንድ ሊተገበር ይገባል ባይ ነኝ። ለተከታታይ አንድ ወር ያህል በሁሉም የመንግሥት የቴሌዥን ቻናሎች የእምነት ተቋማቱ ምዕመኖቻቸውን እንዲያጽናኑ የአየር ሰዓት መፍቀዱም የሚያስመሰግን ተግባር ነው። የኮረና ቫይረስ ጥፋትና ውድመት ዓለምን ማስጨነቁ፣ አገራችንንና ሕዝባችንም ግራ መጋባቱ እውነት ቢሆንም መሸነፉ ግን አይቀርም።
ታሪክና ተረት እንደሚሆንም ጥርጥር አይገባንም። የሃይማኖት ቤተሰቦች በፀሎት፣ የሳይንስ ጠቢባን በምርምር፣ ጀግኖቹ የጤና ባለሙያዎቻችን በጽናት፣ ሕዝባችን በመታዘዝ የየድርሻችንን ከተወጣን የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ተሸንፎ እጅ መስጠቱ አይቀርም። ሳይርቅ በቅርቡ የመንግሥት ጥረት ታክሎበት፣ ተመራማሪዎችና የሕክምና ጠቢባኑ በሚያሳዩን ውጤትና የእምነት አባቶች ባወጁት የጸሎት ኃይል ኮቪድ 19 ተሸንፎ ሀገራዊ የምስጋና ፕሮግራም እንደምናዘጋጅ ተስፋችን ፅኑ ነው። ሰላም ይሁን!!!
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 3/2012
(ጌታቸው በለጠ – ዳግላስ ጴጥሮስ) gechoseni@gmail.com
“በሀገር ጉዳይ ሃይማኖት አይለያየንም”