እንደ መግቢያ
በፈረንጆቹ አቆጣጠር 1918 ዓለም በጭንቅ ውስጥ ነበረች፡፡ እንደ ዛሬው ቴክኖሎጂ በላይ በላዩ ተወልዶና ሉላዓዊነት እንዲህ ትስስሩ ሳይጠብቅ ዓለምን ግን ያስተሳሰረና ሁሉም ስለ አንድ ጉዳይ ብቻ እንዲያወራ ያደረገ አንድ ነገር ተከሰተ፡፡ የ«ስፓኒሽ ፍሉ» ወረርሽኝ፡፡ መነሻው ከዓሣማ እንደሆነ የሚነገርለትና እስካሁንም ድረስ የቫይረሱ ርዝራዥ ከዓሳማ ሰውነት ውስጥ አይጠፋም የሚባለው «ስፓኒሽ ፍሉ» በወቅቱ በዓለም ላይ ከ50 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሕይወትን ገላፈቻ እንዳለ ታሪክ በጥቁር መዝገብ ሰንዶታል፡፡
ዓለምን ከሰሜን እስከ ደቡብ፤ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ በአራቱም ንፋሳት ያካለለው ይህ ወረርሽኝ በታሪክ የማይረሳ አያሌ ጠባሳዎችን ጥሎ አልፏል፡፡ ልክ በአሁኑ ወቅት ኮሮና ቫይረስ የዓለም መነጋገሪያ እንደሆነውና የበርካታ አገራትን ቤተመንግሥት በር እንደሚያንኳኳው ሁሉ «ስፓኒሽ ፍሉ» በወቅቱ የነበሩ የአገራት መሪዎችን ጭንቅ ጥብብ ያደረጋቸው እንደነበር ታሪክ ያወሳል፡፡ ቅጠል በጣሽ ጉድጓድ ማሽ ሁሉ ለመፍትሄው እንዲተጉ የተማጽኖ ጥያቄ ይቀርብላቸው የነበረ ሲሆን ያልተሞከረ ነገርም አልነበረም፡፡
በዘመናዊ ሕክምና በራሳቸው ፊና ሲተጉ በባህላዊ መንገድ ፈዋሽ ናቸው የተባሉ መድኃኒቶችን በዱር በገደሉ የማፈላለጉ ሥራ ተጧጡፎ እንደቀጠለም ታሪክ ያወሳል፡፡ በወቅቱ «እንዲህም ይኖራል» የሚያሰኙ ዓጃኢቦች የታለፉ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት የተከሰተው የኮሮና ቫይረስም ከዚህ ባልተናነሰ መልኩ ዓለምን እየፈተነ ይገኛል፡፡ አሁንም ቢሆን ከባህላዊ እስከ ዘመናዊ ሕክምና እውቀት ተክነናል የሚሉ ሰዎች በየአቅማቸውና በእውቀታቸው ልክ እየፋነኑ ይገኛሉ፤ መጨረሻው ይህ ነው ብሎ መናገር ቢያስቸግርም፡፡
ታዲያ ከመቶ ዓመታት በፊት የተከሰተው ወረርሽ እንዲሁ በቀላሉ ዓለምን በምህረት ያለፈ አልነበረም። እንዲያውም ቁልፍልፍ ችግሮች ውስጥ አስገብቷት መፈናፈኛም አሳጥቷት ነበር፡፡ በተለይም ወረርሽኙ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ በማስከተል ረገድ እስካሁን ወደር አልተገኘለትም፡፡
ምጣኔ ሀብታዊ ቀውስ
በወቅቱ ተከስቶ በነበረው «የስፓኒሽ ፍሉ» ወረርሽኝ የ50 ሚሊዮኖችን ሕይወት በመቅጠፍ ብቻ ያባራ አልነበረም። የዓለምን ምጣኔ ሀብትም ክፉኛ አሽመድምዶ ዓለም ግራም ቀኝም እንዳታማትር አድርጎ ለክፉ ከመዳረጉ በተጨማሪ በየአገራቱ በምጣኔ ሀብት እድገት ላይ ጥሎት ያለፈው ጠባሳ ለማገገም የወሰደበት ጊዜም በእጅጉ የበዛ ነበር፡፡ ወረርሽኙ አምራች ኃይሎችን በብዛት በመቅጠፉ ምርት እጥረት እንዲከሰት አድርጓል፡፡
በአንዳንድ አጋራትም ከፍተኛ የሆነ የምግብ እጥረት እንዲከሰት ምክንያት ከመሆኑም የተነሳ ከበሽታው በተጨማሪም በርሃብ የተነሳ ሰዎች ለህልፈት ሕይወት መደረጋቸውን የታሪክ ድርሳናት ሰንደውታል፡፡ በዓለም ላይ ከተከሰቱ እጅግ አስከፊ በሽታዎች ተርታ የሚመደበው ይህ ወረርሽኝ በወቅቱ ከፈጠረው ጫና ለማገገም ሰፊ ጊዜ እንደወሰደ ይነገራል። ልክ እንደ ዛሬው በደቂቃዎች የሂሳብ ስሌቱ እየተሰራ የምጣኔ ሀብት ላይ የፈጠረው ጫና በባለሙያዎች እየተነተነ ወዲያውኑ ለአድማጭ ተመልካች ባይቀርብም ዓለም ቅርቃር ውስጥ የገባችበት ስለመሆኑ በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ምሁራን ያስገነዝባሉ፡፡ በተመሳሳይ መልኩ 100 ቀናትን ያስቆጠረው የኮሮና ቫይረስም በዓለም ምጣኔ ሀብትን በማንኮታኮት ረገድ የሚስተካከለው አልተገኘም፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስመጥሩ የሆኑ አየር መንገዶች ከወዲሁ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮችን ማጣቸውን እያሳወቁ ነው፡፡ በሌላበኩል የበርካታ አገራት የውጭ እና የውስጥ ንግድ ተቀዛቅዞ የፋይናንስ ፍሰቱን በእጅጉ አዳክሞታል። በርካታ አምራች ኢንዱስትሪዎችም ሠራተኞችን ለመቀነስ ተገደዋል፡፡ የዚህ ችግር ገፈት ቀማሽ ያልሆነ አገር ባይገኝም በድሃ አገራት ወይንም እንደ አፍሪካ ያሉ አህጉራት ግን ቡጢው እጅጉን ከፍቶባቸዋል፡፡
ማህበራዊ ቀውስ
በዓለም ላይ ተፈጥሮ የነበረው «ስፓኒሽ ፍሉ» በወቅቱ የፈጠረው ማህበራዊ ቀውስ እስካሁን ወደር አልተገኘለትም፤ በአሁኑ ወቅት ያለው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የሚያስከትለው የመጨረሻው ውጤት ባይታወቅም፡፡ «በስፓኒሽ ፍሉ» በሽታ በርካታ አገራት ማህበራዊ ቀውሶችን ያስተናገዱ መሆናቸው አይዘነጋም።
ከአንድ ቤተሰብ በርካቶች ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን ይህም በበርካቶች ላይ የሥነ ልቦና ጫና በመፍጠር ሌላ ችግር ውስጥ እንዳስገባቸው በዘርፉ አያሌ ጥናት ያካሄዱ ምሁራን በብዕራቸው ሰድረው አስቀምጠዋል፡፡ ይህም ብቻ አይደለም ጠባሳው ከባድ ከመሆኑ የተነሳ ከዚያ ችግር ለማገገምም ብዙ ጊዜ ወስዶ ነበር፡፡
በዚህም የዓለም ሕዝብ ቁጥር ምጣኔን በእጅጉ ካዛነፉና «የዲሞግራፊ» ለውጥ ካስከተሉ አስከፊ በሽታዎች ውስጥ እስካሁን አንዳችም የሚስተካከለው ወረርሽ እንደሌለ የሥነ ሕዝብ ጉዳይ ይመለከተናል የሚሉ አካላት በተደጋጋሚ ባካሄዱት ጥናት ለማረጋገጥ ችለዋል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥም «የኅዳር በሽታ» ተብሎ የሚጠራው ይህ በሽታ ከፍተኛ የሆነ የሥነልቦናና የማህራዊ ሕይወት መናጋትን ማስከተሉ ይነገራል።
ለአብነት በበሽታው የታየዘ ሰው ቤቱን ክርችም አድርጎ ዘግቶ ለብቻው የሚገለል ሲሆን የሚበላ አሊያም ይጠጣ የነበረው ሁሉ በመስኮት አሊያም በበር ስር በቀዳዳ ይሰጠው ነበር፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እንደማንኛውም ሰው ከሰው ጋር መገናኘት አይችልም። ከዚህ ሰው ጋር የትኛውም ሰው ቢገናኝ የገፈቱ ቀማሽ ስለሚሆን ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅ ግድ ሆኖ ነበር፡፡ መቀራረብ፤ መሳሳምና መደጋገፍ የብዙ ኢትዮጵያውያን የዕለት ተዕለት መስተጋብር ሲሆን በወቅቱ የነበረው በሽታ ግን ይህን አዛብቷል፡፡ በርካቶችም ለሥነልቦና ቀውስ የተዳረጉ ሲሆን ሕይወታቸውንም አጥተዋል፡፡
አሁንም ቅድምም
«ስፓኒሽ ፍሉ» ዓለም ባጥለቀለቀበት በዚያ ወቅት በበሽታው ከተያዘ ሰው ፈንጠር ብለው የሚቀመጡ ወይንም ርቀታቸውን የጠበቁ ሰዎች በበሽታው የመጠቃት ዕድላቸው እጅግ በጣም አነስተኛ እንደነበር ነው የጥናት ውጤቶች የሚያስረዱት፡፡ በእርግጥ በሽታው ሳል ያዘለ ስለነበር በርቀት መቀመጡ ወሳኝ እንደሆነ በመነገሩ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች በባዶ ቤት ይገለሉ ነበር፡፡ ይህ በኢትዮጵያም የተደረገ ሲሆን በርካቶችንም መታደግ ተችሏል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ዓለምን እያመሰ የሚገኘው የኮሮና ቫይረስ በሽታ መዛመትን ለመቀነስ እና ለመከላል እንደ ሁነኛ መፍትሄ ከተቀመጡት መካከል አካላዊ ፈቀቅታ ወይንም ተራርቆ መቀመጥና እንደ አስፈላጊነቱ ዕለታዊ ክዋኔዎችን ማከናወን መፍትሄ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ በተጨማሪም በቫይረሱ የተጠቃ ሰው ራሱን ለብቻው እንዲያገል በጥብቅ ይመከራል፡፡ ታዲያ እነዚህ ሁለት በሽታዎች የጋራ መፍትሄያቸው አካላዊ ርቀትን መጠበቅ አንዱ ነው፡፡ እና አሁንም ቅድምም አካላቂ ርቀት፤ ዋጋ የማይከፈልበት መድኃኒት ስለመሆኑ ሐኪሞች እየተናገሩ ነው፡፡ በግርድፉ አካላዊ ፈቀቅታ አሁንም ቅደምም መፍትሄ እንደሆነ ይነገራል፡፡
እንደ መውጫ
ከአንድ ክፍለ ዘመን በፊት ተከስቶ በነበረው «ስፓኒሽ ፍሉ» ለማገገም ዓለም ብዙ ውጣ ውረዶችን አይታለች። ዛሬም ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለማገገም የባጥ የቆጡን እያለች ነው፡፡ ቫይረሱም የስርጭት አድማሱንና ፍጥነቱን ከቀን ወደ ቀን እያፋጠነ ስመ ገናና ሆኗል፡፡ ዓለም የክተት አዋጅ ጠርታ አገራት የመከላከያ ሠራዊታቸውን ከገጠር እስከ ከተማ አሰማርተው ቫይረሱን ለመመከት እየተጉ ነው፡፡
በተራው ዜጎች ደግሞ በቤት ሆነው አሊያም እየሸሹ ራሳቸውን ከቫይረሱ እንዲጠብቁ እየተማፀኑ ነው። «ስፓኒሽ ፍሉ» በሽታንም ለመከላከል በወቅቱ ከዚህ ያልተናነሳ ርብርብ ሲደረግ እንደነበርም ታሪክ ያስረዳል። አገራትም የመከላከያ ሠራዊታቸውን በሰፊው አሰማርተው እንደነበር ነው የሚነገረው፡፡ የሆነው ሆኖ ዓለም «ከስፓኒሽ ፍሉ» ያመለጠችበት በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ ከተፈጠረው የኮሮና ቫይረስ የማታመልጥት ምክንያት የለም፡፡
ግን ችግሩ እስከሚያልፍ ማልፋቱ አይቀርም፡፡ በዚህ ወቅት ታዲያ በከባድ ፈተና ውስጥ የሚገኙት ደግሞ በርካቶች ናቸው፡፡ በመሆኑም ችግሩን ለመጋፈጥ ሲባል ችግረኞችን እያገዙ ርቀትን እየጠበቁ ነገን ለማየትም እየናፈቁ ኃላፊነት በተሞላው መንገድ መንቀሳቀስ ግድ ይላል፡፡ ኢትዮጵያ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ዓለም የገጠማትን ፈተና ለማለፍ መፈተን ግድ ሆኖባታል፡፡ ታዲያ ይህ ችግር ማለፉ አይቀሬ መሆኑን በመገንዘብ ለመፍትሄው መታተርና መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ያኔም ታልፏል፤ አሁንም ይታለፋል፡፡
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 3/2012
ክፍለዮሐንስ አንበርብር
ያኔም ታልፏል